Forwarded from Finance Today
በአፋር ክልል በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!
በአፋር ክልል ሀሩቃ በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መቁሰላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ጥቃቱን ፈጸሙ የተባሉት የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በዚያኑ ዕለት ምሽት ገዋኔ በተባለ ቦታ በከፈቱት ተኩስ ሁለት የክልሉ መንግስት ሰራተኞች መገደላቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል። የሶማሌ ክልል ጥቃቱ የተፈጸመው “በክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ነው” የሚለውን ውንጀላ አስተባብሏል።
የአፋር ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመድ ሁመድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዛሬ እንደተናገሩት፤ ወደ ክልላቸው ዘልቆ የገባው የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል፣ በሀሩቃ ቀበሌ ጥቃቱን የፈጸመው ከሁለት ቀን በፊት፤ መጋቢት 25፤ ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ ነው። የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ወደ ቀበሌዋ ገብተው ተኩስ መክፈታቸውን የሚገልጹት ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነሩ፣ በጥቃቱም “ከ30 በላይ ንጹሃን ዜጎች ተረሽነዋል” ብለዋል።
[Ethiopia Insider]
YeneTube
@biruke_mereja_media

ፌስቡክ የኢትዮጵያ ምርጫን ተከትሎ ገፁን የተሳሳተ መረጃ ለመልቀቅ የሚጠቀሙ ደንበኞቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ!
ፌስቡክ የኢትዮጵያ ምርጫን ተከትሎ መራጮች ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል ሁኔታ ለማመቻቸት እና ገፁን የተሳሳተ መረጃ ለመልቀቅ የሚጠቀሙ ደንበኞቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከተሳሳተ መረጃ የሚጠበቁበት እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የማህበረሰብ ማነቃቅያ ዘመቻን እንደሚያካሂድም ባወጣው ፅሁፍ አትቷል።
@biruke_mereja_media
@biruke_mereja_media
ፌስቡክ የኢትዮጵያ ምርጫን ተከትሎ መራጮች ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል ሁኔታ ለማመቻቸት እና ገፁን የተሳሳተ መረጃ ለመልቀቅ የሚጠቀሙ ደንበኞቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከተሳሳተ መረጃ የሚጠበቁበት እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል የማህበረሰብ ማነቃቅያ ዘመቻን እንደሚያካሂድም ባወጣው ፅሁፍ አትቷል።
@biruke_mereja_media
@biruke_mereja_media
Forwarded from Finance Today
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሶማሊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ወጣቶችን ይቅርታ ጠየቀ
የሶማሊ ክልል የከተማ ፖሊሶች በጅግጅጋ ከተማ መንገደኛ ወጣቶችን አስቁመው ጸጉር መቁረጣቸውን ተከትሎ የሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሶማሊ ነዋሪ ወጣቶችን ይቅርታ ጠየቀ፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ሚድያ (ፌስቡክ) ገጹ ባሰራጨው የይቅርታ መልእክት ተመሳሳይ ድርጊት ወደፊት አይደገምም ያለ ሲሆን፤ የእስካሁኑ ድርጊትም በኮሚሽኑ ትእዛዝ የተሰጠበት አለመሆኑን አሳውቋል፡፡
ወጣቶች በግዳጅ ጸጉራቸውን ሲቆርጡ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪድዮ) ከዚህ ዜና ጋር ተያይዟል።
@biruke_mereja_media
@biruke_mereja_media
የሶማሊ ክልል የከተማ ፖሊሶች በጅግጅጋ ከተማ መንገደኛ ወጣቶችን አስቁመው ጸጉር መቁረጣቸውን ተከትሎ የሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሶማሊ ነዋሪ ወጣቶችን ይቅርታ ጠየቀ፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ሚድያ (ፌስቡክ) ገጹ ባሰራጨው የይቅርታ መልእክት ተመሳሳይ ድርጊት ወደፊት አይደገምም ያለ ሲሆን፤ የእስካሁኑ ድርጊትም በኮሚሽኑ ትእዛዝ የተሰጠበት አለመሆኑን አሳውቋል፡፡
ወጣቶች በግዳጅ ጸጉራቸውን ሲቆርጡ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪድዮ) ከዚህ ዜና ጋር ተያይዟል።
@biruke_mereja_media
@biruke_mereja_media
Forwarded from Finance Today
#ItsMyDam🇪🇹
"...በጉዳዩ ላይ ይጮሃሉ ፣ ያስፈራራሉ ፣ ማስፈራሪያው ድሮም የነበረ ነው" - የውሃ ጥናት ባለሞያ ፈቅ አህመድ ነጋሽ
ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚነሱ ጫናዎችን ተቋቁማ የመጀመሪያውን የውሃ ሙሌት አካሂዳለች።
አሁን ኢትዮጵያ ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ነው።
ለ2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት የተያዘው ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ጫና እያበረቱ ይመጣሉ።
የውሃ ጥናት ባለሞያው ፈቅ አህመድ ነጋሽ ፥ "... ግድቡ እስከተገነባ ድረስ የውሃ ሙሌቱን መከልከል እንደማይቻል ግብፆቹም ሆነ ሱዳኖች ጠንቅቀው ያውቃሉ" ብለዋል።
ባለሞያው ፥ "...በጉዳዩ ላይ ይጮሃሉ ፣ ያስፈራራሉ ፣ ማስፈራሪያው ድሮም የነበረ ነው፤ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ደግሞ ማስፈራሪያ ሲኖር ይፈራል ፤ ሀገራቶቹ ድንገት ወደግጭት ይገቡና ኃላ የራሳችን ችግር ይሆናል ብለው ስለሚፈሩ፥ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ይፈጥራሉ የሚል እምነት ስላላቸው ነው" ብለዋል።
አክለውም፥ "የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን እንደሉአላዊነት በቆጠረው ጉዳይ ላይ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ፤ መሀል ላይ የሚፈጠሩ የፖለቲካ ጉዳዮች የሚያመጣቸው ውዥንብሮች ቢኖሩም ህዝቡ ግን ምንጊዜም ከድጋፍ ወደኃላ አይልም" ሲሉ ለዋልታ ቲቪ ተናግረዋል።
@ethio_mereja_news

ሱዳን በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለቆ እንዲወጣ ጠየቀች
ሱዳን ይህን ያለችው በኪንሻሳ ሲካሄድ የነበረው የግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት በመጠናቀቁ ነው
ሱዳንና ደቡብ ሱዳን “በይገባኛል”ጥያቄ በሚወዛገቡባት አብዬ ግዛት የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለቆ እንዲወጣ ሱዳን ተመድን ጠይቃለች፡፡
ሱዳን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰቸው በኪንሻሳ የተካሄደው የግድቡየሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ከአብዬ ግዛት እንዲወጣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ሱዳን ገልጻለች።
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ ስር በመሆን በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል በምትገኘውና ሁለቱ ሀገራት ይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡባት አብየ ግዛት በፈረንጆቹ በ2011 ጀምሮ ሰላም ለማስከበር ሰፍሮ ቆይቷል፡፡
አብዬ ግዛት በነዳጅ እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገች ግዛት ናት። በዚህም ምክንያት ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን እንደ በፈረንጆቹ በ2011 ነጻነቷን መቀዳጀቷን ተከትሎ ነበር ሁለቱ ሀገራት ወደ ግጭት ያመሩት።
በሁለቱ ሀገራት መልካም ፈቃድ፣ ኢትዮጵያ በዚች ግዛት ሰላም እንዲሰፍን ከ4 ሺህ በላይ ጦር ወደ ሰፍራው አቅነቶ ሰላም በማስከበር ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ሱዳን እና ግብጽ በሱዳን በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ሱዳን በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ መሬም አልሳዲግ አልመሀዲ በኩል አስታውቃለች።
በአብዬ ግዛት ላይ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ እምነት የለንም ያሉት ሚኒስትሯ ጦሩ በፍጥነት አብዬን ለቆ እንዲወጣ እንፈልጋለንም ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ ግትር አቋም አሳይታለች፤ በኬንሻሳ የተካሄደው የሶሰትዮሽ ድርድር ያለስምምነት የተጠናቀቀው ኢትዮጵያ ስላልፈለገች ነው።
ሚኒስትሯ አክለውም ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ ብዙ ፍላጎት አላት ፤ሱዳን ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጮችን ትጠቀማለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ያለችበትን የውስጥ ችግር ሱዳን ተረድታ ለረጅም ጊዜ ታግሳለች፤በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ተቀብለናል ያሉት ሚኒስትሯ ከእንግዲህ ግን ይህ ያበቃል በቀጥታ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማስከበር ላይ እናተኩራለን ሲሉ በኬንሻሳ ተናግረዋል።

#Its_My_Dam‼️
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ
እንደምን አደራቹ ውድ ኢትዮጵያውያን
#GOODMORNINGETHIOPIA🇪🇹
ክቡራን አባላቶቼ በያላቹበት አለም ዳርቻ ሰላም ጤና ፍቅር ተመኘሁ
ሰናይ ቀን እንዲሆንላቹ ተመኘሁ🙏

Forwarded from ኢትዮ መረጃ - NEWS
ሰበር መረጃ ‼️ በትግራይ ከባድ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው | የሱዳን ድንበር መዝጋት ጉዳይ 👇
https://youtu.be/4FFufvFJ2sg
https://youtu.be/4FFufvFJ2sg
https://youtu.be/4FFufvFJ2sg
https://youtu.be/4FFufvFJ2sg
YouTube
ሰበር መረጃ | የትግራይ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው ተደመሰሱ | የሱዳን ድንበር መዝጋት ጉዳይ | biruke mereja media
ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማረግ ወቅታዊና ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ | biruke mereja media
Forwarded from ኢትዮ መረጃ - NEWS
በእነ ስብሃት ነጋ ላይ ሊሰማ የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ታገደ ተባለ
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በእነ ስብሃት ነጋ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሊያሰማው የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ለጊዜው ታገደ።
ምስክርነቱ የታገደው የተከሳሽ ጠበቆች በምስክር አሰማም ሂደቱ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው ነው።
ዐቃቤ ህግ የአቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ የ42 ተጠርጣሪዎችን የጊዜ ቀጠሮ እየተመለከተ ላለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ከዚህ ቀደም ባቀረበው አቤቱታ፤ የቅድመ ምርመራ የምስክርነት ሂደቱ በዝግ ችሎት እና በስውር እንዲሆን ጥያቄ አቅርቦ ነበር። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ይህንን አቤቱታ ተቃውመው ለችሎት አቤት ቢሉም መቃወሚያቸው ውድቅ ተደርጓል።
ጠበቆቹ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ፤ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የቅድመ ምርመራ የምስክር መስማት ሂደቱ ታግዶ እንዲቆይ በዛሬው ውሎው ወስኗል። ችሎቱ “የይግባኝ ክርክሩ መልስ እስኪያገኝ ድረስ መዝገቡ ተዘግቶ ይቆያል” ሲል በዛሬው ውሎው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ዛሬ መጋቢት 29 በነበረው ችሎት፤ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ 39 ተጠርጣሪዎች በአካል ተገኝተው ተከታትለዋል። በዛሬው ችሎት ሰሎሞን ኪዳኔ እና ብርሃነ ጸጋዬ በህመም ምክንያት አልተገኙም ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

#አዲስ_መረጃ_ለተማሪዎች‼️
የ2013 ዓ./ም የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ መወሰኛ ነጥብ ነገ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይገለጻል ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ#2013 አዲስ ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ነጥብና ከቅበላ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

Forwarded from www.ayerlay.et
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
Forwarded from ኢትዮ መረጃ - NEWS
#MoSHE
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ባልሆነ ፕሮግራም ማለትም (በማታ ፣ ክረምት ፣ ሳምንት መጨረሻ ፣ የርቀት ፣ በበይነ መረብ) እና በግል ተቋማት በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ አማራጮች ለመማር አነስተስተኛው የመቁረጫ ነጥብ ፦ ለወንዶች 330 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 320 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።
በሌላ በኩል
በግል ተቋማት የህክምና መስኮችን ለመማር አነስተኛው የመቁረጫ ነጥብ (ከተፈጥሮ ሣይንስ መስክ ለሚመጡ ብቻ) ለሁለቱም ፆታ 450ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በሌላ በኩል
በ2013 ዓ/ም 147,640 (88,153 ወንድ ፤ 59,487 ሴት) ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ። እነዚህ ተማሪዎች በ46ቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ ይደረግላቸዋል።
በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መቀየር ይቻላል።

Forwarded from Ministry of Science and Higher Education (MoSHE) (Betty)
የ2013 የትምህርት ዘመን አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያን በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከአጠቃላይ ህዝባችን ከሩብ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ዜጎች በተለያየ ደረጃ በትምህርት ላይ ይገኛሉ፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በሌሎች አገራት እምብዛም ባልተለመደ መልኩ መንግስት በየዓመቱ ቁጥራቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በነፃ ሊባል በሚችል ወጪ መጋራት በማስተማር ላይ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ግማሽ ሚሊዮን ለሚደርሱ የመደበኛ ተማሪዎች በመንግስት የሚሸፈነው ዓመታዊ ወጪ በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠር እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ሪፎርም በጀመርንባቸው ያለፉት ሶስት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ቅድሚያ የርብርብ ማዕከላችን በማድረግ የተለያዩ የሪፎርም እርምጃዎች በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡
በዚሁ መሰረት የአንድ ዓመት የፍሬሽማን ፕሮግራም መጀመሩ፣ ዩኒቨርስቲዎችን በትኩረትና በተልዕኮ የመለየት፣ የፕሮግራምና ሥርዓተ ትምህርቶች ግምገማና ክለሳ ማካሄድ፣ የመምህራንና አሰልጠኞች ልማት ማጠናከር፣ የተቋማት አመራርና አሰራር ሪፎርም ትግበራ ማካሄድ እና የመሰረተ ልማት ማሟላትና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማሳደግ ፤ የመረጃ ሥራዎች አያያዝ አስተዳደር ማዘመን ፤ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተቋማት ብቃት ማረጋገጫ አስራር ስርዓት የማዘመን ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
ካለፈው ዓመት ጀምሮ ወደ ትግበራ የገባው የፍሬሽ ማን ፕሮግራም የተማሪዎችን ቆይታ በትንሹ ወደ አራት ዓመት ያሳደገ ሲሆን ተማሪዎች በመጀመሪያው ዓመት የተለያዩ ክህሎቶችን፤ መሰረታዊ እውቀቶችንና እንዲጨብጡ የሚስችሉ ስብዕና ግንባታ ላይ ይዘት ያላቸው የትምህርት አይነቶችን የሚከታተሉባቸው ይሆናል፡፡ በያዝነው ዓመት የሚገቡ ተማሪዎች የመጀመሪያውን ዓመት ፍሬሽማን ፕሮግራም ካጠናቀቁ በኋላ ወደሚመርጧቸው ትምህርት ፕሮግራሞች ገብተው ለመከታተል የሚያስችላቸውን የእውቀትና ክህሎት ምዘና ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ተዘጋጅቶ በየዩኒቨርስቲዎቻቸው የሚወስዱ ይሆናል፡፡ በፍሬሽማን ፕሮግራም ያስመዘገቡት ዉጤት እና በሃገር አቀፍ የሚሰጠውን የፈተና ዉጤት መሰረት በማድረግ በውጤታቸውና በምርጫቸው ተቋማቱ ወደ ፕሮግራሞች ቅበላ ያደርጋሉ፡፡
በዚህ ሂደት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዝቅተኛውን የመግቢያ መስፈርት የሚወስን ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የማሰልጠን፣ የማብቃት፣ የማዘጋጀትና አስፈላጊውን ክህሎት፣እውቀት እና ስብእና ግንባታ በተደራጀና በተሟላ ግብዓት የማስጨበጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ መምህራንም ያላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀምና ከተቋማቸውና ተማሪዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ተማሪዎቻቸው አስፈላጊውን ክህሎትና፣ እውቀትና የተሻለ ስብዕና ይዘው እንዲገኙ የማብቃት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ተማሪዎችም በበኩላቸው ጊዜ ውድና ተመልሶ የማይገኝ መሆኑን በመገንዘብ ያላቸውን ቆይታ በአግባቡ ትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ካልተገቡ ነገሮች ራሳቸውን በማቀብ አስፈላጊውን እውቀት፣ክህሎት እና የተሻለ ስብዕና ይዘው የተሻሉ ሆነው ለመገኘት ቀን ከለሊት የመስራት ግዴታና የዜግነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በቀጣይ ዓመታት ለትምህርትና ሥልጠና ጥራትና ተገቢነት እንዲሁም ልህቀት መረጋገጥ ተጨማሪ እርምጃዎች በሴክተርና በተቋማት እንዲተገበሩ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ተቋማዊ ነፃነት የማረጋገጥና ከዚሁ ጋር የሚጣጣም የተማሪዎች ቅበላ ሥርዓት መዘርጋት ቁልፍ ተግባር ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ብዙ መስተጓጎል ያጋጠመበትን የ2012 / 2013 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ ማስተናገድ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በቀጣይ የትምህርት ጊዚያት የቅበላ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ በዋናነት የሁሉንም ፕሮግራሞች የስራ ገበያ ውጤታማነት የዳሰሳ ጥናት በሀገር ደረጃ የሚደረግ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የጥናቱን ውጤት መሰረት አድርጎ ለሀገራችን ልማት አስተዋጽኦ በሚያደርግ መልኩና የተመራቂዎችን የስራ ዕድል በሚያሰፋ መልኩ የተማሪዎች ቅበላ በየተቋማቱ የሚከናወን ይሆናል፡፡ የትምህርት ፕሮግራሞቻችንም የስራ ገበያን ባማከለ መልኩ እንዲሆኑ ተከታታይነት ባለው መልኩ የመፈተሸ ስራው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህን ተግባር በተገቢው መልኩ ለመፈጸም የምዘና ማዕከላትን የማደራጀት በድጅታል ስርአት ታገዙ የማድረግና የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡ይህንን መሰረት ተደርጎ የተማሪዎች ምዘና ስርአት ግልጽ ሆኖ የሚተገበር ይሆናል፡፡
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

51.jpg
1.8 MB
Forwarded from Ministry of Science and Higher Education (MoSHE) (Betty)
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
#Update
የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦
- በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።
- በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።
ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (@MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ያንብቡ ፤ ለሌሎችም ያጋሩ።
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!

ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል።
በመዲናዋ ትናንት ሌሊት በአራት የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ!
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መልካ ሸኔ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12:50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል።
በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።
እንደ አቶ ጉልላት ገለፃ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 8 የተከሰተው አደጋ መንስኤው አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል።