የግል ዋይፋያችን #WiFi እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን?
ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ላሰብነዉ አገልግሎት እየሰጠ ከሆነ ስለ ደህንነቱ ብዙም ትኩረት ስንሰጥ አይስተዋልም፡፡ ይህም በአንድ በኩል ከቸልተኝነት ወይም የሚያስከትለውን ጉዳት በውል ካለመገንዘብ ሲሆን፤ በሌላም በኩል የግል ዋይፋያችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል እውቀትና ግንዛቤ በአግባቡ ካለመያዝም ሊሆን ይችላል፡፡
ከዚህ አኳያ ለዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ሚስጥራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡
በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከጠላፊዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይመከራል፡፡
1. ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ
የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም የግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ “default username” በመቀየር ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡
2. የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /service set identifier - SSID/
እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡
3. አውታረ-መረባችንን መመስጠር
የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡
4. ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging)
ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) ስናደርግ የዋይፋይ ኔትወርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡
5. የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል
የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ ለመጠቀም የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡
6. የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን
ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ስጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡
7. የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት
የራውተራችንን ፋየርዎል /firewall/ ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር ጥቃቶች እራሳችንን መከላከል ያስችለናል፡፡
📌Join and share 👇👇👇
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✦Join➬
🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
tiktok.com/@basiccomputerskills
instagram.com/basiccomputerskills
Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════