EvaSUE |ኢቫሱ
9.55K subscribers
3.74K photos
16 videos
5 files
518 links
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር [ኢቫሱ] -ከ1950ዎቹ ጀምሮ

#ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:-

<<ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት>>

ኢቫሱ፣ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ #176 የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን በማቀፍ ያገለግላል።

#በዚህ_ቻናል:-
☞ለካምፓስ ሕብረቶች የሚጠቅሙ መልእክቶች ይተላለፉበታል!
Download Telegram
ቅዱሳን ፣ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ዛሬ #የወንጌል_ተልዕኮ ቀን ነው!

ባለፈው ሳምንት መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ስለእግዚአብሔር #ተልዕኮ እንደሚናገር መጽሐፍ የምናይበትን #አስተዋጾ [Outline] እና በፍጥረት እና ውድቀት የታየውን የእግዚአብሔር ተልዕኮ ተመልክተናልን።

#ዛሬ፣ ከዛው በመቀጠል የእግዚአብሔር ተልዕኮን በእስራኤል መመልከት እንጀምራለን።
#ዛሬ በዋናነት የምናየው:--

#የአብርሃምን መጠራት እና በመጠራቱ ውስጥ የተገለትጸውን አስደናቂ የእግዚአብሔር #ህዝቦችን የመባረክ ዕቅዱን ነው!

በዋናነት የምናየው የመጸሐፍ ቅዱስ ክፍል ዘፍጥረት 12፡1-4 ሲሆን፤

ጆን ስቶት የተባሉት የቃሉ አስተማሪ ስለዚህ ክፍል ሲናገሩ ይህን ብለዋል
“ዘፍጥረት 12፡1-4 የመጽሐፍ ቅዱስ ማእከላዊ ወይም አጣማሪ ክፍል ነው፤ የእግዚአብሔር ዓላማ እዚህ ክፍል ውስጥ በአጭሩ ተጠናቅሮ ተቀምጧል”።

ጳውሎስም በዚህ ክፍል የተገለፀውን የእግዚአብሔር ዓላማ ‘የቀደመው ወንጌል’ ሲል ይገልጸዋል።

ስለዚህም በሚከተሉት ጥያቄዎች እና ምንባብ ላይ እንድታሰላስሉ [Reflect] እና ሀሳባችሁን እንድታካፍሉ እጠይቃለሁ!

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል-

👉🏿 ዘፍጥረት 12፡1-4

በተጨማሪም
ዘፍ 18፡18፣ ዘፍ 22፡17-18፣ ዘፍ 26፡2-4፣ ዘፍ 28፡13-14፣ ማቴ 8፡11 እና ገላ 3፡8

1. ዘፍጥረት 12፡1-4 እና የቀደመውን ምዕራፍ የሚያይዛቸው ሀሳብ አለ? ካለ ምንድነው?

2. በዘፍጥረት 12፡1-4 ተገልጦ የምናየው ተስፋ ምንድነው?

3. በዚህ ክፍል መሰረት መባርክ ማለት ምን ማለት ነው?

4. መጽሐፍ ቅዱስን እንደ አንድ መጽሐፍ ለመረዳት ይህ ክፍል የሚያበረክተው አስተዋጾ ምንድነው?
------
ጌታ ይባርካችሁ፤ለበረከትም ያድርጋችሁ!
#Missio_Dei