ሚገኝበት ቦታ
የሰው ልጅ በህይወት ጎዳና ሲጓዝ መንገዱን የሚጀምረው በመወለድ ፤ የሚጨርሰው ደግሞ በሞት ነው። በሕይወቱ ውስጥ የተለያዩ ምዕራፎችን ቢያልፍም ድምድማቱ ሞት ፍፃሜው ከአፈር በታች መሆን ነው። ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው የሆነው የጌታ ኢየሱስ ህይወት ግን እንደዚህ አልነበረም። ጅማሬ የሌለው የዘላለም አምላክ የሆነው እርሱ ስጋን ለብሶ ወደ ምድር ወረደ። የአባቱን ፈቃድ እየፈፀመ ኖረ። ለሰው ልጆች ሀጢያት ሲል በመስቀል ላይ በመሞት ዋጋን ከፈለ። የአለም ቤዛ ፤ ለሰው ልጆች መድሀኒት ሆነ። ሞት ሊገታው መቃብር ውጦ ሊያቀረው አልቻለም ፤ በመቃብሩ የተከረቸመው ዲንጋይ እና በዙሪያው ያሉ መቃብሩን የሚጠብቁ ወታደሮች ሊያስቆሙት አልቻሉም። ተነስቷል ሞትን ድል ነስቷል። በማለዳ ወደመቃብሩ ሽቱ ይዘው ለሄዱ ሰዎች " ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" እንዳሏቸው ሁሉ እኛስ ይህንን የትንሳኤውን ጌታ የት ነው እየፈለግነው ያለነው? በፆም በፀሎት በህብረት ውስጥ በቅዱስ ቃሉ ውስጥ ነው? ወይስ በአለማዊነት በመዋከብ ሰሞነኛ በመሆን? በሀጢያታዊ ሕይወት፤ በአመፃ ምልልስ ከሆነ "እሱ(ኢየሱስ) በዚያ የለም" ። በንሰሀ በመመለስ ፤ በፅድቅ ኑሮ በመኖር እና እሱን በመታመን ከሆነ ግን እርሱ(ኢየሱስ) በዚያ አለ። እርሱ በሚገኝበት ፍለጋችንን እናደርግ ዘንድ ፀጋው ይርዳን!

❤120🎉7🥰5🤩2🤔1
መመለስ
እግዜሩ እንደልቤ ያለው ንጉስ ዳዊት ሀጢያትን ሰራ፤ ሳተ ተሳሳተ ። ሚስቱ ያልሆነች ሴት ጋር ተኛ። አዳም ሀጢያትን ከሰራ በኃላ እርቃኑን መሆኑን ሲያውቅ ቅጠል በማገልደም የራሱን ችግር ከእግዜሩ ሸሽቶ በራሱ ለመቅረፍ እንደተጣጣረ ሁሉ ንጉስ ዳዊትም ይህ ሀጢያቱን ለመሸፈን ሌላ ሀጢያትን አደረገ። አብሯት የተኛትን ሴት ባል አስገደለ። እግዚአብሔርም ነብዩን ናታንን ልኮ ዳዊትን ገሰፀው በዚህ ጊዜ ዳዊት አላስተባበለም ፤ ለመካድ አልሞከረም፤ "ንጉስ ነኝኮ እንዴት እንደዚህ ትናገረኛለህ" አላለም ፤ ጥቅስ ጠቅሶ ስህተቱን ለማፅደቅ አልፈለገም ይልቁንስ ልቡን ለእግዜሩ አጋለጠ ፤ ያደረገውን እያንዳንዷን ሀጢያት በአንደበቱ እየተናዘዘ ምህረትን ለመነ ፤ ራሱን ለእግዚአብሔር ምህረት አሳልፎ ሰጠ። እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ተወዳጅተን ለመቀጠል ካስፈለገን በመንገዳችን ላይ ላጋጠመን ሀጢያት እና ጥፋት በንሰሀ የመመለስ አለብን እንጂ "ካፈርኩ አይመልሰኝ" በማለት በጥፋት መንገድ መጓዝ ትልቅ ክስረት ነው።መንገዳችንን ማስተካከል ፤ ከጠፋንበት መመለስ ፤ ልባችንን ለቃሉ ተግሳፅ ማጋለጥ ፤ በትህትና እና በተዋረደ መንፈስ እውነትን እየተናዘዙ በጌታ ፊት ግልፅ ሆኖ መቅረብ ሁነኛ መድሀኒት ነው። እኛም ለሀጢያታችን እና ለጥፋቶቻችን አቃቂር ከማውጣት ይልቅ እንፈወስ ዘንድ ፊታችንን ወደ እግዜሩ መመለስ ይሁንልን
✍️ ካሌብ ካሳሁን

❤109🔥16👍8