Hadiya zone communication
1.17K subscribers
2.52K photos
58 videos
10 files
25 links
This is Hadiya Zone Govern. Comm. official Telegram channel.
የሀድያ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግሥት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በመገንባት መንግ
Download Telegram
''ያሆዴ''የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል አብሮነትንና ፍቅርን በሚያጠናክር መልኩ ማክበራቸውን የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናገሩ

።።።።5/1/2017።።።

በሀዋሳ ከተማ  በድምቀት የተከበረው''ያህዴ''በዓል አብሮነትንና ፍቅርን በሚያጠናክር መልኩ መከበሩን የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በሀዋሳ የተከበረው ''ያሆዴ በዓል''ከሀዲያ ብሔር በተጨማሪ የሲዳማና የኦሮሞን ብሔር  ባሳተፈ መልኩ በድምቀት መከበሩንና ''የያሆዴ''ባህላዊ ስርዓት አስደናቂ መሆኑን ጠቁመው÷ ይህም አብሮነትን ፣ ሰላምንና አንድነትን ከማጠናከር አንፃር ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በዓሉ እርስበርስ እንድንተዋወቅ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ከመሆኑም በተጨማሪ ባህልን ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

በተለይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔሩ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩበት ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ ባሳተፈ መልኩ መከበሩ''ያሆዴን''በዩኒስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝም ገልፀው፥

የዞኑ መንግስትም በዓሉን በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እያደረገ የሚገኘውን ጥረት አጠናክረው እንድቀጥል ጠይቀዋል።

በምህረተአብ ዘለቀ
ያሆዴ በዓል የህዝቦች ትስስርን ከማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተገለፀ

ሀዋሳ፡ መስከረም 05/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ያሆዴ በዓል የህዝቦች ትስስርን ከማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተገለፀ።

ያሆዴ የ2017 የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል በዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በአሉን በምርቃት ያስጀመሩት ሀገር ሽማግሌዎችም አዲሱ አመት የሰላም፣ የአንድነትና የበረከት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ቦጋለ እንደተናገሩት የያሆዴ በዓል ከዚህ ቀደም በሀዲያ ዞን ባሉት መዋቅሮች ብቻ ይከበር እንደነበር አንስተው የዘንድሮ በአል ድሬዳዋና ሀዋሳን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዘንድሮ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ ሀዋሳ ከተማ የሀዲያ ብሔር ተወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር በፈቃዱ ገብረሀና በየዓመቱ በመላው የሀዲያ ማሕበረሰብ ዘንድ በጉጉት ተጠብቆ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የያሆዴ በዓል ነዉ ብለዉ በዓሉም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑን አንስተዋል።
ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/photo/?fbid=934275372072192&set=pcb.934276082072121
የራሳችን የሆነ የማንነት መገለጫ ያለን የቱባ ባህል ባለቤቶች ነን፦የሀዲያ ዞን ም/አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ሀላፊ በፍቃዱ ገ/ሃና(ዶ.ር)

የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ''ያሆዴ''በዓል በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ''ባህሌን እጠብቃለሁ ያሆዴን አከብራለሁ''በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።መስከረም 6/2017፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የሀዲያ ዞን ም/አስተዳዳሪ በፍቃዱ ገ/ሃና በዓሉ አከባበር ላይ ባደረጉት ንግግር÷የሀዲያ ብሔር የራሱ የሆነ የማንነት መገለጫ ያለው የቱባ ባህል ባለቤት ህዝብ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሀዲያ ህዝብ የብዙ ባህላዊ እሴቶች፣ወጎችና ልማዶች የአለባበስ ስርዓት፣ጨዋታ፣የእርቅ ስርዓት እና ሌሎችም የራሱ የሆነ የማንነት መገለጫ ያለው የቱባ ባህል ባለቤት እንደሆነ ጠቁመው፦

እንደ ህዝብ ከያዝናቸው ዕሴቶች አንዱ''ያሆዴ''በዓል እንደሆነ ተናግረዋል።

የበዓሉ መከበር ከባህላዊ ዕሴቱም ባለፈ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ የገለፁት ም/አስተዳዳሪዉ፥

የቱሪዝም ዘርፍ እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚገኝበት እንደ መንግስት ደግሞ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠበት በመሆኑ የበዓሉ መከበር በኢኮኖሚው የሚያበረክተው ሚና የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዓል አንዱ ብሔር የሌላውን ብሔር ባህል እንዲያውቅ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ በህዝቦች መከከል አብሮት፣መተባበር፣ሠላም እና መቀራረብ እንድኖር በማድረግ በማህበራዊ ዘርፍ ከፍተኛ ጠቃሜታ እንዳለው ገልፀዋል።

በቀጣይም በዓሉን ከሀገር ውጪ በሌሎች የዓለም አከባቢዎች ለማክበር ዕቅድ መያዙን ጨምረው ገልፀዋል።

የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ቦጋለ ባደረጉት ንግግር ሀዲያ ብሔር የበርካታ ባህላዊ ትውፊት ባለቤት ህዝብ መሆኑን ጠቁመው፦

የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ''ያሆዴ''በዓል ከዞን ውጪ መከበር የእርስበርስ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ ባህልና እሴትን ለሌሎችም ለማስተዋወቅ የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡

አያይዘውም ከአባቶቻችን የተረከብነውና የማንነት መገለጫ የሆነውን''ያሆዴ''በዓል ወግና ክብሩን እንደጠበቀ ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል ብለዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ÷ የሀዲያ ዞን ም/አስተዳዳሪ በፍቃዱ ገ/ሃና ጨምሮ የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እቴነሽ ሙሉጌታ፣የብሔር ተወላጆች፣የሲዳማና የኦሮሞ የባህል ሽማግሌዎች እንዲሁም የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በበዓሉ አከባበር የሀዲያን ባህል፣ ወግና ልማድ የሚያሳዩ ባህላዊ ክዋኔዎችና በአባቶች ምርቃት ተከብሯል።

በምህረተአብ ዘለቀ