LearnEthiopia(ExitExam/EntranceExam/NationalExam-G8/JobExam/GATExam)
10.3K subscribers
939 photos
5 videos
7 files
1.16K links
Ethiopian Universities Entrance Exam/Exit Exam & GAT Exam/Jobs Exam/National Exam. Largest Harmonize E-Library, Jobs and Scholarship Portal.
Download Telegram
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ seneexit2016@gmail.com ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል
#MoE
ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸው ስህተትን መቀነስን ጨምሮ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም

የበይነ መረብ ፈተና አንድ ጥያቄ ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ Click የመሔድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ Flag በማድረግ ተመልሶ የመስራት ዕድልን ይሰጣል።

ጊዜ ቆጣቢ ነው

በአንድ Click የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል።

የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው

የበይነ መረብ ፈተናዎች በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡

የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በፍጥነት በራሱ ይልካል

በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ በፍጥነት ይልካል።

ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል

በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ ዕድል ይሰጣል።

ተማሪዎች በቤታቸው እያደሩ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣል

ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ ዕድል ይፈጥራል።
#ማስታወቂያ #MoE

በተለያየ ምክንያት የ “ Management, Business administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship” ፈተና ያልወሰዳችሁ ተፈታኞች ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደተመደባችሁበት ተቋም በመሄድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
• ሁሉም ተፈታኞ ፈተናው ከመጀመሩ ከ 30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣብያ መገኘት ይኖርባቸዋል፣
• ሁሉም ተፈታኞ User Name Password ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።