Event Addis/ሁነት አዲስ
8.82K subscribers
5.05K photos
5 videos
3 files
3.81K links
https://eventaddis.com

ለአስተያየትና ማስታወቂያ: @Tmanaye
Download Telegram
ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ ዓለምአቀፍ ሞዴል ጆዝሳ እስዝተር ኒኮሌቴን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥራት ፣ደረጃቸው የተመሰከረላቸው የሜሊስ ፋሽን እና ትሬዲንግ ልዩ ልዩ የፋሽን እና የዲዛይን ምርቶች የሚቀረቡባቸው ሱቆች መከፈቱን በማስመልከት ዓለምአቀፍ እውቅና ያላትን የሃንጋሪይ ተወላጅ ከሆነችው ኢንተርናሽናል ሞዴል ጆዝሳ እስዝተር ኒኮሌቴን ጋር አብሮ ለመስራት የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር ይፋ ማድረጊያ ሥነሥርዓት ሐሙስ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሀያት ሪጀንሲ አካሄዷል።

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በኢንተርናሽናል ሞዴል እና ዲዝይነር ሜላት ሚካኤል የተመሰረተ ሲሆን ፤ በቻይና ጉዋንዡ ሆንግኮንግ እና ሻንጋይ ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ዕውቅ የፋሽንና ዲዛይን ምርቶችን እንዲሁም ብራንዶችን ለዓለም ገበያ የሚያቀርብባቸው ሱቆችን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኘ ተገልጿል።

ኢንተርናሽናል ሞዴል እና ዲዝይነር ሜላት ሚካኤል በዓለምአቀፉ ፋሽን መድረክ ላይ የእሷን አሻራ ለማሳረፍ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ በኩነቱ ላይ ገልጻለች።

ሜሊስ ፋሽን እና ትሬድንግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥራት ደረጃቸው የተመሰከረላቸው የሜሊስ ፋሽን እና ትሬዲንግ ልዩ ልዩ የፋሽን ሱቆች እንደፈከትም ይፋ አድርጓል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የማይ ሶሮባን ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “ሒሳብ ትምህርት ይከብዳል” የሚል የተሳሳተ አመለካከት በማስወገድ ጉብዝና ያሽልማል › በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት እና የስሌት ውድድር በሀገራችን በሚገኙ ሁለም ትምህርት ቤቶች ለማከናወን የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው የሒሳብ ትምህርት አወዳዳሪ ተቋም ነው፡፡

በማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ የ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሒሳብ ትምህርት ውድድር ከ50 ከተሞች የተውጣጡ ከ2ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች እና ከ3መቶ ሺ በላይ ተማሪዎችን አሳትፏል፡፡

ውድድሩ በአጠቃላይ ስድስት ዙሮች ሲኖሩት አምስቱ ዙሮች በየከተሞቹ የተከናወኑ ሲሆን የመጨረሻው ወይም ስድስተኛው ዙር የፍጻሜ ውድድር ከሁሉም ከተሞች የየከተማው አሸናፊ ተማሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሚሊኒየም አዳራሽ የመጨረሻውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ለከፍተኛ ሽልማት ይወዳደራሉ፡፡ የዚህ ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች በጠቅላላ አራት ሚሊዮን ብር የሚፈጅ የገንዘብና የአይነት ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል።

በዳኝነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የኮተቤ መምህራን ዩኒቨርስቲ መምህራን ሲሳተፉ የየከተማ ተወካዮቻቸውም በታዛቢነት እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የመዝጊያው መርሃግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 1 2016 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ ዛሬ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ኮሜዲያን ቤቲ ዋኖስ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
በኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ ስም የተሰየመ የድረገጽ አገልግሎት ይፋ ተደረገ

ታሪካዊው በሆነው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ስያሜ የተሰራው ድረገጽ  ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የምሥራቅ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በራማዳ ሆቴል በተከናወነው መርሐግብር ይፋ ተደርጓል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም  እየተከናወነ ያለውን የግንባታ ኘሮጀክት ያስተዋውቃል የተባለው ድረገጹ በገዳሙ እየተሰራ ያለውን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያኗንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ማድረግን ዓላማ አድርጎ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።

www.kidusyaredzedebrehawi.com በገዳሙ እየተከናወነ ያለውን ፕሮጀክት አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን ገዳሙን በገንዘብ በቀጥታ ማገዝ እንድችሉ ተደርጎ እንደበለጸገ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

ቅዱስ ያሬድ ከ1500 አመታት በፊት የኖረ፣ የመጀመሪያው የአለማችን  የዜማ አውጭ፣ የመጀመሪያው የመፃሕፍት ደራሲ፣ ታላቅ የፍልስፍና ሰው፣ የብዙ ነገሮች ሊቅ፣ ባለቅኔ የሆነ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ግዙፍ ባለጸጋ ነው።

ቅዱስ ያሬድ ባስተማረበት በመጨረሻም በተሰወረበት ስፍራ፣ በሰሜን ተራራ ላይ በደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም በርካታ ልማቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ማህበሩ አስታውቋል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
ካውሰር ( ሻሊና ሄልዝ ኬር)የተሰኘ ድርጅት አራት የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶችን ያስተዋውቀበትን ኩነት አካሄድ

ካውሰር PLC( ሻሊና ሄልዝ ኬር) በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያተረፈ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ይዟቸው የመጣቸውን አዳዲስ ምርቶች ሰኔ 6 2016 ዓ.ም አስተዋውቋል።

ከነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱ ሞናሊሳ ሲባል ይህም የቆዳ እንክብካቤን ለመጠበቅ የሚያስችል ሎሽንና ክሬም ነው።

ኤፒግሎው የተሰኘው ደግሞ ለአፍሪካ ቆዳ የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ጥቁር ነጠብጣቦች እና ዥንጉርጉር ፊትን እና የተለመዱ የቆዳ ስጋቶችን በ28 ቀናት ውስጥ በመቀነስ ብቻ የሚታይ ለውጥ የሚሰጥ የቆዳ መንከባከቢያ እንደሆነ ተገልጿል።

ሌላው ፍሎደንት የተባለው የጥርስ ሳሙና ምርት ሲሆን በፍሎራይድ ለተጠቃ ጥርስ፣ ለአፍ ጤንነት፣ የጥርስ መቦርቦርን የሚታደግ እንደሆነ ተነግሯል።

የመጨረሻው ምርት ጀርሞል የተሰኘ ሳሙና ሲሆን  ሰውነትን ከጀርሞች ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል።

ሻሊና ሄልዝ ኬር 40 አመትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን እስካሁን በ22  የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሰርቷል።

ድርጅቱ በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ላይ 6 ክፍለ ከተሞች ላይ ስራ የጀመረ ሲሆን 1000 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል።

ቴሌግራም: @EventAddis1
የኔ መኪና እና የኔ ዴልቨሪ አገልግሎቶች ይፋ ሆኑ

ቲዎስ ቴክኖሎጂ "የኔ መኪና" እና "የኔ ዴልቨሪ" የተሰኙ ሶፍትዌሮችን በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባቱን ሰኔ 6 2016 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በተሰናዳ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።

"የኔ መኪና" የትራንስፖርት ዘርፉን ከማዘመን አኳያ በርካታ ጥቅሞች እንደሚሰጥ የተነገረ ሲሆን በተለይም በመንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣንና በተሽከርካሪ ባለንብረቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ያለምንም ክፍተት በመናበብ ስራቸውን ምቹ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረግም በላይ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን ማሳደስ ያለባቸውን ነገሮች በማስታወስ ከቅጣት እና አላስፈላጊ እንግልት የሚያድን ሶፍትዌር እንደሆነ ተገልጿል።

ሌላኛው "የኔ ዴሊቨሪ" ሶፍትዌር ሲሆን የተለያዩ ዶክመንቶችን፣ ሰነዶችን፣ እቃዎችን እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ቴከኖሎጂ በመጠቀም ለግለሰቦች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለሆስፒታሎች ለማድረስ የበለጸገ ሶፍትዌር እንደሆነ ተነግሯል።

ቲዎስ ቴክኖሎጂ ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ሶፍትዌር መተግበሪያዎችን በማበልጽግ እየሰራ የሚገኘ ድርጅት ነው።

ቴሌግራም: @EventAddis1
ድምጻዊ ጉቱ አበራ "ጋፊኮ" የተሰኘ አልበሙን በሚቀጥለው ሳምንት ለአድማጮች ያደርሳል

ድምፃዊ ጉቱ አበራ “ጋፊኮ” የተሰኘ የመጀመሪያው አልበሙን ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ድምፃዊ ጉቱ አበራ በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች በርካታ አድናቂዎችን አፍርቷል።

ከ15 ቀን በፊት ኢዮሌ የተሰኘ ቪዲዮ ክሊፕ የተሰራለት ነጠላ ዜማ ለቆ ተወዶለታል።

አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ፋስት መረጃ ከድምፃዊው ያገኘው መረጃ ያሳያል።

አልበሙ የራሱን የዩቲዩብ ቻናልን ጨምሮ በሌሎችም ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በላይ ይለቀቃል ተብሏል።

📍መረጃው የፋስት መረጃ ነው።

ቴሌግራም: @EventAddis1
የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ የሥዕል አውደርዕይ ተከፈተ

የእውቁ ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ "የይቅርታ ጉዞ" የተሰኘ የሥዕል አውደርዕይ ሰኔ 6 2016 ዓ.ም ቦሌ አትላስ መብራት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሜትሮፖሊታን የሥዕል ማሳያ ውስጥ የሥዕል ወዳጆች በተገኙበት ለእይታ እንደበቃ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ይህ የሥዕል አውደርዕይ እስከ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም ለሳምንታት በእይታ ላይ ይቆያል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
"ሜላድ"አውደርዕይ ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል

ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማዕከል"ሜላድ የብራና ማዕድ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 እና ነገ እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም አዘጋጅቷል።

ይህ አውደርዕይ ከዛሬ ቅዳሜ ከጠዋት 3፡00 ላይ ተከፍቶ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ በቦሌ ደብረ ሳሌም ካቴድራል ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
"የአባቶች የአእምሮ ጤና:የቤተሰብ ብርታት" የተሰኘ ተከታታይ የሥነልቦና ውይይት ከእሁድ ጀምሮ ይካሄዳል

የአእምሮ ጤና ተሟጋች የሆነው እና የቤተሰብ የአእምሮ ደህንነት ላይ በመስራት የሚገኘው ሜንታል ሄልዝ አዲስ “የአባቶች የአእምሮ ጤና፡ የቤተሰብ ብርታት” በሚል መሪ ቃል ተከታታይ  መርሐግብር ለማሰናዳት እየተዘጋጀ እንደሆነ አስታውቋል።

ይህም አባቶች ጤናማ እና ብርቱ ቤተሰብ በማጎልበት ረገድ ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና አፅንዖት ለመስጠትም ያለመ ነው ተብሏል።

ዝግጅቱን በዓለም አቀፍ የአባቶች ቀን እሁድ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በርካታ አባቶች በተገኙበት አባትነትን በመዘከር የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚደረግ ኤቨንት አዲስ ደስታ ድረገፅ ሰምቷል።

የዚህ መርሐግብር መግቢያ ሁለት መቶ ብር ነው።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት በዚህ ወር ይካሄዳል

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት የፊታችን ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሃጫሉ ሽልማት በ11 የሽልማት ዘርፎች፤ በአፋን ኦሮሞ የተሰሩ የዓመቱ ምርጥ አልበም፣ የአመቱ ምርጥ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ አቀናባሪ፣ ምርጥ የባህል ዘፈን፣ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ፣ የዓመቱ ምርጥ ወንድ እና ሴት አርትስቶች፣ የኣመቱ ምርጥ አዲስ ሙዚቀኛ (ሴት እና ወንድ)፣ ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ ሲኒማቶግራፊ እና ምርጥ ባህላዊ ውዝዋዜ በሚሉ ዘርፎች እንደሚሸለሙ ታውቋል፡፡

በሽልማት ውድድሩ ውስጥ ሚካተቱ የሙዚቃ ስራዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የወጡ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
እማዬ እንዳለች ኑ ቡና ጠጡ ብላለች!

በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ነገ ሰኔ 9 2016 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ህዝብ ቡና በነፃ እየተጋበዘ ነው።

ይህ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ነፃ ቡና ዝግጅት ሙዚቃ ፣ፋሽን ሾዎችን መዝናኛዎችን እና የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶችን ማሰናዳታቸውን እና ህብረተሰቡ በነጻ ቡና እየጠጣ እንዲዝናና አዘጋጆቹ ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አሴቲክስ ሶሉሽን እና ከሊያን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#Ads

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
የወንዲ ማክ አልበም ሰኔ 14 ይለቀቃል

የድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) "ይንጋልሽ" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን ሰኔ 14 2016 ዓ.ም ለአድማጮች እንደሚደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ድምጻዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁም "እነሆ አርብ ሠኔ 14 ቁርጥ ቀን ሆነ "ይንጋልሽ " ብለን ከንጋት የተቃጠርንበት አልበማችንን ወደ እናንተ የምናደርስበት ሠላም ያቆየን" ብሏል።

ይህም አልበም ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ ተመረጠ፡፡

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዜናዎቹ የምናዉቀውና በያዝነው አመት መጀመሪያ አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥንን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን የ"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ "የኢትዮጵያ ተወካይ ሆኖ እንደተመረጠ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

ጋዜጠኛ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መረጃ "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" መቀመጫውን በህንድ ሙምባይ ከተማ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

የጋዜጠኞችን ሙያዊ ክህሎት እና ቤተሰቦቻቸውን  ህይወት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ድርጅቱ በመላው ዓለም ያሉ ጋዜጠኞችን "ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በሚል ስያሜ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ለማስተባበር እየሰራ ያለ ተቋም ነው። ዋና ዋና አምስት መርሆችን አሉኝ የሚለው ድርጅቱ ጋዜጠኝነትን ማስፋፋት እና የጋዜጠኞችን አኗኗር ማሻሻል ላይ አልሞ የሚሰራ ነው፡፡ 

ኢቨንት አዲስ ከጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰን ባገኘው መረጃ  "ድርጅቱ በዋናነት የጋዜጠኞችን የመኖሪያ ቤት፣ የጤና፣ የጋዜጠኛ ልጆችን በትምህርት መደገፍን ጨምሮ የጋዜጠኞችን ክህሎት እና የድህረ ጡረታ ፈተናዎች ላይ ትኩረቱ አድርጎ ይሰራል፡፡"

"ቮይስ ኦፍ ሚዲያ" በኢትዮጵያ ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ጋዜጠኛ ፀጋዬ ወንድወሰንን በበጎ ፍቃደኛ ተወካይነት ሲመርጥ ፤ በዋናነት ለዚሁ ስራ በጎ ፈቃደኛ እና ተነሳሽነት ያላቸውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችንም የሚያካትት መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
#ዮቶር_ድግስ

የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ የ25 ዓመት የሙዚቃ ጉዞ የሚዘከርበት ኮንሰርት ቅዳሜ ይካሄዳል

የተወዳጁ የሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲውን አለማየሁ ደመቀን የሩብ ክ/ዘመናት የሙዚቃ ጉዞ የሚያወሳ እና እርሱንም የሚዘክር "ዮቶር ድግስ" የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ዓ.ም በማሪዮት ሌግዥሪ ሆቴል ይካሄዳል ተብሏል።

በሙዚቃ ባለሙያው የ25 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የእርሱን ተወዳጅ እና ዘመን ተሻጋሪ የግጥምና ዜማ ስራዎች ወስደው ከተጫወቱ ድምፃውያን መካከል ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ግርማ ተፈራ ካሣ ፣ ሐሊማ አብዱራህማን፣ ሔለን በርሔ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ፣አንተነት ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ ዳግማዊ ታምራት ፣መስከረም ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ እንደሚሳተፉ የሙዚቃ ስራቸውንም እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

ከድምጻዊያኑ በተጨማሪም ኢትዮ ለዛ ባንድ፣ ሻኩራ ባንድ፣ ብርኩማ ባንድ የተሰኙ ባንዶች ድምጻዊያንን ያጅባሉ ተብሏል።

በዕለቱም በ "ዮቶር ድግስ" ከኮንሰርቱ በተጨማሪም በቅርቡ ለአንባቢያን የደረሰው  "ዮቶር ቁጥር 2" መጽሐፍ ይመረቃል ስለመባሉ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

የኮንሰርቱ መግቢያ 3000 ብር ሲሆን ትኬቱን በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ፣በማርዮት ሆቴል ፣ በአቻሬ ጫማ እንደሚገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

አለማየሁ ደመቀ ከ1991 ዓ.ም አንስቶ ከ250 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎችን ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን “ዮቶር 1 : ኮብላዩ ካሕን” እና በቅርቡ ለንባብ የበቃውን “ዮቶር 2 ” ለሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ያበረከተ ሲሆን ላለፉት 25 ዓመታት በሙያው፣ በክህሎቱ እና በተሰጥዖው አገር እና ወገንን ሲያገለግል እንደቆየ ይታወሳል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ዕውቅና ተሰጠው

ቴክሳስ ዳላስ የሚገኘው አድዋ የታሪክና የባህል  ህብረት  በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት በግለ ታሪክ ዘርፍ ጋዜጠኛ  ዕዝራ እጅጉን ልዩ ተመስጋኝ አድርጎታል።

ጋዜጠኛ ዕዝራ፣ ጸሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድን የመሠሉ የሀገር ባለውለታዎችን የህይወት ታሪክ በሲዲና በዲቪዲ ያሳተመ ሲሆን ይሄንኑ ታሪክ በእንግሊዝኛ  አዘጋጅቶታል።

በተጨማሪም ከ20ዐ9 አንስቶ ባለፉት 7 ዓመታት የ45 ሠዎችን ታሪክ በሲዲ ሠርቶ  ለማስመቅ ችሏል።

በተጨማሪም በአገራችን  ታዋቂ የሆኑ እንደ ማማ በሰማይ ፤ ማህሌት፣ የአክሊሉ ማስታወሻ፤ የመሳሰሉት 30 የሚጠጉ መጽሀፎችን ወደ ድምጽ በመቀየር ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች እዝራ እና ድርጅቱ "ተወዳጅ ሚዲያ" መላ ዘይደዋል።

በተጨማሪም የታዋቂ ኢትዮጵያን ታሪክ በባለታሪኮች እና በልጆቻቸው አሰሪነት ተጠይቆ 14 መጽሀፎችን አዘጋጅቷል፡፡

እዝራ ታሪክን የሚሰንድበት "ተወዳጅ ሚዲያ" የተሰኘ የራሱ ድረገጽ፤ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ያለው ሲሆን ወደ ፊት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ በአንድ ገጽ ብቻ ታሪካቸውን ጽፈው እንዲልኩ እየጣረ እንደሚገኝ ለኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተናግሯል።

በዘንድሮው 8ኛው የአርአያ ሰው ሽልማት 16 የሚሆኑ ተሸላሚዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የቱሪዝም አባት አቶ ኃብተስላሴ ታፈሰ ፣አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ ፣ጸሀፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ዶክተር  እንዳለጌታ ከበደ እና ሌሎችም  ይገኙበታል ተብሏል።

የአርአያ ሠው ሽልማት ሰኔ 13 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ የሽልማት ሥነሥርዓት ይከናወናል።

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የተዘጋጀው የሥነጽሑፍ ሥልጠና በሚመጣው የክረምት ወቅት ይካሄዳል

በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በየዓመቱ የሚዘጋጀው የክረምት የሥነጽሑፍ ስልጠና ዘንድም ለዘጠኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል።

ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስምንት ዙሮች በርካታ የሥነጽሑፍ ወዳጆች ስልጠናውን እንደወሰዱ ተነግሯል።

በልቦለድ ክሂል ፣በልቦለድና ኢ ልቦለድ፣ በግጥም ፣ በፎክሎር ፣ በሥነጽሑፋዊ ታሪክ ፣በሥነሂስ በሌሎችም የሥነጽሑፍ ዓይነቶች ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ ምዝገባ እንደተጀመረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ለበለጠ መረጃ በተከታዩ ስልክ ቁጥር ደውሉ  0911448297 ተብላችኋል።

📍ሼር ያደርጉ:

ለተጨማሪው :https://t.me/EventAddis1
የጆርጋ መስፍን ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ የተሰኘው አልበም ባንድ ካምፕ ዴይሊ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ከሙዚቃዊ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘ደጋጎቹ‘ በሚል ርዕስ ለአድማጮች ያደረሰውና በድጋሜ ተሰርቶ "ከሁሉ የላቀው ደግ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የኢትዮ ጃዝ አልበም ባሳለፍነው ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል እንደተለቀቀ ይታወሳል።

በሙዚቃ ሞያ ውስጥ ፕሮፌሽናል ሙዚቀኛ በመሆን ከ17 ዓመታት በላይ ያሳለፈው ሙዚቀኛ  ጆርጋ መስፍን ቀደም ሲል ‘የላቁት ደጋጎች’ አሁን ደግሞ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ በሚል ርዕስ በቅርቡ ያወጣው አልበም ነው፡፡

የጆርጋ መስፍን"ከሁሉ የላቀው ደግ" አልበም  ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው "አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል" በአፍሪካ ጃዝ ቪሌጅ ተመርቋል።

በ1999 ዓ.ም ጆርጋ ከጓደኞቹ ጋር በመሰባሰብ የቀረጸው ይህ አልበም የጆርጋ መንፈስን ያንጸባርቃል ተብሏል።

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 የተመሰረተውና ዋና መስሪያ ቤቱን አሜሪካ ካሊፎርንያ ያደረገው ባንድ ካምፕ በግንቦት ወር ‘በባንድ ካምፕ ላይ የሚገኙ ምርጥ ጃዞች’ በሚል ካካተታቸው አልበሞች አንዱ እንደሆነ አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
አርቲስት መስከረም አበራ የክብር እንግዳ የሆነችበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር  ረቡዕ ሰኔ 12  2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱ አርቲስት መስከረም አበራ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ ትገኛለች።

እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።

ማስታወሻ :ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ሰኔ 10 2016 ዓ.ም ለአንባቢያን እንደቀረበ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና አሁን ላይ በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው የጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ "እነሆ ማሟሻ" የተሰኘ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ መጽሐፉ ነው ተብሏል።

መጽሐፉ በ200 ገፆች የተነበበ ሲሆን በ250 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

መጽሐፉን በጃፋር ፣በእነሆ እና በእውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች ላይ ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ "መጠሪያዬ" አልበም

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ"መጠሪያዬ" የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሟን በዚህ ዓመት ነሐሴ 17 2016 ዓ.ም ለአድማጭች እንደምታደርስ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ የ29ኛ ዓመት ልደቷን እያከበረች የምትገኘው ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"መጠሪያዬ" የተሰኘዉ ሶስት ዓመት የለፋሁበት ብዙ ያየሁበት የመጀመርያ አልበሜ ነሐሴ 17 ይለቀቃል " ብላለች።

በተጨማሪም "ከዚህ በኃላ የምለቃቸዉ ፎቶዎች ላይ ስለ አልበሙ አንድ አንድ ነገሮች እላችዋለው አዳዲስ ነገሮችም አሉ "ስትል ሀሳቧን አስፍራለች።

ይህ የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ" መጠሪያዬ" የተሰኘ አዲስ አልበም ሶስት ዓመት ገደማ እንደፈጀም ተነግሯል።

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ከዚህ ቀደም ኩርፊያ  ፣ ጥፍጥ አለኝ ፣ ተው ፣አበባዬ ፣እናነዬን ጨምሮ ሌሎችንም ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጮች አድርሳለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊ ፍፁም ቲ አልበም አርብ ይለቀቃል

የድምጻዊ ፍፁም ቲ "አያዳላም" የተሰኘ አዲስ አልበም የፊታችን አርብ ሰኔ 14 2016 ዓ.ም በፍፁም ቲ የዩቲዩብ ቻናል እና በሌሎችም የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደሚለቀቅ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ሰምቷል።

አልበሙን ወንድወሰን ይሁብ በሪኮርዲንግ ፕሮዲዩሰርነት ያዘጋጀው ሲሆን በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

"አያዳላም" አልበም ይጣራል ፣ድክም አለኝ፣ እኔ አልዋስም፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አስር የሙዚቃዎች ስራዎችን ይዟል ተብሏል። ከእነዚህም የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ ለአንዱ የሙዚቃ ቪዲዮ ተዘጋጅቶለታል።

ድምጻዊ ፍፁም ቲ ይህን አልበም ለመስራት ከአሜሪካ አትላንታ ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ እንደቆየ አስታውቋል።

ድምጻዊው ፍፁም ቲ "አዲስ አባ" በተሰኘው ሙዚቃ ስራው በርካቶች ያስታውሱታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1