EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
136K subscribers
20.5K photos
169 videos
79 files
10.6K links
Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)
Download Telegram
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን ያስመዘገበችው 2፡11፡53 ሰዓት በሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ ጸደቀ
****

አትሌት ትዕግስት አሰፋ ባለፈው ዓመት በበርሊን ማራቶን ያስመዘገበችው 2፡11፡53 ሰዓት በሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ እንደጸደቀላት የዓለም አትሌቲክስ ዘግቧል።

አትሌቷ ከወራት በኋላ በፈረንሳይ በሚካሄደው የ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ከአትሌት አማኔ በሪሶ እና ከአትሌት መገርቱ ዓለሙ ጋር ኢትዮጵያን በመወከል በሴቶች ማራቶን ትሳተፋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) ሥራ አስጀመሩ
************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያከናወናቸው የዲጂታል ሪፎርም ሥራዎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ወንጀልን የመከላከል አቅሙን ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዛሬ አመሻሹን የፌደራል ፖሊስ የዜጎች መረጃ መቀበያ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የለማ እና ዜጎች ወንጀልን በቀላሉ ለማዕከሉ የሚጠቁሙበት EFPApp የተሰኘ መተግበሪያንም ስራ አስጀምረዋል።

ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መከወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውስተው፤ በመንግሥታዊ ተቋማት ከ500 በላይ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መደረጋቸውን ጠቅሰዋል።

ፌደራል ፖሊስም በማሻሻያው የዲጂታላይዜሽን አሠራርን በመተግበር ህብረተሰቡ በየትኛውም አካባቢ ሆኖ የወንጀል ድርጊትን መጠቆም የሚችልበትን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረጉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት ተናግረዋል።

ሁሉም ዜጋ መተግበሪያውን በመጠቀም ወንጀልን በጋራ የመከላከል ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሮዛ መኮንን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የወባ መርሃ ግብር የወባ መድሃኒትን በኢትዮጵያ ለማምረት የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ
*****************

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጃ ዱጉማ እና ሌሎች የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የወባ በሽታ መርሃ ግብር ፒኤምአይ (PMI) ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በቀጣይ ዓመት የወባ ቁጥጥርና ማጥፋት ስራ ወቅት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራትን በጋራ ለይቶ ለመተግበር ያለመ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር መቅደስ፥ በኢትዮጵያ የወባ በሸታን በመቆጣጠር እና በበሽታው ምክንያት የሚከሰተውን ሞት በመቀነስ ረገድ የሚያበረታታ ውጤት ቢመዘገብም፤ ከአየር ንብረት ለውጥ፣ የዝናብ መቆራረጥ፣ ድርቅና የሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ባለፉት ዓመታት ለትንኝ መራቢያ ምቹ አጋጣሚዎች በመፈጠራቸው የወባ በሸታ ታማሚዎች ቁጥር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።

ይህን ተከትሎም ሰው ሰራሸና ተፈጥሮዊ ተግዳሮቶችን ከግምት ያስገባ ፈጣን የወባ መመርመሪያ ኪት እና የወባ ትንኝ መከላከያ የመኝታ አጎበርን ያካተተ አዲስ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት።

ሚኒስትሯ አያይዘውም፥ ፒኤምአይ የወባ መድሃኒትን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው፥ መንግሥት የወባ ስርጭትን ለመግታት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለጸው፤ በዚህ ረገድ ፒኤምአይ እያደረገው ስላለው ድጋፍ አመስግነዋል።

መርሃ ግብሩ የወባ ስርጭትን ለመግታት በሚደረጉ ጥረቶች እንዲሁም በመረጃ አያያዝ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
"በመካከላችሁ ምክክር ይኑር" የሚለው የቁርዓን አንቀፅ ቤተሰብን ብቻ ሳይሆን ሀገርን ጭምር የሚመለከት ነው፦ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ
*********************

"ሀገራዊ ምክክር" የሚለውን ሀሳብ "በጎ ነገር ሁሉ መልካም ነው" በሚለው ብሂል መሰረት መቀበል ተገቢ ከመሆኑ በተጨማሪ፤"ምክክር" የሚለው ቃል ቁርዓናዊ መሰረት ያለው መሆኑን ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ገለጹ።

የእስልምና ሐይማኖት መምህሩ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ሀገራዊ ምክክር ምርጫ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን በመጥቀስ፤"አላህ በመካከላችሁ ምክክር ይኑር” ሲል የደነገገው ትዕዛዝ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

“በመካከላችሁ ምክክር ይኑር” የሚለው የቁርዓን አንቀፅ ቤተሰብን ብቻ ሳይሆን ሀገርን ጭምር የሚመለከት ነው ብለዋል።

“የእስልምና እምነት ለሰላም የሚሰጠው ዋጋ በጣም ትልቅ ነው፤ ከጌታችን አላህ ምርጥ ስሞች መካከል አንዱ ‘አሰላም’ (ሰላም) የሚለው ነው” ሲሉ አመላክተዋል።

"በየዕለቱ 5 ጊዜ ሰላት ሰግደን (ጸሎት አድርገን) ስናበቃ የምንደመድመው ‘አላህ ሆይ፥ አንተ ሰላም ነህ፤ ሰላም የሚመነጨው ከአንተ ነው’ በማለት ነው፤ ይህ ደግሞ እስልምና ለሰላም ያለውን ትልቅ ቦታ ያሳያል" ነው ያሉት።

ሀገራዊ ምክክሩ አንዱ ተሸናፊ፣ አንዱ አሸናፊ በማይሆንበት መንገድ የሚካሄድ በመሆኑ፤ እንደ እስልምና አስተምህሮ የተበደለ ሰው ይቅርታ ቢያደርግ ትልቅ ይባላል እንጂ አያንስም ብለዋል።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02RrpqG9ESqzkpCNftqhpvrYCXzT7YGZLVdJxjTzXmpuJRJ2voeZFKULBhpAAQBtGBl
Live stream finished (1 day)
አስገራሚ እውነታዎች- ስለ ፅንስ እና እርግዝና
*********

• ፅንስ በማህፀን ውስጥ እያለ ያለቅሳል፤ ፅንሱ ከሚለማመዳቸው ነገሮች ማለትም ከፊት እና ከአፍ እንቅስቃሴ ቀጥሎ አንዱ ማልቀስ ስለሆነ ነው፤ ሆኖም ግን የሽርት ውኃ ውስጥ ባሉ የቅባት እና የጡንቻ ፈሳሾች ምክንያት ድምፁን መስማት አይቻልም፡፡

• ፅንስ ከሰባተኛው ወር ጀምሮ ማሽተት የሚችል ሲሆን በተለይ መጥፎ ሽታን የመለየት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡

• ከ18ኛው ሳምንት ጀምሮ ድምፅ መስማት የሚችሉ ሲሆን፤ ከተወለዱ በኋላ የእናታቸውን እና በተደጋጋሚ የሰሙትን ሰው ድምፅ በፍጥነት መለየት ይችላሉ፡፡

• ፅንስ በማህፀን ውስጥ በሚተኛበት ወቅት ህልም ሊያይ ይችላል፤ ህልሙም በማህፀን ውስጥ ስለሚያውቃቸው ነገሮች ነው፡፡

• ጨቅላ ህፃናት በተወለዱ ከ1 እስከ 2 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይፀዳዳሉ፤ ሆኖም ግን በማህፀን ውስጥ ሊፀዳዱም ይችላሉ፤ ይህም በተፈጥሮ እና የመውለጃ ግዜ በማለፍ ምክንያት የሚከሰት ሲሆን የመፈጠር እድሉም እስከ 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡

• ቁመቷ 1.65 ሜትር እና ከዚያ በላይ የሆነች ሴት መንታ የመፀነስ እድሏ ከፍተኛ ነው፤ይህም ረዘም ያሉ ሴቶች ከጉበት የሚያገኙት የፕሮቲን መጠን ከፍ ያለ በመሆኑ የሚመረተውን ዕንቁላል መጠን ለመጨመር አስተዋፆ ስለሚያደርግ ነው፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid04UXZeuFGczpoZ1ysE5DFTwmwMjiTuCai67ov4v4QfsMzpLr1muQpto1kWvimHut7l
የኮሪደር ልማት ስራዎች
Live stream finished (1 day)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለተሻለ ነገ እናንብብ
ታላቅ የመጻህፍት አውደ ርዕይ  እና ሽያጭ በኢቢሲ ግቢ
Live stream finished (3 hours)