G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
በእነ ስብሃት ነጋ ላይ ሊሰማ የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ታገደ ተባለ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በእነ ስብሃት ነጋ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሊያሰማው የነበረው የቅድመ ምርመራ ምስክርነት ለጊዜው ታገደ።

ምስክርነቱ የታገደው የተከሳሽ ጠበቆች በምስክር አሰማም ሂደቱ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለታቸው ነው።

ዐቃቤ ህግ የአቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ የ42 ተጠርጣሪዎችን የጊዜ ቀጠሮ እየተመለከተ ላለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ችሎት ከዚህ ቀደም ባቀረበው አቤቱታ፤ የቅድመ ምርመራ የምስክርነት ሂደቱ በዝግ ችሎት እና በስውር እንዲሆን ጥያቄ አቅርቦ ነበር። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ይህንን አቤቱታ ተቃውመው ለችሎት አቤት ቢሉም መቃወሚያቸው ውድቅ ተደርጓል።

ጠበቆቹ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ መጠየቃቸውን ተከትሎ፤ የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የቅድመ ምርመራ የምስክር መስማት ሂደቱ ታግዶ እንዲቆይ በዛሬው ውሎው ወስኗል። ችሎቱ “የይግባኝ ክርክሩ መልስ እስኪያገኝ ድረስ መዝገቡ ተዘግቶ ይቆያል” ሲል በዛሬው ውሎው ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ዛሬ መጋቢት 29 በነበረው ችሎት፤ አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ 39 ተጠርጣሪዎች በአካል ተገኝተው ተከታትለዋል። በዛሬው ችሎት ሰሎሞን ኪዳኔ እና ብርሃነ ጸጋዬ በህመም ምክንያት አልተገኙም ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#አዲስ_መረጃ_ለተማሪዎች‼️

የ2013 ዓ./ም የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ መወሰኛ ነጥብ ነገ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይገለጻል ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ#2013 አዲስ ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ነጥብና ከቅበላ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from www.ayerlay.et
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
#MoSHE

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ባልሆነ ፕሮግራም ማለትም (በማታ ፣ ክረምት ፣ ሳምንት መጨረሻ ፣ የርቀት ፣ በበይነ መረብ) እና በግል ተቋማት በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ አማራጮች ለመማር አነስተስተኛው የመቁረጫ ነጥብ ፦ ለወንዶች 330 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 320 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።

በሌላ በኩል

በግል ተቋማት የህክምና መስኮችን ለመማር አነስተኛው የመቁረጫ ነጥብ (ከተፈጥሮ ሣይንስ መስክ ለሚመጡ ብቻ) ለሁለቱም ፆታ 450ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

በሌላ በኩል

በ2013 ዓ/ም 147,640 (88,153 ወንድ ፤ 59,487 ሴት) ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ። እነዚህ ተማሪዎች በ46ቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ ይደረግላቸዋል።

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መቀየር ይቻላል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የ2013 የትምህርት ዘመን አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያን በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከአጠቃላይ ህዝባችን ከሩብ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ዜጎች በተለያየ ደረጃ በትምህርት ላይ ይገኛሉ፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በሌሎች አገራት እምብዛም ባልተለመደ መልኩ መንግስት በየዓመቱ ቁጥራቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በነፃ ሊባል በሚችል ወጪ መጋራት በማስተማር ላይ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ግማሽ ሚሊዮን ለሚደርሱ የመደበኛ ተማሪዎች በመንግስት የሚሸፈነው ዓመታዊ ወጪ በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠር እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ሪፎርም በጀመርንባቸው ያለፉት ሶስት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ቅድሚያ የርብርብ ማዕከላችን በማድረግ የተለያዩ የሪፎርም እርምጃዎች በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡

በዚሁ መሰረት የአንድ ዓመት የፍሬሽማን ፕሮግራም መጀመሩ፣ ዩኒቨርስቲዎችን በትኩረትና በተልዕኮ የመለየት፣ የፕሮግራምና ሥርዓተ ትምህርቶች ግምገማና ክለሳ ማካሄድ፣ የመምህራንና አሰልጠኞች ልማት ማጠናከር፣ የተቋማት አመራርና አሰራር ሪፎርም ትግበራ ማካሄድ እና የመሰረተ ልማት ማሟላትና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማሳደግ ፤ የመረጃ ሥራዎች አያያዝ አስተዳደር ማዘመን ፤ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተቋማት ብቃት ማረጋገጫ አስራር ስርዓት የማዘመን ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

ካለፈው ዓመት ጀምሮ ወደ ትግበራ የገባው የፍሬሽ ማን ፕሮግራም የተማሪዎችን ቆይታ በትንሹ ወደ አራት ዓመት ያሳደገ ሲሆን ተማሪዎች በመጀመሪያው ዓመት የተለያዩ ክህሎቶችን፤ መሰረታዊ እውቀቶችንና እንዲጨብጡ የሚስችሉ ስብዕና ግንባታ ላይ ይዘት ያላቸው የትምህርት አይነቶችን የሚከታተሉባቸው ይሆናል፡፡ በያዝነው ዓመት የሚገቡ ተማሪዎች የመጀመሪያውን ዓመት ፍሬሽማን ፕሮግራም ካጠናቀቁ በኋላ ወደሚመርጧቸው ትምህርት ፕሮግራሞች ገብተው ለመከታተል የሚያስችላቸውን የእውቀትና ክህሎት ምዘና ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ተዘጋጅቶ በየዩኒቨርስቲዎቻቸው የሚወስዱ ይሆናል፡፡ በፍሬሽማን ፕሮግራም ያስመዘገቡት ዉጤት እና በሃገር አቀፍ የሚሰጠውን የፈተና ዉጤት መሰረት በማድረግ በውጤታቸውና በምርጫቸው ተቋማቱ ወደ ፕሮግራሞች ቅበላ ያደርጋሉ፡፡

በዚህ ሂደት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዝቅተኛውን የመግቢያ መስፈርት የሚወስን ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የማሰልጠን፣ የማብቃት፣ የማዘጋጀትና አስፈላጊውን ክህሎት፣እውቀት እና ስብእና ግንባታ በተደራጀና በተሟላ ግብዓት የማስጨበጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ መምህራንም ያላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀምና ከተቋማቸውና ተማሪዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ተማሪዎቻቸው አስፈላጊውን ክህሎትና፣ እውቀትና የተሻለ ስብዕና ይዘው እንዲገኙ የማብቃት ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ተማሪዎችም በበኩላቸው ጊዜ ውድና ተመልሶ የማይገኝ መሆኑን በመገንዘብ ያላቸውን ቆይታ በአግባቡ ትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ካልተገቡ ነገሮች ራሳቸውን በማቀብ አስፈላጊውን እውቀት፣ክህሎት እና የተሻለ ስብዕና ይዘው የተሻሉ ሆነው ለመገኘት ቀን ከለሊት የመስራት ግዴታና የዜግነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በቀጣይ ዓመታት ለትምህርትና ሥልጠና ጥራትና ተገቢነት እንዲሁም ልህቀት መረጋገጥ ተጨማሪ እርምጃዎች በሴክተርና በተቋማት እንዲተገበሩ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ተቋማዊ ነፃነት የማረጋገጥና ከዚሁ ጋር የሚጣጣም የተማሪዎች ቅበላ ሥርዓት መዘርጋት ቁልፍ ተግባር ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ብዙ መስተጓጎል ያጋጠመበትን የ2012 / 2013 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ ማስተናገድ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

በቀጣይ የትምህርት ጊዚያት የቅበላ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ በዋናነት የሁሉንም ፕሮግራሞች የስራ ገበያ ውጤታማነት የዳሰሳ ጥናት በሀገር ደረጃ የሚደረግ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የጥናቱን ውጤት መሰረት አድርጎ ለሀገራችን ልማት አስተዋጽኦ በሚያደርግ መልኩና የተመራቂዎችን የስራ ዕድል በሚያሰፋ መልኩ የተማሪዎች ቅበላ በየተቋማቱ የሚከናወን ይሆናል፡፡ የትምህርት ፕሮግራሞቻችንም የስራ ገበያን ባማከለ መልኩ እንዲሆኑ ተከታታይነት ባለው መልኩ የመፈተሸ ስራው የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህን ተግባር በተገቢው መልኩ ለመፈጸም የምዘና ማዕከላትን የማደራጀት በድጅታል ስርአት ታገዙ የማድረግና የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡ይህንን መሰረት ተደርጎ የተማሪዎች ምዘና ስርአት ግልጽ ሆኖ የሚተገበር ይሆናል፡፡
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
51.jpg
1.8 MB
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
#Update

የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦

- በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

- በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (@MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ያንብቡ ፤ ለሌሎችም ያጋሩ።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል።

በመዲናዋ ትናንት ሌሊት በአራት የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ!

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መልካ ሸኔ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12:50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል።

በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።

እንደ አቶ ጉልላት ገለፃ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 8 የተከሰተው አደጋ መንስኤው አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ማስተካከያ‼️

ትላንት ይፋ በተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመቁረጫ ነጥብ ላይ የተደረገ ማስተካከያ (መስማት ለተሳናቸው እና ለአይነስውራን) እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተፈጥሮ ሳይንስ ፦

- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 275 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

ማህበራዊ ሳይንስ ፦

- መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 265 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- ለአይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 240 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

- ለአይነስውራን ሴት ተማሪዎች 235 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ

መረጀውን ያገኘነው ከMoSHE ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ባለፈው ወር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ300 በላይ ሰዎች እንደሞቱ እና 369 ደሞ እንደቆሰሉ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እንዳለ ኃይሌ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

የኦሮሞ አስተዳደር ዞን አንድ ሃላፊ ደሞ በዞኑ ብቻ 68 ሰዎች እንደተገደሉ እና 114 እንደቆሰሉ ተናግረዋል።

ለግጭቱ መንግሥት የሰጠው ምላሽ የዘገየ እንደነበር የጠቀሱት የፌደራሉ እንባ ጠባቂ፣ አሁንም ፌደራል መንግሥቱ ችግሩን ለመፍታት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸውን ዘገባው አመልክታል።

ዋዜማ - ራዲዮ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🔝 ምርጥ 11 ተማሪዋች (2012) 👏👏👏

1️⃣ 669 BROOK BALKACHEW NIGATU
ST.JOSEPH A-A(R) 361757
2️⃣ 665 NAOL BELETE ADUGNA
EXCEL(R) 342175
3️⃣ 657 AEMIRO DEMEMEW YILAKU
QUARIT(R) 40895
3️⃣ 657 BILEN MEHALEK DANA
WOLAYTA LIQA(R) 350501
5️⃣ 656 ABENEZER TADESSE AMANUEL
SCHOOL OF TOMORROW(YE)(R) 369782
6️⃣ 655 BINIYAM GETACHW MENA
WOLAYTA LIQA(R) 350502
6️⃣ 655 TADIWOS YEHUALASHET KEBEDE
KIDUS RAGUEL(R) 353940
8️⃣ 653 LEUL WUJIRA BERHE
ETHIO BIHERAWI(R) 354931
8️⃣ 653 NAOL SAMUEL EREGA
ODA-SPECIAL BOARDING(R) 342015
🔟 652 MILLION TOLESSA SEDI
WOMBERA(R) 277313
🔟 652 ISRAEL WOLDEGIORGIS WANGORE
WACHAMO(R) 292519

#SHARE
"...ግብፅ 2ኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት" - ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም

[አል ዓይን ኒውስ]

የግብፅ ባለሥልጣናት በመጪው የክረምት ወቅት ሊሞላ ለታቀደው ሁለተኛ ዙር የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ሀገሪቱ በመዘጋጀት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

የግብፅ መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም ትላንት ለ “አል-አረቢያ” ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ፥ ግብፅ ሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ የግድቡን 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጽዕኖ ለመቀነስ በመስኖ መስክ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ መግባታቸውን አንስተዋል፡፡

“ይሁን እና በዓባይ ውሃ ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት እንዳልተውን እናረጋግጣለን” በማለት በውሃ ክፍፍል ረገድ ግብፅ ያላት አቋም የጸና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም ፥ “በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የሁሉም ወገኖች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የምንጥር በመሆኑ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ የተወሰነ የአቋም ለውጥ ማሳየት አለባት” ብለዋል፡፡

“መረጃ ከመለዋወጥ በፊት በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እንፈልጋለን” ሲሉም ነው ኢንጂነር ሞሐመድ የሀገራቸውን አቋም የገለጹት፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ቱርክ ሰራሽ  ሽጉጦች መያዙን የጎንደር ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ህገወጥ የጦር መሳሪያው የተገኘው በተለምዶ ህዳሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግለሰብ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው፡፡

የመኖሪያ ቤቱ  ባለቤት ለጊዜው የተሰወሩ ሲሆን ግለሰቧን ለመያዝና የህገወጥ የጦርመሳሪያውን  ምንጭ ለማወቅ ፖሊስ እየሰራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ  ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች ተደመሰሱ - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ
በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች መደምሰሳቸውን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል፡፡

የጁንታው ቡድን ወታደሮች እና ጠባቂዎች በትግራይ ሲያደርግ የነበረው የሽፍታ እንቅሰቃሴ በመከላከያ ሠራዊቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ውጊያ በማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህገ ወጥ ቡድኑ ወደ መቐለ እርዳታ እና ሌሎች ነገሮችን ለማጓጓዝ የሚያስችሉ ወሳኝ ቦታዎችን በመያዝ ሲዋጋ የነበረ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊቱ ተደምስሷል ነው የተባለው፡፡

አሁን ላይ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑ ተመላክቷል፡፡