ISLAMIC SCHOOL
12.9K subscribers
369 photos
164 videos
7 files
1.05K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
#ማሻ_አላህ!
ሼይኽ ሀሰን አዘ-ዘያት ይባላል የ33 አመት ጎልማሳ ነው። የዛሬ አራት《4⃣》 አመት የአለም ትልቁ ቁርአንን ለመፃፍ እቅድ ይዞ ይኸው እንዲ እየፃፈ ይገኛል። በዚህ አመት መጨረሻ ለእይታ ሚቀርብ ይሆናል።
🤲አላህ ይርዳህ ያሼይኽ🤲

።።።።።።።።።።።።።።
@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
።።።።።።።።።።።።።።

🚫 Share it now
እዉነተኛ እና አሳዛኝ ታሪክ

😢 #በመተት_የተሰናከለች_ነብስ_
                 #Part 6⃣


#እውነተኛና_አሳዛኝ_እንዲሁም_አስተማሪ_ታሪክ

    ህይወት አንዱ ሰካራም እንዳይደፍራት ስትፈራ ከቆየች ቡሃላ አክስቷ ጋር ለመሄድ አሰበች አማራጭ ስላጣች ነው እንጂ ዘመድ ጋር መኖር አይደለም ዘመድ ማየት አስጠልቷታል ከብዙ ሀሳብ ቡሃላ የአክስቷ ባል ጋር ደወለች ከዛም ስላለችበት ችግር ነገራው እንዲወስዳት ስጠይቀው ስራ ነኝ ሲል መለሰላት በርግጥ አውቆ ነበር የሱን ዘመዶች ካልሆነ የሚስቱ ዘመዶች እቤት ሲቀመጡበት አይወድም... ለዛ ነበር ስራ አለኝ ያለው ... በኋላ ላይ ግን ደብረ ዘይት ደርሳ ስትደውልለት ያለችበት ድረስ መቶ ወሰዳት ...
   ህይወት ከአክስቷ ጋር መኖር ከጀመረች 2ወር ሞላት ሁሌም አክስቷ ሀኪም ቤት ትወስዳት ነበር... ይህ በእንዲህ እንዳለ የአክስቷን ባል ፀባይ መቆጣጠር አቃታት ጨቅጫቃ ከመሆንም ባለፈ ህይወትን እዛ ቤት ማየት አይፈልግም ይሄኔ ህይወት ስራ መፈለግ ጀመረች እናም እዛው አካባቢ ፊስታል ፋብሪካ ውስጥ ስራ አግኝታ ተቀጠረች ህይወት ቀልጣፋ በመሆኗ ባጭር ግዜ ውስጥ ነበር እድገት ያገኘችው ...
   ታድያ የህይወት አክስት ሌላ ቦታ ቤት ቀይራ ሄደች እናም በመጀመርያ የነበሩበት ቤት የተከፈለበት ቀን ሲያበቃ እነሱ ጋር እንድትሄድ ነገሯት እሷም የተባለችበትን ቀን ጨርሳ ልትሄድ ስትል ስላመማት ሌላ ሁለት ቀን ሴት ጓደኛዋ ጋር አድራ ወደ አክስቷ ሄደች ይሄኔ ግን የአክስቷ ባል ሁለት ቀን ስትንዘላዘይ አድረሽ መጣሽ በሚል ቤት ውስጥ ጥል ተነሳ ህይወት ከህመሟም ተጨማሪ የሱን አላስፈላጊ ቃላት መስማት አልቻለችም ነበር ንግግሩ ሁሉ ከጎረምሳ ጋር ስትማግጥ እንደቆየች ነበር ያስመሰለው ህይወትም እኔ ወንድ ብፈልግ መቼ ይሄ ሁሉ ችግር ይደርስብኝ ነበር ስትል አሰበች ዳግም ከዛ ሰውዬ ጋር ላለመነጋገርም ሁሉም እንደተኙ ወጥታ ጠፋች...
    በመንገዷ ላይም አንድ የሩቅ ዘመዳቸውን አግኝታው እቤቱ ወሰዳት በርግጥ ህይወት የምታውቀው ዘመዳቸው እንደሆነ ብቻ ነው ሌላ የምታውቀው ነገር ቢኖር ሚስት እንዳለችው እሷም አረብ ሀገር ለስራ እንደሄደች ነው ... ታድያ ህይወትን ያክስቷ ባል ወደ ቤት እንድትመለስ ፈልጎ የነበር ቢሆንም ይሄ ዘላለም የተባለው ዘመዷ በፍፁም ለጅብ አውትቶ ከሰጠሽ ቡሃላ እሱ ጋር አትሄጂም ሲል ከአክስቷ ባል ጋር ሳይቀር ተጣልቷል...
    ህይወት ከዘላለም ጋር መኖር ከጀመረች ቀናት አለፉ ሰውን ለካ እንደመፅሃፍ ገልጠው ካላነበቡት ውስጡ እንደ ድፍን ዳቦ ነው ዳቦን ሲቆርሱት ውስጡ ፀጉር ሊገኝበት ይችል የለ? ሰውንም በደንብ ስንቀርበው ነው ማንነቱን የምናውቀው እናም ዘላለምም ልክ እንደዛው ነበር ህይወት በቀረበችው ቁጥር አፀያፊ ማንነቱን ማወቅ ጀመረች...
ዘላለም 3 ሚስት በየ አረብ ሀገራቱ ልኳል ከነዛም ውጪ እዛው ደብረ ዘይት የሬፍት ፋልይ ዩንቨርስቲ ተማሪ ከሆነች ወጣት ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምሯል ... ታድያ ህይወት ይሄን በማወቋ ለሱ ያላት አመለካከት ጥሩ አልሆንልሽ አላት ሴት በመሆኗ በብዙ ሴት መጫወቱ ያበሳጫታል ... ታድያ አንድ ቀን ከዚ መሄዴ አይቀርም እያለች ከሱ ጋር ኑሮዋን ቀጥላለች ... ከለታት አንድ ቀን ዘላለም አምሽቶ መጣ ህይወትንም በስርአት ሰላም ሳይላት ተቀመጠ ከሁኔታው እንደተረዳችው እዚ ያለችው ፍቅረኛው አርግዛበት መሆኑን አውቃለች...
በሷ ንዴት እያጉረመረመ እራቱንም አልበላም ህይወትም ምንም ማድረግ ስላልቻለች ተኛች ከቆይታ ቡሃላ ስትባንን እየሆነ ያለውን ማመን አቃታት...
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science



🤙🤙 ይህ ታሪክ ምን ያህል ሰዉ እንደሚከታተለዉ ለማወቅ እና ቀጣዩን ክፍል ቶሎ ለማገኘት አሁኑኑ🤙🤙🤙 በlike ይግለፁ👇
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 6⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal



ወደ ደብረዘይት እየተጓዝን ነዉ ሁለታችንም ተፈራራን እሱ ሂኩ አለኝ
እኔም አቤት
መኪና መንዳት ትችያለሽ አለኝ
...እኔም አልችልም መንጃ ፍቃድ የለኝም አልኩት
......እሱም ኢንሻ አላህ እኔ ነኝ የማወጣልሽ...እኔስ ያለመኪና መንቀሳቀስ አይሆንልኝም ይሄን መኪና አባቴ ነዉ ገዝቶ የሰጠኝ አላህ እድሜዉን ይጨምርለት አለኝ፡፡

........እኔም አዎ ትክክል ነህ የታክሲዉም ወጭ አለ ታክሲ በፈለክበት ሰአት አይገኝም ብታገኝም በየቦታዉ ስለሚቆም አላህ እርዚቅ ለሰጠዉ ሰዉ መኪና ገዝቶ መገላገል ይሻላል አልኩት፡፡
..
ደብረዘይት ደርሰን ወደ የት ነዉ የምንሄደዉ አልኩት
.....እሱም ባቡጋያ ሪዞርት ነዉ አለኝ፡፡ ባቡጋያ ሪዞርት የአዲስ አበባ ባለሀብቶች እሁድ ከቤተሰቦቻቸዉ የሚዝናኑበት ሁሉንም ያካተተ መዝናኛ ነዉ በጣም የሚያምር የደስ ደስ ያለዉ ብዙ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተማሪዉ የመንግስት ሰራተኛዉ የሚመርጠዉ መዝናኛ ነዉ፡፡
.... ደብረዘይት ደረስን ወደ ባቡጋያ ሪዞርት መኪናዉ ጉዞ ጀመረ፡፡
 ባቡጋያ ሪዞርት ገብተን መኪናዉን አቆመ ፡፡ የሚያምር መዝናኛ ነበር ፡፡  እየዞርን አብረን ሰልፊ ፎቶ እየተነሳን እስከ አስር አንድ ሰአት  ቆየን....

አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ሂኩ አይንሽን ጨፍኚ አለኝ እሺ ብየ ጨፈንኩኝ...... በስጦታ እቃ የተጠቀለለ ሰጠኝ.....ክፈችዉ አለኝ እሺ ብየ ስከፍተዉ የሚያምር የወርቅ የአንገት ሀብል ነበር፡፡
ያየሁትን ማመን አቃተኝ ለእኔ ነዉ ?? አልኩት እሱም አዎ ብሎ አንገቴ  ላይ አረገለኝ .......በጣም ደስ አለኝ እሱም የወደፊት የእኔ ነሽ ብሎ ...ከንፈሬን ሳመኝ ሲስመኝ በጣም ደነገጥኩ  .... ግን የደስታ ድንጋጤ ሳይሆን አይቀርም እኔም ደስ ብሎኝ በቃ ከምነግራችሁ በላይ ወደድኩት በመሳሳም የእሱን ፍቅር ልገልፀዉ አልቻልኩም.....ከአላህ ህግጋት ዉጭ ጭልም ወዳለዉ በእጅ የማይጨበጠዉ ፍቅር የሚባል የሚባል ነገር ተጃጃልኩ፡፡ የቀራሁት ቁርአን ሀዲስ እኔን ሊያስቆመኝ እኔን ሊከለክለኝ እኔን ከወንጀል ሊታደገኝ ካልቻለ የአላህ ቃል ቁርአን ካልመለሰኝ፡፡ የነብዩ ሀዲስ ለኔ ሂወት መስመር የማያሲዘኝ  ከሆነ፡፡ ዲኔ እኔን በሂወት ዉጣ ዉረድ ላይ ባስቀመጠዉ ህግ የማልተዳደር ከሆነ ቁርአን ሀዲስ መቅራቱ እንደኔ ላሉ ሴቶች በቀኝ ጆሮ አዳምጦ በግራ ጆሮ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡

ብቻ ቃል ግባልኝ
እውነቴን ነው ፍቅሬ ምንም አልዋሸሁም
ማስመሰል ማካበድ ፈፅሞ አላስብም
አንድ እውነት አለኝ የልቤን ልንገርህ
ከኔ አስበልጨ ነው እኔ አንተን የምወድህ !
ለምን ያልከኝ እንደሁ ሁሉ ነገሬ ነህ::

አሳ ከውሃ ውስጥ ወጥቶ እንደማይኖረው
እኔም ካንተ ብርቅ ሂወቴ እንደዛው ነው
ድብርቴ ወደር አልባ ፍፁም መራራ ነው::
መብላት መጠጣቴ መሳቅ መቦረቄ
አንተ ጋር ስሆን ነው አውቃለሁ ጠንቅቄ

እና ምን ልልህ ነው አትራቀኝ ውዴ!
እኔ ካንተ ሌላ ሂወት አለኝ እንዴ?
ድጋሜ ልንገርህ የምኖር ላንተ ነው
ያንተን ደስታ ማየት ከስኬት በላይ ነው
ከኔ ከራከኝ ግን የምሞት ያኔ ነው
አደራ እንዳትርቀኝ እስትንፋሴዬ አይንህ ነው::

ግን ፍቅሬ....
ይህን ሁሉ መንገር ለምን አስፈለገሽ
ቆይ አታውቅም እንዴ እኔ እንደምወድሽ?
ብለህ እንደምትለኝ አልጠራጠርም
እንደው ብሰጋት እንጅ ሳላምንህ አይደለም!
ይገርምሀል ውዴ ብዙ እጨነቃለሁ
ቀኑ ይቅር እና ለሊሊት አስባለሁ
እኔ
እስካለም ፍፃሜ ምንግዜም ያንተው ነኝ
ፍቅሬ ይህን ስልህ አትጨነቅብኝ
ከኔ እንደማትርቀኝ ብቻ ቃል ግቢልኝ ??
 
እሱን ሳየዉ ደስታ ይሰማኛል እሱ ጋር አብሮ መዝናናቱ ፎቶ መነሳቱ በጣም ደስተኛ እያረገኝ ነዉ ፡፡
ሰኞ አስራ አንድ ሰአት ተኩል ሆነ ፡፡
 ባቡጋያ ሪዞርት እየተዝናናን ነዉ ጥንድ ጥንድ ሁነዉ የሚዝናኑባቸዉ ለሁለት ሰዉ ብቻ የተሰሩ የሚመስሉ ጎጆዎች አሉ እነሱ ዉስጥ ሁለታችን ብቻ ገብተን ቁጭ አልን ፡፡የሚበላ ነገር አዘን  ቁጭ ብለን አይን አይኔን ያየኛል እኔም እያየሁት በቃ የሚያረገኝ ግራ ገባኝ
....ሳላስበዉ አንድ ድንገተኛ ጥያቄ ከሀይደር አፍ ወጣ ግን ሂኩ  ለምን ዛሬ አብረን አናድርም አለኝ...ጥያቄዉ አስደነገጠኝ ዝም ብየ አይን አይኑን ማየት ጀመርኩ....ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል ወደ አዲስ አበባ ከምንመለስ እዚሁ ደብረዘይት አድረን ነገ እንመለሳለን፡፡ አንድ ላይ እንደር እመኚኝ ለወደፊት የትዳር አጋሬ አንቺ ነሽ..ይህን የአንገት ሀብል  የገዛሁልሽ ስለማከብርሽ ስለምወድሽ ነዉ...
እመኚኝ ሂኩ አለኝ.............
ሀይደር ይቅርብን እኔ ከቤቴ ዉጭ አድሬ አላቅም እናቴም ትቆጣለች ተረዳኝ እባክህ
እሱም እንዴ የአንቺ ደስታ ደስታየ ነዉ መከፋትሽ ሁሌም ያስከፋኛል፡፡ ወላሂ እመኝኝ መቼም አልተዉሽም የመጀመሪያየ ነሽ ..አለኝ

....እኔም እናቴ ትቆጣኛለች ማደር አልችልም..ነገም ትምህርት እገባለሁኝ፡፡ አንተ የማትመልሰኝ ከሆነ እኔዉ እሄዳለሁ በትራንስፓርት መቼም ቢሆን አንተ ጋር ማደር አልችልም ሳንጋባ ኒካህ ሳናስራ አላህን ልንፈራ ይገባል፡፡ አልኩት ቆጣ ብየ
ግን ሀይደር የሚነግረኝ የሚሸመግልብኝ ቃላቶች ከኔ በላይ ሆነ መልስ ምቱን ከሀይደር እኔ ከማወራዉ እሱ የሚመልሰዉ እያመዘነ ይመስለናል፡፡ ሀይደር ጋር ልደር አልደር እናቴስ ምን ትለኛለች እያልኩ በተለያየ ሀሳብ ተምታትቻለሁ፡፡  እመኝኝ የሰዉ ልጅ ካልተማመን ለወደፊት ትዳር አንተማመንም ማለት ነዉ ሂኩ ለኔ አንቺ አመለካከትሽ ምንድን ነዉ ? እኔን አግብተሽ መኖር አፈልጊም እንዴ ንገሪኝ ቁርጤን ልወቀዉ እስከ አሁን እወድሀለሁ የምትይኝ ዉሸትሽን ነዉ ማለት ነዉ ይለኛል ሀይደር በሚያሳዝን አገላለፅ አለማመን ፡፡
እኔም ..ለመወሰን ግራ ተጋባሁ ግን አንድ ዉሳኔ ዛሬ ግድ ነዉ......


ሂክማ እሺ የምትል ይሆን በቀጣዩ ክፍል እናያለን

#Part 7⃣

ይ............ቀ..............
..........ጥ.............ላ..............ል

▶️ ሼር አይዘንጉ
4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
#ሀቢቢ_ባባ_ረጀብ_ጠይብ_ኤርዶጓን😍
በ1071 የዘመን አቆጣጠር ቱርክ በቤዛንታይን ላይ የተቀዳጀችውን 947ተኛ የድል ቀን በማስመልከት
አሚር ኤርዶጓን ለህዝቡ ባስተላለፉት መልእክት
" ህብረታችንን ማጠንከር አንድነታችንን ማጥበቅ አለብን እኛ ከተዳከምን እና ከተለያየን የውጭ ጠላት ሊቀራመቱን በር እንከፍታለን
ምዕራባውያን በቱርክ ላይ የከፈቱት ዘመቻ እኔን በግሌ ስለሚጠሉ አልያም ከስልጣን ሊያስወግዱኝ አስበው ከመሰላችሁ ስታችዋል የእነሱ ጦርነት ከእስልምና ጋር ነው የእነሱ ጥላቻ ከአዛን ድምፅ ጋር ነው
ጠላትን ማንበርከክ ልማዱ የሆነው የቱርክ ህዝብ መካ ፣ መዲና እንዲሁም የእየሩሳሌም ባለንብረት መሆኑን አውቆ ከጠላት ሊከላከላቸው ይገባል እነዚህ ቅዱስ ስፍራዎች በተለያዩ ቦታዎች ይገኙ እንጂ ሁላችንም ባለቤቶች ነን '
Via Bilal Zayed

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
.. ISLAMIC SCHOOL CHANNEL.. 💠
🏷   @Islam_and_Science @Islam_and_Science 🔗 JOIN US  🔗

💐💐💐 #ከተረሱ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች ዉስጥ:-
1. አልፎ አልፎ በባዶ እግር መጓዝ
2. በሶስት ጣቶች ብቻ ምግብን መመገብ እና ጣቶችን በሶፍት ወይም በሌሎች መሰል ማበሻዎች ከማጽዳት በፊት በምላስ መላስ
3. ከእንቅልፍ ሲነቁ ፊትን በእጆች ማበስ
4. ወንጀል ላይ ከወደቁ በኋላ ዉዱእን ባማረ መልኩ አድርጎ ሁለት ረከዓ የተውባ ሶላቶችን መስገድና ቀጥሎም የአላህን ማርታ መጠየቅ
5. ከተቀመጡበት ሲነሱ ፣ቁርአንን አንብበው ሲጨርሱ ወይም ዉዱእን ሲያጠናቅቁ ሱብሀነከ አላህመ ወቢሀምዲከ ላኢላሃ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ የሚለዉን ዱዓእ ማድረግ
6. በሌሊት ሰአት እቃዎችን ሁሉ መክደን ወይም መታሰር የሚችሉ ነገሮችን ማሰር
7. ለሁሉም ሶላቶች እና ለሁሉም ዉዱእ ጥርስን መፋቅ
8. ለእያንዳንዱ ፈርድ ሶላት ዉዱእን ማደስ
9. ሰዎች ቤት ለመግባት ሲያስቡ ሶስት ጊዜ ፍቃድን መጠየቅ
10. ከቤት ሲወጡ ወይም ወደ ቤት ሲገቡ ሁለት ረከዓ መስገድ
11. ቤት ሲገቡ በሲዋክ መጀመር
12. ለህጻናቶች ኢስላማዊ ሰላምታን ማቅረብ
13. ተራራማ (ዳገትማ ) ቦታዎች ላይ ሲወጡ ትንሽ ድምጽን ከፍ አድርጎ አላህ አክበር ማለት እና ረባዳ ወይም ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ሲደርሱ ሱብሀን አላህ ማለት
14. ለሚያውቁትንም ይሁን ለማያውቁት ሰው ኢስላማዊ የሆነዉን ሰላምታ ማቅረብ
15. ቁጭ ብሎ መጠጣት
16. ሶላት ላይ ወስዋስ ሲያጋጥመው ከሸይጧን በአላህ ከተጠበቁ በኋላ ወደ ግራ ጎኑ ሶስት ጊዜ ቱፍ ቱፍ ማለት
17. ሲተኙ በዉዱእ ሆኖ መተኛት
18. ፈገግታን ማንጸባረቅ
19. በጫማዎች መስገድ
20. ምግብን አለማነወር
21. ከእንቅልፍ በፊት የሚነበቡ ምእራፎችን ማንበብ
22. የዱሀ ሶላትን መስገድ
23. ገላን ከመታጠብ በፊት ዉዱእ ማድረግ
24. አድስ ልብስ ሲለብሱ ዱዓእ ማድረግ
25. የዶሮ ጩኸትን ሲሰሙ ዱዓእ ማድረግ / የአህያን ድምጽ ሲሰሙ ከሸይጧን መጠበቅ
26. ከእያንዳንዷ ሶላት በኋላ አያተልኩርሲይን መቅራት
27. ከመንገድ( ሰፈር ) ሲመለሱ መጀመሪያ መስጂድ ላይ ማረፍ እና ሁለት ረከዓዎችን መስገድ
28. ቋሚ የሆኑ ሱና ሶላቶችን ማዘውተር( በየእለቱ 12 ወይም 10 ረከዓዎቹን)
29. ሽበትን ከጥቁ ር ዉጭ ባለ ቀለም ማቅለም
30. ዊትር ሶላትን አዘውትሮ መስገድ
31. ወተት እና መሰል መጠጦችን ከጠጡ በኋላ መጉመጥመጥ
32. ሱና ሶላቶችን ቁጭ ብሎ መስገድ ( በእንቅልፍ ወይም በድካም ምክንያት
33. ለወንድም በስዉር ( በሩቅ) ዱዓእ ማድረግ
34. አስደሳች ዜና ሲያጋጥም የምስጋና ሱጁድ ማድረግ
35. አድስ ዝናብ በሚወርድበት ጊዜ ሰውነትን ገልጦ ማስመታት( ዐውራህ ያልሆነዉን )
36. የወደቀ ምግብን ካነሱ በኋላ የነካዉን ቆሻሻን አስወግዶ መብላት
37. ሌሊቱ ሲገባ ልጆች ከቤት እንዳይወጡ መቆጣጠር
38. ከመተኛት በፊት ፍራሹን መጥረግ
39. ለህመም ዱዓእ ሲያደርጉ እጆችን ህመም ከሚሰማብን ቦታ ላይ አስቀምጦ ዱዓዉን ማድረግ
40. ከእንቅልፍ ሲነሱ ወዲያዉኑ በአፍንጫ ዉሀን በመሳብ ከዚያም በኋላ ወደዉጭ ማስወጣት

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
እዉነተኛ እና አሳዛኝ ታሪክ

😢 #በመተት_የተሰናከለች_ነብስ_
                 #Part 7⃣


     ከእንቅልፏ የባነነችው ዘላለም ሲነካካት ነበር በእንቅልፍ ልቧም ዞላ ምን ሆነሃል ስትል ጠየቀችው እሱም ከሷ ጋር ወሲብ መፈፀም እንደሚፈልግ ነገራት የሰማችውን ማመን አልቻለችም ሰው እንዴት የገዛ ስጋውን ገላ ይመኛል? ህይወትና ዘላለም ለረጅም ሰአት ታገሉ አልፈቅድ ስትለውም እስከዛሬ ቀልቤሻለውና እንደፈለኩ ማድረግ እችላለው ሲል መታገሉን ቀጠለ ሊደፍራት ግን አልቻለም ...
ልክ ሲነጋ ዘላለም ሽጉጥ አውጥቶ "ለሊት የተፈጠረውን ለአንድ ሰው ትንፍሽ ብትይና ከዚች ቤት ንቅንቅ ብትይ በዚ መሳርያ አናትሽን ብዬ እገላግልሻለው!" አላትና ቤት ቆልፎባት ወጣ ህይወት ግንባሯ ላይ የተፃፈ ይመስል ያያት ሁሉ ወንድ ለወሲብ ይመኛታል ይሄ እድሏ ከልጅነቷ ጀምሮ አለቅሽ ያላት ህይወት ታድያ "ይሄ እጣ ፈንታ ነው ወይስ አለመታደል??" አለችና ጠየቀች ለራሷ ከዛም መልሳ "አይ ፈጣሪ ስለማያውቀኝ ነው በመከራ ላይ መከራ የሚደረብብኝ"...

     ህይወት ስራ አቁማ ቤት መዋል ከጀመረች ሳምንት አለፋት ሁሌም ሲመጣ ስራ ለመስራት እንዲፈቅድላት እሷም ለማንም እንደማትናገር ምላ ተገዝታ ትለምነዋለች እሱ ግን ከቤተሰብ አንድ ሰው ቢያውቅ መዘዙን ስለሚፈራ በፍፁም አልፈቅድም ይላታል ...ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ምሽት ላይ ዘላለም እቤት ገብቶ ህይወትን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚፈልግና ስራም እንዳገኘላት እንዲሁም በስራው በጣም እንዳፈረ ይነግራታል እሷም ከሁኔታው በርግጥም ተፀፅቷል ብላ በማመን ይቅርታውን ትቀበላለች ... ከዛም እራት ልታቀርብ ስትል ሂዊዬ ለምን እንደውም ውጪ አልጋብዝሽም ስራም ስለተገኘልሽ የደስደስ ነው ይላታል እሷም አይ እዚ እንብላ ችግር የለም ግን ዞላዬ የእውነት ስራውን ትፈቅድልኛለህ? ስትል ትጠይቀዋለች እሱም በሚገባ እንዲያውም ጥሩ ስራ ነው የተገኘልሽ ይላታል... ከዛም ግን ደጋግሞ ስለጠየቃት በሀሳቡ ተስማምታ ውጪ እራት ሊበሉ ወጡ...

     ዘላለም ያቀደው እቅድ ስለነበር ነው ውጪ ሊጋብዛት የፈለገው በዛም መሰረት ራት በልተው ሲጨርሱ እሷ ለስላሳ አዘዘች  .እኔ ወደ መፀዳጃ ሆድኩ ስመለስ ለስላሳዉን ጠጣች፡፡ ለስላሳዉ ዉስጥ ዘላለም እንቅልፍ እንዲወስዳት መድሀኒት አርጎበት ነበር፡፡  ከትንሽ ቆይታ ቡሃላ እራሷን አታውቅም ... ጠዋት ስትነቃ የዘላለም ሴራ ተሳክቶለት ሙሉ ህይወቷን መስዋት ያረገችለት ክብሯ በገዛ ስጋዋ ፈርሷል ይህን ማመን አቃታት ከዛ ቡሃላ ያለቀሰችው እምባ የተፈጠረውን የሚመልስ ቢሆን ክብረ ንፅህናዋን ቀርቶ የሞተውን አባቷን በመለሰው ነበር...

    ህይወት ቅስሟ ተሰብሮ ቀን ከሌት ማልቀሷን ቀጥላለች ትናገርብኛለች በሚል ፍራቻ ከቤት እንዳትወጣም ከልክሏታል በርግጥ ዘላለም የሚፈልገው ድንግልናዋን መገርሰስ ብቻ ነበር ከዛ ቡሃላ ዳግም አብሯት መተኛትን አላሰበም ... ህይወት ትምህርቷ ተቋርጦ ከቤተሰብ ተለይታ የሴጣን መጫወቻ መሆኗ ሳያንስ ዘመዴ ብላ የተጠጋችው ወንድ ይህን አይነት አስነዋሪ ድርጊት ፈፀመባት... ይህ በእንዲህ እንዳለ የዘላለም የሰማንያ ሚስት ከአረብ ሀገር መጣች በሷ ብር ጥሩ ቤት ቢሰራም ስትመጣ ግን ምንም አይነት ገንዘብ ሳያካፍላት ከዳት ህይወት ከራሷም አልፋ ለዚች ምስኪን ሴት አዘነችላት...

    ከዛ ግዜ ቡሃላ ለመጥፋት ብዙ ግዜ ሞክራ ይይዛትና ብትጠፋ ወይ ለሰው ብታወራ እንደሚገላት ያስጠነቅቃታል ህይወትም አርፋ የተገኘላትን ስራ ልትሰራ ወሰነች እናም እሱ ያገኘላት ስራ ሄዳ ተቀጠረች ሆኖም ስለከበዳት ከዛ ወታ የመጀመርያው ስራዋ ቦታ ተቀጠረች...
ከዚ ቡሃላ ነበር አዲስ አበባ የመሄድ እድል ያገኘችው በስራው ምክንያት ይሄኔ አንድ ሃሳብ መጣላት እሱም አረብ ሃገር መሄድ ነበር...

#part 8⃣

ይ............ቀ................
...........ጥ................ላ.............ል

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════••••••════•
.. ISLAMIC SCHOOL CHANNEL.. 💠
🏷 @Islam_and_Science 🔗 JOIN US  🔗

📚📚📚ከመፅሃፍት:-


📕ፅና መፈጠርህን የምታመሰግንበት የደስታ ቀን
ይመጣል፡፡ (እፎይታ)

📕ሕይወት ለውጥ ካልታከለበት ህልውናህ
አይታወቅም፣ የህልውናህ ምርት መገላበጥ ነው፤
አለበለዚያ አረህ መቅረትህ ነው፡፡ (የቃተተች
ነፍስ)

📕በዚህ አለም ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም
ትኖራለህ ወይ ትሞታለህ፡፡ (ኦሮማይ)

📕ደስታና መከራ ባገኘህ ጊዜ ሁለቱንም
በመጠንና በእርጋታ ተቀበል እንጂ በደስታ ጊዜ
ፈንጠዚያ በመከራ ጊዜ መጨነቅ አታብዛ፡፡
(መከረኞች)

📕ለመኖር መግደል የከይሲዎች ባህሪ ነው፡፡
ለመኖር ሌሎችን መበደል የብዙዎች በሽታ ነው፡፡
ለማኖር መኖር የጠቢባን ስጦታ ነው፡፡ (ከጣምራ
መንፈስ)

📕የሚያምር ቦታም ቢሆን እንኳ ከታሰሩበት
በስቃይ የተሞላ ነው፡፡

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🍃•••════•
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 7⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal


ሂኩ ዝም አልሽ እሳ አለኝ ....እቤት እናቴ ትቆጣለች  ከእናቴ ተነጥየ አድሮ አላቅም የት አደርሽ ብትለኝ  ምን እላለሁ አልኩት
...እሱም ምክንያት ፍጠሪ አለኝ፡፡
ነገም ሰኞ ነዉ ትምህርት አለኝ እንዴት ብየ እቀራለሁ ብየ የማምለጫ ሀሳብ ባቀርብ የኔ ሀሳብ አንድሱ በሚሰጠኝ መልስ ላስምነዉ አልቻልኩም እምቢ የምልበት ምክንያት አጣሁ፡፡ በዛ በዚህ ብሎ አሳመነኝ  ..እምቢ የምልበት ቃል የለኝም......

በመጨረሻም እሺ አልኩኝ....እሱም በደስታ ከንፈር ለከንፈር ጨዋታችንን አጧጧፍነዉ...በቃ የተለየ ስሜት ገባን እኔም ሁኔታዉ ስላላማረኝ ተረጋጋ ሁሌም ፧በሰአቱ  ይደርሳል አልኩት፡፡
...እቤት ደዉለሽ አስፈቅጂ አለኝ
......እኔም  ለእናቴ ደወልኩኝ
..እናቴም ስልኩን አነሳችዉ
 ሀሎ ልጄ ልደዉልልሽ ስል ደወልሽልኝ እንዴት ዋልሽ አለችኝ ጊዜዉ ወደ መቅሪብ ሶላት ደርሷል፡፡
እኔም ደህና ነኝ እናቴ ያዉ እንደነገርኩሽ የጓደኛየ ቤት አቂቃዉ በስራ ዉጥርጥር ብየ ነዉ አልኳት
እናቴም አይዞሽ ጓደኛሽ አይደለች የእሷን ደስታም ሀዘንም አብረሽ መወጣት አለብሽ አለችኝ
....እናቴ .አሁንም እዛ ላድር ነዉ  ስራዉ አላለቀም ፡፡ እናዳትሰጊ ልደዉልልሽ ብየ ነዉ አልኳት
.....እናቴም ቅር እያላት ሙሉቀን ሳላይሽ ዋልኩ አሁንም ቀረሽብኝ እሺ ምን አረጋለሁ ልጄ አደራሽን ተጠንቀቂ አለችኝ፡፡ ጭራሽ እኔን ወንድ ጋር ትሄዳለች ብላ አስባዉም አታቅ እናቴ በኔ የምትተማመንብኝ ነኝ ወይኔ ሂክማ ምን አረጋለሁ በሀራም መንገድ ፍቅር ዋሽቼ የማላቀዉን ለወደፊት ተስፋ እና በስጦታ አንበሽብሾ ይሄዉ ለሀይደር ብየ እየዋሸሁ ነዉ፡፡
...እኔም እሺ አልኩኝ
.......እናቴም ግን ሙሉቀን ምግብ ቀምሰሻል አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ አልኩኝ የእናት አንጀት የምታስበዉ አሁንም ለኔ ነዉ፡፡
....እናቴም እሺ ንፋስ እንዳይመታሽ ከምታድሪበት የጓደኛሽ ቤት ሹራብ ደረብ አርገሽ ስሪ ልጄ ...አይዞሽ ደህና እደሪ..ነገ ግን በጠዋት ነይ ዛሬ ሙሉቀን አላየሁሽም ...አንቺዉ ነሽ ያለሽኝ ትናፍቂኛለሽ ነገ አይንሽን እንዳይሽ አለችኝ
...እኔም እሺ እናቴ ደህና እደሪ ብየ ስልኩን ዘጋሁት ፡፡

ሀራም ለመስራት እናቴን ስንቱን ዉሸት ዋሸሁ..እናቴ አምናኝ አልጠረጠረችም ምን ይደረጋል...ሀይደርም ማሻ አላህ በዉሸት ማሳመን ትችያለሽ ማለት ነዉ አለኝ፡፡

እኔም ምን ላርግ ብለህ ነዉ ምንም አማራጭ የለኝ ፡፡
ለአንተ ብየ ነዉ እንጂ እንደዚህ የምዋሸዉ እናቴን ዋሽቼ አላቅም ነበር ምን ይደረጋል አልኩት፡፡
እሱም ነገ እናትሽ የጓደኛሽን ቤት አሳይኝ ብትልሽ እሳ አለኝ
....እኔም እናቴ ታምነኛለች አትለኝም አልኩት፡፡

አንተስ አታስፈቅድም እንዴ አልኩት
..እሱም አስፈቅጃለሁ አለኝ፡፡ አሁን ሰአቱ ከምሽቱ 1:30 አካባቢ ሁኗል የጨረቀዋ ዉበት ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ደስ የሚል ድባብ ነበረዉ፡፡ ግን የሚገርማችሁ አሱር እና መቅሪብ ሶላት አልሰገድንም ነበር፡፡ እሱም እንስገድ አላለኝም....
እዛዉ ባቡጋያ ሪዞርት እራት አዘዝን እሱም ማደሪያ መኝታ ክፍል ያዘ፡፡
እኔም ሀይደር  ዛሬ እኮ አሱር እና መቅሪብ አልሰገድንም እኮ አልኩት
...እሱም ሂኩ የሚገርም ነዉ እየቀለደ ሙሳፊር ነን እኮ በዛም ላይ  የአንቺ ፍቅር ሶላት አስረሳኝ በይ ዉዱእ እናርግ እና እንስገድ አለኝ፡
 ባቡጋያ ሪዞርት በሚገኘዉ እዛዉ መዝናኛዉ ዉስጥ አነስ ባለች ቤት መስገጃ ቦታ በተዘጋጀች ቤት እኔ መጀመሪያ አሱር መቅሪብ ቀዷዉን  ኢሻን በወቅቱ  ሰገድኩ

እኔ ሰግጄ ስጨርስ እኔ ወጣሁ እሱ ገብቶ ሶላቱን ጀመረ አሱር መቅሪብ ኢሻ  ለመስገድ ገባ፡፡....ግን ቶሎ ብሎ ሶስቱን  ሶላት ጨርሶ ከመስገጃ ቤቱ ወጣ ፡፡ ...... ሀይደር ሶላት የሰገደ ሳይሆን የህሊና ፃለት አርጎ የመጣ ነዉ የሚመስለዉ፡፡ በጣም ፈጠነብኝ ..እኔም ፈጠንክ ልለዉ አልኩና ዝም አልኩት፡፡
      የአዘዝነዉ እራት ደረሰ እየተጎራረስን በላን በቃ የሚምር እራት ግብዣ ነበር፡፡ አንቺ ጋር እራት ስበላ የመጀመሪያየ በጣም ደስተኛ ነኝ ሀዩ አንቺስ አለኝ...
  እኔም ደስተኛ ነኝ አልኩት
እሱም ኢንሻ አላህ ዛሬ ሆቴል ብላን ለወደፊት አንድ ላይ ልጆቻችንን ይዘን እቤታችን ነዉ የምንበላዉ ብሎ ጉንጬን ሳመኝ፡፡

በልተን ጨረስን አሁን ሰአቱ ከምሽቱ 2:30 ሁኗል ፡፡ ሂኩ ወደ መኝታ ክፍል እንሂድ አለኝ ፡፡ እኔም ቅር እያለኝ ደስም እያለኝ ተያይዘን መኝታ ክፍል ገባን ......በሩን ሲከፍተዉ የሚያምር ክላስ ነዉ ሻማ የበራበት ነበር፡፡ ሂጄ አልጋዉ ጋር ቁጭ አልኩኝ እሱም በሩን ዘግቶ ከጎኔ መጥቶ ቁጭ አለ፡፡ ጨዋታዉ ጀመረ ...ሀይደር  ወደ እኔ ተጠጋ እና ሂኩ አለኝ .....እኔ በእሱ ፍቅር ተሸንፊያለሁ የሚያረገኝን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ...........ወደ እኔ ተጠግቶ  ሂኩ እወድሻለሁ ብሎ ..........,

#part 8⃣

ይ......................ቀ
...........,ጥ.............ላ...........ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
ይህ በፎቶው ላይ የምታዩት ኢስማኤል ካሪሚ የተባለ ኢራናዊ መምህር ከሚኖርበት ከዋና ከተማው ከቴራን 90 ኪ-ሜትር ወደ አድራቢ የምትባል አነስተኛ መንደር እየተጏዘ ትምህርት መማር ላልቻለ ብቸኛው የከተማዋ ልጅ በየጊዜው ትምህርት አስተምሮት ይመለሳል !!!

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ሁሉን ለአንተ ሰጠው!
ሰው ቢወድህ ፥ለግዜው ነው፣
ቢቀርብህም፥ ለወረት ነው ፤
ሁሌ ፊቱን ፥የማያዞር፣
ግዜ አይቶ ፥ማይቀየር፣
ማይሰለችህ፥ የማይጥልህ፣
ሁሌም ከፊት ፥ሚደርስልህ።
የችግር፥ የህመምህ ፈዋሽ፣
ሀዘን ሽሮ፥ ደስታን ለጋሽ ።
ፈጣሪ ነው ፥አንድ ጌታ ፣
የማይጥልህ ፥ቀንም ማታ ።
✿ሰውማ ሰው ነው ✿
በቁስልህ ፥እንጨት ከቶ፣
አስደግፎህ ፥ጥሎህ ሸሽቶ፣
ልብን ሰብሮ ፥አስከፍቶ፣
ይሳለቅብሃል ፥በፌስቡክ ጎልቶ።
በሰውም ሰው፥ ቅን ልቦና፣
ያለው ቢኖር፥ ያየ ፈተና፣
የሚረዳ ፥የሰው ችግር፣
ለጊዜው ነው ፥ቢፈጥር ግርግር፤
ቅን ቢሆን እንጂ ፥ቢያዝንልህ፣
መቸም ጤናን ፥አያዝልህ ።

።።።።።።።።።።።።።።
@Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
።።።።።።።።።።።።።።

🚫 Share it now
እዉነተኛ እና አሳዛኝ ,ታሪክ

😢 #በመተት_የተሰናከለች_ነብስ_
                 #Part 8⃣


ህይወት አረብ ሀገር ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመረች ይሄን ያረገችው ከዘላለም በመደበቅ ነበር ...ታድያ አንድ ቀን አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ መሄድ ፈልጋ እንግዳ ስለነበረች ለቦታው ግር ይላታል ይሄኔ ኤፍሬም የሚባል ጠይም ረዘም ያለ የደስ ደስ ያለው ወጣት ወደሷ መጥቶ የኔ እህት ምን ልርዳሽ ? ይላታል እሷም ጠላቶቿ የሆኑትን ወንዶች ረስታ ቦታ እንዲያሳያት ጠየቀችው ኤፍሬምም በቅንነት ተባበራት ... ከዛ ቡሃላ ግንኙነታቸው ጠበቀ ብዙ ግዜ እዛ ስትሄድ ይገናኛሉ ... ህይወት ለመጀመርያ ግዜ ወንድ ልጅ ልቧ ውስጥ ቤት ሰራ ... ኤፍሬምን የወደደችው ከነ ሙሉ ማንነቷ ስለወደዳት ነው።
     ህይወት በርግጥም ከበፊቱ አሁን ደህና ናት የሚያስጮሃት ቀንሷል...
ከወራት ቡሃላ ተሳክቶላት አረብ ሀገር ቤሩት እንድትሄድ ቪዛ መጣላት ይሄንም ለዘላለም ስትነግረው በዛን ሰአት ሁለተኛ ሚስቱ ከአረብ ሀገር ተመልሳለት ስለነበር ምንም ሊላት አልቻለም ቀኑ ሲደርስ የዘላለም ሚስት ስለአረብ ሀገር ትንች መረጃ ሰጠቻትና ሞባይሏን ይዛ ሄዳ በዋይፋይ እንድትጠቀም መከረቻት ከዛም አዲስ ከተዋወቀችው ነገር ግን ሙሉ እሷነቷን ከሰጠችው ኤፍሬም ጋር በለቅሶ ተለያይተው ወደ ቤሩት ከተማ ገባች ... በኤፍሬም ጥረትም ቤተሰቦቿን ሄዳ ተሰናብታቸዋለች!

    ህይወት ቤሩት ገብታ የስደትን ኑሮ 'ሀ' ብላ ጀመረች ወድያው እንደሄደች ለአራት ወራት ያህል ስልክ ስላልተፈቀደላት ማንንም ለማዋራት እድል አላገኘችም ነበር ልክ ባራተኛ ወሯ ግን ለኤፍሬም ደወለችለት ... ከዛ ሴትየዋ ስትወጣላት ዋይፋይ ሞልታ ፌስቡክ መጠቀም ጀመረች ከዛም ከኤፍሬም ጋር ብቻ ታወራ ጀመር ከሱ ጋር ማውራት ለሷ ትልቅ ደስታ ነበር በብዙ ፈተናዎች መሃልና ከብዙ መሰናክሎች ቡሃላ በልቧ የነገሰ ብቸኛ ሰው ነው ከልቧ ታፈቅረዋለች...
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ቆሻሻ ልትጥል ከፎቅ ስትወርድ አንዲት ኢትዮጵያዊ አገኘቻት እናም የት እንደምትሰራ ስትጠይቃት ነገረቻት ልጅቷም "አሰሪሽን አውቃታለው ክፉ ናት ካንቺ በፊት አንዷን 6አመት አንዷን 10ወር አስፈግታ ባዶ እጃቸውን ልካቸዋለች " አለቻት አስከትላም ቢሮሽ የት ነው? ስትል ጠየቀች ህይወትም በጭራሽ ቢሮ ሄዳ እንደማታውቅና ወረቀቷም እንዳልተሰራ ነገረቻት...
      በተጨማሪም እዛ ቤት ውስጥ ሰራተኛ የሚቆየው ሴትየዋ በመተት ስለምታስር ነው ብላ ነገረቻት...
ከዛ ቀን ጀምሮ ህይወት መፍራት ጀመረች ሳትቀደም ለመቅደምም ወሰነች ታድያ አንድ ቀን ሴትየዋ ህይወትን ለብቻዋ የምትወስዳት ቦታ እንዳለ ነገረቻት ይሄኔ ከፈራችው ነገር ጋር ስለተጋጨባት በፌስቡክ ከተዋወቀቻት ጠፍታ እዛው ሀገር ከምትሰራ ጓደኛዋ ጋር በመነጋገር ጠፋች ልጅቷም ያለችበት ድረስ በመሄድ እሷ የምትኖርበት ቤት ወሰደቻት ልጅቷ ሰብለ ትባላለች እዛው ቤሩት ጠፍታ መስራት ከጀመረች ረጅም ግዜን አስቆጥራለች ...
ህይወት ሰብለ ጋር ስትሄድ በመጀመርያ ደስተኛ ነበረች ከዛ ግን እዛ ያለው ነገር ደስ አልልሽ አላት ከሰብለ ጋር የሚኖሩት ብዙ ናቸው በዛ ላይ ይጠጣሉ ያጨሳሉ ህይወትንም ይገፋፏታል እሷ ግን ይሄን ህይወት ፈፅሞ አትፈልግም ... ይባስ ብሎ አንድ ቀን ሰብለ ከሱዳናዊ ወንድ ጋር ህይወትን ልትሸጣት ስትደራደር ህይወት ድንገት ሰማች ...
#Part 9⃣

#ይ............ቀ
........ #ጥ.......... ላ ......... ል



🏷   @Islam_and_Science @Islam_and_Science 🔗 JOIN US  🔗
ዘመናዊነቴ

ዘመናዊነቴን ይቀማኛል ብለሽ ፣
ዘመነኛ መሆን ቁሳዊነት መስሎሽ ፣
ብጫቂ ደርበሽ ገላሽን አራቁተሽ ፣
በውዳቂ ስክሪን አይኖችሽን ተክለሽ፣
ዝነኛ ላልሻቸው ለሀጭ አዝረክርከሽ፣
በህልም በእውንሽ እነሱን እያለምሽ፣
የሆኑትን ሁሉ ለመሆንም ቃጣሽ፣

የሰይጣን አሽከሮች መሆናቸው ጠፍቶሽ፣
የእነሱ ባሪያ ከሆንሽም ሰነበትሽ፣
ህይወትን በከንቱ ብቻ እየገፋሽ ፣
በሰቀቀን ኑሮ ከጌታሽ ተጣልተሽ ፣
ለሰዎች ምስጋና ደፋ ቀና እያልሽ ፣
ከነጎደ ወዲህ ይህ አጭሩ እድሜሽ ፣
ደምም ብታለቅሺ ምንም አይፈይድሽ ፣
ተመለሽ እህቴ በግዜ ልምከርሽ ፣
የነጮች ግርግር ስሜትሽን ቀስቃሽ፣
የስልጣኔ ጥግ ለስጋሽ መምነሽነሽ፣
ልብሽ ቀፎ ሆኖ ለስሜት ርካሽ ፣
ሆኖ ካገኘሽው በቃ አለቀልሽ ፣
ፈጣሪን ረሳሽ ከምንም ያስገኘሽ፣

ይሄን ማንነትሽ ላንቺ የለገሰሽ ፣
ከጌታዬ ቅጣት እኔ ብሰጋልሽ ፣
በርህራሄ ልብ ከቶ ባስብልሽ ፣

በቃላት ድርደራ ልብሽ እንዲፀና ፣
ከጎንሽ ለመሆን ፋናሽ እንዲቃና፣
ማለት ጀምሬያለሁ ላንቺ ደፋ ቀና፣
ሰላትን ጀምረሽ ሂጃብሽን ለብሰሽ
ከኮተት ርቀሽ ልብሽን አርጥበሽ፣
ሩቅን አልመሽ የድሮው ትተሽ፣
ወኔሽን ሰብስበሽ አልቀርም ሳላይሽ፣
በቅርቡ ተዉበሽ በኢማን ታጅበሽ፣


..👇👇👇👇👇👇
🏷   @Islam_and_Science @Islam_and_Science 🔗 JOIN US  🔗
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 8⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal


በእሱ ቁጥጥር ሁኛለሁ የመጀመሪያየ ነበር እሺም እሞቢም የማለቱ ድፍረቱን አጥቻለሁ በስሜት ወድቂያለሁ፡፡ ሀይደር እንደፈለገ ያረገኝ ይዟል ሲፈልግ ይስመኛል ........... በቃ የማላቀዉ አለም ዉስጥ ገባህ እንጃ የዛን ጊዜ የእሁድ ምሽቱን ለመናገር ይቀፈኛል፡......ልብሴን እንኳ እራሴ አላወጣሁም የሚሆነዉ ነገር ማስታወስ አልቻልኩም ስሜት ላይ ነበርኩኝ.......

 ፍትጊያዉ ጀምሯል፡፡ የሆነ ሰአት ላይ ካቅሜ በላይ ሁኖ ብቻ ስጮህ አስታዉሳለሁ፡፡
እሱም አይዞሽ ሂኩየ እያለ ወደ ማላቀዉ አለም የትንሽ ሰአታት ደስታ የዘላለም ሂወት ማጨለሚያ የሆነዉን አፀያፊ ስራ እየሰራሁ ነዉ፡፡ ፍትጊያዉ አልቻልኩትም ጮሀኩን የሚሰማኝ የለ....,.,..,,,ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ  ያ ያማረ ነጭ አንሶላ በቀይ ደም መልኩን ቀየረ፡፡
.....ክብሬን ለሀይደር በሀራም መንገድ አስረከብኩ...ቀይ ደም ሳይ ደነገጥኩኝ.....ወዳዉ እዛዉ መኝታ ክፍል ሻወር ነበር ታጠብኩ ...ከታጠብኩ ቡሀላ ወደ ግድግዳ ዙሬ ተኛሁ እሱም ወደ እኔ ዙሮ ሂኩ ሲለኝ ቆይ ትንሽ ልረፍ ደክሞኛል አልኩት፡፡

...እሱም እሺ ብሎ ተኛ እኔም ተኛሁ፡፡ ግን ተኝቼ መጨነቅ ጀመርኩ ቢተወኝስ እያልኩኝ...እናቴን ለዚና ዋሸሁኝ....,እናቴ ብታየኝ ምን ትለኛለች አምናኝ እናቴን ከደሇት...

ሱብሂ ሶላት ደረሰ  ዉዱእ አርጌ ሰገድኩ ግን ዱአየ አላህ ዚና ሰራሁ ማረኝ ሳይሆን....አላህ ሀይደርን  የትዳር አጋሬ አርግልኝ ነበር፡፡
...እኔም ሱብሂ ተነስ ስገድ አልኩት እሱም እሺ እሺ እያለ ሳይሰግድ ቀረ፡፡

የማይነጋ የለም ነጋ ቁርስ እዛዉ ኩሪፍቱ ሆቴል
አዘዘ በላን ሂኩየ በጣም ነዉ ያኮራሽኝ ማሻ አላህ ዘልዛላ አይደለሽም ማሻ አላህ ኮራሁብሽ አለኝ፡፡ ቁርስ በልተን ጨረስን ....ከዛ ከደብረ ዘይት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ጉዟችንን ቀጠልን  ከደብረዘይት ተመልሰን ገርጂ ደረስ በመኪና ሸኘኝ ከዛም ተሳስመን፡ተለያየን፡፡ አሁን እኔም ወደ እናቴ ጋር እቤቴ ድረስ ሸኘኝ እኔን እቤቴ ካደረሰኝ ቡሀላ እሱም ወደ ቤቱ ተመለሰ.......
......እቤቴ ሄድኩኝ እናቴ እንኳን ደህና መጣሽ ብላ ግንባሬን ሳመችኝ...የእናት ነገር ብርድ ሳይበርድሽ አደረ ልጄ አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ አልኳት
......በይ አረፍ በይ ስራዉን አጠቃለላችሁ ጓደኛሽን አግዥሻት አለችኝ
....እኔም አዎ እናቴ አልኩኝ፡፡
ቁርስ ብይ አለችኝ
እኔም ጓደኛየ ቤት በልቼ ነዉ የመጣሁት አልኳት፡፡
እናቴም እሺ አለችኝ፡፡ መቼም የዛሬዉ ትምህርት ቀርቷል ነገ ድካሙ ሲለቅሽ ትሄጃለሽ አለችኝ፡፡

     ዚና ስሰራ እንዳደርኩ የሴትነት ክብሬን እንደተነጠኩ ብሰማ እናቴ ምን ትለኝ ይሆን......
ብየ ብቻየን አለቀስኩኝ ........እንባዬ ዱብ ዱብ ይላል ግን የማለቅሰዉ እኔም ግራ ገብቶኛል፡፡ ሀይደር ይተወኛል ብየ አስቤ ነዉ ??ወይስ ላተቅረቡ ዚና ጌታየ ብሎኝ እኔም የጌታየን ትእዛዝ መጣሴ ነዉ?? ነገ አላህ ፊት ሲጠይቀኝ መልስ ይኖረኝ ይሁን ብቻ እንባየ በሁለቱ ጥያቄ እየጠየኩ ብቻ መልስ በሌለዉ ጥያቄየ እያለቀስኩ ነዉ፡፡

 ውስጤ ብሶት አለ
.
እንደ ጥገኛ ትል ከሆድ የማይጠፋ
ውስጤ ችግር አለ ከሀገር የሚሰፋ
ስኖር በዚች አለም ስርክ የገበርኩለት
በዋይታ በዬዬ....እልፍ ያለቀስኩለት
በእንባዬ ብቻ.....በትግስት ያለፍኩት
አካልን አድምቶ .... ሆድ የበጠበጠ
ከጠጠር ጠጥሮ ውስጥ የተቀመጠ
ብሶት አለ ውስጤ
,
ቃላት ማይገልፀው ከሆድ ማይጠፋ
አካሌ ላይ አፎ.....ሁሌም የሚፋፋ
እንባ እየወለደ ...ሀዘን የሚያረግዝ
ደስታዬን በዝብዞ ልብ የሚጠዘጥዝ
እንደ ጥገኛ ትል ከሆድ የማይጠፋ
ውስጤ ችግር አለ ከሀገር የሚሰፋ
ውስጤ ብሶት አለ ፈፅሞ እማይጠፋ

      ምሳ ሰአት ላይ ትናንት ዋሽቼ የለ ያደርኩት እጓደኛየ ቤት አቂቃ አለ ብየ ...እናቴን ሄድኩ ብየ ከቤት ወጣሁ በአዲስ አበባ ጎዳና ከገርጂ ተነስቼ እስከ ጎሮ ድረስ በእግሬ እየሄድኩ ብቻየን እያለቀስኩ እንደ መሳቅም እያልኩ ጅል ይመስል የተለያየ የተዘበራረቀ ስሜት እየተሰማኝ እየሄድኩ ነዉ  ግን የት እንደምሄድ አላቀዉም...........ብቻ እግሬ ወደ መራኝ ቦታ  እየሄድኩ ነዉ፡፡

      ሳላስበዉ ድንገት ስልኬ ጠራ የደወለዉ ሀይደር ነበር ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ የት ነሽ ምሳ ልጋብዝሽ አለኝ፡፡ እኔም ያለሁበትን ቦታ ነገርኩት መኪና ስላለዉ ብዙ ደይቃዎች አልፈጁበትም  ቶሎ መጥቶ ወደ ወበሪ ሆቴል ሂደን ምሳ ጋበዘኝ፡፡ ምሳ ከበላን ቡሀላ ከሰአት የት ነሽ አለኝ ፡፡ እኔም የምሄድበት የለም አልኩት
..........ሂኩ ለምን ደብረ ዘይት አንሄድም ዛሬ ግን ለመዝናናት ብቻ ነዉ ፡፡ ደብረዘይት ከተማዋን አይተናት ለመመለስ ነዉ እንጂ ለሌላ አይደለም አለኝ አይን አይኔን እያየ... እኔም እምቢ የማለት ድፍረት አጣሁ አንዴ ልቤን ሀይደር ወስዶታል፡፡ እሺ ስለዉ  እዛዉ ተሳሳምን አይ ወንጀሌ ...............
ጉዞ ዳግም ወደ ደብረዘይት ለስለስ ያሉ የሱዳን  ነሽዳዎች መኪናዉ ላይ ከፍቶት ጉዟችንን ቀጠልን፡፡

    የኔ ነገር ገና አላለቀም ዳግም ትናንት ክብረ ንፅህናየን የተነጠኩበት ደብረዘይት  እየሄድኩ ነዉ ፡፡ የወደፊቱ ባሌ ሀይደር ጋር ነኝ፡፡ እሁድም ደብረዘይት ሰኞም ደብረዘይት   በሚቀጥለዉ part ጋር የሰኞ ከሰአት  ጉዴን አጫዉታችሇለሁ

#Part 9⃣

ይ.......ቀ..........
..............ጥ..........ላ..................ል
▶️ሼር ለምን እንደማታረጉ አይገባኝም ሼር አይዘንጉ አያስከፍልም እኮ ☺️
4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
እናት ሁሌ ትታይ በፍቅር እይታ
የትውልድ ምሰሶ የሐገር አለኝታ
ማለቂያ የለውም የእናት ውለታ
ዘጠኝ ወር በሆዳ ከዛም ተሸክማ
የምታሳድግ ናት ሲታመሙ ታማ
መቼስ አይከፈል የናት ውለታዋ
አለሁልሽ እንበል ከፊት ከሁዋላዋ
በጤና እንዲኖር መላ ህፃናቱ
እንክብካቤ ያርግ ሁሉም ሰው ለናቱ
ማረፊያዋ እንሁን ወንድም ሆነ ሴቱ
*
** በያ…… በያችን

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ሰበር ዜና
አማርኛ የአፍሪካ ህበረት ስድስተኛው የሥራ ቋንቋ ሆነ።
አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ህበረት ስድስተኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹የኢትዮጵያ ክብር፣ በተለይም በአፍሪካ ያላት ጥናታዊ ታሪክ እና ለአፍሪካውያን አንድነት፣ ክብርና ነፃነት ያደረገችው አስተዋፆ ዛሬ ምላሹን አገኘ።

🇪🇹💚🇪🇹💐🇪🇹💛🇪🇹💐🇪🇹❤️🇪🇹
..
🏷   @Islam_and_Science @Islam_and_Science 🔗 JOIN US 🔗
አቡኬ በአወሊያ ግቢ እንዲህ አለ
<ስነ ምግባር ማለት መቅለስለስ አይደለም። ጀግንነት የታላቅ ስነ ምግባር መገለጫ ነው!>
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እማራለሁ ፕሮግራም ላይ

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
ማሻ አላህ😍
#ይህ ወጣት ሙሉ #ቁርአንን_በእጁ ከትቦ!
ለውድ ባለቤቱ" መህር "ሰጥቷል ! እሷም የአላህን ቃል በደስታ ተቀብላለች! #ከአላህ_ቃል የበለጠ ምን ያማር መህር አለ !
እሷም ቀርታበት የጀነት ቤትዋን ስትሰራ !
እሱም በቀራቹ ጊዜ ሀሰና እየተመዘገበለት ይኖራሉ!
አላህ ስራቸን ወዶላቸው ዳግም በጀነተል ፍርዶስ አብሮ የሚሞሸሩ ያድርጋቸው

🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋
﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋ ﹋﹋ ﹋
JOIN
telegram.me/Islam_and_Science

telegram.me/Islam_and_Science
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄
🌸«::::::::::::» «:::::::::::» «::::::::::::::»🌸
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 9⃣

ፀሀፊ #አሚር #ሰይድ
በIslamic university channal

9
     ደብረ ዘይት   ደረስን በመኪና እየዞርን አየናት ከዛ ሰአቱም አሱር ደረሰ ሶላታችንን ሰገድን .... ደብረዘይት የሚገኘዉ ባቡጋያ ሪዞርት ወደ እዛ ሄድን፡፡
ባቡጋያ ሪዞርት ደረስን አንድ ላይ ሁነን ሰልፊ ፎቶ ተነሳን በቃ ሁለታችንም ተቅበጠበጥን እየሄድን መሳሳም ፎቶ መነሳት ሆነ .....ከዛም ሂኩ ይህን ሁለት ቀን በጣም ደስተኛ ነኝ አንቺስ አለኝ እኔም አዎ ብየ መለስኩለት...........
........ተቃቀፍን ሳመኝ.....ነይ የማሳይሽ ነገር አለኝ ብሎ ወደ  ባቡጋያ ሪዞርት የሚገኘዉ መኝታ ክፍል ይዞኝ ገባ፡፡
ሀይደር  ነገሮቹን አመቻችቶ ጨርሷል ፡፡ እመኝታ ክፍል ኬክ አዘጋጅቶ በሁለታችንም ስም የተፃፈበት ኬክ አብረን ቆረስን ......በኬኩ እየተጎራረስን በቃ መደባደብ ጀመርን ኬኩን ሲቀባኝ እኔም ስቀባዉ የሌለ መነካካት ...ምን ልበላችሁ ሰዉ ከሚሰራዉ ነገር ወጣ ያለ ነገር እየሰራን ነዉ...እሱም ልብሱን አወለቀ ...በመቀጠልም የእኔን ልብስ አወለቀዉ፡፡ እምቢ የምልበት ድፍረቱ የለኝም.......
፡.......ሁለተኛዉ የሀራም የስሜቴን እርካታ ሰኞ ከአሱር ቡሀላ እስከ መቅሪብ ድረስ ለወደፊቱ ባሌ ይሆነኛል ብየ የአሰብኩት ሀይደር ጋር በ ባቡጋያ ሪዞርት መኝታ ክፍል.....በሚያስጠላ እንስሳዊ በሆነ ስሜት ትንቅንቅ አደረግን ፡፡ መቅሪብ ላይ ይበቃናል ....እናቴ ምንም የማስፈቅድበት ምክንያት የለኝም ጊዜዉ መሸ ትናንት ስላደረኩ ዛሬ ማደር አልችልም  እንዳትቆጣ ወደ አዲስ አበባ  እንመለስ አልኩት.......
......እሱም እሺ አለኝ...እቅፉ ዉስጥ እንዳለሁ ..
ሂኩ ምን እንደናፈቀኝ እንደ ቸኮልኩ ታቂያለሽ አለኝ
.......እኔም አረ አላቅም አልኩት
..........እሱም እናትሽ ጋር እስከ መተዋወቅ በጣም ቸኩያለሁ አለኝ
....እኔም ወላሂ በል አልኩት
.........እሱም ወላሂ አለኝ፡፡ አመንኩት በጣም ከስከዛሬዉ በበለጠ መልኩ ወደድኩት......ግን እሱ ጋር ሀራም መስራቴ የአላህን ትእዛዝ መጣሴ ምንም አልመሰለኝም.......
ከመኝታችን ተነስተን ባቡጋያ ሪዞርት ወጥተን
 ወደ አዲስ አበባ እየተመለስን ነዉ.....
አዲስ አበባ ደረሰን እቤቴ  ገርጂ ድረስ ሸኘኝ ከንፈር ለከንፈር ተሳስመን ተለያየን....እቤቴ እናቴን እንዴት ዋልሽ ብየ ገብቼ የደስታ ስሜት እየተሰማኝ አልጋየ ጋር ጋደም ብየ ስለ ሀይደር ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በጣም ወድጀዋለሁ ለእሱ የሴትነት ክብሬን  ማስረከቤ እንደ ክብር እንጂ ወንጀል መስሎ አልታየኝም......የሰጠኝን የጣት ቀለበት እያየሁ ደስተኛ ሁኛለሁ፡፡

 በቃ እወድሀለሁ
——————
ለምን አትበለኝ ምክኒያት የለኝም፣
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም፣
ብቻ እወድሀለሁ መዉደዴም ጥልቅ ነዉ፣
ፍቅርህ ለእኔነቴ የልቤ ዙፋን ነዉ፣
ህያዉ የምሆነዉ አንተን በማፍቀር ነዉ፣
ሀቁ ቃል ይሄ ነዉ ሰርክ አዲስ የማምነዉ፣
ቂልነት አይደለም ሁሌ አንተን ማለቴ፣
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርህ መክሳቴ፣
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ፣
በቃ አንተን መዉደድ ነዉ ደስታ መደሰቴ፣
ዉለታን ፈልጌ ዉደደኝ አላልኩም፣
ፍቅር ሰጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም፣
እንዴት ለምን ካልከኝ እኔም አላወኩም፣
በቃ እወድሀለሁ ማለቴን አልተዉኩም፣
አዎ እወድሀለሁ፣
አዎ አፈቅርሀለሁ፣
ፍቅርቅር አድርጌህ በፌሽታ እኖራለሁ፣
ዉድድ አድርጌህ አንተን እፎይታ አገኛለሁ፣
ዉዴን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ፣
በፍቅርህ ዉቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ፣
አንተ ካለህልኝ ለምን እፈራለሁ
ባላገኝህ እንኳ በተስፋላይ ሁኘ ሌላይቱን አለም
እቀላቀላለሁ ሁሌም እወደሀለሁ ።

ሰኞ ማታ ስገላበጥ እሱ ጋር አብረን ያሳለፍነዉን ትዝ እያለኝ እንደ መፀፀት በደስታ ስገላበጥ አደርኩኝ፡፡ ግን በጣም ግራ ተጋብቻለሁ እኔ ነኝ ማለት ነዉ ሂክማ ያ ቆራጥ አመራሬ በትምህርት ቤት ጓደኞቼ መምህሮቼ እንደ ሂክማ ሁኑ ተብሎ በጥሩ ባህሪየ ስነምግባር የምታወቀዉ በሀይደር እንደዚህ እሆናለሁ ብየ መቼም አስቤዉ አላቅም፡፡ ብቻ ሰዉ የሚሸወደዉ በመወሰኑ አይደለም ለምን ኸይር ስራም ቢዝነስም ማንኛዉም ህይወት በዉሳኔ የፀናች ሲሆን ግን ሳናጣራ ግንዛቤዉ ሳይኖረን የምንወስነዉ ዉሳኔ የወደፊት ሂወት ሊያጨልምብን ይበራል ይደምቃል ብለን ያሰብነዉ በተዘዋዋሪ ሊጨለም እና  ከጭልመቱም በላይ ብርሀን ቢያገኝ እንኳ አስፈሪ ቁጭት ያለዉ ጨለማ ሊሆን ይችላል፡፡

     ጠንቃቃ ነጋዴዌች የሚሉት አሉ ሶስት ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ይላሉ አዉነት ነዉ፡፡ ሀሳብም ቢሆን አንድ ሀሳብ በሶስት መልኩ ማየት መቻል አለብን ፡፡ አንደኛዉ የመጀመሪያዉ መጥፎ ጎኑን ..መጥፎ ጎን ይዞ ቢመጣ በምን ወደነበረበት መመለስ እችላለሁ ወይ ሲሆን....ሁለተኛዉ ጥሩ ጎኑን መሳብ አለብን ...ጥሩ ጎኑ ለኔ ምን ያህል ጠቃሚ ነዉ ብለን ማሰብ መቻል አለብን፡፡ ሶስተኛዉ ዱንያ ስለሚሆን ጥሩ ተስፋ በአእምራችን ላይ ሙሉ በሙሉ መስጠት አያስፈልግም፡፡ የሰዉ ልጅ በጣም የሂወቴ መርህ መለወጫየ ነዉ ብሎ ተስፋ ካረገ ይህ ተስፋ ያረገዉ ነገር ካልተሳካ በጣም የሞራል ዉድቀት እና መልሶ ተስፋ እንዳያደርግ እና በጌታ ላይ ተወኩል ማረግ ሊዘናጋ ይችላል፡፡ ተስፋዎች ማሰብ ባይከፋም ...ግን ኔጌቲቭ ሀሳቦች አብሮ ማሰብ ያሰፈልጋል ዱንያ ነዉ አላህ ከፃፈልን ዉጭ የማይሆን ነገር ነዉ ይህ የአሰብኩት ተስፋ ግብ ካልመታ ወደ በፊቱ ያለበት እስቴፕ ቶሎ መመለስ መቻል አለበት፡፡ ወደ በፊቱ ማንነት ለመመለስ ደግሞ ካሳለፍነዉ የጨለማ ሂወት ያለፉ ታሪኮች ሊከብድ ስለሚችል ያንን በብቃት መወጣት መቻል አለብን፡፡


  እኔ ለራሴ የወደፊት ባሌ ሀይደር ነዉ ብየ 100% .እርግጠኛ ነኝ፡፡ ማንም የሚወስድብኝ እሱን የሚያፈቅርብኝ ያለ አይመስለኝም፡፡ እሱም እንደነገረኝ ከእኔ ዉጭ እንደማያገባ የቃልኪዳን ቀለበት እና ሀብል ሰጥቶኛል፡፡ ግን ልቤን ጭንቅ ይለኛል ቢተወኝስ እላለሁ እንደገና አይ ሀይደር በጭራሽ አያረገዉም እላለሁ እንደማያረገዉም እርግጠኛ ነኝ.........

#part 🔟

ይ...................ቀ
............ጥ.............ላ...................ል

4 another channal👇
             @Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
   
  T..➳ telegram.me/IslamisUniverstiy_public_group
እዉነተኛ እና አሳዛኝ ,ታሪክ

😢 #በመተት_የተሰናከለች_ነብስ_
                 #Part 9⃣


        ህይወት ሰብለ ጋር ከሄደች ቡሃላ ስራ ፈልገው አስገቧት ሆኖም የገባችባት ሴት እጅግ በጣም ክፉ ነበረች ስለሆነም ኩንትራቷን መጨረስ አቅቷት ወጣች ... ከስራ ወታ ሰብለ ጋር ስትሄድ አጋጣሚ የለችም ይሄኔ ደውላ ያለችበትን በመጠየቅ ቁልፍ ልትቀበላት ሄደች ስትደርስ ቤት ውስጥ ጥንድ ጥንድ ሆነው ተቀምጠው ሺሻ ያጨሳሉ ይጠጣሉ ... ህይወትም ቁልፍ ተቀብላ እስክትወጣ ጨነቃት ሆኖም አብረን እንሄዳለን ብለው አስቀመጣት እሷም ብቻዋን ተቀመጠች፡፡
በዛን ሰአት ሰብለ ከአንድ ሱዳናዊ ጋር ስለ ህይወት በአረብኛ ታወራለች ህይወትም ትኩረቷን ስለሳቧት መስማት ትቀጥላለች ይሄኔ አትሰማንም ብለው ስለራሷ ኖሮዋል የሚያወሩት ግን ህይወት ሁሉንም ትሰማ ነበር... "አንቺ ብቻ እሷ እሺ እንድትለኝ አርጊ እንጂ በብር ጉዳይ ምንም አታስቢ" ይላል ሱዳናዊው ወጣት... "ችግር የለውም እሷን ለኔ ተዋት" ትላለች ሰብለ ሰዳናዊው ወጣትም ነገርኩሽኮ እስከዛሬስ የቤት ኪራይሽን ማን የቻለሽ መሰለሽ ግን በቃ እንድታመልጠኝ አልፈልግም! አላት...

     ህይወትም የሁለቱን ቃለ ምልልስ ከሰማች ቡሃላ ምንም እንዳልሰማ ሰው ዝምታን መረጠች ከቆይታ ቡሃላም ሰብለ ወደ ህይወት በመምጣት እድለኛ ነሽ ልጁ ወዶሻል እናም ጓደኛው እንድትሆኚ ይፈልጋል አለቻት ህይወት ግን ይህ ፈፅሞ እንደማይሆን አስረዳቻት ይሄኔ ወደድሽም ጠላሽም ይሄ ህይወት የግድ ያስፈልግሻል እዚ ሀገር ሁሌ ስራ የለም የቤት ኪራይና ሆድ ግን ሁሌም አለ ስለዚህ የመጣልሽን ሲሳይ አታባሪ ስትል አስጠነቀቀቻት... ከዚ ግዜ ቡሃላ ግን ሰብለ ህይወትን ወደ ሱስ እንድትገባላት ትገፋፋት ጀመር... የሱዳናዊው ወጣት ወንድምና ጓደኞችም ልጁ የፈለገውን ማግኘት አለበት ስለዚህ እሺ ካላለች የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ዛቱ ሰብለ ብዙ ወንዶችን በፍቅር ብታውቅም ህይወትን የወደዳት ሰዳናዊ ወንድም የሰብለ ፍቅረኛ ነው ለዛም ሰብለን ህይወትን በእጃቸው እንድታስገባላቸው መቀመጫ ያሳጧት ጀመር...
......ህይወት በሴት ጓደኛዋ ግፊት ያልሆነ ህይወት መጀመሯ ግድ መሆኑን ስታውቅ አንድ ነገር ማሰብ እንዳለባት ታወቃት አንድ ቀን ከሚደፍራት በዘዴ ነገሮችን ማስተካከልን መረጠች እናም እሺ ለአንገቴና ለጣቴ እንዲሁም ለጆሮዬ ወርቅ ከገዛህልኝ አብረን መቀጠል እንችላለን አለችው እሱም በሀሳቧ ተስማምቶ ደሞዝ እስኪቀበል ጥቂት ቀን ስጪኝ አላት። ህይወትም በፈጠረችው መላ ደስ እያላት እስከዛ ስራ እንድታገኝ መፀለይ ጀመረች... ኢትዮጵያ ላለው ፍቅረኛዋ ግን ምንም ነገር ነግራው አታውቅም መጥፋቷን እንኳን አያውቅም...
ይህ በሆነ በ3ተኛ ቀኑ ሰብለ ሻውር እየወሰደች ነበር ይሄኔ ስልኳ ጠራ ህይወትም አነሳችው የደወለው ኢትዮጵያዊ ነበር እናም ሰብለ የለችም እንዴ ሲል ጠየቀ ህይወትም ሻውር እየወሰደች ነው ስትል መለሰችለት እሺ እየመጣሁ መሆኑን ንገሪልኝ ብሎ ስልኩን ዘጋው ሰብለ ግን ልትወጣ ስለነበር ተይው ባክሽ ብላት ወደ ቀጠሮዋ ሄደች ..
,....... ልጁ ልክ ሲመጣ ህይወትን ብቻዋን አገኛት ሰላም አላትና ዳኒ እባላለው ምን ሆነሽ ነው ቆዝመሻል አላት ፈገግ ብሎ ለሰላምታ እጁን እየዘረጋ ህይወትም በየዋህነት የገጠማትን ነገረችው ዳኒም የሰብለን ማንነት ያውቅ ስለነበር በጣም አዘነ ህይወትም ምን ሆነሃል ፊትህ ተቀየረ ስትል ጠየቀችው ዳንኤልም በጣም አዝናለው ሰብለ ማለት ብዙ የሀገሯን ሴቶች የምትረዳ መስላ በመስጠፋት ለባዳ መሸጥ ነው ስራዋ ይሄ የሷ ገቢ ነው አላት... ህይትወም በጣም ፈራች ለማንኛውም ተንጠቀቂ ስተኚ ጠብቃ እንዳታስደፍርሽ ሲል አስጠነቀቃት...
እጣ ፈንታዋ ሆኖ አለቅሽ ያላት ፈተና ህይወትን እጅግ በጣም እረበሻት ለዳኒም ስራ እንዲፈልግላት ነገረችው እሱም አገኘላትና ጀመረች ነገር ግን አሁንም የሷ ስቃይ አላበቃም ጠፍታ ስለምትሰራ ብትያዝ እንደምትታሰርና ምንም ሳትይዝ ሀገር እንደምትላክ ስለሚያውቁ ሱዳናዊው እና ሰብለ አሲዝሻለው ሲሉ ያስፈራርዋት ጀመር

#መጨረሻው_ክፍል

_ይ..................ቀ
..........ጥ................ላ......................ል

#Share_ማድረግ_አይርሱ

Join👇👇👇👇

🏷   @Islam_and_Science @Islam_and_Science 🔗JOIN US 🔗
⚠️⚠️⚠️እንጠንቀቅ!!

🇪🇹 #ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። ትንሽ ስህተት ሁላችንም ወደ # እልቂት ስለሚወስደን ከተቻለን

🇪🇹 #እንጠንቀቅ ካልሆነም በየቦታው እየገቡ ከመቀባጠር

🚫 #እንቆጠብ !! ሁለት ህይወት የለም!! 🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያ ከጥይት እሩምታ፤ ከቦንብ ፍንዳታ፤ ከእርስ በእርስ ግጭት #ብትርቅ የምትጠቀመው አንተ እና ምስኪን ትንንሽ ልጆችህ ናቸው!! ለራስህ ስትል ስለሰላም ሌት ተቀን ዘምር!! ኮሽ ሲል በቦሌ አድርጎ ከሀገር ከሚወጣ ሰው ጋር ህብረት ፈጥረህ ከወንድምህ እንዳትጣላ፤ እሳቱ ሚበላው አንተን ነውና!!
🇪🇹🇪🇹 #የሰላም # የፍቅር # የአንድነት ቀን ይሁንልን!

.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. @Islam_and_Science @Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•