EvaSUE |ኢቫሱ
9.56K subscribers
3.74K photos
16 videos
5 files
518 links
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር [ኢቫሱ] -ከ1950ዎቹ ጀምሮ

#ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:-

<<ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት>>

ኢቫሱ፣ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ #176 የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን በማቀፍ ያገለግላል።

#በዚህ_ቻናል:-
☞ለካምፓስ ሕብረቶች የሚጠቅሙ መልእክቶች ይተላለፉበታል!
Download Telegram

የ2012 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች #ለ2_ወራት ተምረው እንዲመረቁ አቅጣጫ ተቀመጠ!

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት አቋርጠው በቤታቸው የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎችን #ያቋረጡትን ትምህርት #ከ45 ቀን እስከ #2_ወር በሆነ ጊዜ ውስጥ ተምረው በማጠናቀቅ እንዲመረቁ አቅጣጫ መቀመጡን 'አዲስ ማለዳ ጋዜጣ' በዛሬው ዕትሙ መረጃውን ይዞ ወጥቷል።

የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደገለፀው ከተመራቂ ተማሪዎች በተጨማሪ ሌሎች በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች በተቀመጠው ጊዜ #ያለፋቸውን #ትምህርት #አጠናቀው ወደ #2013 የትምህርት ዘመን እንዲሸጋገሩ ውሳኔ ላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠው አቅጣጫ ተማሪዎች #መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚመለሱ #ቀን #እንዳልተቆረጠለት ተመላክቷል። ይህ የሆነበት ምክንያት ተማሪዎቹ መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለስ እንዳለባቸው ኮቪድ-19 ያለበትን ደረጃ ያገናዘበ የመንግስትን ውሳኔ የሚፈልግ ጉዳይ በመሆኑ ነው ተብሏል።
---------------------------
@tikvahethiopia