ELiDA Ethiopia
209 subscribers
323 photos
6 videos
19 files
68 links
Inspiring women, Girls and Youth to contribute and lead in building sustainable peace and strong democratic culture. ELiDA works for the protection and well-being as well as the economic, social, and political empowerment of women, Youth, Girls..........
Download Telegram
Forwarded from solomon Yohannes
📍 #ሴቶችና #ምርጫ #በኢትየጵያ
=================
🇪በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች ተሳትፎ ርዕስ ሆኖ ሲነሳ እንደ ‹ወርቃማ ዘመን› የሚጠቀሰው ወደኋላ መቶ ዓመታትን ተመልሶ የምናገኘው #እቴጌጣይቱ አልያም የንግሥተ ነገሥት #ዘውዲቱ ታሪክ ነው። የእነዛን ብርቱ #ሴቶች አረአያነት የተከተለ #የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ግን ከዛ በኋላ እምብዛም ሲነሳ አንሰማም።
📖እንዲውም የመንግስት አስተዳደር ምስረታ ወጥነት ማጣቱና፣ ተከትሎም ፖለቲካን አስፈሪ አውድ አድርጎ መግለጽ ያመጣው ችግር፣ እንደማንኛውም የማህበረሰብ አካል #ሴቶችንም ለፖለቲካ ቁጥብና እንግዳ እንዲሆኑ ያደረገ ይመስላል።
መለስ ብለን በኢትዮጵያ ምርጫ የተካሄደባቸውን ጊዜያትና #የኢትዮጵያ #ሴቶችን እናንሳ። እንደሚታወቀው #ኢትዮጵያ ሦስት ሺሕ እንደሆነ በሚታመነው ታሪኳ በርካታ የአስተዳደር ሥርዓቶችን እና እጅግ በርካታ መሪዎችን አስተናግዳለች።
መለኮታዊ ፈቃድ ተሰጥቶናል ብለው ከሚያምኑ ነገሥታት እስከ ወታደራዊ፣ በውጊያ ሥልጣንን ከሚናጠቁት አንስቶ ታግለው ሥልጣን እስከያዙት ድረስ፣ #በአገርአስተዳደርናመንግሥት ምሥረታ ዙሪያ የተጻፈው #የኢትዮጵያ ታሪክ በርካታ ነው።
#ምርጫ ግን ሩቅ የሚባል ዘመንን ያስቆጠረ አይደለም፣ 5️⃣0️⃣ ዓመት እንኳ በቅጡ አልሞላውም። #ዴሞክራሲ የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ሳይቀጠልበት በፊትም በቀዳማዊ #አጼኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ምርጫ #በኢትዮጵያ ተካሂዷል። ይህም የመጀመሪያው ሕገመንግሥት በ 1️⃣9️⃣2️⃣3️⃣ በንጉሠ ነገሥቱ እንዲወጣ መደረጉን ተከትሎ ነው።
📖በሕገመንግሥቱ መሠረት ሕዝቡንና መንግሥትን የሚያገናኝ እንዲሁም የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ከሕዝብ ተወካዮች ጋር የሚመክርበት ኹለት ክፍል ያለው የአማካሪዎች ምክር ቤት እንዲኖር ተባለ። በዚህም የተነሳ የአማካሪዎች ምክር ቤት እንዲሁም ፓርላማ ተቋቋመና ምርጫ አጀንዳ ሆነ። አልዘገዩም፣ የሕዝብ እንደራሴዎች በሕዝብ እንዲመረጡ፣ ምርጫው ግን በቀጥታ በሕዝብ ሳይሆን በተወካይ እንዲሆን ተባለ።
📌📌1️⃣9️⃣4️⃣9️⃣የመጀመሪያው የሕዝብ እንደራሴዎች #ምርጫ #በኢትዮጵያ ተካሄደ። ይህም #ምርጫ እስከ 1️⃣9️⃣6️⃣5️⃣ ድረስ #5️⃣ ጊዜ ያህል የተካሄደ ነው። #የምርጫ ማስፈጸሚያ አዋጅም ተዘጋጀ። በጊዜው የመምረጥ መብት ያላቸው እድሜያቸው ከ2️⃣ 1️⃣በላይ የሆኑ ሁሉ ናቸው። ሴቶችም ተሳትፈዋል። በአንጻሩ እድሜያቸው ከ2️⃣ 1️⃣ በታች የሆኑትን ጨምሮ
👉እስረኞች፣
👉በሕግ የሲቪል መብቶችን ያጡ ግለሰቦች፣
👉የአእምሮ ጤንነት መታወክ ያለባቸው በመራጭነት አይሳተፉም።
📌በተጓዳኝ #ተመራጭ ለመሆን ከ #2️⃣5️⃣ ዓመት በላይ መሆን፣ ግምቱ #2️⃣ ሺሕ ብር የሚጠጋ የማይንቀሳቀስ እንዲሁም #አንድ ሺሕ ብር የሚገመት የሚንቀሳቀስ ንብረት ያላቸው፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባህል ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፣ #በምርጫ ወቅት 2️⃣5️⃣0️⃣ እንዲሁም ቀጥሎ 5️⃣0️⃣0️⃣ ብር ማስያዝ የሚችሉ ናቸው።
የማስፈጸሚያ አዋጁ በጾታ ላይ የተመሰረተ ምንም አይነት ልዩነት አላስቀመጠም፡፡

📌ይህም 🇪🇹#ኢትዮጵያን የሴቶች የመምረጥና የመመረጥ መብትን #ምርጫ ማድረግ ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ በህግ ያረጋገጠች ሀገር ያደርጋታል፡፡ ብንጽጽር ለምሳሌ የፕሬዝዳነታዊ ምርጫን በ1️⃣7️⃣7️⃣8️⃣ አ.ም የጀመረችው 🇺🇸አሜሪካ #የሴቶችን የመምረጥ መብት በህግ ያጸደቀችው በ1️⃣9️⃣2️⃣0️⃣፣ ከ1️⃣4️⃣2️⃣ አመታ በኋላ ነበር፡፡ ይህም የአሜሪካ ሴቶች መብታቸውን ለማረጋገጥ ከመቶ አመት በላይ የፈጀ ትግል እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል፡፡ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ #የሴቶችን የመምረጥና የመመረጥ መብት ለመጀመሪያ ጊዜ በተግባር ያስከበረችው #ኒውዚላንድ ናት፤ በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1️⃣9️⃣8️⃣3️⃣ ነው። የመጨረሻዋ ደግሞ #ሳውዲአረብያ፣ ከ5️⃣ ዓመት በፊት በ2️⃣0️⃣1️⃣5️⃣/1️⃣6️⃣

📌1️⃣9️⃣4️⃣9️⃣ #በኢትዮጵያ በተካሄደው የመጀመሪያው #ምርጫ3️⃣ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመምረጥ ተመዝግበው ከ #2️⃣.5️⃣ሚሊዮን በላይ የሆኑት መርጠዋል። በዚህ ምርጫ ታድያ #የሴቶች ተሳትፎም ጀምሮ ነበር። ሥማቸው በተደጋጋሚ ሲጠራ የምንሰማቸው
#ስንዱገብሩ የመጀመሪያዋ የምክር ቤት አባል በመሆን የተመረጡት በዚሁ ምርጫ ነው።

📖 መዛግብት እንደሚያስረዱን #በስንዱገብሩ መመረጥ ምክንያት ለዚህ ሥራ የተነሳሱና በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት ያደረባቸው #ሴቶች ጥቂት አልነበሩም።

እንደውም በ1️⃣9️⃣5️⃣7️⃣ ምርጫ በተመራጭነት የተሳተፉ #አምሳለወርቅአስፋው የተባሉ ሴት ተከታዩን ተናግረዋል፤
‼️‹‹#በአለፈዉ_ጊዜ_ሴቶች_የምክር_ቤቱ_አባል_በመሆን_ከምርጫ_ውድድር_ገብተዉ_በወገናቸው_ድጋፍ_ተመርጠዉ_ከሥራዉ_ላይ_ከወንዶች_ጋር_ሰልፈዉ_ታይተዋ_እኔም_በበኩሌ_ችሎታዬ_ይፈቅድልኛል_በማለት_በምርጫዉድድር_ገብቻለሁ።››‼️ ብለዋል።

✍️#ከስንዱ_ገብሩ በኋላ በ1️⃣9️⃣6️⃣1️⃣ #የሺእመቤት_ወንድማገኘሁ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን የምርጫ ወረዳ፣ በ1️⃣9️⃣6️⃣5️⃣ #አልማዝ_አጥናፍሰገድ በዛው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ማማ ምድር በሚባል ምርጫ ወረዳ እንዲሁም #መንበረወርቅ_አድማሱ በወሎ ጠቅላይ ግዛት ላስታ የምርጫ ወረዳ ላይ መመረጣቸው ከሚታወስ #ሴቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

✍️በድምሩ በ1️⃣9️⃣6️⃣5️⃣ ምርጫ 5️⃣ #ሴቶች አልፈው ነበር። ከዛም ባለፈ ደግሞ #ሴቶቹ እንደሚጠበቀው #የአዲስ_አበባ ነዋሪ የሆኑ ብቻ ወይም የተማሩ ብቻ አይደሉም። በወቅቱ በሁሉም ጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙ ነበሩ።

✍️ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በዘመኑ በተካዱ ምርጫዎች በጾታ ምክንያት ሴቶች ከመመረጥም ሆነ ከመምረጥ አልተገደቡም ነበር። እንደሚያውም በተመራጭነት ከወንዶች የተሻለ ድምጽ እንደሚያገኙ ተጠቅሷል።

✍️ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በዘመኑ በተካዱ ምርጫዎች በጾታ ምክንያት #ሴቶች ከመመረጥም ሆነ ከመምረጥ አልተገደቡም ነበር። እንደሚያውም በተመራጭነት ከወንዶች የተሻለ ድምጽ እንደሚያገኙ ተጠቅሷል።

✍️ይህ በንጉሡ ዘመን ይደረግ የነበረው ምርጫ #በደርግ ዘመነ መንግሥት አልቀጠለም። ይልቁንም ከ1️⃣9️⃣8️⃣9️⃣ አንድ ብሎ ጀምሮ እነሆ #የ2️⃣0️⃣1️⃣3️⃣_ዘመን 6️⃣ኛው አገራዊ #ምርጫ ላይ ደርሰናል።
✍️ #ባለፉት_ስድሰትምርጫዎች_የሴቶች_ተሳትፎ_በርካታ_ለውጦች_አሳይቷል_የሴቶች_በመራጭነትም_ሆነ_በተመራጭነት_በቁጥርም_በአቅምም_እየጨመሩ_መምታጣቸው_የሚታይ_እውነታ_ነው፡፡

📌📌 #Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA

ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/joinchat/dFJkU4AbZgJkYWM0
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
Forwarded from solomon Yohannes
#Opening_Speech
Zinet Yimer
Executive Director !
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
🎤ኢምፓቲ ፎር ላይፍ ኢነተግሬትድ ዴቨሎፕመነት አሶሴሽን (ኤሊዳ) የተቀናጀ የልማት ስራን በመስራት ሴቶችን፣ ልጃገረዶችን፣ ወጣቶችን እና ህፃናትን በትምህርት፣ በጤና እና በኢኮኖሚ በመደገፍ እንድሁም በድሞክራሲ ባህል ግንባታ እና ዘላቂ ሰላም ላይ የሚሰራ እና ማህበራዊ ሀላፊነታቸዉን የሚወጡ፣ ምርታማ እና አርቆ አሳቢ ዜጎችን ለማፍራት በማለም እ.ኤ.አ 2008 በሴቶች )የተቋቋመ አገር በቀል የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ነዉ፡፡
🎤ኤሊዳ ላለፉት 14 አመታት ከተለያዩ ደጋፊ አካላት ጋር በመሆን በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ ወረዳዎቸ፣ በደሴ ከተማ አስተዳደር፣ በአፋር ክልል እና በአድስ አበባ ከተማ መስተዳደር የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ሲተገብር ቆይቷል፡፡
🎤በዋናነትም የገጠር ስንቀኛ ሴት ተማሪዎችን ከስደት ይልቅ በአገራቸዉ ተምረዉ መለወጥ እንድችሉ ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢ መፍጠር፣ ለልጃገረዶች የማጠናከሪያ ትምህርት/የቱቶር እንድሰጠቸዉ በማድረግ እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመስጠት ለሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና/ማትሪክ ማዘጋጀት፣ ልጃገረዶች ከፆታዉይ ጥቃት እራሳቸዉን እንድጠብቁ ግንዛቤ መፍጠር፣ የስደትን አስከፊነት ለሴት ተማሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ለማህበረሰቡ በማስገንዘብ የሴት ተማሪዎች ቤተሰቦች እና ከስደት የተመለሱ ሴት እሀቶች እና ወንድሞችን የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት እና በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ በማሰማራት ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
🎤አሁንም የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን እየተገበረ ይገኛል፡፡
ከዚህም ዉስጥ ኤሊዳ International Republican institute (IRI) ከተባለ አጋር ድርጂት በተገኘ ድጋፍ -‘Enhancing Women Political Participation and decision making power through Media engagement‘- የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ እና ዉሳኔ ሰጭነት ሚና ከሚድያ ጋር አጋር በመሆን ማሳደግ የሚል የአጭር ጊዜ ፕሮጄክት በአድስ አበባ እና ደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር እና የተለያዩ ሚድያ ተkማት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነዉ፡፡
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/joinchat/dFJkU4AbZgJkYWM0
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
Forwarded from solomon Yohannes
7Q0A9875.JPG
5.3 MB
Social Media for Political Campaigning
Tesefa Yemer

#የማህበራዊ_ድህረ_ገጾችን ለምርጫ ቅስቀሳ መጠቀም ለማህበረሰቡ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ እና የባህሪ ለውጥ ለመፍጠር ይጠቅማል
በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ማተኮር ካለብን ቁልፍ ጉዳዮች መካከል
🔑ማን ጋር ነው ልደርስ የምንፈልገው ?
🔑በግለሰብ ደረጃ የማህበራዊ ድህረ ገጾችን ተጠቃሚዎች ዓላማቸው ምንድን ነው ?
🔑ተገቢ የሆነ የመገናኛ ዘዴዎች ተደራሽ የሆኑትን ለይቶ መጠቀም
🔑ተገቢውን ግዜና ጥረት ላይ ያተኮረ መሆን ይገባዋል
🔑 በግልጽ ተግባቦት የሚፈጠርበትን መንገድ ማወቅም አለብን

#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA

ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/joinchat/dFJkU4AbZgJkYWM0
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
Forwarded from solomon Yohannes
#Public_Dialogue_Two

📷 Selected Photos Report from The workshop

📍 Topic: -

#Women_candidates_and_political_campaigning_in_the_2013_national_election

🎤Moderator:-Sindu Tekalgne (Legal researcher)

🎤Facilitator: - Sebel T / Berhan (legal and public relation Expert)

🎤Presenter: - Konjit Brhan (author and politician)
Tesefa Yemer (Social Media for Political Campaigning)

And Sharing Experience




#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA
Forwarded from solomon Yohannes
#Public_Dialogue_Two

📷 Selected Photos Report from The workshop

📍 Topic: -

#Women_candidates_and_political_campaigning_in_the_2013_national_election

🎤Moderator:-Sindu Tekalgne (Legal researcher)

🎤Facilitator: - Sebel T / Berhan (legal and public relation Expert)

🎤Presenter: - Konjit Brhan (author and politician)
Tesefa Yemer (Social Media for Political Campaigning)

And Sharing Experience




#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA
📍የሴት መራጮች ውሎ

✍️ ታዛቢዎች እንደመሰከሩት፣ በ2013 ምርጫ የመራጭ #ሴቶች ቁጥር ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡
በየምርጫ ጠቢያው ከታዩ ረጃጅም ሰለፎች ላይ በርካታ ነጠላ የለበሱ፣ ልጆቻቸውን ያዘሉና
ያስከተሉ እናቶችና አያቶች፣ በጋራና በተናጠል የተሰለፉ ወጣት ሴቶች ደከመንና ሰለቸን
ሳይሉ፣ ዝናብና ጸሀይ ሳይበግራቸው ድምጻቸውን ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡

✍️ ማንበብም ሆነ መጻፍ አለመቻላቸው ያልገደባቸውን ጨምሮ፣ ዱላና መቋሚያቸውን
ተደግፈው፣ ነፍሰጡር መሆናቸውን ሰበብ ሳያደርጉ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያዊያት #በሰኔ_15
ውሎዋቸውን በየምርጫ ጣቢያው አድርገዋል።


✍️ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ግራ የተጋቡ፣ የልጆቻቸውና የቤተሰባቸው እጣ ፋንታ መስቀለኛ
መንገድ ላይ መሆኑን የተገነዘቡ #ሴቶች፣ ተስፋቸውን ሰላማዊና ዲሞክሪያሲዊ ምርጫ ላይ
ጥለዋል፡፡ ‹‹#የሰላም_መጉደልና_ያልተረገጋ_የፖለቲካ_ሁኔታ_የሚያስከተለውን_ችግር
#በተግባር_እያየነው_ነው_ዲሞክራሲያዊ_ስርአትን_ማበረታታትና_ሰላማዊ_የስልጣን
#ሽግግር_ምን_ማለት_እንደሆነ_ለልጆቻችን_በተግባር_ማሳየት_ይኖርብናል_ለሰአታት
#የተሰለፍኩትና_የመረጥኩትም_ለዚሁ_ነው::›› ያለችን የሶስት ልጆችና እናትየባንክ
ሰራተኛ የሆነችው የአዲስ አባባ ነዋሪዋ #ሰላማዊት_ደረጄ ነች፡፡

✍️የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያ ሴቶች ማህበር ባወጣው ሪፖርት መሰረት፣ #ሴቶች በከፍተኛ
ቁጥር በታዩበት #በ2013 ምርጫ በአንዳንድ ቦታዎች ጥቃትና #የሴቶችን የመምረጥ
መብት የሚያስተጓጉሉ ድርጊቶች ታይተዋል፡፡ ይህ ግን፣ ሴት መራጮችን #እስከምሽቱ
#ሶስት_ሰአት ደረስ በተደረገው ምርጫ ከመሰለፍና ከመምረጥ አላገዳቸውም፡፡

✍️ ‹‹#ሰልፉ_ረጅም_ስለነበርና_ጣቢያውም_በጊዜ_ስራ_ስላልጀመረ_ወደ_ስራዬ_መመለስ
#ነበረበኝ_ሰአቱ_መራዘሙን_ስሰማ_ሱቄን_በሰአቱ_ዘግቼ_ለመምረጥ_መጣሁ_ካርዴ_ባለመባከኑ_ደስ_ብሎኛል፡፡ #ውጤቱ_ምንም_ይሁን_ምን_ስርአት_የምናከብርን #በህግና_በዲሞክራሲ_የምናምን_ሰዎች_መሆናችንን_ለአለም_ለማሳየት_ምርጫው_ጥሩ_አጋጣሚ_ይመስለኛል፡፡››
ያለችን ደግሞ የሀያ ሶስት አመቷ ወጣት የደሴ ከተማ ነዋሪዋ ሶፊያ አህመድ ነች፡፡

✍️ ‹‹ማንበብም ሆነ መጻፍ አልችልም። እድሜዬን ያሳለፍኩት ልጆቼን በማስተማርና
ቤተሰቤን በመንከባከብ ነው። ባለቤቴን በሞት ያጣሁት ልጆቻችን ገና ትንሽ ሳሉ ነበርና
እነርሱን ከቁምነገር ለማድረስ ስባትል ለመማር ጊዜ አላገኘሁም ነበር። ያኔ ያሳስበኝ
የነበረው አለመማሬ ሳይሆን የልጆቼ ነገር ነው። ዛሬ ልጆቼ ከቁምነገር ደርሰዋል፤ የልጅ
ልጅም ዐይቻለሁ። አሁን ደግሞ የሚያሳስበኝ የአገር ሰላም ነው፤ የልጅ ልጆቼ በሰላም
የሚኖሩባት አገር እንድትኖርላቸው እፈልጋለሁ። ባልማርም፣ በጣት አሻራዬም ቢሆን
በመራጭነት ተሳትፌአለሁ። ለዛሬ ባይሆን ለነገ የአገር ሰላምና እንደሚባለው ለዴሞክራሲ
የኔም ድምጽ ድርሻ እንዳለው ስለማምን ነው የመረጥኩት።››።

✍️ ይህን ያሉት የአራት ልጆች እናትና የ57 ዓመቷ ባልቴት አሰለፈች ቦንሳ የምርጫ ካርድ
ባወጡበት የምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን ለመስጠት ማልደው ነው የተሰለፉት። በነበሩበት
የምርጫ ጣቢያ የተወሰኑ መስተጓጎሎች ተፈጥረው የምርጫ ሂደቱ ጥቂት ዘግይቶ
በመጀመሩ አልሰለቹም፣ ቤታቸው ተመልሰው መድኃኒት ውጠው መመለስ ግድ ያላቸው
ቢሆንም አላስመረራቸውም።

✍️ የሚመርጡትን እጩ ግለሰብ እንዲሁም ፓርቲ ለመለየት አልተቸገሩም ወይ ብለን
ጠይቀናቸዋል።

‹‹#ፎቶ_ተለጥፎ_ዐይቻለሁ_ቀድሞ_በቅስቀሳ_የተወሰኑትን_አውቅ_ስለነበር_የምመርጠውን_ለመለየት_አልተቸገርኩም_ልንመርጥ_ስንገባም_ገለጻ_ተደርጎልን_ነበርና_ረድቻለሁ።›› ይላሉ፤
አሰለፈች።።

✍️ እንደ እርሳቸው መጻፍም ሆነ ማንበብ የማይችሉ፣ ነገር ግን ምስሎችን እና የምርጫ
ምልክቶችን በማየት የመረጡ የሚያውቋቸው ሰዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል።
‹‹#አለመማሬ_ከመምረጥ_አልከለከለኝም_መጻፍና_ማንበብ_ባልችልም_በአገሬ_ጉዳይ_ላይ
#እንድሳተፍ_እድል_እስከተሰጠኝ_ድረስ_የማልጠቀምበት_ምክንያት_የለም_መሃይም_ናት
#አታውቅም_ቢሉኝ_ግድ_የለኝም_ለዛም_ብዬ_አልሸሽም።›› ሲሉም ደፈር ብለው
ይናገራሉ።

✍️ #እንደ_አሰለፈች ዓይነት ማንበብም ሆነ መጻፍ የማይችሉ ነገር ግን ከምርጫ ቦታ
ድምጻቸውን ለመስጠት የተገኙ እናቶች ጥቂት አይደሉም። አንዳንድ ጣቢያዎች ላይ በዚህ
ምክንያት ዘርዝሮ ለማስረዳት ከጊዜ አንጻርም ሆነ ለምርጫ ተዓማኒነት ፈታኝ በመሆኑ፣
የተቸገሩም አልጠፉ። እንዲያም ሆኖ ግን ብዙዎቹ በትጋትና የድምጻቸውን ዋጋ በማመን
በመራጭነት ተሳትፈዋል።

✍️ በምርጫ ክልሉ በታዛቢነት ከተሳተፉ መካከል ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ
ግለሰብ በጉዳዩ ላይ ሐሳብ አካፍለዋል። በተለይም የሴቶችን ተሳትፎ በመጥቀስ፣ ‹‹#መጻፍም_ሆነ_ማንበብን_ተቸግረው_ካየናቸው_ውስጥ_ሴቶች_ይበዛሉ#እነርሱም_ግን_ከመጠየቅ_ወደኋላ_አላሉም#ድምጻቸው_እንዳይባክንም_ተጠንቅቀው_ሲጠይቁ_ዐይቻለሁ።›› ሲሉ አብራርተዋል። አያይዘውም ‹‹#ይህ_ዛሬ_ላይ_ላይታወቀን_ይችላል#ስርዓቱ_በዚህ_ማስቀጠል_ከተቻለ_ግን_በቀጣዩ_አገራዊ_ምርጫ_ጉልህ_ለውጦችን_እናያለን_ተጨባጭ_የፖለቲካ_ውጤትም_እንመለከታለን_የሴቶች_ተሳትፎም_ከዚህ_የላቀ_ይሆናል_ብዬ_አምናለሁ።›› ብለዋል።

✍️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ካርድ ተሰጥቶ መጠናቀቁን ተከትሎ
ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ በድምሩ 38 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በመራጭነት መመዝገባቸውን
አስታውቋል። ከእነዚህም መካከል 17 ሚሊየን ያህሉ ሴቶች ናቸው።


#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA
ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/joinchat/dFJkU4AbZgJkYWM0
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍#የምርጫ_ቅስቀሳና_ሴት_መራጮች
================

✍️ ከምርጫ ቅድመ ሂደቶች መካከል አንደኛው ነው፤ #የምርጫ_ቅስቀሳ_ዘመቻ። የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፓርቲ እንዲሁም የግል እጩዎች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ የመራጩን ቀልብ እና ልቦና ለመግዛት የሚያደርጉት ተግባር ነው። የምርጫ ቅስቀሳ አማራጭ ፖሊሲዎችንና የመፍተሄ አቅርቦ መራጭን ለማመረክና የፖለቲካ ሀሳብን ለመሸጥ የሚደረግ ጠንካራ እንቅስቃሴ ሲሆን፤ ይህም የምርጫው ወሳኝ ክፍል መካከል አንደኛው ነው፡፡ በዲሞክራሲ ምህዳር ፖለቲከኞች ራሳቸውን ከሕዝብ የሚያስተዋውቁበትና ሊሠሩ ያቀዱትን የሚስረዱበት እድል በመሆኑ በምርጫ ሂደት ዋነኛ ክፍል እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

✍️ ለምርጫ ቅስቀሳ በቅድሚያ ቢያንስ ከአንድ ዓመት በፊት ሊሠሩ የሚገቡ ሥራዎች እንዳሉ ኢሕአፓ መሪ የሆኑት #ቆንጂት_ብርሃን ይናገራሉ። ቅስቀሳውም እንዲሁ በሐሳብ ታስቦ በቃል የሚፈጸም ሳይሆን፣ በጽሑፍ ሊሰፍርና በሚገባ ሊታቀድ የሚገባ እንደሆነ ሳያነሱ አልቀሩም። #የምርጫ_ቅስቀሳ ከፍተኛ የገንዘብ የጊዜና የጉልበት ወጪን የሚጠይቅ፣ የተደራጀና በእቅድ የሚመራ መሆን አለበት፡፡ ውጤታማ ለመሆንም ተሳታፊዎቹ ተናግሮ ማሳመንን ጨምሮ የተለያዩ ክህሎቶችን ያዳበሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ዘመናዊውን ማህበራዊ ሚዲያ ጨምሮ፣ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀንን በአግባቡ የመጠቀምን ልምድና ችሎታ ፖለቲከኞች ሊያተኩሩበት የሚገባ የዘመቻው አካል ነው፡፡

✍️ በተለይም #የሴት_እጩዎች ቁጥር ጎላ ብሎ በታየበት የ2️⃣0️⃣1️⃣3️⃣ ምርጫ፣ የቅስቀሳ ዘመቻው ከሴቶች ተሳትፎ አንጻር ውጤትም ፈተናም የታየበት እንደነበር ተወዳዳሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በ2️⃣0️⃣1️⃣3️⃣ በተካሄደው 6️⃣ኛው አገራዊ ምርጫ #በኮቪድ_19 ምክንያት መራዘሙ #የምርጫ_ስቀሳ ዘመቻን በጥሩ ሁኔታ አቅዶ ለመከወን እንዳገዛቸው የሚናሩት የኢዜማዋ #ካውሰር_ኢድሪስ ያም ሆኖ የተለያዩ ፈተናዎች እንደነበሩ አልሸሸጉም። በተለይም #ከሴት ተመራጮች ጋር በተያያዘ ገና ለእጩነት ከሚቀርቡበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ቅስቀሳ ሥራዎች ድረስ አስቸጋሪ ሁኔታዎችና አጋጣሚዎች ነበሩ ይላሉ።

✍️ በራስ መተማመን ያላቸው፣ ብቁ እና ንቁ የሆኑ #ሴት_ፖለቲከኞች ወይም ተመራጮችን ለማፍራትና ስኬታማ የምርጫ ቅስቀሳም ለማድረግ ከኮታ ይልቅ አቅም ያላቸውን ሴቶች ወደ ሥራ ማምጣት ላይ መሠራት አለበት ባይ ናቸው ካውሰር እንድሪስ። ይህም በሂደት የማኅበረሰቡን ዕይታ ስለሚለውጥ ሴቶችን በብዛትና በብቃት በፖለቲካው ላይ ለማሳተፍ ጥሩ መንገድ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

✍️ ከ30 ዓመታት በላይ በፖለቲካው ውስጥ እንዲሁም በፖለቲካው ዙሪያ ተሳትፎ የነበራቸው ቆንጂት፣ በኢትዮጵያ ከውይይትና ምክክሮች ይልቅ በትንንሽ ጉዳዮች እሰጥ አገባ በብዛት ይስተዋላል ይላሉ።ፖለቲካውም ከአገር ጉዳይ ወጥቶ ግለሰብ ወይም ጥቂት ሰዎች ላይ ማተኮሩ፣ ከሐሳብ ይልቅ ሰዎች ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አድርጓል። በዚህም የተነሳ የምርጫ ቅስቀሳ ፈታኝና አስቸጋሪ መሆኑ እንደማይቀር አውስተዋል። ይህ ደግሞ ካለው የማኅበረሰብ እሳቤና ዕይታ አንጻር በሴቶች ላይ የከፋ ጫና እንዳለው አስረድተዋል።

✍️ በእርግጥ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት አካሄድ በየዘመኑ አስቸጋሪና ፈታኝ እንደሆነ የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም። ቆንጂት ብርሃንም በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ። ይህም የጾታ ጉዳይ ሳይሆን ራሱ የፖለቲካ ስርዓቱ ያለበት ችግር መሆኑን ጠቅሰው፣ እንዲያም ሆኖ ጫናው በሴቶች ላይ ይበረታል ብለዋል።

✍️ ለዚህና ከላይ ለተጠቀሱት ሴቶች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ለገጠማቸው እንዲሁም በጠቅላላው በምርጫ በመሳተፍ ሂደት ውስጥ ካሳለፉት ፈተና አንጻር፣ በቀጣይ ሊያስተካክለው ይችላል ያሉትን የመፍትሔ ሐሳብም አቅርበዋል። ይልቁንም ሴቶችን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ማውጣት፣ የሴቶችን ጨምሮ የማኅበረሰብን አመለካከት መለወጥና ማስተካከል፣ እንዲሁም ከምርጫው ቀደም ብሎ መዘጋጀትና መሥራት በዋናነት ትኩረት ያሻቸዋል ብለዋል።

✍️ በአንጻሩ ሴቶች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅስቀሳ በሚደረግበት ጊዜ፣ ጥያቄ የሚቀርብላቸው ሴቶች ‹እንኳን እኛም ልንገባ፣ ፖለቲካው ውስጥ ለሉ ሴቶችም እናዝናለን!› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤ ይሰጣሉ።

✍️ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የሚተላለፈውን መልዕክት ትተው #በሴት_እጩዎች መልክና አቋም ዙሪያ ሐሳብ የሚሰጡም ጥቂት አልነበሩም። በተለይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች በሚቀርቡ የሴቶች እጩዎች የምርጫ ቅስቀሳ ምስሎች ስር የሚሰጡ አስተያየቶች ለዚህ ማሳያ ሆነው የሚጠቀሱ ናቸው።

✍️ ግሩም ተሰማ የብልጽግና ፓርቲ ታዛቢ ሆነው በምርጫው ተሳትፎ አድርገዋል። #የሴቶችን_የምርጫ_ቅስቀሳ በሚመለከት በቅርበት የታዘቡትንና በቅርብ የሰሙትን አካፍለውናል። ራሳቸው በመረጡበት የምርጫ ጣቢያና በአካባቢው ከገጠማቸው በመነሳት ሲያስረዱ፣ ሴቶች እጩዎች በቅስቀሳ ወቅት ረዳትና አድማቂ እንጂ እጩ ተወዳዳሪ የማይመስሏቸው ጥቂት እንዳልነበሩ መታዘባቸውን ጠቅሰዋል።

✍️ የምርጫ ቅስቀሳ አደባባይ ተወጥቶ በሕዝብ ፊት የሚደረግና በራስ መተማመንን የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል። ‹‹ሴቶች ይህን አሟልተው በራስ መተማመን ይዘው ከበረቱ ይህኛው ምርጫ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንና በቀጣይ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ይረዳል›› ሲሉም ነው የተናገሩት።

#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA

ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍#ምርጫን_የታዘቡ_ሴቶች
=============

✍️ 6️⃣ኛው አገራዊ ምርጫ #የሴቶች_ተሳትፎ በብዛት የተስተዋለበት እንደሆነ ብዙዎቻችን መታዘብ የቻልነው እውነት ነው። ምንም እንኳ ይህ ይበቃል ወይም ‹#በቂ_ነው_የሴቶች የእኩል የፖለቲካ ተሳትፎ ጥረት ተሳክቷል› ለማለት የሚያስች ባይሆንም፣ እያንዳንዱ ወደፊት የሆነ እርምጃ ሊበረታታ እንደሚገባ እሙን ነው።

✍️ የቅድመ ምርጫ ሂደት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች #የሴቶችን_ተሳትፎ እንዲያሳድጉ ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥረት ማድረጉ የቅርብ ትውስታ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች በተወሰነ መጠንም ቢሆን እንኳ ሴቶችን እንዲያሳትፉ ግድ ለማለት የተደረገው ጥረት ባይሳካም፣ ሴቶችን በብዛት ተሳታፊ ለሚያደርጉ የተለየ ማበረታቻ
እስከመስጠት ደርሷል።

✍️ በተጓዳኝ ግን በቦርዱ የሴት ባለሞያዎችና ሠራተኞች፣ በምርጫ ወቅት የተሳተፉ #የሴት_ታዛቢዎች እንዲሁም የሴት መራጮች ቁጥር ያንን ሁሉ ያካካሰው ይመስላል። ለአሁን ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የሲቪል ማኅበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን መሥራት እንዳለባቸው አቅጣጫ ጠቋሚ ነው። ከዛም በላይ ሴቶች
ራሳቸው ተነሳሽነትን እንዲያሳዩ ይረዳል።

✍️ ዛሬ ጥቂት ስለ #ታዛቢዎች ልናነሳ ነው። በምርጫ ወቅት ትልቅ ድርሻ እና ተሳትፎ ካደረጉት መካከል የምርጫ ታዛቢዎች ይጠቀሳሉ። በ 6️⃣ኛው አገራዊ ምርጫ ደግሞ በዚህ የታዛቢነት ሥራ ላይ ሴቶች በብዛት ተሳትፈዋል።

✍️ መለስ ብለን መረጃዎችን እንቃኝ። ምርጫ ቦርድ #ምርጫውን_ለመታዘብ ፍላጎት ላላቸው የአገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ሊሰጥ መሆኑን ባስታወቀ ጊዜ #አንድ_መቶ_ዐስራ_አንድ ድርጅቶች ተመዝግበው ነበር። ከእነዚህም መካከል በተለያየ መስፈርትና አካሄድ 3️⃣6️⃣ ድርጅቶች ምርጫውን እንዲታዘቡ ተመርጠዋል።

✍️ ከተመረጡ ታዛቢ ድርጅቶች መካከል ደግሞ #8ቱ_በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሠሩ ሲቪክ ማኅበራት ናቸው። በዚህም መሠረት በጠቅላላው
🔹134 ሺሕ 109 ታዛቢዎች ሲቀርቡ፣ ከዛም መካከል
🔹61 ሺሕ 851 ማለትም 46 በመቶ #ሴቶች ናቸው።

✍️ ይህ በቁጥርም ደረጃ ብቻ ቢሆን የታየ እንደሆነ ይበል የሚያሰኝ ደረጃ መሆኑ እሙን ነው። በተለይም #ሴቶች እንዲህ ባለው መንገድ ወደ ፖለቲካ ተሳትፎ መቅረብና በሚቀጥሉት አገራዊ ምርጫ የሚኖራቸው ተሳትፎም እያደር እንደሚጨምር ማሳያ ሊሆን ይችላል። ምቹ በማይመስለውና ብዙ ምቹ ያልሆነ መልክ ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ ተሳትፎ ሊዘራ ይችላል የሚል ዕይታም አለ።

✍️ በምርጫው ሂደትና ድኅረ ምርጫ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰጡ የነበሩ የአገር ውስጥ እንዲሁም ዓለማቀፍ ተቋማትም ይህን #የሴቶች_ተሳትፎ ታዝበዋል። እንደ ማሳያ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ምርጫ ታዛቢ ልዑክ በምርቻ የነበረውን የጾታ ተዋጽኦ በመሚመለከት አስተያየት ሰጥቷል። በዛም መሠረት በድምጽ ሰጪዎች ዘንድ አጥጋቢ የሚባል የጾታ ተዋጽኦ ነበር ብሎ በመጥቀስ፣ ከምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች መካከል 3️⃣4️⃣በመቶ እንዲሁም ከአገር ውስጥ ታዛቢዎች 8️⃣4️⃣ በመቶ ሴቶች መሆናቸውን አስታውቋል።

✍️ #አስመረት_ፈቃዱ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው። በ6️⃣ኛው አገራዊ ምርጫ በመራጭነትም በተሳተፉበት የምርጫ ጣቢያ በታዛቢነት ተሳትፎ ማድረጋቸውን ነግረውናል። በዛም ከነበሩ ታዛቢዎች መካከል በርከት ያሉት ሴቶች እንደነበሩ እንደሚያስታውሱ ጠቅሰዋል። ወጣቶች መኖራውንና እንደውም
በእድሜ ገፋ ያሉት እናት እርሳቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

✍️ ‹‹ከዚህ ቀደም በነበረውና በማስታውሰው #ምርጫ_በታዛቢነት መሳተፍ አይደለም ለመምረጥ እንኳ የመሄድ ፍላጎት አልነበረኝም።›› ሲሉ የሚያስታውሱት አስመረት፣ ዘንድሮ ግን በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች ለታዛቢነት እንደሚሳተፉ ሲነግሯቸው ተነሳሽነትን እንዳገኙ ገልጸዋል።

✍️ ታድያ እንዴት ነበር ስንል ጠይቀናቸዋል። እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ ‹‹ብዙ ሴት ይኖራል ብዬ አልጠበቅኩም። እኔም ስፈራ ስቸር ነው ፈቃደኛ የሆንኩት። የሆነውን ስመለከትና ብዙ ሴቶች ሳይ ግን፣ እድሜ ይስጠን እንጂ በቀጣዩ ምርጫም በታዛቢነትም ቢሆን መሳተፌ የሚቀር አይመስለኝም።›› በአስመረት ዕይታ መሠረት በዚህ አጋጣሚ #ወጣት_ሴቶች የበለጠ ተነሳሽነትን ሊያገኙ ይችላሉ።

✍️በእርግጥ ይህ እውነት ሆኖ ወጤቱም በቀጣይ ምርጫዎች እውን ሆኖ ሊታይ ይችላል። በተጓዳኝ በምርጫው #የሴቶች_በብዛት_በታዛቢነት መሳተፍ ለምርጫው ሰላማዊነት ያበረከተው አስተዋጽኦ ሊኖር እንደሚችል ብዙዎች ያምናሉ። በእርግጥ ጉዳዩ የተወሰነ ጥናት
የሚያስፈልገው ቢሆንም፣ በድምሩ ግን #የሴቶች_ተሳትፎ መጨመሩ መልካም ውጤት እንደሆነ ግልጽ ነው።

✍️ ከምንም በላይ አስመረት እንዳሉት ምርጫው #ሴቶች በበለጠ በፖለቲካው ለመሳተፍ ተነሳሽነትን ሊፈጥርባቸው የሚችል ነው። የግድ ምቹ የፖለቲካ ምህዳር መፈጠር ላይኖርበት ይችላል። እንደ ወንዶች ሁሉ #ሴቶችም የፖለቲካ መረዳትና ብቃት መሠረት ባለው ኹኔታ ውስጥ ገብተው መታገል፣ አጋጣሚዎች ሲገኙም በመሳተፍ ለውጥን ማጽናት
እንደሚችሉ አሳይቶ የሚያተጋቸው ነው።

🔹🔹🔹🔹🔹

#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA
ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
Public dialogue
➡️ Engaging women building sustainable peace and conflict
resolution
📍Moderator: - Sumeya Mohammed (lawyer and humanitarian
worker)
📍Presenter: - Bilen Asrat (Democratic Institution Support Expert)
September 17, 2021 from 8: 30 am – 6: 30
Hub Hotel
📢 Public dialogue
➡️ The role of stakeholders to engaging women in peace building
and conflict resolution
📍 Moderator: Seble T/Birhan (Legal & public Relation Expert)
📍 Presenter: - Mussa Adem (Political annalist)
September 18, 2021 from 8: 30 am – 6: 30
Hub Hotel
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
Why and How Should Women be involved in peace process
Women are important to the peace building process. Because:-
👉 They constitute half of every community and the difficult task
of peace building must be done by men and women in
partnership.
👉 Women are also the central caretakers of families and
everyone is affected when they are excluded from peace
building.
👉 Women are also advocates for peace, as peacekeepers, relief
workers and mediators.
Belen Aserat (Democratic Institution Support Expert)
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 Public Dialoged three: - ‘Engaging Women
in building sustainable peace’
📷 Participant
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 Public Dialoged three: - ‘Engaging Women
in building sustainable peace’
📷 Participant
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 Public Dialoged three: - ‘Engaging Women
in building sustainable peace’
📷 Participant
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 Public Dialoged three: - ‘Engaging Women
in building sustainable peace’
📷 Participant
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 Public Dialoged three: - ‘Engaging Women
in building sustainable peace’
📷 Participant
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 Public Dialoged three: - ‘Engaging Women
in building sustainable peace’
📷 Participant
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
➡️A lack of resources such as a lack of access to employment opportunities and to productive assets such as land, capital, health services, training and education.
➡️Women’s movements do not have established mechanisms to monitor and evaluate the implementation of the gender agenda in post-conflict settings. For example, in Somalia male-dominated structures have not seen the need to implement agreed affirmative action.
🎤Mussa Adem
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia
📍 who should include women?
➡️ Families
➡️ Communities
➡️ Professionals
➡️ Political Parties
➡️ Civil Societies
➡️ Governments
➡️ Media
➡️ intellectuals
📍 Success Stories
➡️ Before the passage of the U.N. Women, Peace and Security act,
a review of 664 peace agreements from 1990-2000 by U.N.
Women noted that only 11% of them included any reference to
women’s security and inclusion. And from 1992-2011, only 4%
of signatories and less than 10% of negotiators were
women(USIP).
➡️ Narrowing the gender gap is the only solution for our
sustainable peace
➡️ Women should be included in the process of mediation
They should not seen only as a victims but contributors for
peace
🎤 Musa Adem
#Empathy_for_Life_integrated_Development_Association
#ELiDA
👉ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
👉ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
👉ቴሌግራም፦ https://t.me/ELiDAEthioopia
👉ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia