Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
32.2K subscribers
5.36K photos
99 videos
13 files
937 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች /ክፍል አንድ/
ያለገደብ እና በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አሉ ከእነኚህ ውስጥ ያለ ገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎችን ክፍል አንድ መረጃ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
1. ተቀጣሪ ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
2. የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
3. በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
4. በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
5. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው፡- ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ እና ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ
6. በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት:-
• አንድን ቴክኖሎጅ ለማሻሻል፣ አዲስ የፈጠራ ስራ በመስራት ወይም ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ስራ ላይ በማዋል የሚሰጥ ሽልማት
• በአለም አቀፍ ደረጃ በሚደረግ ውድድር አገርን ወክሎ ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በህግ በተቋቋመ ድርጅት በሚደረግ ማንኛውም ውድድር የሚሰጥ ሽልማት
• በፌደራል፣ በክልል፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መንግስት የላቀ የስራ ክንውን ላስመዘገበ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን ሽልማቱ ከገቢ ግብር ነጻ ሊሆን የሚችለው ከፈጠራ ስራው ጋር ግንኙነት ያለው የመንግስት አካል ለፈጠራ ስራው እውቅና የተሰጠው ወይም የፈጠራ መብት ሲኖረው ነው
7. በተቀጣሪው ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
8. ስጦታው የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
9. በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
10. ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
ቀጣዮቹን በቀጣይ ክፍል ይጠብቁን፡፡
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌግራም፦ ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን አርብ ማታ ከ3፡00 ጀምሮ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ
በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን
እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!
ማስታወቂያ

መጋቢት 30፣ 2014 (ገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግብር ከፋይነት ለተመዘገባችሁ 654 ድርጅቶች በሙሉ፡-

ግብር ከፋዮች ግብር/ታክስ የማሳወቅ ግዴታ ያለባችሁ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ማሽን ጋር በተያያዘ በህግ የተቀመጡ ግዴታዎችን ካልተወጡ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር - 983/08 መሰረት በአስተዳደራዊና በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑ በህግ ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት ስም ዝርዝራችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘራችሁ 654 ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ በጽሑፍ ተአማኒነት ያለውን ማስረጃ በመያዝ የድሮው ለም ሆቴል አካባቢ የሚገኘው ኮሜት ህንጻ ቁጥር 2 ቀርባችሁ በድርጅቱና በስማችሁ የተመዘገበውን የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ያለበትን ሁኔታ እንድታሳውቁ እየገለጽን ግዴታችሁን ካልተወጣችሁ ግን በታክስ አስተዳደር አዋጁ ላይ በተቀመጠው የሕግ ድንጋጌ መሰረት የአስተዳደራዊ ቅጣትና የወንጀል ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌግራም፦ ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን አርብ ማታ ከ3፡00 ጀምሮ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራሞቻ