Hadiya zone communication
1.16K subscribers
2.38K photos
58 videos
10 files
25 links
This is Hadiya Zone Govern. Comm. official Telegram channel.
የሀድያ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግሥት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በመገንባት መንግ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ"ያሆዴ" በዓል" ባህሌን እጠብቃለሁ፤ ያሆዴን አከብራለሁ"በሚል መሪ ቃል በከተማ አስተዳደር እና ወረዳዎች ተከበረ
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሕልፈተ-ሕወት ተከትሎ የሀዲያ ዞን አስተዳደር የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ።

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

::::::::::::::::::መስከረም 7፣ 2017:::::::::

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት እንደነበሩም በማንሳት

በህክምና ሲረዱ የቆዩት ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የዞኑ አስተዳደር የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለመላው የዞናችንና የሀገራችን ሕዝቦች መፅናናትን ይመኛል።
የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ።

።።።።።።።። መስከረም 6/2017 ዓ.ም።።።።።።።።።።።

የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለፁ ሲሆን፤ ለቤተሰባቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መፅናናትን ተመኝተዋል።

አቶ ማቴዎስ አኒዮ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በመምህርነት እና ተመራማሪነት ባገለገሉባቸው ዓመታት ትልቅ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ተግባራትን በትጋትና በሀገር ፍቅር ስሜት ማከናወናቸውን ተናግረው፣

በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ህዝባቸውን ወክለው ተከራክረዋል፤ ባገኙዓቸው መድረኮች ሁሉ ሳይሰለቹ የህዝብን ጥያቄ ሲያሰሙ የቆዩና እንዲሁም በሀገራችን ፖለቲካ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል እንዲዳብርና እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሚና ያበረከቱ ትልቅ ፖለቲከኛ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም ፕሮፌሰር በየነ የሕዝብን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችና ፍላጎቶች እንዲመለሱ ከሕዝብ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና አደራ በትጋትና በቁርጠኝነት ተወጥተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመድ አዝማድ ወዳጆች እንዲሁም ለመላው የሀድያ ዞን ነዋሪዎችና የሀገራችን ሕዝቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።
የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሀንዲሶ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ።

።።።።።።።።።። መስከረም 7/2017 ዓ.ም።።።።።።።።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በርካታ የሀገር ውለታ ያለባቸው ልሂቃን እና ፖለቲከኞች ተፈጠረውባት ለሀገራቸው ልዋላዊነት እና እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተው አልፈውባታል።

ከእነዚህ ልሂቃን እና ሠላማዊ ፖለቲኮኞች መካከል አንዱ የሆኑት፤ ለበርካታ አመታት ዴሞክራሲ ጫካ በመግባትና ከተማን በማተራመስ የሚመጣ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት ብቻ የሚመጣ መሆኑን አምነው ለበርካታ አመታት በመታገል ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል በማካሄድ የሚታወቁ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ስም አስተላልፋለሁ።

ፓርቲያችን ብልጽግና የሚከተለውን የመሀል ፖለቲካ አስቀድሞውኑ የተረዱት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከመደበኛ የሳይንስና ምርምር ስራቸው ጎን ለጎን የብሔር ብሔረሰቦች መብት ከብሔራዊ አንድነት ጋር ተጣጥሞ እንዲሄዴ እና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትገነባ የበኩላቸውን ጥረት ሲያበረክቱ ኖረዋል።

ፕሮፌሰሩ ምንም እንኳ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪና አባል ቢሆኑም ፓርቲያችን ብልጽግና በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጠላለፍ ፖለቲካ ቀርቶ አካታች የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር መንግስታችን የሰጣቸውን መንግስታዊ ኃላፊነት በብቃት ሲወጡ መቆየታቸው ምስጋና የሚቸራቸው ሲሆን፤

በመጨረሻም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በደረሰባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርታ ቅ/ጽ/ቤት ስም በድጋሚ እየገለጽኩ፤ በፕሮፌሰሩ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ለተሰማችሁ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመጆች ፈጣሪ መጽናናቱን ይስጥልን።
የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ''ያሆዴ'' በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሀዲያ ዞን ፖሊስ አስታወቀ፤

የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከሆሳዕና ከተማ ከሌሞ ወረዳና ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመሆን ''የያሆዴ'' በዓል አከባበርን በተመለከተ የጋራ የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል፤

።።።።።።።።መስከረም 8/2017 ።።።።።።።።።።
የሀድያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ያካሄደው የጋራ የምክክር መድረክ ውይይት የጀመረዉ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።

በጋራ የውይይት መድረኩ ላይ የሀዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ዋ/ኢ/ር ተሾመ ባቲሶ እንደገለፁት በዞኑ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ ''ያሆዴ'' በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው እንዳብራሩት፤

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅም የዞኑ ፖሊስ ከሆሳዕና ከተማ ፣ ከሌሞ ወረዳና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከሰላም የወጣት አደረጃጀቶችና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል።

ዞኑ የሠላም ተምሳሌት እንደሆነ የገለፁት ዋና ኢንስፔክተር ተሾመ ይህም ሊሆን የቻለዉ በየደረጃው የሚገኘው ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን የራሱንና የአካባቢውን ሰላም ቀመጠበቅ እያደረገ ካለው ብርቱ ጥረትና አስተዋጽኦ እንደሆነ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በዞኑ ለሚገኘው ሰላም የህዝቡ ሚና የላቀ መሆኑን የጠቆሙት ዋና አዛዡ ዋና ኢንስፔክተር ተሾመ፤

በቀጣይም ህብረተሰቡ የአከባቢውን ሠላምና ፀጥታ የሚያውኩና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካለት ጥቆማ በመስጠት የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚሁ ጋር በተያዘም የሚከተሉትን የስልክ ቁጥሮች አድራሻን በመጠቀም፦

ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ 0465553211

ሀድያ ዞን ፖሊስ 0465550330

ለፀጥታ መዋቅር ተቋማት ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል አሳስበዋል።

በሞህረተአብ ዘለቀ