ELiDA Ethiopia
209 subscribers
324 photos
6 videos
19 files
68 links
Inspiring women, Girls and Youth to contribute and lead in building sustainable peace and strong democratic culture. ELiDA works for the protection and well-being as well as the economic, social, and political empowerment of women, Youth, Girls..........
Download Telegram
Forwarded from solomon Yohannes
📍 #ሴቶችና #ምርጫ #በኢትየጵያ
=================
🇪በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች ተሳትፎ ርዕስ ሆኖ ሲነሳ እንደ ‹ወርቃማ ዘመን› የሚጠቀሰው ወደኋላ መቶ ዓመታትን ተመልሶ የምናገኘው #እቴጌጣይቱ አልያም የንግሥተ ነገሥት #ዘውዲቱ ታሪክ ነው። የእነዛን ብርቱ #ሴቶች አረአያነት የተከተለ #የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ግን ከዛ በኋላ እምብዛም ሲነሳ አንሰማም።
📖እንዲውም የመንግስት አስተዳደር ምስረታ ወጥነት ማጣቱና፣ ተከትሎም ፖለቲካን አስፈሪ አውድ አድርጎ መግለጽ ያመጣው ችግር፣ እንደማንኛውም የማህበረሰብ አካል #ሴቶችንም ለፖለቲካ ቁጥብና እንግዳ እንዲሆኑ ያደረገ ይመስላል።
መለስ ብለን በኢትዮጵያ ምርጫ የተካሄደባቸውን ጊዜያትና #የኢትዮጵያ #ሴቶችን እናንሳ። እንደሚታወቀው #ኢትዮጵያ ሦስት ሺሕ እንደሆነ በሚታመነው ታሪኳ በርካታ የአስተዳደር ሥርዓቶችን እና እጅግ በርካታ መሪዎችን አስተናግዳለች።
መለኮታዊ ፈቃድ ተሰጥቶናል ብለው ከሚያምኑ ነገሥታት እስከ ወታደራዊ፣ በውጊያ ሥልጣንን ከሚናጠቁት አንስቶ ታግለው ሥልጣን እስከያዙት ድረስ፣ #በአገርአስተዳደርናመንግሥት ምሥረታ ዙሪያ የተጻፈው #የኢትዮጵያ ታሪክ በርካታ ነው።
#ምርጫ ግን ሩቅ የሚባል ዘመንን ያስቆጠረ አይደለም፣ 5️⃣0️⃣ ዓመት እንኳ በቅጡ አልሞላውም። #ዴሞክራሲ የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ሳይቀጠልበት በፊትም በቀዳማዊ #አጼኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ምርጫ #በኢትዮጵያ ተካሂዷል። ይህም የመጀመሪያው ሕገመንግሥት በ 1️⃣9️⃣2️⃣3️⃣ በንጉሠ ነገሥቱ እንዲወጣ መደረጉን ተከትሎ ነው።
📖በሕገመንግሥቱ መሠረት ሕዝቡንና መንግሥትን የሚያገናኝ እንዲሁም የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ከሕዝብ ተወካዮች ጋር የሚመክርበት ኹለት ክፍል ያለው የአማካሪዎች ምክር ቤት እንዲኖር ተባለ። በዚህም የተነሳ የአማካሪዎች ምክር ቤት እንዲሁም ፓርላማ ተቋቋመና ምርጫ አጀንዳ ሆነ። አልዘገዩም፣ የሕዝብ እንደራሴዎች በሕዝብ እንዲመረጡ፣ ምርጫው ግን በቀጥታ በሕዝብ ሳይሆን በተወካይ እንዲሆን ተባለ።
📌📌1️⃣9️⃣4️⃣9️⃣የመጀመሪያው የሕዝብ እንደራሴዎች #ምርጫ #በኢትዮጵያ ተካሄደ። ይህም #ምርጫ እስከ 1️⃣9️⃣6️⃣5️⃣ ድረስ #5️⃣ ጊዜ ያህል የተካሄደ ነው። #የምርጫ ማስፈጸሚያ አዋጅም ተዘጋጀ። በጊዜው የመምረጥ መብት ያላቸው እድሜያቸው ከ2️⃣ 1️⃣በላይ የሆኑ ሁሉ ናቸው። ሴቶችም ተሳትፈዋል። በአንጻሩ እድሜያቸው ከ2️⃣ 1️⃣ በታች የሆኑትን ጨምሮ
👉እስረኞች፣
👉በሕግ የሲቪል መብቶችን ያጡ ግለሰቦች፣
👉የአእምሮ ጤንነት መታወክ ያለባቸው በመራጭነት አይሳተፉም።
📌በተጓዳኝ #ተመራጭ ለመሆን ከ #2️⃣5️⃣ ዓመት በላይ መሆን፣ ግምቱ #2️⃣ ሺሕ ብር የሚጠጋ የማይንቀሳቀስ እንዲሁም #አንድ ሺሕ ብር የሚገመት የሚንቀሳቀስ ንብረት ያላቸው፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባህል ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ማንበብና መጻፍ የሚችሉ፣ #በምርጫ ወቅት 2️⃣5️⃣0️⃣ እንዲሁም ቀጥሎ 5️⃣0️⃣0️⃣ ብር ማስያዝ የሚችሉ ናቸው።
የማስፈጸሚያ አዋጁ በጾታ ላይ የተመሰረተ ምንም አይነት ልዩነት አላስቀመጠም፡፡

📌ይህም 🇪🇹#ኢትዮጵያን የሴቶች የመምረጥና የመመረጥ መብትን #ምርጫ ማድረግ ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ በህግ ያረጋገጠች ሀገር ያደርጋታል፡፡ ብንጽጽር ለምሳሌ የፕሬዝዳነታዊ ምርጫን በ1️⃣7️⃣7️⃣8️⃣ አ.ም የጀመረችው 🇺🇸አሜሪካ #የሴቶችን የመምረጥ መብት በህግ ያጸደቀችው በ1️⃣9️⃣2️⃣0️⃣፣ ከ1️⃣4️⃣2️⃣ አመታ በኋላ ነበር፡፡ ይህም የአሜሪካ ሴቶች መብታቸውን ለማረጋገጥ ከመቶ አመት በላይ የፈጀ ትግል እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል፡፡ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ #የሴቶችን የመምረጥና የመመረጥ መብት ለመጀመሪያ ጊዜ በተግባር ያስከበረችው #ኒውዚላንድ ናት፤ በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1️⃣9️⃣8️⃣3️⃣ ነው። የመጨረሻዋ ደግሞ #ሳውዲአረብያ፣ ከ5️⃣ ዓመት በፊት በ2️⃣0️⃣1️⃣5️⃣/1️⃣6️⃣

📌1️⃣9️⃣4️⃣9️⃣ #በኢትዮጵያ በተካሄደው የመጀመሪያው #ምርጫ3️⃣ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለመምረጥ ተመዝግበው ከ #2️⃣.5️⃣ሚሊዮን በላይ የሆኑት መርጠዋል። በዚህ ምርጫ ታድያ #የሴቶች ተሳትፎም ጀምሮ ነበር። ሥማቸው በተደጋጋሚ ሲጠራ የምንሰማቸው
#ስንዱገብሩ የመጀመሪያዋ የምክር ቤት አባል በመሆን የተመረጡት በዚሁ ምርጫ ነው።

📖 መዛግብት እንደሚያስረዱን #በስንዱገብሩ መመረጥ ምክንያት ለዚህ ሥራ የተነሳሱና በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት ያደረባቸው #ሴቶች ጥቂት አልነበሩም።

እንደውም በ1️⃣9️⃣5️⃣7️⃣ ምርጫ በተመራጭነት የተሳተፉ #አምሳለወርቅአስፋው የተባሉ ሴት ተከታዩን ተናግረዋል፤
‼️‹‹#በአለፈዉ_ጊዜ_ሴቶች_የምክር_ቤቱ_አባል_በመሆን_ከምርጫ_ውድድር_ገብተዉ_በወገናቸው_ድጋፍ_ተመርጠዉ_ከሥራዉ_ላይ_ከወንዶች_ጋር_ሰልፈዉ_ታይተዋ_እኔም_በበኩሌ_ችሎታዬ_ይፈቅድልኛል_በማለት_በምርጫዉድድር_ገብቻለሁ።››‼️ ብለዋል።

✍️#ከስንዱ_ገብሩ በኋላ በ1️⃣9️⃣6️⃣1️⃣ #የሺእመቤት_ወንድማገኘሁ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን የምርጫ ወረዳ፣ በ1️⃣9️⃣6️⃣5️⃣ #አልማዝ_አጥናፍሰገድ በዛው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ማማ ምድር በሚባል ምርጫ ወረዳ እንዲሁም #መንበረወርቅ_አድማሱ በወሎ ጠቅላይ ግዛት ላስታ የምርጫ ወረዳ ላይ መመረጣቸው ከሚታወስ #ሴቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

✍️በድምሩ በ1️⃣9️⃣6️⃣5️⃣ ምርጫ 5️⃣ #ሴቶች አልፈው ነበር። ከዛም ባለፈ ደግሞ #ሴቶቹ እንደሚጠበቀው #የአዲስ_አበባ ነዋሪ የሆኑ ብቻ ወይም የተማሩ ብቻ አይደሉም። በወቅቱ በሁሉም ጠቅላይ ግዛቶች የሚገኙ ነበሩ።

✍️ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በዘመኑ በተካዱ ምርጫዎች በጾታ ምክንያት ሴቶች ከመመረጥም ሆነ ከመምረጥ አልተገደቡም ነበር። እንደሚያውም በተመራጭነት ከወንዶች የተሻለ ድምጽ እንደሚያገኙ ተጠቅሷል።

✍️ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በዘመኑ በተካዱ ምርጫዎች በጾታ ምክንያት #ሴቶች ከመመረጥም ሆነ ከመምረጥ አልተገደቡም ነበር። እንደሚያውም በተመራጭነት ከወንዶች የተሻለ ድምጽ እንደሚያገኙ ተጠቅሷል።

✍️ይህ በንጉሡ ዘመን ይደረግ የነበረው ምርጫ #በደርግ ዘመነ መንግሥት አልቀጠለም። ይልቁንም ከ1️⃣9️⃣8️⃣9️⃣ አንድ ብሎ ጀምሮ እነሆ #የ2️⃣0️⃣1️⃣3️⃣_ዘመን 6️⃣ኛው አገራዊ #ምርጫ ላይ ደርሰናል።
✍️ #ባለፉት_ስድሰትምርጫዎች_የሴቶች_ተሳትፎ_በርካታ_ለውጦች_አሳይቷል_የሴቶች_በመራጭነትም_ሆነ_በተመራጭነት_በቁጥርም_በአቅምም_እየጨመሩ_መምታጣቸው_የሚታይ_እውነታ_ነው፡፡

📌📌 #Empathy_for_Life_integrated_Development_Association

#ELiDA

ድረ ገጽ፦ https://elidaethiopia.org/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/elidaethiopia/
ቴሌግራም፦ https://t.me/joinchat/dFJkU4AbZgJkYWM0
ትዊተር፦ https://twitter.com/elidaethiopia