Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
21.6K subscribers
2.94K photos
80 videos
13 files
463 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
የንግድ ምዝገባን ከግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ጋር ለማስተሳሰር ስምምነት ተደረገ

ግንቦት 07/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የንግድ ምዝገባን ከግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tax Identification Number/TIN) ጋር በማስተሳሰር እና በኦንላይን ለማግኘት የሚያስችል አሰራር ለመተግበር የገቢዎች ሚኒስቴር ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት በስካይላይት ሆቴል አደረጉ።

ስምምነቱ የንግድ ደረሰኝን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርን ከንግድ ምዝገባ ሲስተሙ ጋር እንዲናበብ በማድረግ ለኢኮኖሚው አንቀሳቃሾች የተሳለጠ አገልግሎት በመስጠት ውጤታማነትን ለመጨመር የሚያግዝ እንደሆነ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ተናግረዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/f2wdpi
ባለፉት 10 ወራት ከ425 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል

ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ባለፉት 10 ወራት ብር 442.85 ቢሊዮን ገቢ የመሰብሰብ ግብ ተጥሎ ብር 425.27 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 96.03 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገለጹ፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ54.77 ቢሊዮን ብር ወይም የ14.78 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/g3fw3q
ባለፉት 10 ወራት 49.14 ቢሊየን ብር ለክልሎች እንዲተላለፍ መደረጉ ተገለጸ

ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በዘሬው ዕለት ለመገናኛ ብዝኋን ባለሙያዎች የገቢ አሰባሰብና ጉምሩክ ተግባራት ጋር በተያያዘ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፉት 10 ወራት 49.14 ቢሊየን ብር ለክልሎች እንዲተላለፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/d861qv
ከፍተኛ ቅንጅት የታየበት ውጤታማ ተግባር

ግንቦት 09/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ አካላት፣ የሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ባደረጉት ከፍተኛ ቅንጅት ለአንድ ወር ያህል በተደረገ ሚስጢራዊ ክትትል በአንድ ቀን ውስጥ በ9 ትራከር እና 7 አይሱዙ በድምሩ በ16 ተሸከርካሪዎች ወደ መሀል ሀገር ሊገባ የተዘጋጀ የኮንትሮባንድ እቃ በቀን 08/08/2016 ልዩ ስሙ ቢዮባሃይ በተባለ አካባቢ ተከማችቶ እያለ በቁጥጥር ስራ ማዋል ተችሏል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/bj58tc
የታክስ እና ጉምሩክ ህግ ለሀገር ተረካቢዎች

ግንቦት 09/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን የጅማ ቅ/ፅ/ቤቶች የሁለተኛ ዙር የታክስና የጉምሩክ ክበብ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በጅማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ከጅማ ዞን እና ከተማ የተውጣጡ ዘጠኝ ት/ቤቶች የተመረጡ 18 ተማሪዎች የተሳተፉበት የጥያቄና መልስ ውድድር ሲሆን ከፍተኛ ፉክክርም ተደርጎበታል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/qk3e2v
#ማስታወቂያ

የገቢዎች ሚኒስቴር በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 115(4) በተሰጠው ሥልጣን የታክስ አሰተዳደራዊ ቅጣት አነሳስ መመሪያ ለማውጣት ረቂቅ መመሪያ ያዘጋጀ ሲሆን በረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያያት ያለው ስው አስተያየቱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣውበት ግንቦት 08/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ለገቢዎች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማቅረብ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ረቂቅ መመሪያውን ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡- https://rb.gy/jtq27l
"ግብር ሀገርን ከተመፅዋችነት በመፋቅ አንፃራዊ ነፃነትን ያጎናፅፋል" - አቶ ደሜ ከበደ በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ

ግንቦት 10/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ለታክስ ህጉ ተገዢ በመሆንና የሞጁላር ስልጣና በውጤታማነት ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች በጅማ ከተማ የእውቅናና ሽልማት ስነ-ስርዓት እያካሄደ ይገኛል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/50kv8i