Event Addis Media
9.39K subscribers
5.78K photos
10 videos
3 files
4.42K links
Connect with Addis artistic community!

Website: https://eventaddis.com

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"ቀለም" ዲጂታል መጽሔት ዛሬ ለንባብ ይበቃል

የቀለም ዲጂታል መጽሔት አዘጋጆች "የወር ሰው ይበለን! ተባብለን በተለያየን በ30 ቀናችን ይሄው በዛሬው ዕለት ቅፅ 1/ ዕትም 2 ነሐሴ 10 አመሻሽ 12:00 ላይ ለንባብ ይበቃል" ብለዋል።

የቀለም መጽሔት ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ።
https://t.me/kelemofficial
🔥31
📌 "ፓሌሮዳ" አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

የሕክምና ባለሙያ በሆነው ዶ/ር ደሳለው ካሳሁን የተፃፈውና በስነጹሑፋ ባለሙያዎች የተመሰከረለት እንዲሁም በኢትዮጵያ ስነጽሑፍ በአዲስ አቀራረብ የተጻፈ መፅሐፍ ነዉ የተባለለት “ፓሌሮዳ” ኢትዮጽያ ለምን ? የተሰኘዉ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቅቷል።

“ ፓሌሮዳ “ መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክን፣ ሜታፊዚክስን፣ የህክምና አብዮትን፣ ጂኦፖለቲካንና ሀገራዊ አብርሆትን አንድ ላይ አሰናስሎ፣ ያቀረበ መጽሐፍ ሲሆን ሀገራዊ ብሎም አለመአቀፋዊ ፋይዳ ያላቸውን ሀሳቦች የያዘ መጽሐፍ ነው።

በ “ ፓሌሮዳ “ በገሃዱ አለም ተጨባጭ ሁነቶች ላይ ተመስርቶ፣ በተለያየ መነሻ የተሰባሰቡ ምሁራን የመጽሐፈ ሄኖክን መፍቻ አትላሶችን ፍለጋ አብርሆት በተሰኘ ህቡዕ ማህበር ስር ታቅፈው ከኢትዮጵያ ገዳማት እስከ የአውሮፓ የምድር ውስጥ ቤተመጻሕፍት ድረስ የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ ጉዞ የሚያሳይ ሳይንሳዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፍልስፍና ቀመስ እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ልቦለድ ነው።

መፅሐፉን በ ሀሁ መጻህፍት  መደብር እና በሁሉም የመፅሐፍ መደብሮች ያገኙታል ሲል ይትባረክ ዋለልኝ ነግሮናል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
📌የዘቢብ መልኬ አዲስ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው

የደራሲ ዘቢብ መልኬ "ፉካ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ የፊታችን ረቡዕ ነሐሴ 14 2017 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ ውስጥ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይመረቃል።

"ፉካ" የደራሲ ዘቢብ መልኬ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሐፍ ነው።

ደራሲዋ ከዚህ ቀደም “ስብጥር “ግጥም እና የወግ ስብስብ መፅሐፍ፣ “ኮላዥ “ የአጭር ልቦለዶች ስብስብ መጻሕፍትን ለንባብ ማብቃቷ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
4
📌ሁለቱም ጋዜጠኞች የገቡበት አልታወቀም

አንጋፋው ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ ከቀናት በፊት በደኅንነት አካላት ተይዘው መወሰዳቸው እና እስካሁንም የደረሱበት እንደማይታወቅ እና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ተሰማ።

ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ ሰኞ ነሐሴ 5/2017 ቀን ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍኖ መወሰዱ የታወቀ ሲሆን ከቆይታ በኋላ ግን በመንግስት የደኅንነት ኃይሎች እንደተያዘ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይም የሪፖርተር ጋዜጣ ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ዮናስ አማረም ሐሙስ ነሐሴ 8/2017 ከቢሮ እንደወጣ በመንግስት የደኅንነት ኃይሎች ተይዞ መወሰዱ ተነግሯል።

ምንም እንኳን ጋዜጠኞች በመንግስት የደኅንነት አካላት ተይዘው ቢወሰዱም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ድረስ ያሉበት ስፍራ እንደማይታወቅ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውም በጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ደግሞ የአብዱልሰመድ ባለቤት ልጇን ከተገላገለች ጥቂት ቀናት በመሆኑ በአራስ አቅም በየፖሊስ ጣቢያው ለመዞር እንደተገደደች ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ በሪፖርተር ጋዜጣ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ዘገባዎችን እንዲሁም ቃለ ምልልሶችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጠኛ አብዱልሰመድም በአሐዱ ራዲዮ ቀዳሜ ገበያ የተሰኘ ፕሮግራም በማዘጋጀት ለአድማጭ ሲደርስ ቆይቷል፡፡

ጋዜጠኞች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለዘፈቀደ እስር፣ ገድያ እና እንገልት መዳረጋቸው የተለመደ ጉዳይ መሆኑ በርካታ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡

©️መረጃው የሆርን ፍሪኩዌንሲ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
😢1210😱3🤬3
📌“በሆቴሎች ውስጥ የሚደረግ ስብሰባ አይኖርም"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በሚቀጥለው በጀት ዓመት  ሁሉም ክፍለከተማዎች እና ተጠሪ ተቋማት “የሆቴል አገልግሎት ግዢ” እንዳይፈጽሙ አሳስቧል። ቢሮ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው የተመደበው በጀት “የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት እንዲችል” መሆኑን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 350 ቢሊዮን ብር ማፅደቁ ይታወሳል። ከዚህ በጀት ወስጥ 70 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል ሥራዎች የተመደበ ነው። ቀሪው ደግሞ ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው። ከተማዋ በዚህ  በጀቷ “ውጤታማ የሆኑ ሥራዎችን በቁጠባ ለማከናወን” እና “የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት” እንድትችል ተጠሪ ተቋማት እና ክፍለ ከተማዎች በሆቴሎች ውስጥ የሚደረጉትን “ስብሰባዎች” እና “ሥልጠናዎች በመንግሥት  መሰብሰቢያ አዳራሽ ብቻ” እንዲያከናውኑ በደብዳቤ ተገልጾላቸዋል።

በከተማዋ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከው ደብዳቤ “ለልዩ ልዩ ስብሰባዎች፣ ሥልጠናዎችና ግምገማዎች የሆቴል ግዢ አገልግሎት መፈጸም እንደማይችሉ” ይገልጻል። ተቋማቱ ስብሰባ እና ሥልጠና ማካሔድ ካለባቸው በራሳቸው የመሰብሰቢያ አዳራሽ መሆን እንደሚገባው ቢሮ አስታውቋል። ለዚህ እንዲያገለግል “የመንግሥት መሰብሰቢያ አዳራሾችና ካፍቴሪያዎችን በማጠናከር መገልገል” እንዳለባቸው አሳስቧል።

©️ኢትዮ ቲዩብ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
6👍3👏1
📌የደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ይፈፀማል

የአርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

የአርቲስት ደበበ እሸቱ ሥርዓተ ቀብር በተመለከተ በብሔራዊ ቴአትር የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ ሰጥቷል።

አርቲስት ደበበ እሸቱ /ጋሽ ደቤ/ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያኖረ አርቲስት እንደነበር ተገልጿል።

የአርቲስት ስርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።

ከዚያ በፊት አምስት ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የክብር ሽኝት እንደሚደረግለትም ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
7😭5🖕1
📌ስፑትኒክ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ሥርጭት ጀመረ

የስፑትኒክ አፍሪካ ፕሮግራም በአዲስ አበባና አካባቢዋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኤፍ ኤም ለአድማጮች መቅረብ ጀምሯል።

ስፑትኒክ በሀገሪቱ አንጋፋ በሆነው ዩኒቨርሲቲ የሬዲዮ ጣቢያ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የትንታኔ ፕሮግራሞችን ለ6 ሚሊየን አድማጮች ማቅረብ መጀመሩ ተመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል እና የሬዲዮ ማሰራጫ በ36 ቋንቋዎች ፕሮግራሞቹን የሚያቀርብ ሲሆን÷ በዓለም ዙሪያ 15 የይዘት ማዕከላት አሉት፡፡

በአማርኛ ቋንቋ የሚሠራ ብቸኛው የሩሲያ ሚዲያ የሆነው ስፑትኒክ ዘርፈ ብዙ የይዘት ማዕከሉን በፈረንጆቹ 2025 በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡

በተጨማሪም በ7 የአፍሪካ ሀገራት ማለትም በናይጄሪያ፣ ጊኒ፣ ዛምቢያ፣ ካሜሩን፣ ማሊ፣ ኒጀር እና ቦትስዋና ፕሮግራሞቹን እያስተላለፈ ይገኛል፡፡

በአፍሪካ ባሕል ዙሪያ በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞቹ በምርጥ የሬዲዮ መጽሄት እና በምርጥ የሬዲዮ ፕሮግራም ምድቦች የሕብረቱን ሽልማት አግኝቷል፡፡

ስፑትኒክ አፍሪካ የአፍሪካ ብሮድካስቲንግ ሕብረት አባል እና ተሸላሚ እንዲሁም ሰሜናዊ አፍሪካን በሚሸፍነው የዓረብ ብሮድካስቲንግ ሕብረት አባል ነው ሲል FMC ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1‌‌
15👎2👏2🥰1
📌ቻናል 1 ቴሌቪዥን ነሐሴ 18 ይጀምራል

ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦችን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ ዓላማ በማድረግ ስያሜውን "ቻናል 1" ያለው ቻናል ዋን ቴሌቪዥን ጣቢያ ነሐሴ 18  2017 ዓ.ሞ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ  "እሁድን አንድ ላይ" በተሰኘ ፕሮግራም መደበኛ ስርጭቱን እንደሚጀምር  ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከጣቢያው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ጣቢያው ቀደም ብሎ በርካታ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ እንደከረመ እና አዳዲስ የፕሮግራም ይዘቶችን ለተመልካች ይዞ ለመምጣት ዝግጅት ሲያደርግ እንደቆየ ተገልጿል።

ቻናል 1 ወደ መደበኛ ስርጭቱ ሲገባ ከ80 መቶ በላይ አዳዲስ (ኦርጂናል)ይዘት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ድራማዎች፣ ኮሚዲዎች፣ ሪያሊቲ ሾዎች፤ጌም ሾዎች፣ ስፖርታዊ ፕሮግራሞች፣ ሙዚቃዎች፣ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች፣ የልጆች ዝግጅቶች ለትውልድ በሚመጥን መልኩ የተዘጋጁ ሲሆን ቀሪዎቹ 20 ከመቶ የሚሆኑት ይዘቶችም የኢትዮጵያን ቤተሰብ ባህልና ወግ እና ልምድ ግምት ውስጥ ያስገቡ ፕሮግራምች ናቸው ተብሏል።

በፕሮግራም አቅራቢነት ናፍቆት ትዕግሥቱ፣ሊያ ሳሙኤል፣ ስንታየሁ ብዙነህ እና ሌሎችም በጣቢያው በሚተላለፉ ፕሮግራሞች ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው ሙሉ በሙሉ የመዝናኛ ጣቢያው ባይሆንም ዋና ትኩረቱ መዝናኛ እንደሆነም ተነግሯል።

"ቻናል 1" ቴሌቪዥን ጣቢያ ሳምንቱን ሙሉ የ24 ሰዓታት ስርጭት ይኖረዋል ተብሏል።

ጣቢያው በኢትዮ-ሳት ላይ በ11545 H 45000 ፍሪኩዌንሲ ላይ ይገኛል።

ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
👍117
📌ኢትዮጵያ የፈቃድ ሞትን ተግባራዊ ልታደርግ ነው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ጥር ወር በሕክምና ባለሙያ የታገዘ ሞት የሚፈቅድ አዋጅ ማፅደቁን ተከትሎ፤ ጤና ሚኒስቴር ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱ ተዘግቧል።

ረቂቅ መመሪያው ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት በትንሹ ሶስት የጤና ባለሙያዎች በምርመራው ላይ መስማማት እንዳለባቸው ይደነግጋል። በተጨማሪም የቅርብ ዘመዶች የሕመምተኛው ሕይወት ማቆያ ድጋፍ እንዲነሳ በጽሁፍ በፈቃዳቸው መጠየቅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል።

አዋጁ በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲቋረጥ ይፈቅዳል፡፡ ሕጉ ተግባራዊ የሚሆነው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

ሕጉ በማይድን ህመም የሚሰቃዩ ዜጎችን ለመርዳት ያለመ ነው ተብሏል ሲል ሰፑትኒክ ዘግቧል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8🤬2🕊1
📌የደብረ ታቦር በዓል በደብረታቦር ከተማ ተከበረ

የደብረ ታቦር ዓመታዊ በዓል በዛሬው ዕለት በደብረታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተከብሯል፡፡

በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ነሐሴ 13 የሚከበር ሲሆን÷ በደብረታቦር ከተማ ርዕሰ አድባራት ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በደብረታቦር ኢየሱስ ሙዚየም ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡን የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢያለ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
26
📌የቲያትር ቲኬት ዋጋ 200 ብር ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር የመግቢያ ትኬት ዋጋን ከስምንት ዓመት በፊት ከነበረበት 80 ብር ወደ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል።

ቲያትሩ ከ1948 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ኪነጥበብ ከፍ ማለት እና መከበር አለበት በሚል ዋጋዉን ለማሻሻል ጥናት ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ የኪነጥበብን ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና የቲያትር ቤቱን አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች፣ የቲኬት ዋጋው ከዚህ ቀደም በጣም ዝቅተኛ ስለነበር፣ አሁን የተደረገው ጭማሪ ሳይሆን 'ማሻሻያ' ነው ሲሉ አብራርተዋል። የዋጋ ማሻሻያው "ማንንም የማይጎዳ መልኩ" መሆኑን በማስረገጥ፣ የቲኬት ዋጋው ለሁሉም ትያትሮች በ200 ብር መወሰኑን ገልጸዋል።

ኦንላይን ትኬት ሽያጭ እና ሌሎች ለውጦች
ከተመሠረተ 70 ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ ቲያትር፣ አዳዲስ ለውጦችን በማምጣት ተመልካቹን ለማርካት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ከለውጦቹ መካከል ተመልካቾች ከየቤታቸው ሆነው ትኬት መግዛት የሚያስችላቸውን 'ኦንላይን' የቲኬት ሽያጭ ሥርዓት ማመቻቸቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም፣ የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች በቀጣይ ሁሉም ክልሎች የሚሳተፉበት ሥልጠና በብሔራዊ ቲያትር እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህ የዋጋ ማሻሻያ እና ሌሎች ተያያዥ ለውጦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት እና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያግዝ ይጠበቃል ሲል ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👏2211🤯3😱1😭1
📌የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት መዝሙር

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው "ያዘኝ" በሚል ርዕስ አዲስ የመዝሙር ቪድዮ በቅርቡ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

"ያዘኝ" የሚለው የአዲሱ መዝሙር ርዕስ፣ "በፈተና ጊዜ እግዚአብሔር ደግፎኛል" የሚል መንፈሳዊ ትርጉም ያለው ሲሆን፣ መዝሙሩም ተመሳሳይ የምስጋና እና የተስፋ መልዕክትን ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

ይህ ስራቸው፣ ከዚህ ቀደም ካወጧቸው መዝሙሮች እና ካሳተሟቸው መጽሐፍት የቀጠለ የጥበብ ስራቸው አካል ነው።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ከመዝሙር ጥበብ ስራዎቻቸው በተጨማሪ፣ በጽህፈት ቤታቸው በኩል በተለያዩ ማህበራዊ ስራዎች ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ሲገለጽ ቆይቷል።

የአዲሱ የመዝሙር ቪድዮ መቼ እንደሚለቀቅ ዝርዝር መረጃው ገና ይፋ አልተደረገም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁12👎75
📌በአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ  ምክንያት "ከትዳር በላይ" ቴአትር ዛሬ ከመድረክ ይሰናበታል

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተጽፎ በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ የተዘጋጀው "ከትዳር በላይ" የኮሜዲ ቴአትር ከወራት በኃላ በአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ ምክንያት ዛሬ ከመድረክ እንደሚሰናበት ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከተውኔቱ ደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ባለፉት 6 ወራት በዓለም ሲኒማ ሲታይ የቆየው "ከትዳር በላይ" ቴአትሩ ከመድረክ የሚወርድበት ምክንያት አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ በተዋናይነት የሚሳተፍበት "ወደ ማዶ" የተሰኘ ቴአትር በቅርቡ ዓለም አቀፍ ጉዞ ስለሚያደርግ እንደሆነም ተነግሯል።

ከየካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ሲቀረብ የቆየው ቴአትሩ ዛሬ ነሐሴ 14 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ከመድረክ ይሰናበታል።

በቴአትሩ ላይ መስከረም አበራ፣ ሸዋፈራው ደሳለኝ፣ የማታወርቅ ታደሰና መዓዛ ገብረሕይወት፣ ዕፀሕይወት አዳንከኝ፣ ቸርነት ፍቃዱ በተዋናይነት ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
12👏3
📌የሐናን "ሻደይ" ሙዚቃ ለአድማጮች ቀረበ

የወጣቷ ድምጻዊት ሀናን አብዱ "ሻደይ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የሙዚቃ ስራ ከቀናት በፊት በናሆም ሪከርድስ ዩቲዩብ ቻኛል ለሙዚቃ አፍቃሪያን ቀርቧል።

"ሻደይ" ሙዚቃ ላይ በዜማ ይግዛው በላይ በአማርኛ ግጥም ተስፋ አብርሃ በኽምጥኛ ግጥም ይግዛው በላይ በቅንብር ኪዱ አድማሱ ተሳትፈዋል።

የሙዚቃ ቪዲዮውን ዳይሬክተር ያደረገው ይግዛው ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6
📌የኪያ ካሣሁን "ምልምልወይ" ሙዚቃ ተለቀቀ

የድምጻዊት ጠረፍ ካሣሁን (ኪያ) "ምልምልወይ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ የሙዚቃ ስራ በናሆም ሪከርድስ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች ቀርቧል።

በ"ምልምልወይ" ሙዚቃ ላይ በግጥምና ዜማ ይግዛው በላይ በሙዚቃ ቅንብር ኪዱ አድማሱ ተሳትፈዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
7
📌ሎጆችና ሬስቶራንቶች ደረጃ ሊሰጣቸው ነው

የቱሪዝም ሚኒስቴር ቀደም ሲል በሆቴሎችና ሪዞርቶች ላይ ብቻ ሲካሄድ የቆየውን የደረጃ ምዘና ሥራ፣ ሎጆችንና ሬስቶራንቶችን ጭምር እንዲያካትት የሚያስችል አዲስ ሀገራዊ መመዘኛ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

ይህ አዲስ የደረጃ አሰጣጥ ሥርዓት አገሪቱ ለቱሪዝም ዘርፍ የምትሰጠውን ትኩረት ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ የዘርፉን ጥራትና አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ ነው ተብሏል።

የተዘጋጀው መመዘኛ በረቂቅ ደረጃ ተጠናቅቆ፣ በቀጣይነት ለባለድርሻ አካላት ውይይት ቀርቦ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል፣ ከ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ አዳዲስ ሆቴሎች በተገቢው ጊዜ የደረጃ ምደባ እንዲያደርጉ የታቀደ ቢሆንም፣ የደረጃ ምደባው ሂደት ላይ ችግሮች መፈጠራቸው ታውቋል።

የተፈጠሩት ችግሮች ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች እንዳሏቸው ተጠቁሟል። አንደኛው፣ ባለሀብቶች በተያዘው ጊዜ የኮከብ ደረጃ ለመመደብ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አብዛኞቹ ተቋማት የኮከብ ደረጃ ለመመደብ ብቁ ሆነው አለመገኘታቸው ነው። ይህ ደግሞ የቱሪዝም ዘርፉን ጥራት ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ላይ ፈተና እንደሚሆን ተገልጿል ሲል ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌የአነጋጋሪው ሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ማታ ይለቀቃል

የድምጻዊ ናቲ ኬር "ነገር ነገር " የተሰኘ ርዕስ የተሰጠውና በቲክቶክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መድረክ በርካቶች የተቀባበሉት ሙዚቃ ቪዲዮ ነገ አርብ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በድምጻዊው የዩቲዩብ ቻናል ለአድማጮች ተመልካች ይቀርባል ተብሏል።

"ነገር ነገር ባይልሽ ነገር - ተሸክሜ አኖርሽ ነበረ"

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8👍2🔥2
📌 የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሹም ሽር

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ከታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጌትነት ታደሠ ከኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኃላፊነታቸው ተነስተው የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንደተሾሙ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አቶ ጌትነት ታደሰ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሸን ኮሚሽነር ኃላፊ ሆኖ የተመደቡት በአምባሳደር ሽፍራው ሽጉጤ (ዶ/ር) ምትክ መሆኑንም ሰምተናል።

አቶ ጌትነት ታደሠ ከኢቢሲ ስራ አስፈፃሚነታቸው አስቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ እንደነበሩ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍52😁2🤣1
📌በአዲስ አበባ የጋረዱ አሟሟት መነጋገሪያ ሆነ

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 22 አካባቢ በሚገኘው "ቪ.አይ.ፒ ላውንጅ" በተሰኘው ጭፍራ ቤት (ክለብ) ውስጥ በጠባቂነት(ጋረድ) ሆኖ ሲሰራ የቆየው ወጣት ልደቱ አየነው (አቢ) በድንገተኛ ጥቃት እንደተገደለ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በወቅቱም የሟች አስክሬን ለምርመራ የተወሰደ ሲሆን ውጤቱም ከ15 ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ተነግሯል።

ወጣት ልደቱ አየነው (አቢ) በሚሰራበት ቪ.አይ.ፒ ላውንጅ ውስጥ ስራ ላይ እያለ በጩቤ ተወግቶ መገደሉንም የቅርብ ቤተሰቦቹ በማህበራዊ ገፆቻቸው ሲናገሩ ተመልክተናል።

የሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች የሚሰራበት ሆቴል ሰራተኛው ተገደሎበት ለአንድ ቀን እንኳ ስራውን ሳያቆም እየሰራ እንዳለና የአዲስ አበባ ፖሊስ ገዳዮቹን ለህግ በማቅረብና ለጠፋው ህይወት ተመጣጣኝ ፍትህ ለመስጠት ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጉንም ጭምር እየተናገሩ ይገኛሉ።

በዚህም ምክንያት "ፍትህ ለአቢ" እና "ሕጉ ይከበር፣ ፍትህ ይስፈን" በሚል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እያካሄዱ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻቸውም 1ኛ ግልጽና ፍጥነት ያለው ምርመራ እንዲፈጸም 2ኛ የተጠረጠረው አካል በህግ ፊት የሚገባውን ፍርድ እንዲያገኝ 3ኛ ፍትህ ሳይዘገይ በተግባር እንዲፈጸም በአጠቃላይ ለወጣት ልደቱ ፍትህ እንዲሰጠው ጥያቄዎችን እየቀረቡ ይገኛል።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ከአዲስ አበባ ፖሊስና እና ከቪ.አይ.ፒ ላውንጅ ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ቢሞክርም አልተሳካም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8😭8🤔2
Event Addis Media
📌በአዲስ አበባ የጋረዱ አሟሟት መነጋገሪያ ሆነ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ 22 አካባቢ በሚገኘው "ቪ.አይ.ፒ ላውንጅ" በተሰኘው ጭፍራ ቤት (ክለብ) ውስጥ በጠባቂነት(ጋረድ) ሆኖ ሲሰራ የቆየው ወጣት ልደቱ አየነው (አቢ) በድንገተኛ ጥቃት እንደተገደለ ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በወቅቱም የሟች አስክሬን ለምርመራ የተወሰደ ሲሆን ውጤቱም ከ15 ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን…
📌የፖሊስ መግለጫ ስለ ጋረዱ አሟሟት

ቪ አይ ፒ ላውንጅ በሚባል ሆቴል በሁለት ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የሰው ህይወት ማለፉን ተከትሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
                          
ድርጊቱ የተከሰተው ነሀሴ 07 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7 ሰዓት ከሩብ ገደማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሃያ ሁለት አካባቢ በሚገኘው" ቪ አይ ፒ ላውንጅ"  በተባለ ሆቴል ውስጥ ነው።

በዕለቱ በድርጅቱ በጋርድነትና በዲጄ ሰራተኝነት ተቀጥረው በሚሰሩ ልደቱ አያኖ እና ናትናኤል ልዑል በተባሉ ግለሰቦች መካከል ምክንያቱ ባልታወቀ አለመግባባት በተፈጠረ ጸብ ምክንያት ናትናኤል ልዑል የተባለው ግለሰብ ጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረስበት መሆኑን ፖሊስ በስፍራው ደርሶ ካሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።

በቅርብ ርቀት የነበሩ ሰዎች ተጎጂውን ወደ ህክምና በመወሰድ ልደቱ አያኖ የተባለው ግለስብ ከአካባቢው እንዳይሸሽ እየጠበቁት በነበረበት አጋጣሚ  ድብደባው በተፈፀመበት አልጋ ክፍል ቁጥሩ 505 አምስተኛ ፎቅ ላይ ባለ ክፍል ውስጥ ገብቶ በሩን ከውስጥ በመዝጋት ከክፍሉ ባለ መስኮት ወደ መሬት ወድቆ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እርዳታ እየተደረገለት ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ትክክለኛ የአሟሟቱን ሁኔታ ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል።                         

ከባድ ጉዳት የደረሰበት ናትናኤል ልዑል የተባለው ግለሰብ አሁንም በህክምና ተቋም ውስጥ ተኝቶ ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማስረጃ የማሰባሰብ ስራዎችን በመስራት እና የአስክሬን ምርመራ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል የምርመራ ስራው እንደተጠናቀቀ ሙሉ መረጃውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

@EventAddis1
6😭1