EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
124K subscribers
15.3K photos
107 videos
79 files
9.67K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሥጋና አቀረቡ
****************

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምሥጋና አቅርበዋል።

ሙሉ መልዕክቱ ቀጥሎ ቀርቧል፦

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተፈጥሮ ፀጋ የታደለችውን እና የተፈጥሮ ውበቷን የበለጠ ፍንትው አደርጎ በማውጣት የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን የወርቃማ ዕድል ባለቤት በሆነችው ጎርጎራ፤ ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን ስለሀገር ክብር እና ስለሕዝብ ጥቅም በዝርዝር ከመከሩ በኋላ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም የሁሉም ክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች እና ሚኒስትሮች በተገኙበት በውቢቷ ባሕር ዳር ከተማ በመገኘት በዓለማችን ትልቁ ወንዝ በሆነው ዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባውን ታላቁን ድልድይ መርቀው ሥራ አስጀምረውልናል። ለዚህ በጎ ተግባርዎ፤ በታላቁ የክልላችን ሕዝብ እና በአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ስም ምሥጋናዬን በታላቅ አክብሮት አቀርባለሁ። https://www.facebook.com/EBCzena/posts/851696680317846
"በሳምንቱ መጨረሻ በአማራ ክልል ከነበረን ቆይታ ተመልሰን ከከፍተኛ የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጎንደር የሚገኙ ሶስት እጅግ አስፈላጊ ፕሮጀክቶችን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም የሚጠናቀቁበትን መንገድ አስቀምጠናል። የፕሮጀክቶቹ ስራዎች የመገጭን ግድብ ማጠናቀቅ፣ የጎንደር ከተማን የውሃ አቅርቦት ማሻሻል እና የአዘዞ ጎንደር 11 ኪሎ ሜትር መንገድ ሥራ መፈፀም ናቸው። በዛሬ ጠዋቱ ግምገማ በመመስረት ስራዎቹ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቁ የፕሮጀክቶቹ አስተዳደር ማሻሻያ እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቻለሁ።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሞታችንን ለምን ይዘን እንዞራለን? 12 ሚሊዮን ሰዎችንስ ለምን እናጣለን?
*************************

ሰዎች በተፈጥሮ ሂደት ኖረው መሞታቸውን ላሰበ ሰው ሞቱን ይዞ የሚዞር ፍጡር ስለመሆኑ ሊገነዘብ ይችላል። ደግሞም ሰው እያወቀም ሆነ ሳያውቅ መጥፊያው የሆነን ነገር በተደጋጋሚ እየከወነ ሞቱን ሲያፋጥን መመልከት ምነው ሰው ሞቱን ይዞ ለመዞር ፈቀደ ሊያስብል ይችላል።

በሰዎች በተደጋጋሚ የሚከወኑ ድርጊቶች አንዳንዴ ጠቃሚ እንደሆኑ ሁሉ ጎጂም ሆነው እስከ ሞት ሲያደርሱ የተመለከትንባቸው ሂደቶች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ።

ለዚህም ነው አንድን ተደጋጋሚ ድርጊት በመመልከት ይሄ ነገር ማህበረሰባዊ ጥፋት ያመጣል እና ከወዲሁ መላ ይበጅለት የሚሉ ሀሳቦች በባለሙያዎች የሚቀርቡት።

ከእንደዚህ ዓይነት ማህበረሰባዊ ጉዳትን ያስከትላሉ ከሚባሉ ልማዳዊ ድርጊቶች ውስጥ አንዱ ታዲያ የአካባቢ ንፅህና ጉድለትን የሚያመጡ ድርጊቶች ስለመሆናቸው መጥቀስ ይቻላል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0K84pxvjapKmMgCEidfPa9K4db7kcb9TVzkYhQKrH8TN1KMN1BfE2bVYdvLetW9wXl
የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ አውደ ርዕይ ተካሄደ
****************

የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ አውደ ርዕይ አዲስ አበባ በሚገኘው የሕብረቱ ዋና መስሪያ ቤት ዛሬ ተካሂዷል።

በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፣ የሕብረቱ የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት የግንቦት ወር 2024 ሊቀ-መንበር አምባሳደር ኢኖሰንት ሺዮ፣ የሕብረቱ ኮሚሽነሮች፣ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እርዳታና የልማት አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

አውደ ርዕዩ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽንና የልማት አጋሮች በአህጉሪቱ ያከናወኗቸውን የሰብዓዊ ስራዎችና የሰብዓዊ እርዳታ ምላሾች የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ግጭቶችን በመከላከል፣ ምላሽ በመስጠትና በመፍታት ያከናወኑት ተግባር በአውደ ርዕዩ ላይ ለዕይታ ቀርበዋል። https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02jvFfedwV5ktHvEbW1ZmwBFDGigjUMdQGLHRuLY7XFmrg8uoS9xGCrQeuYmM9U1EYl
Live stream finished (3 days)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ መሥራች እና ፕሬዚደንት ጋር ተወያዩ
***********

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ መሥራች እና ፕሬዚደንት ጄሚ ኩፐር እና ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ፤ ቢግ ዊን በሰቆጣ ቃል ኪዳን አተገባበር እና ከመንግሥት ጋር በሚሰራው ሌሎች የልማት ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ይህን የትብብር ምዕራፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በተጀመሩ እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቆሙት።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ በግብርና፣ በትምህርት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና ድህነት ቅነሳ ዘርፎች አበረታች ስራዎች መስራቱንም ጠቅሰዋል።