የዕዙ ስታፍ ሴት የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች የስራ አፈፃፀም ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ባካሄደው ውይይት የጠቅላይ መምሪያው ሴት የሠራዊት አባላት የተሰጣቸውን ግዳጅና ተልዕኮ በውጤታማነት መፈፀማቸውን የዕዙ ሴቶችና ማኀበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ሸዋዬ ካህሳይ ተናግረዋል።
እንደ ዕዝ ሴቶችን በሁለንተናዊ መስክ ለማብቃት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች የተሻለ አፈፃፀም ነበራቸው ያሉት ሌተናል ኮሎኔል ሸዋዬ ካህሳይ የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣አሠራርና መመሪያው በሚፈቅደው መሠረት የመብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው ያለ አመራር ያሳየው ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነትና ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።
ከውይይቱ ማጠቃለያ በኋላ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለዕቅዱ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ዘጋቢ አለምፀሃይ ተሾመ
ፎቶግራፍ አንዷለም ከፍያለው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
የሁሉም ዕዞች ጤና መምሪያ ሃላፊዎችና የደረጃ -3 ሆስፒታል አዛዦች ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘውን የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኙ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው የ2016 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የአዲሡን በጀት ዓመት የስራ እቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ የተሳተፉ የሁሉም ዕዞች ጤና መምሪያ ሃላፊዎችና የደረጃ-3 ሆስፒታል አዛዦች ቢሾፍቱ ከተማ ተገኝተው የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን ተዘዋዉረው ተመልክተዋል።
በዕለቱም ለጎብኝዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የተቀበሉትና ስለ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታሉ የስራ እንቅስቃሴ ገለፃ ያደረጉት የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሸዋዬ ሃይሌ መከላከያ ተቋማዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ የሠራዊቱን ተልዕኮ የሚመጥን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግና የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደትን የሚያሳልጡ የጤና መሠረተ-ልማቶችን ለማስፋፋት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ሠራዊታችን ዘመኑን የሚመጥን፤ የተሟላ እና ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት ማግኘት ይገባዋል ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራል ሸዋዬ ሃይሌ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ከሠራዊታችን ጤና መበልፀግና የተሟላ ፈውስና እንክብካቤ ማግኘት ባሻገር እንደ ሃገር የጤናውን ዘርፍ አንድ እርምጃ የማራመድ አቅምን የተጎናፀፈ እጅግ ዘመናዊ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሆስፒታሉ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድ ተመርቆ በይፋ ስራ መጀመሩን ያስታወሡት የሆስፒታሉ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሸዋዬ በአሁኑ ወቅትም ታካሚ የሠራዊት አባላትን ተቀብሎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንና በሂደትም የመጨረሻ አቅሙን ሙሉ በሙሉ አሟጦ ግልጋሎት መስጠት እንዲችል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ሆስፒታሉን ተዘዋዉረው ከጎበኙ የጤናው ዘርፍ ስራ አመራሮች መካከል
በጦር ሃይሎች ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሜዲካል ሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ሙሉ ተስፋዬ እና የሠሜን ምዕራብ ዕዝ ደረጃ-3 ሆስፒታል አዛዥ ኮሎኔል ዶክተር ታደገ አበራ በሠጡት አስተያየት በተቋማዊ ሪፎርም ትግበራው የሠራዊቱ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ እያገኘ መሆኑን ጠቁመው በማናቸውም ግዳጅ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ቢደርስብኝ ታክሜ መዳን እችላለሁ የሚል መተማመንን የሚፈጥር ተቋም ተገንብቶ በማየታችን ክብር ተሠምቶናል ብለዋል።
መከላከያ በጤናው አገልግሎት ዘርፍ እያሳየ ያለው እምርታ ዛሬን ብቻ ሳይሆን መጪውን ዘመን እና ትውልድን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የተመለከቱት የተራቀቀ ቴክኖሎጂን የታጠቀው ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አረጋግጦልናል ያሉት ከፍተኛ መኮንኖቹ እነዚህ ጅምሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በየተመደቡበት የስራ ሃላፊነት ጠንክረው እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በአዳማ ያካሄደውን የ2016 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የመጪውን አዲስ በጀት ዓመት የስራ እቅድ ትውውቅ መድረክ ሲያጠናቅቅ የስራ መመሪያ የሠጡት የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በመጪዎቹ ስምንት እና ሰባት ዓመታት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና ተመራጭ የሆነ የጤና አገልግሎትን ዕውን ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ስለመሆኑ መግለፃቸው የሚታወስ ነው።
ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶ ግራፍ እንደሻው ስሜ

ስልጠና ለፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በህዳሴ ኮር ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ የመቶ አመራሮች በሰራዊት ስነ ልቦና ግንባታ እና የታችኛው አመራር ሚናን በሚመለከት ትምህርት ሠጥተዋል።
ሠራዊት በየጊዜው ስልጠናዎችን በማከናወን ዘመኑ ከሚጠይቀው ቴክኖሎጂ ጋር ራሱን እያስተዋወቀ በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ሰራዊት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በስልጠና የሚገኘውን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የምትመሩትን ሰራዊት መመሪያ እና አሰራርን ብቻ በመከተል ለጠንካራ አሃድ ግንባታ ስራ ማዋል ይገባችኋል ሲሉ አሥገንዝበዋል።
የኮሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ደስታው ተመስገን በበኩላቸው የኮሩ የሰራዊት አባላት ከግዳጅ ጎን ለጎን ስልጠናዎችን እያደረገ የቆየ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የሰራዊቱን ስነ ልቦና የሚያጠናክሩ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
ዘጋቢ ቃኘው ካሳሁን
ፎቶግራፍ ቃኘው ካሳሁን

የሠራዊቱ ህይወት
የምስራቅ ዕዝ ሠራዊት አገር የማፅናት ተጋድሎ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ኢትዮጵያ ዘመናዊና ጠንካራ የጦር ኃይል እንዲኖራት ከነበራቸው ፍላጎት በመነሳት በ1935 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ 11 ሻለቆችን የያዘ መደበኛ ሠራዊት አቋቋሙ።
ከነዚህ ሻለቆች መሃከልም የአሁኑ ምስራቅ ዕዝ የያኔው 3ኛ ሻለቃ በኋላም ወደ ክፍለ ጦር በማደጉ ብርጋዲየር ጀኔራል አሰፋው ወልደ ጊዮርጊስ የ3ኛ ክፍለጦር አዛዥ ሆነው ተመደቡ፡፡
በ180 ወታደሮች የተመሰረተው 3ኛ አንበሳው ክፍለጦር አደረጃጀቱን በማስፋት 2ኛና 5ኛ ሚሊሺያ ክፍለጦር የተባሉ ተጨምረው የዚያድ ባሬን ወረራ ለመከላከልና የተጋረጠብንን አገራዊ የደህንነት ስጋት ለመቀልበስ እንደ አዲስ በማደራጀት ምስራቅ ዕዝ ነሃሴ 21 ቀን 1969 ዓ.ም በሐረር ከተማ ተመሠረተ፡፡
ምስራቅ ዕዝ እንደተቋም የተሰጠው ግዳጅ ግልፅ እና ወቅታዊ ነበር ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ወረራውን እያስፋፋ የመጣውን የሶማሊያ ወራሪ ኃይል በመልሶ ማጥቃት በወረራ ተይዘው የነበሩ የኢትዮጵያን ግዛቶች ማስመለስና ሉዓላዊነትን ማስከበር ነው፡፡
ምስራቅ ዕዝ የነበረው ሃይል እና የታጠቀው መሳሪያ ከሶማሊያ ዝግጅት አንፃር እጅግ በጣም አነስተኛ ስለነበር በጎዴ ይገኝ የነበረውን አነስተኛ የወገን ሃይል ለማጠናከር የ79ኛ ሚሊሺያ ብርጌድ ከ219ኛ ነበልባል ጦር ጋር ተደርቦለት የጠላትን እንቅስቃሴ ሊገታ ችሏል፡፡
በመስዋዕትነቱም ደማቅ ታሪክን ፅፏል፡፡
የሶማሊያ ጦር የጦርነት ቀጠናውን እያሰፋ በዋርደር፣ በደገሃቡር፣ በቀብሪደሃርና በሌሎችም ስፍራዎች የነበሩት የወገን አነስተኛ የሰራዊት ክፍሎች በርካታ ሃይል ተጠቅሞ ለመደምስስ ቢሞክርም አልተሳካለትም።
ጀግኗቻችን እየተጣደፈ የሚመጣውን የጠላት ሃይል በመጋፈጥ ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው በከፈሉት መስዋዕትነት የጠላትን ሃይል በማዳከምና መሳሪያዎቹን በማውደም እስከ መጨረሻዋ የህይወት ፍፃሜ ድረስ ተዋግተዋል፡፡ ድልም አምጥተዋል።
በዳንኤል አወል

"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን ለማተራመስ የሚደረግን እርምጃ በዝምታ አትመለከትም" ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በቀጣይ የሚኖረው አዲስ የሰላም ተልዕኮ አወቃቀር ሁኔታ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ላይ አዲስ ስጋት ይዞ መምጣቱ ኢትዮጵያን የሚያሳስብ ሆኗል፡፡
የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዚሁ አዲስ ሽግግር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፣ ቀጠናው ሊተነበይ ወደማይቻል ፈተና ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡ በሁኔታው ላይ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ ወታደር ያዋጡ አገሮች ተደጋጋሚ ጥሪዎችና አስተያየቶች ትኩረት አልተሰጣቸውም፡፡
የመከላከያ ሠራዊታችንን መልካም ስምና ዝናን እንዲሁም መስዋዕትነት የሚያጠለሹ ተከታታይ መግለጫዎች ሲወጡ ኢትዮጵያ በዝምታ እንድታልፍ ከአንዳንድ ወገኖች በኩል ፍላጐት መኖሩ ይታያል፡፡ ሌሎች ተዋናዮች የአፍሪካ ቀንድ ክልልን ለማተራመስ እርምጃ ሲወስዱ ኢትዮጵያ በዝምታ አትመለከትም፡፡ ይህም በመሆኑ በቀጣናው የብሄራዊ ደህንነቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ሁሉ በንቃት እየተከታተለች ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ ለሶማሊያና ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ መስፈን፣ ለጋራ ዕድገት እና በክልሉ ያሉ ህዝቦች መካከል ያለውን የጠበቀ የእርስ በርስ ትስስር ይበልጥ እንዲጎለብት ያላሰለሰ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች፡፡
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ መንግስት ጋር ያለውን ወቅታዊ አለመግባባት ለመፍታት እንዲያስችል በተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ላይም በንቃት ተሳትፎ አድርጋለች፡፡ በእነዚህ ንግግሮች ተጨባጭ ውጤቶችም ታይተዋል። የሶማሊያ መንግስት እነዚህን ሰላም ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች ከማጠናከር ይልቅ ቀጠናውን ለማተራመስ ከሚሹ የውጭ ኃይሎች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡
በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደውን አዲስ የሰላም ተልዕኮ የማዘጋጀት እና የመፍቀድ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ሁሉ በቀጠናው የሚገኙና ቀደም ሲል ወታደር አዋጭ የሆኑ አገራትን ተገቢ የሆኑ ስጋቶች ሁሉ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡ ለአጭር ጊዜ ፍላጎታቸው እና ከንቱ አላማቸው ሲሉ በክልሉ ውጥረትን ለማቀጣጠል የሚሞክሩ ኃይሎች ዕኩይ ተግባራቸው የሚያስከትሏቸዉን መዘዞች መሸከም ይኖርባቸዋል፡፡ ቀደም ሲል አህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን አበረታች ውጤት አደጋ ላይ የሚጥሉና የሚቀለብሱ ድርጊቶች ኢትዮጵያ አትታገስም።
ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ከሶማሊያ ህዝብ እና ከአለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል አሁንም ቁርጠኛ አቋም አላት፡፡
ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፤ኢትዮጵያ

ዕዙ ለሐረሪ ክልል ሰላም እና እድገት የከፈለውን መስዋዕትነት ህዝባችን መቼም አይረሳውም ፦
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ነሃሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም
የሀረሪ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት ለሀረሪ ክልልም ሆነ ለምስራቅ ኢትዮጵያ ሰላም እና እድገት እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መከላከያ ሰራዊቱ በተለይም ምስራቅ ዕዝ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡
አቶ ኦርዲን በድሪ ከምስራቅ ዕዝ ሚዲያ ቡድን ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ እንደገለፁት፡-ምስራቅ ዕዝ በጣም አንጋፋ ተቋም በመሆኑ የምስራቁ የአገራችን ክፍል መገለጫ ብለን ልንገልፀው እንችላለን፤ይህን ለማለት የሚያስችለን ደግሞ የቀጠናውን በተለይም የክልላችንን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ የከፈለውን መስዋዕትነት በማየት ነው ብለዋል።
ለኛ ሲባል የተከፈለውን ውድ መስዋዕትነት የሐረሪ ክልል ህዝብ እና መንግስት መቼም ቢሆን አንረሳውም ነው ያሉት ርዕሠ መስተዳድሩ፡፡
በተለይም ከለውጡ ዋዜማ ጀምሮ በክልላችን የህግ የበላይነት አለመከበር ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ የፀጥታ ችግሮች ሲፈጠሩ ቀድሞ የሚደርሰው ምስራቅ ዕዝ ነበር፣ይህም የሆነበት ምክንያት የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ማለትም ፖሊስ እና ሚሊሽያ ጠንካራ ቁመና ያልነበራቸው እና ነፃ እንዲሁም ገለልተኛ ሆነው ባለመደራጀታቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ሥለነበር ነው ሲሉም ገልፀዋል።
በአሁኑ ሰዓት በተለይም በምስራቁ የአገራችን ክፍል ያለው ሠላም የተሻለ እንዲሆን ህዝቡ በተረጋጋ ሁኔታ ኑሮውን እንዲመራ፣ሰላማዊ ህይወት እንዲኖረው ከማድረግ በኩል የምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ ድጋፍ እና እገዛ አድርጓል፤በተለይም በሐረሪ ክልል በኩል ሠላም እና ደህንነትን ከማረጋገጥ ባሻገር በልማቱ ላይ የምስራቅ ዕዝ ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲ በድሪ የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ስናከብር ዕዙ እና አጠቃላይ መከላከያ ሠራዊታችን አንድነቱን የበለጠ የሚያጠናክርበት፣ ድሎቹን የሚያሰፋበት አጋጣሚ እንደሚሆን እምነቴ ነው ብለዋል።
እንደ ሀረሪ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን እንደ አንድ መልካም አጋጣሚ እንወስደዋለን አጋጣሚው ከዕዙ የሠራዊት አባላት ጋር የነበረንን መልካም ግንኙነት የበለጠ የምናጠናክርበት እና የምናድስበት በሰላም፣በልማት እና በፀጥታ በኩል ያስመዘገብናቸውን ድሎች የምናሰፋበት አዲስ ምዕራፍ ይሆናል ብየ አስባለሁ ብለዋል ርዕሠ መስተዳደሩ፡፡