FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
33.7K subscribers
22.4K photos
8 videos
9 files
6.03K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የክፍለ ጦሩ ሠራዊት ግዳጁን በብቃት እና በውጤት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሽፈራው ምናሉ በክፍለ ጦሩ የተለያዩ ክፍሎች ከተውጣጡ የሠራዊቱ አመራሮችና አባላት ጋር አሁናዊና የነበረውን የግዳጅ አፈፃፀም አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል ።

በውይይቱ ላይ የክፍለ ጦሩ ሠራዊት ሀገርና ህዝብ የሠጡትን ሃላፊነት በብቃትና በታማኝነት በድል እየተወጣ ነው ብለዋል ።

እስካሁን ባደረግናቸው ስምሪቶች ፅንፈኞችን በመደምሰስ እኩይ የሴራ ጥንስሳቸውን አምክነን በየአካባቢው ህዝቡ በሠላም ወጥቶ እንዲገባና በተረጋጋ ሁኔታ መደበኛ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን ማድረግ ችለናል ያሉት የክፍለ ጦሩ አዛዥ በቀጣይም ይህንኑ ተግባር አጠናክረን በማስቀጠል የህዝብን ሠላም የሃገርን ደህንነት እናፀናለን ሲሉ ተናግረዋል ።

በውይይቱ የተሳተፉ የክፉለ ጦሩ የሠራዊት አባላትና አመራሮች የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በፅናት በመሻገር የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ በድል በማጠናቀቅ የአካባቢውን ሠላም በዘላቂነት ለማስቀጠል እየሰሩ መሆኑን እና ይህንኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል ።

ዘጋቢ አህመድ ሰይድ
ፎቶግራፍ አጥናፉ አለሙ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ህዝብ በከሚሴ ከተማ የመከላከያ ሠራዊትን በመደገፍ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡  

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
    
በከሚሴው ሰላማዊ ሰልፍ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በከተማችን የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የመከላከያ ሰራዊታችን በዞኑ የሚያደርገውን ወደር የሌለው ሰላም የማስፈን ስራ ለመደገፍ እና ለማመስገን መሆኑን እና ምንጊዜም በማንኛውም ወቅትና ሰዓት ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን መሆናችንን ለጠላትም ለወዳጅም ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ የህዝብ አንድንት ለማጠናከርና የዞኑ ብሎም የሀገር የሰላም ጠንቅ የሆኑትን የፅንፈኛውን እና የሸኔን ቡድን ለማውገዝ እንዲሁም የሠራዊቱን ሞራል ለመገንባት የተካሄደ ሰልፍ መሆኑንም ገልፀዋል።  

የሰልፉ ተሳታፊዎች በሰላማዊ ሰልፍ በፀረ-ህዝብ ሀይሎች በዞኑ የሚታየውን የህገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውርን እና በፅንፈኞችና በአሸባሪው ሸኔ ስውር ሴራ በሰሜን ሽዋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች ሲከሰት የቆየው አለመግባባት የሰላማችን ዘብ በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን በመወገዱ ለሠራዊቱ ያለንን ክብር እና ምስጋና ለመግለፅ ነውም ብለዋል።

የፅንፈኛውንና የሸኔን መጥፎ ተግባር ከሰራዊታችን ጎን ሆነን ለመታገል ያለንን ዝግጁነት በማሳየት ሁሌም ከሠራዊታችን ጎን መሆናችንን እናረጋግጣለን ሲሉ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡

ዘጋቢ ስመኘው እንየው
ፎቶግራፍ ሳሙኤል ነጋ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ተቋማዊ ግቦችን ለማሳካት የፈጠራ ስራዎችን ማበረታታት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
       
በምዕራብ ዕዝ ሙያተኞች ተቋማዊ ተልዕኳቸውን ለመወጣት የፈጠራ ስራዎችን ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸውን የዕዙ መገናኛ እና ኢንፎርሜሸን መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል አማረ ዋኘው ተናግረዋል። በመገናኛ ክፍሉ እየተሰሩ የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች ለተልዕኮ ስኬታማነት ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውንም ገልፀዋል።
       
ኮሎኔል አማረ የግዳጅ ጄኔሬተሮችን እና የመገናኛ ሬዲዮኖችን በወቅቱና በአግባቡ ጠግኖ ለግዳጅ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የመለዋወጫ እጥረት ሲያጋጥም የፈጠራ ስራዎችን በመጠቀም በርካታ ወጪዎችን ማስቀረት ችለናል ነው ያሉት።
     
ባሳለፍነው በጀት አመት የራዲዮ ትራንስፎርመር፣ የጄኔሬተር ስኬተር እና የጄኔሬተር አርማቸሮችን በሞደፊክ ሰርተው ለአገልግሎት በማብቃት ከ400 ሺህ ብር በላይ ወጪ ማዳን መቻሉንም ሃላፊው ገልፀዋል።
        
ለተቋማዊ ግቦች መሳካት የፈጠራ ሙያተኞች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራትና የዕዙን የግንኙነት ስርዓት በየትኛውም ጊዜ ወይም ሁኔታ ሚስጢራዊነቱን በጠበቀ መንገድ በፍጥነት ማከናወን ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ሃላፊው ምዕራብ ዕዝ ህዝባዊና ሃገራዊ ግዳጁን በአስተማማኝ ብቃት እንዲወጣ ክፍሉ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።
       
በተለያዩ ጊዜና ቦታዎች በግዳጅ ወቅት የሚያጋጥሙ የግንኙነት ማቴሪያል ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እንደሚያደርጉ የተናገሩት በክፍሉ የጥገና ሙያተኛና የፈጠራ ባለቤት የሆኑት ሻምበል አዲስ ዓለም በበኩላቸው በቀጣይም በዚህ የፈጠራ ተግባር ይበልጥ ችግር ፈች በሆነ አግባብ ጠንክረው እንደመሚሠሩ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ሰማሀኝ ጥላሁን
ፎቶግራፍ ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ኮሩ በወሰደው እርምጃ አሸባሪው ሸኔ እየተደመሰሰና እየተማረከ ይገኛል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

በምዕራብ ሸዋ ዞን ሠሞኑን በቀጠናው የሚገኘው የኮሩ ሠራዊት በወሰዱት እርምጃ የሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የምዕራብ ዕዝ የኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ረሽድ ኢብራሂም ተናግረዋል።

የኮሩ ሠራዊት በከፍተኛ ሞራልና ወኔ ተልዕኳቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ የተናገሩት ኮሎኔል ረሽድ፤ ሚዳቀኝ ወረዳ ገራዶ ቡተች ሆራ በተባሉ ቦታዎች በተደረገ ስምሪት ሰባ አምስት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ሲደመሰሱ አሥራ አንዱ መማረካቸውንም ገልፀዋል።

በዘመቻው 01 ድሽቃ ፣23 ክላሽ 13 የወገብ ትጥቅ፣ 40 የክላሽ ካዝና ፣ ተተኳሽና ጥይት ከሽብር ቡድኑ ማስቀረት መቻሉን ተናግረዋል።

መቶ አለቃ ጀማል በበኩላቸው ሸኔን በማሰስ አካባቢውን ሠላም ለማድረግ ከህዝቡ ጋር በጥምረት የምናደርገው  ሥራ ውጤት እያመጣ በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ዘጋቢ አሸናፊ መሸሻ
ፎቶ ግራፍ አሸናፊ መሸሻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ምስራቅ ዕዝ ባለፉት አራት አስርተ ዓመታት የፈፀማቸውን ገድሎች ቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡  
                  የዕዝ አመራሮች 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጀኔራል ግዛው ኡማ እንደተናገሩት ምስራቅ ዕዝ በርካታ የህይወት መስዋዕትነትን በመክፈል የምስራቁን የአገራችን ክፍል ሰላም ያረጋገጠ ነው።

አገር የገጠማትን የህልውና ማዳን ግዳጅም ቀድሞ በመድረስ የጠላትን የሃይል ሚዛን በማዛባት የውጊያ ግለቱን ጠብቆ በጠላት ላይ ድንገተኝነትን በማትረፍ አገርን ከብተና በመታደግ ኦፕሬሽናል አመራሩ ከአባሉ ጋር በመቀናጀት ግዳጁን በቁርጠኝነት ተዋጥቷል ብለዋል፡፡

ምስራቅ ዕዝ ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበለ የመጣና በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች አንፀባራቂ ድሎችን እያስመዘገበ ያለ እነዚህን ድሎቹን አቅቦ በማስቀጠል ቀጣይ የሚሰጡትን ግዳጆች በአኩሪ ተጋድሎ በመፈፀም የአገራችንን ሰላም እንደሚያሥጠብቅም ሜጄር ጄኔራል ግዛው አረጋግጠዋል።

የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሜጄር ጄኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ በበኩላቸው የዕዙ የሰራዊት አባላትና አመራር የውጊያ ድጋፍና አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች በመጣመር ግዳጃቸውን በሚገባ በመፈፀም መስዋዕትነት በመክፈል አገርን ከብተና አድነዋል ብለዋል። ዕዙ ግዳጆችን ሲወጣም ህዝቡ ከሰራዊታችን ጎን ተሰልፎ ድጋፍ በማድረግ የተለያዩ አልባሳትና ምግቦችን በማቅረብ እንዲሁም ለሰራዊቱ ሞራል በመስጠት ትልቅ አቅምና ጉልበት ሆነዋል ነው ያሉት።

ዕዙ በምስራቅ የሚነሱ የአልሸባብና የሸኔ ትንኮሳዎችን ከመመከት ባሻገር በአማራ ክልል ህግ-የማስከበር ግዳጁን እየፈፀመ ያለ መሆኑን አውስተው ቀደም ባሉ  ዓመታት በአሚሶም ጥላ ስርና ድጋፍ ሰጪ ሃይል በመሆን በተፈለገው አቅጣጫ በመንቀሳቀስ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የቻለ ጠንካራ ዕዝ ነው ብለዋል፡፡

ዕዙ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ አገርን ያፀና ገድሎችን የፈፀመ በርካታ ጀግኖች አመራሮችን እና አባላትን ያፈራ መሆኑንም ገልፀዋል።

ዘጋቢ አወል መሃመድ
ፎቶግራፍ አወል መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ሠራዊቱ ከዞኑ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ሠላም ማረጋገጡን የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ተናገሩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ
በምስራቅ ወለጋ ዞን ሰራዊቱና የዞኑ የፀጥታ ሀይል በሰሩት የተቀናጀ ስራ ዞኑ የልማት ስራዎችን ያለምንም ስጋት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ህዝብን ሲዘርፍና ሲገድል የነበረው አሸባሪው የሸኔ ቡድን በተገቢው መንገድ በመቀጥቀጡ ከሰራዊታችን ፊት ቆሞ የመዋጋት አቅም አጥቶና ተስፍ ቆርጦ መበታተኑንም ተናግረዋል።

ሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና ሲቪል አመራሮች ከሠራዊቱ ጋር ተጣምረው በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ዘራፊና አውዳሚ ሀይል ሙሉ በሙሉ ከዞኑ በማጥፍት ለሰላም ናፍቂው ህዝብ የተሟላ ሰላም ማረጋገጥ አለብን ሲሉ አመላክተዋል።

አሁን የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ሁላችንም ከትላንት በተሻለ ደረጃ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወጋሪ ነገራ በበኩላቸው ጠላት ያቀደውን የጥፋት ሴራ በማክሸፍ ከሰራዊቱ ጋር በርካታ ስራዎችን በጋራ በመሰራት ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን አሥረድተዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው ለቀጠናው ሰላምና መረጋገጥ ጀግናው ሰራዊታችን በዞኑ ሰላም እንዲሰፍን ለከፈለው መስዋዕትነት ክብር ይገባዋል ብለዋል።

ዘጋቢ ጌትነት አስናቀው
ፎቶ ግራፍ ቃኘው ካሳሁን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official