Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
23.4K subscribers
3.4K photos
86 videos
13 files
569 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
ተቋማዊ ውጤታማነትን እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ሊያረጋግጥ የሚያስችል ረቂቅ የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ለውይይት ቀረበ

ሰኔ 14/10/2016 ዓ,ም( የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴርንና የጉምሩክ ኮሚሽንን ተቋማዊ ውጤታማነትን እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ሊያረጋግጥ የሚያስችል ረቂቅ የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ በዛሬው ዕለት ለውይይት ቀርቧል፡፡

ውይይቱ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴን ጨምሮ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች የሁለቱ ተቋማት ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት በተገኙብት ተካሂዷል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://rb.gy/q5ojye
ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ስለመሆን

ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡ ከመቀጠር ከሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነጻ የሚሆኑባቸው ሁኔታዎች አሉ ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡-¬

— ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
— በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
— በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/s84gb8
በገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ የተገነባው የሐዋሳ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንፃ ከሐምሌ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

ሰኔ 16/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከሚያስገነባቸው የህንጻዎች ች ማካከል የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አንዱ ነው፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከሐምሌ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ባስገነባው ህንፃ አገልግሎጽ መስጠት ሊጀምር መሆኑን በገቢዎች ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ፕላንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ታደሰ ጠቁመዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/z97oyj
የቀረጥ ነጻ መብት ጋር ተያይዞ ከሚጣሉ ቅጣቶች ውስጥ አንዱ

የቀረጥ ነጻ መብት ሳይኖር ከሚፈጸሙ ጥፋቶች ጋር በተያያዘ ከሚጣሉ ቅጣቶች ውስጥ የሚከተለው አንዱ ነው፡-
የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሳይኖረው የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ያለው በማስመሰል በማንኛውም የተጭበረበረ ሁኔታ ቀረጥ ሳይከፈልበት እቃ ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ወይም ከአገር ያስወጣ ወይም ወደ አገር ለማስገባት ወይም ከአገር ለማስወጣት የሞከረ እንደሆነ ከሰባት ዓመት በማያንስ እና ከአስር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና 100 ሺህ በማያንስ እና ከብር 200 ሺህ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
በፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@ministryofrevenuesofeth.../featured
በቲክቶክ፡- tiktok.com/@ministry_of_revenues
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ፣ ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኃላ፣ ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣ በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ. በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን
ከሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ጋር ውይይት ተካሄደ

ሰኔ 17/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከተፈቀደላቸው ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ጋር በሙያዊ አገልግሎት አሰጣጥ እና በታክስ አስተዳደር አሰራር ስርዓት ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት አድርጓል።

በውይይት መድረኩ በሚኒስቴሩ የታክስ ስርአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ የሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ግብር ከፋዮች ወደትክክለኛው የታክስ አከፋፈል ስርአት እንዲገቡና አገር ከታክስ ማግኘት ያለባትን ገቢ እንድታገኝ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።

የታክስ ስርአት አለመዘመን ወይም በቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆን ለታክስ ስወራ እና ማጭበርበር እያጋለጠ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው በተለይም ከደረሰኝ አስተዳደር ጋር የሚነሱ ችግሮችን እንዲቀርፍ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እየለሙ መሆኑን አሳውቀዋል።

ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች ሙያዊ ብቃት ተላብሰው እና ሙያዊ ኃላፊነትን ባከበረ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባ የጠቆሙት ደግሞ በሚኒስቴሩ የታክስ የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ አበበ ናቸው።

በህይወት ገ/መድህን
ፎቶ:- እስከዓለም ሰፊው
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች

ሰኔ 18/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 8 (2) እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ ቁጥር 79/1995 ከአንቀጽ 19 እስከ 33 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግ በመመሪያ ቁጥር 1006/2016 የተዘረዘሩ እቃዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ተደረገዋል፡፡

የመመሪያውን ዝርዝር ጉዳይ ለመመልከት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ፡- https://rb.gy/7qpiyl

በተጨማሪም ከታክስና ጉምሩክ ህጎች ጋር የተያያዙ አዋጆችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን ለማግኘት ድረ-ገጽችንን www.mor.gov.et ይጎብኙ፡፡
"ገቢያችን ህልውናችን" (15ኛ ዓመት የግንቦት ወር 2016 ዓ.ም ቁጥር 173 እትም ጋዜጣ)

ሰኔ 18/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

"ገቢያችን ህልውናችን"በገቢዎች ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እየተዘጋጀች የምትሰራጭ ወርሃዊ ጋዜጣ ስትሆን ጋዜጣዋን ለማገኘት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://rb.gy/akakni
ከ247 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሰኔ 18/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሰኔ 7 ቀን እስከ 13/ 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 233 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 247 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ