Event Addis/ሁነት አዲስ
9.06K subscribers
5.13K photos
5 videos
3 files
3.87K links
https://eventaddis.com

ለአስተያየትና ማስታወቂያ: @Tmanaye
Download Telegram
#ዮቶር_ድግስ

የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል

የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።

በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

ከድምጻዊያኑ በተጨማሪም ኢትዮ ለዛ ባንድ፣ ሻኩራ ባንድ፣ ብርኩማ ባንድ የተሰኙ ባንዶች ድምጻዊያንን ያጅባሉ ተብሏል።

በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው  "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

አለማየሁ ደመቀ ከ1991 ዓ.ም አንስቶ ከ250 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎችን ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን “ዮቶር 1 : ኮብላዩ ካሕን” እና በቅርቡ ለንባብ የበቃውን “ዮቶር 2 ” ለሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ያበረከተ ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት በሙያው፣ በክህሎቱ እና በተሰጥዖው አገር እና ወገንን ሲያገለግል እንደቆየ ይታወሳል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1