EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
136K subscribers
19.1K photos
163 videos
79 files
10.4K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ፡-አቶ እውነቱ አለነ
****************

ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰላምና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የኢትዮጵያ ሚዲያ ለኢትዮጵያውያን ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር" በሚል መሪ ሃሳብ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከግል የሚዲያ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው።

አቶ እውነቱ፤ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ ከገለልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚቀርብበት ወቀሳ በሕግ የተፈታ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ቢሆንም፤ ምክር ቤቱ ስራውን ከማገዝ ያለፈ ጣልቃ አይገባበትም ነው ያሉት።

መገናኛ ብዙኀንም የተሳካ ምክክር እንዲደረግና ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04hxbS8AFHy8nHr5gMtGK3NaiJXkXZP9yDSbacoPfHRbmRgWx22GSabBmg5kkJduRl
በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወን አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ የተለዩ ባለድርሻ አካላት
***********

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ለሚያከናውነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ለይቷል፡፡

በኮሚሽኑ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት በሚቀርብላቸው ይፋዊ ጥሪ መሰረት በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች በሚከናወነው አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ እንዲንፀባረቅላቸው የሚፈልጓቸውን አጀንዳዎች እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል ሲል ኮሚሽኑ በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና መወጣት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ
*****************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሮች እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለድርሻዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ዲጂታላይዜሽን አይቀሬ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ኢኒሼቲቮችን ቀርፃ መተግበር ጀምራለች ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን የግድ የሆነባቸው ምክንያቶች አሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንደኛው፥ ዲጂታላይዜሽን ዕድገትን የሚያፋጥን በመሆኑ ነው ብለዋል።

ሁለተኛው፥ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚያግዝ ታምኖ መሆኑን ገልፀዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02BJCBnEqHA4JPZAvatSgtSuYM5Lpd1dSefoDZufYqZr2B2wP4MP5zr3EtQsaW6fYwl
ኤፍ ኤም አዲስ 97.1ን በቴሌግራም ቻናላችን የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ
https://t.me/FMADDIS
www.ebc.et
**********
በእጅዎ ባለ ስልክ፣ቢያሻዎ በኮምፒውተርዎ መከታተል እንዲችሉ ዘምኖ እና ምቹ ሆኖ ቀርቦልዎታል፡፡
ከዘመኑ ሚዲያ ተቀዳሚ አማራጭ እየሆነ የመጣው የድረ ገፅ አካል የሆነው www.ebc.et በአዳዲስ ገጽታዎች እና አቀራረብ ወደ እናንተ መድረሱን ይቀጥላል፡፡
"በአየር መንገዱ ላይ የተከሰተ የእሳት አደጋ የለም፤ አካባቢው ላይ ተከስቶ የነበረው አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል”፦ የአዲስ አበባ ከተማ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
********************

በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት አካባቢ ዛሬ ከቀኑ 9፡41 ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና አደጋው ከአየር መንገዱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋው ከአየር መንገድ ግቢውም ሆነ ከተርሚናሉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ያሉት አቶ ንጋቱ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች እና ሚዲያዎች የእሳት አደጋው በአየር መንገዱ ውስጥ እንደተከሰተ አድርገው የሚያሰራጩት ዘገባ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አደጋው በአንድ የድንገተኛ እሳት አደጋ ባለሞያ ላይ ቀላል ጉዳት ማድረሱንም አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል።
የእሳት አደጋው በኮሚሽኑ ባለሞያዎች፣ በአየር መንገዱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ርብርብ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል።
የእሳት አደጋው መነሻ ምክንያት እና ያስከተለው የጉዳት መጠን የማጣራት ስራው ሲጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግም ባለሞያው ገልፀዋል።
በሜሮን ንብረት
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid0wN9WyTuiJwEaetkr5Cc9AtSJkvk5rYRnBNKXcLWVxSRmiGBGk7GCWjhrun3xjgZ4l&id=61550945701729
በአማራ ክልል የተፈጠረው ሰላም የተሻሉ የልማት ስራዎችን ለማከናወን ዕድል መፍጠሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ
**************

በክልሉ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ያጋጠመው የሰላም ማጣት ችግር የልማትና የመልካም አስተዳደር እክል ፈጥሮ ቆይቷል ብለዋል ርዕሰ መስተዳደሩ።

መንግሥት በክልሉ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ ባከናወነው የሕግ ማስከበር ስራ፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ8 ወረዳዎች በስተቀር፣ በ258 ወረዳዎች መደበኛ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች መጀመራቸውን ነው የገለጹት።

የህዝቡ ዋንኛ ጥያቄ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ነው ያሉት አቶ አረጋ፤ ጥያቄውን ለመመለስም መንግሥት በትኩረት እየሰራ መሆኑን በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል።

በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ እየቀረበ መሆኑንም ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በተወሰኑ አካባቢዎች አሁንም የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት በመኖሩን ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሰላም እና በልማት እጦት ዋንኛው ተጎጂ ህዝቡ ነው ያሉት ርዕስ መስተዳድሩ፤ ህብረተሰቡ መንግሥት በክልሉ ሰላምን ለማረጋገጥ እያደገው ያለውን ጥረት በመደገፍ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል ህዝብን ጥያቄና ፍላጎት ለማርካት በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር እና ባለድርሻ አካላት በንጽህና እና በአገልጋይነት ስሜት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ግብርና፣ ኢንዱስትሪ ማዕድን እና ቱሪዝም የክልሉ መንግሥት በቀጣይ የህብረተሰቡን ተቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት የሚሰራባቸው የልማት መስኮች መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል።

በላሉ ኢታላ
በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ሊሻሻሉ ይገባል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*************************

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የሚስተዋሉበትን የመዘግየት እና ለተገልጋይ ምቹ ከባቢ የመገንባት ክፍተቶች ፈጥነው ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ሚኒስቴሩ የየብስ፣ የአየርና የባህር ትራንስፖርት አገልግሎቶችን በማሳለጥ የሀገሪቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፍላጐት ለማሟላት እየሰራቸው ያሉ ተግባራትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሪፎርሙ በኋላ የደረሰበት ደረጃ እና ምቹ የስራ ከባቢን ለመፍጠር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁንም ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የሚስተዋሉ የመዘግየት፣ ለተገልጋይ ምቹ ከባቢ የመገንባት እና የስራ ከባቢ መራራቅ ክፍተቶች ስለመኖራቸው እና እነዚህም ፈጥነው ሊታረሙ የሚገባቸው ስለመሆናቸው ከመግባባት ተደርሷል ብለዋል።

በቀጣይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያሉበትን ማነቆዎች ተወያይቶ በጋራ ለመፍታት አቅጣጫ መቀመጡን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ በኋላ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።