LearnEthiopia(ExitExam/EntranceExam/NationalExam-G8/JobExam/GATExam)
10.3K subscribers
939 photos
5 videos
7 files
1.16K links
Ethiopian Universities Entrance Exam/Exit Exam & GAT Exam/Jobs Exam/National Exam. Largest Harmonize E-Library, Jobs and Scholarship Portal.
Download Telegram
#ማስታወቂያ #MoE

በተለያየ ምክንያት የ “ Management, Business administration, Business Management እና Business Management and Entrepreneurship” ፈተና ያልወሰዳችሁ ተፈታኞች ነገ ቅዳሜ ሰኔ 15 /2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ጀምሮ ፈተናው ስለሚሰጥ ወደተመደባችሁበት ተቋም በመሄድ መፈተን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
• ሁሉም ተፈታኞ ፈተናው ከመጀመሩ ከ 30 ደቂቃ በፊት የፈተና ጣብያ መገኘት ይኖርባቸዋል፣
• ሁሉም ተፈታኞ User Name Password ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።
#Update

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል።

የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።
#RayaUniversity

በራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 97.55% አልፈዋል👏

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 14/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተሰጠ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከተፈተኑት 325 ተማሪዎች 97.55% በማሳለፍ እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

ይህ ታላቅ ውጤት እንዲመጣ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲው ሥራ  አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ እና መካከለኛ  አመራሮች፣ መምህራን፣ የICT ባለሙያዎች፣ Lab Assistant፣ የኤሌክትሪክ ቴክኒሻኖች፣ ጀነሬተር ኦፕሬተሮች፣ የፀጥታ እና ደህንነት አካላት፣ የማይጨው ዲስትሪክት መብራት ሃይል ሰራተኞች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ሪጅን ቅርንጫፍ ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ዩኒቨርሲቲው ታላቅ ምስጋናውን አቅርቧል።

መላው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የግቡው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ 👏👏
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪ እንዳለፈ ይፋ አደርጓል።

መረጃው ከሀዋሳ የተማሪዎች ህብረት የተገኘ ነው።
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት።

ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ደጋግሞ በመሞከር ውጤት መመልከት ይቻላል።
Remedial ተማሪዎች አሁን የምታዩት ውጤት ከ 70% ነው። የግቢው 30% ተጨምሮ ከግማሽ በላይ ካመጣችሁ አልፋችኋል።

🔖ለ Natural Science ከ 70% (350) + 30% (150) =500 ስሆን 250 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ አልፋችኋል።

🔖ለ Social Science ከ 70% (280) + 30% (120) =400 ስሆን 200 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ አልፋችኋል።

📍ውጤት ለማየት ያስቸገራችሁ VPN ተጠቀሙ።