Basic Computer Skills
1.9K subscribers
1.23K photos
100 videos
576 files
838 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
Basic Computer Skills
Photo
Telegram Passkey

ቴሌግራም  አካውንታችን ላይ login ለማድረግ የሚያገለግለን የpasskey feature እንዳስተዋወቀ ታውቃላችሁ።

♦️Passkey password-less የsign in መንገድ ሲሆን ባህላዊ የፊደልና የቁጥር የይለፍ ቃሎችን የሚተካ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣንና ቀላል login መንገድ  ነው።

Passkey Public-key cryptographic መንገድ ስለሚጠቀም ከጣትና ከፊት አሻራችን እንዲሁም የscreen ፒንና ፓተርን የተያያዘ private key የቀፏችን ሃርድዌር ላይ ይቀመጣል።

ስለዚህ ማንኛውንም የPasskey feature ያለው አፕሊኬሽን ስልካችን android ከሆነ ከGoogle password manager ጋር iphone ከሆነ ደግሞ ከiCloud Keychain ጋር በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።

♦️Passkey መጠቀም ብዙ ጥቅም አለው።
✔️ፊደል ወይም ቁጥር ስላልሆነ ልንረሳው አንችልም።
✔️ለፊሺንግ ጥቃት የተጋለጠ አይደለም።
✔️ሰርቨር ላይ አይቀመጥም።

አዲስ ስልክ ስንቀይርስ እንዴት login ማድረግ እንችላለን?
አዲስ ስልክ ቀይረን በGoogle አካውንታችን login ስናደርግ ፓስኪን ጨምሮ ሁሉም ከgoogle አካውንታችን ጋር የተገናኙ አካውንቶችን መጠቀም እንችላለን።
ስለዚህ የGoogle አካውንታችንን(Gmail) እንደ አይን ብሌን መጠበቅ ይኖርብናል። እዚጋ መታወቅ ያለበት google አካውንታችን ሃክ ቢደረግ ራሱ የሞላነው Passkey ግን safe ነው።

♦️ይህ የPasskey feature በአዲስም ሆነ በነባር የስልክ ቀፏቸን ላይ ስልክ ቁጥር ማስገባት ሳይጠበቅብን ቴሌግራም አካውንታችን ላይ login ለማድረግ ይጠቅመናል።
ነገር ግን ብዙ ሰው  passkey እና 2-step verification ትዝ የሚለው አካውንቱ ሃክ ከተደረገ በኋላ ነው።

ስለዚህ አሁኑኑ ቴሌግራም አካውንታችንን passkey register ማድረግ አለብን።
ይህን ለማድረግ

Settings -- Privacy and Security -- Passkey

አሁኑኑ አስተካክሉት።

©️
3
3
📚 የ8ኛ ክፍል በቪድዮ የተለቀቁ የትምህርት አይነቶች (ምዕራፎች)

ማስፈንጠሪያዎቹን (ሊንኮቹን) በመንካት ቪድዮዎቹን በቻናሉ ማግኘት ትችላላችሁ!!

📚 Grade 8 General Science: Unit 2 (6 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1398?single

📚 Grade 8 General Science: Unit 3 (2 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1535?single

📚 Grade 8 General Science Unit 4 (11 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1440

📚 Grade 8 General Science Unit 5, 6 and 7 (ሶስቱም ምዕራፎች በአንድ ቪድዮ)

https://t.me/Grade8Info/1901


📚 Grade 8 Social Studies Unit 1 (2 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1480

📚 Grade 8 Social Studies Unit 4 (6 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1895?single

📚 Grade 8 Social Studies Unit 5 (6 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1453

📚 Grade 8 Social Studies Unit 6 (8 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1453

📚 Grade 8 Social Studies Unit 7 (3 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1453

📚 Grade 8 Mathematics Unit 4 (11 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1542

📚 Grade 8 Mathematics Unit 1 - 4 Review Exercise with Explanation (አራቱም ምዕራፎች በአንድ ቪድዮ)

https://t.me/Grade8Info/1908

📚 Grade 8 Citizenship Unit 2 (4 ቪድዮዎች)

https://t.me/Grade8Info/1480

📚 Grade 7 English All Review Questions

t.me/Grade8Info/2120

📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
Part 1

https://t.me/Grade8Info/2121

📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
Part 2

https://t.me/Grade8Info/2123

📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
Part 3

https://t.me/Grade8Info/2124

══════════════
🌟 ውድ ተማሪዎቻችን፣ የልፋታችሁን ፍሬ የምታጭዱበት ወርቃማው ወቅት ቀርቧል! 🌟

​ትኩረታችሁን ሙሉ በሙሉ በንባብ ላይ አድርጉ፤ ጊዜያችሁንም በአግባቡ ተጠቀሙ። አላህ መንገዱን እንዲያገራላችሁና የጣራችሁለትን ስኬት እንዲሰጣችሁ ዱዓችን ነው። 🤲📖
3🤔1
ቴሌግራም ተጠቃሚዎች በሙሉ፤ ጥብቅ ማሳሰቢያ
==============================
(አካውንታችሁ ሀክ ተደርጎ አጸያፊ ነገሮች ከመላካቸው በፊት አሁኑኑ አንብቡት)
||
✍️ ሰሞኑን የብዙ ወንድምና እህቶች የቴሌግራም አካውንት እየተጠለፈ (Hack እየተደረገ) በተለያዩ ግሩፖች፣ ቻናሎች እና በውስጥ መስመር Inbox ላይ አጸያፊ እና ሐራም የሆኑ ሊንኮች በስማቸው እየተላኩ ነው። ይህ ድርጊት የሰዎችን ክብር ከማጉደፍም ባለፈ፣ ወዳጅ ዘመድን ለማያስፈልግ ፈተና እና ለሐራም እይታ እያጋለጠ ይገኛል።

ይህ ሁሉ ችግር ከየት መጣ⁉️
ዋናው የችግሩ ምንጭ ብዙዎቻችን ኦፊሴላዊውን የቴሌግራም መተግበሪያ ትተን ሌሎች ቴሌግራም መሰል የዘ
ሦስተኛ ወገን (Unofficial) አፖችን መጠቀም መጀመራችን ነው። እነዚህ አፖች (ለምሳሌ፦ Nicegram, Mobogram, Vidogram, Plus, Huligram, Telega ወዘተ) የእናንተን የግል መረጃ አሳልፈው ለሌቦች የሚሰጡ አደገኛ መተግበሪያዎች ናቸው።

➤ ቴሌግራም ኩባንያም ይህን በመረዳት እነዚህን አፖች በሚጠቀሙ ሰዎች ፕሮፋይል ላይ "Warning Label" (የማስጠንቀቂያ ምልክት) ማሳየት ጀምሯል። እርምጃ ካልወሰዳችሁ አካውንታችሁ በዘላቂነት ሊዘጋ ይችላል!

እነዚህን አፖች መጠቀም ምን አደጋ አለው?

♦️ የመረጃ ስርቆት፦ የግል ሚስጥራችሁ፣ ፎቶዎቻችሁ እና መልዕክቶቻችሁ በሌሎች እጅ ይወድቃሉ።

♦️ አካውንት መነጠቅ፦ የይለፍ ቃል (OTP Code) በመስረቅ አካውንታችሁን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው፣ በናንተ ስም ወንጀልና ማጭበርበር ይሰራሉ።

♦️ ያለፍቃድ ግሩፕ መግባት፦ ሳታውቁት የተለያዩ የክሪፕቶ፣ የፕሮፖጋንዳ እና የብልግና ግሩፖች ውስጥ ያስገቧችኋል።

መፍትሄው ምንድን ነው? አሁኑኑ ማድረግ ያለባችሁ 3 ወሳኝ እርምጃዎች፦

ትክክለኛውን ቴሌግራም ብቻ ተጠቀሙ:
አሁኑኑ ስልካችሁ ላይ ያሉትን ኦፊሴላዊ ያልሆኑ አፖች (Nicegram, Mobogram...) አጥፉና (Uninstall አድርጉና)፣ ትክክለኛውን በሰማያዊ ምልክት የሚታወቀውን "Telegram" ከፕሌይስቶር ወይም ከአፕስቶር ላይ ብቻ አውርዳችሁ ተጠቀሙ።

አሁኑኑ ሌቦችን ከአካውንታችሁ አስወጡ (Terminate Sessions)
አካውንታችሁ ሀክ መደረጉን ለማወቅ እና ለማስወጣት ይህንን ተከተሉ፦
ወደ ቴሌግራም Settings ግቡ።
Devices (ወይም Privacy and Security ገብታችሁ Active Sessions) የሚለውን ተጫኑ።
እዛ ላይ ከእናንተ ስልክ ውጪ የገቡ ሌሎች መሳሪያዎች (ኮምፒዩተርም ሆነ ሌላ ስልክ) ካያችሁ ወዲያውኑ "Terminate All Other Sessions" የሚለውን ቀይ ጽሑፍ ተጭናችሁ ሁሉንም አስወጡ!

Two-Step Verification አብሩ:
አካውንታችሁን ማንም ሰው እንዳይገባበት በፓስዎርድ ቆልፉት። (Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ገብታችሁ ፓስዎርድ አስገቡ)።

ያላወቀው እንዲያውቅ፣ የተዘናጋውም እንዲነቃ ይህንን ወሳኝ መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ ከስርቆት እና ከሐራም ድርጊቶች እንታደጋቸው!

©️ Murad Tadesse
3
Basic Computer Skills
Photo
📢 የልጆቻችን ስኬት "ሁለገብ" ቀመር

መግቢያ፦

​ውድና የተከበራችሁ ወላጆች፤ ልጆቻችንን ወደ ትምህርት ቤት ስንልካቸው አእምሯቸውን ለዕውቀት፣ ልባቸውን ለሥነ-ምግባር አሳልፈን እየሰጠን ነው። ነገር ግን ትምህርት ቤት ዘሩን የሚዘራበት "ማሳ" እንጂ፣ ፍሬው እንዲበቅል የሚያደርገው ብቸኛው "ዝናብ" አይደለም። እውነተኛው ለውጥ የሚመጣው በትምህርት ቤት የተጀመረው ብርሃን በቤት ውስጥ ባለው የጥናት ሥርዓትና በወላጆች ጥበብ የታከለበት ክትትል ሲታጀብ ከሁሉ በላይ ደግሞ በጌታችን አላህ (ሱ.ወ) እገዛና በረካ ሲባረክ ብቻ ነው።
​ይህ መልዕክት ውጤት ላይ ብቻ ያተኮረውን ጭንቀት ገሸሽ አድርጎ፣ በአላህ ፈቃድ ለልጆቻችን ስኬት መሠረት የሚሆንና የልብ ለልብ ጥሪን የሚያስተላልፍ መመሪያ ነው።

ክፍል 1፦ የትምህርት ቤትና የቤት "ቅንጅታዊ ሚስጥር"
​ትምህርት ቤት መሄድና ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የተማሪን ሕይወት ለመቀየር የመጀመርያው እርምጃ እንጂ የመጨረሻው ግብ አይደለም። ብዙዎቻችን "ውድ ትምህርት ቤት አስገብተን ለምን ለውጥ የለም?" ብለን እንጠይቃለን። እውነታው ግን፤ እውቀት በትምህርት ቤት ተቀምሮ ቤት ውስጥ ካልተከለሰ፣ ልክ እንደ ውሃ ላይ ምስል ቶሎ ይረሳል። ትምህርት ቤት ግብዓትን (Information) ይሰጣል፤ ቤት ደግሞ ያንን መረጃ ወደ እውቀት (Knowledge) እና ወደ ስብዕና (Character) የሚቀይርበት ማብሰያ ኩሽና ነው።
​ያለ ቤት እገዛ ትምህርት ቤት ብቻውን እንዲለወጥ መጠበቅ፣ ያለ ውሃ መሬት ላይ ዘር ጥሎ ፍሬ እንደመጠበቅ ነው። እውቀት በክፍል ውስጥ ይዘራል፣ በቤት ውስጥ ይኮተኮታል፣ በፈተና ወቅት ደግሞ ይታጨዳል። ኮተኮታው (ቤት ውስጥ ያለው ክትትል) ከሌለ ግን አዝመራው እንክርዳድ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው።
♦️ ከዚህም ባለፈ ወላጆች በዓመት አንዴ የካርድ ቀን ብቻ ሳይሆን፣ አልፎ አልፎ ትምህርት ቤት ብቅ እያሉ ከመምህራን ጋር አጫጭር ውይይት በማድረግ የልጆቻቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን በትብብር መከታተል አለባቸው።

🎤 ​ታላቁ ሊቅ ሼይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እውቀት ማለት መረጃን መደርደር ሳይሆን፣ አላህ በልብ ውስጥ የሚጥለውና ወደ ተግባር የሚመራ ብርሃን ነው።" ይህ ብርሃን ደግሞ በወላጅ ፍቅርና ክትትል ካልታጀበ በስተቀር በትምህርት ቤቱ ድካም ብቻ አይመጣም።

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ ለልጄ "ወላጅ" ነኝ ወይስ "ባንክ"? ልጄ ከትምህርት ቤት ሲመጣ የምጠይቀው ስለደኅንነቱ ነው ወይስ ስለ ውጤቱ?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ ዛሬ ማታ ልጃችሁ ሲመጣ ቢያንስ ለ 15 ደቂቃ ስለ ውጤት ሳታነሱ፣ ትምህርት ቤት ውስጥ ስላሳለፈው ስሜትና ስለገጠመው አዲስ ነገር ብቻ በጥሞና አዳምጡት።

ክፍል 2፦ የ"በረካማ ወቅቶች" እና የአእምሮ ፊዚዮሎጂ
​በትምህርት ቤቱ በኩል በኮሙኒኬሽን ደብተራቸው ላይ የተዘጋጀው የጥናት ፕሮግራም ሁለት ወሳኝ ወቅቶችን ታሳቢ ያደረገ ነው። ከሱብሂ በኋላ (ጧት) አእምሮ አዲስ መረጃን ለመቅዳት ንጹሕ ነው፤ ከኢሻዕ በኋላ (ማታ) ደግሞ የዋለበትን ትምህርት በአእምሮው ውስጥ ለማደራጀት (Memory Consolidation) ወሳኝ ሰዓት ነው። አእምሮአችን እንደ ባትሪ ነው። ጧት ላይ ሙሉ ኃይል አለው፤ ማታ ላይ ደግሞ ተሞልቶ (በእንቅልፍ) ራሱን እንዲያድስ ይፈልጋል።
​ሳይንሱ እንደሚነግረን በጧት ክፍለ ጊዜ የአእምሮ ንቃት ደረጃ (Alertness) እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህ ሰዓት የሚጠና ትምህርት በቀላሉ የመያዝ ዕድሉ ሰፊ ነው። ማታ ላይ ደግሞ አእምሮ ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ከመሄዱ በፊት ያነበበውን ነገር እንደ ፋይል የማደራጀት ተፈጥሮ አለው። ልጆቻችን ጧት ተኝተው የሚረፍዱ ከሆነ፣ ቀኑን ሙሉ የዛለና ያልተነቃቃ አእምሮ ይዘው ነው የሚውሉት።

የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
❝አላህ ሆይ! ለኡመቴ በጧት ጊዜያቸው ላይ በረካን አድርግላቸው።❞ [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል]

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የቤቴ ድባብ ለበረካማው የጧት ጊዜ ምቹ ነው? ወይስ ልጆቼ በእንቅልፍ እጦት እየዛሉ ነው የሚነቁት?

ክፍል 3፦ የጥናት ቀመር፦ ጥራት ከሰዓት ይበልጣል
ልጆቻችን እንዲያጠኑ ስንነግራቸው "ለሰዓታት ተቀመጡ" ማለት ሳይሆን "በትኩረት ስሩ" ማለት ነው። በትምህርት ቤቱ የተዘጋጀው የጥናት ቀመር ሳይንሳዊ መሠረት አለው። የአንድ ተማሪ ትኩረት (Attention Span) ውሱን ነው። አእምሮ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፤ ለረጅም ሰዓት ያለ እረፍት ሲሠራ ይዝላል።

◉ በፕሮግራሙ መሠረት ልጆች ማታ ላይ ብቻ ሊያጠኑ የሚገባው የጊዜ እርዝማኔ፦
♦️ 1ኛ እና 2ኛ ክፍል፦ለማታ ጥናት 1፡30 ሰዓት
♦️ 3ኛ እና 4ኛ ክፍል፦ ለማታ ጥናት 2፡15 ሰዓት
♦️ 5ኛ እና 6ኛ ክፍል፦ ለማታ ጥናት 2፡30 ሰዓት
♦️ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል፦ለማታ ጥናት 2፡45 ሰዓት
የፖሞዶሮ (Pomodoro) ቴክኒክ እንደሚያረጋግጠው፣ አእምሮ ለረጅም ሰዓት ካለእረፍት እንዲያጠና ከተገደደ፣ መረጃን ከመቀበል ይልቅ ራሱን መከላከል (Shut down) ይጀምራል። አጫጭር እረፍቶች አእምሮን እንደገና ለማነቃቃት (Brain Reboot) ይረዳሉ። ታዋቂው የፈጠራ ሰው ቶማስ ኤዲሰን እንኳ ለረጅም ሰዓት ከመሥራት ይልቅ አጫጭር እረፍቶችን በመውሰድ ለፈጠራ አእምሮውን ያድስ ነበር። ጥራት ያለው ጥናት ማለት የተቀመጡበት ሰዓት ሳይሆን፣ አእምሮ የተቀበለው እውቀት ነው።

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ መጽሐፍ ከፍቶ ስለታየኝ ብቻ እያጠና ነው ብዬ አምናለሁ? ወይስ የጥናቱን ጥራት እከታተላለሁ?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ በቤታችሁ ውስጥ የጥናት ሰዓት ሲጀምር በሰዓት (Timer) በመታገዝ ልጁ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራና በፕሮግራሙ መሠረት እረፍት እንዲያደርግ አበረታቱት።
♦️ የማታ ጥናቱ እስከ ሦስት ትምህርቶችን ሊያካትት ስለሚችል፣ ልጆች ከላይ የተጠቀሰውን የጊዜ ገደብ አሟልተው ጧት በንቃት እንዲነሱ፤ 1ኛ እና 2ኛ ክፍል ቢበዛ 3:00 ሰዓት ላይ፣ 3ኛ እና 4ኛ ክፍል እስከ 3:30-4:00 ሰዓት ባለው፣ እንዲሁም ከ5ኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪዎች ከ4:00 - 5: 00 ሰዓት ባለው እንዲተኙ ቋሚ ሥርዓት ይዘርጉ።

ክፍል 4፦ "የአቅም ልክ" እና ቁርኣናዊው ፍትሕ
​አንዱ ልጅ በሒሳብ ጎበዝ ሲሆን፣ ሌላው በቋንቋ ወይም በስነ-ጥበብ ድንቅ ይሆናል። ሁሉም ልጅ 100/100 እንዲያመጣ መጠበቅ፣ የተፈጥሮን ሕግ እንደመጋፋት ይቆጠራል። እያንዳንዱ ልጅ የተሰጠው አቅም የተወሰነ ነው። አላህ ሰዎችን የፈጠረው በተለያዩ ችሎታዎችና አቅሞች ነው።
​አንድ ተማሪ ሒሳብ ላይ 60 አምጥቶ ስነ-ጽሁፍ ላይ 95 ካመጣ፣ ያ ልጅ ደካማ ሳይሆን ተሰጥኦው ሌላ ቦታ ነው ማለት ነው። አቅሙን ያላገናዘበ ጫና መፍጠር ልጁ በትምህርቱ ላይ ጥላቻ እንዲያድርበትና በራስ መተማመኑ እንዲጠፋ ያደርጋል። ወላጅ መሆን ማለት የልጁን "ጣሪያ" ማወቅና ከዚያ በላይ አለመጫን ማለት ነው።

​ጌታችን በቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ይላል፦
❝አላህ ማንኛይቱንንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም (አይጭንባትም)።❞ [አል-በቀራህ 2፡286]

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ ልጄን የምመዝነው በራሱ አቅም ነው ወይስ ጎረቤት ካለው ተማሪ ጋር በማወዳደር?
Basic Computer Skills
Photo
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ባለፉት ሦስት ወራት ልጃችሁ የትኛው ትምህርት ላይ የተሻለ ዝንባሌ እንዳለው መዝግቡ። ደካማ በሆነበት ላይ ድጋፍ አድርጉ እንጂ ወቀሳ አታውርዱበት።

ክፍል 5፦ የተሰጥኦ ሚስጥር፦ "እያንዳንዱ ለተፈጠረለት ይገራል"
​እያንዳንዱ ልጅ ለተፈጠረለት አላማ የተመቻቸ ነው። ወላጅ የልጁን ደካማ ጎን ብቻ ከመመልከት ይልቅ፣ ጠንካራ ተሰጥኦውን መፈለግ አለበት። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሶሐባዎቻቸውን የገመገሙት በተለያየ መስክ ነበር። አቡበክር (ረ.ዐ) በለገስነታቸው፣ ዑመር (ረ.ዐ) በጥንካሬያቸው፣ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ በጦር መሪነታቸው እንደተመሰገኑት ሁሉ፤ የእናንተም ልጅ ነገ ለዓለም የሚተርፍበት የራሱ መስክ ይኖረዋል።
​ሳይንቲስቱ አልበርት አንስታይን እንዲህ ይላል፦ "ሁሉም ሰው ሊቅ ነው፤ ነገር ግን አንዲትን አሳ ዛፍ ላይ የመውጣት ችሎታዋን መለኪያ አድርገህ ብትመዝናት፣ እድሜዋን ሙሉ ጅል እንደሆነች አስባ ትኖራለች።" የልጃችሁን የ"ዋናተኛነት" ተፈጥሮ ሳታዩ ለምን እንደ ዝንጀሮ ዛፍ ላይ አልወጣህም ብላችሁ አትውቀሱት።
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
❝ስሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ለተፈጠረለት ነገር የተገራ/የተመቻቸለት ነው።❞ [ቡኻሪና ሙስሊም]

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የልጄ "የተገራለት" (ተፈጥሯዊ) ዝንባሌ ምንድነው? እኔስ እሱን ለማሳደግ ምን አድርጌያለሁ?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጁ ከትምህርት ውጪ የሚያሳያቸውን የፈጠራ ስራዎች በጥሞና ተከታተሉና አድናቆት ስጡ።

ክፍል 6፦ የኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) የትምህርት ፍልስፍና
​የልጆቻችንን አቅም እንዴት መገምገም እንዳለብን ሊቃውንት ትልቅ ጥቆማ ሰጥተውናል። ትምህርት ማለት የመረጃ ጭነት ሳይሆን የተሰጥኦ ጥበቃ ነው። የልጁን ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ማስተዋልና እሱን ማሳደግ ከሁሉ በላይ ዋጋ አለው።
​ሳይንቲስቱ ሃዋርድ ጋርድነር "የብዝሃ-እውቀት" ቲዎሪውን ሲያቀርብ፣ ሰው በስምንት የተለያዩ መንገዶች ሊቅ ሊሆን እንደሚችል አረጋግጧል። ሒሳብ ላይ 100 ያላመጣ ልጅ በንግግር፣ ከሰው ጋር በመግባባት ወይም በቴክኖሎጂ አቻ የሌለው ሊቅ ሊሆን ይችላል።
🎤 ​​ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጅ የልጁን የተፈጥሮ ዝንባሌ ማስተዋል አለበት። ልጁ ዝንባሌ በሌለው ትምህርት በግድ እንዲወጠር ማድረግ የለበትም። ዝንባሌውን ያገኘ ልጅ በዚያ መስክ የላቀ ይሆናል፤ የማይወደውን የተጫነ ግን ሁለቱንም ያጣል (አዲሱንም አያውቅም፣ የራሱንም ተሰጥኦ ይገድላል)።"

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ የምገነባው የልጄን ስብዕና ነው ወይስ የእኔን ያልተሳካ ህልም በእሱ ላይ ለመጫን እየሞከርኩ ነው?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጃችሁ የማይወደውን ትምህርት ለምን እንደማይወደው በረጋ መንፈስ ጠይቁት። ችግሩ ከተፈጥሮ ዝንባሌ ከሆነ አማራጭ መንገዶችን ፈልጉ።

ክፍል 7፦ "ጥረት" ከ "ውጤት" ይበልጣል
​እንደ ወላጅ ትኩረታችን መሆን ያለበት ልጆቻችን ባመጡት "ቁጥር" ላይ ሳይሆን፣ ባሳዩት "ጥረት" ላይ ነው። ውጤት በብዙ ነገሮች ሊለዋወጥ ይችላል፤ ጥረት ግን ቋሚ ስብዕና ነው። ቶማስ ኤዲሰን መብራትን ከመፍጠሩ በፊት 10,000 ጊዜ ወድቆ ነበር። እናቱ ግን "ውድቀት" ብላ አልጠራችውም፤ "ለመስራት የማይችሉ 10,000 መንገዶችን አገኘህ" ብላ አበረታታችው እንጂ። ዛሬ በጥረት ያገኘው 80፣ ነገ ወደ 100 ያደርሰዋል። ጥረትን ማድነቅ ተማሪው ተስፋ እንዳይቆርጥ ያደርገዋል።
🎤 ​ኢማም አሽ-ሻፊዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እውቀት ማለት መረጃን በቃል መያዝ ሳይሆን፣ ለተግባር የሚጠቅመውና ሰውን የሚቀይረው ነው።"

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ ዛሬ ቢለፋም ውጤቱ ባይመጣ፣ ጥረቱን አይቼ "አይዞህ" እለዋለሁ? ወይስ "ጊዜዬን አባከንክ" ብዬ እገስጻለሁ?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ "100 ስላመጣህ ጎበዝ ነህ" ከማለት ይልቅ "ዛሬ 40 ደቂቃ ሙሉ በጥሞና ስላጠናህ ኩራት ይሰማኛል" የሚለውን አገላለጽ ተጠቀሙ።

ክፍል 8፦ የቤት ድባብ፦ የዕውቀት ቤተ-ሙከራ
​ቤት የዕውቀት ድባብ ከሌለው ትምህርት ቤት የሰጠው እውቀት ይከስማል። እናንተ ስልካችሁን እያያችሁ ልጁን "አጥና" ብትሉት ውጤት የለውም። የልጁ አርአያ እናንተ ናችሁ። ልጁ በሚያጠናበት 40 ደቂቃ ውስጥ እናንተም መጽሐፍ ወይም ቁርኣን በመያዝ የንባብ ድባብ ፍጠሩ። ቤቱ የቲቪና የስልክ ጫጫታ ከሆነ፣ የልጁ አእምሮ በትምህርቱ ላይ ሊያተኩር አይችልም።
♦️ በተጨማሪም የጥናት ቦታው አካላዊ ዝግጅት ወሳኝ ነው። ልጆች አልጋ ላይ ተኝተው እንዳያጠኑ ማሳሰብ ይገባል፤ አእምሮ አልጋን ከእንቅልፍ ጋር ስለሚያያይዘው ትኩረት ይበተናል። ጸጥታ ያለበት፣ በቂ ብርሃንና ንጹህ አየር ያለው ማዕዘን ለጥናት ሊመደብላቸው ይገባል።
🎤 ​ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጅ ለልጁ ምሳሌ የሚሆን ተግባር ካላሳየ ምክሩ ብቻውን ፍሬ አያፈራም።"

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ቤቴ የዕውቀት ማዕከል ነው ወይስ የመዝናኛ ስፍራ? ልጆቼ ሲያጠኑ እኔ ምን እያደረግኩ ነው?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ የጥናት ሰዓት ሲጀምር በቤቱ ውስጥ ያሉ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን (ቲቪ፣ ስልክ) በሙሉ ለተወሰነ ሰዓት የመዝጋት ልማድ አዳብሩ።

ክፍል 9፦ ስሜታዊ ደኅንነት፦ የመማር ቁልፍ
​አእምሮ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ሲሆን የመማር አቅሙ ይዘጋል። ልጆች በትምህርታቸው ውጤት ካላመጡ ምናልባት ውስጣቸው ሰላም አጥቶ ሊሆን ይችላል። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ለልጆች የነበራቸው ርህራሄና ፍቅር ልባቸውን እንዲከፍቱ ያደርጋቸው ነበር። ፍቅርና መረጋጋት ባለበት ቤት ውስጥ ተማሪው የትምህርት ቤት ፕሮግራሙን ለመተግበር አይቸገርም።
♦️ ልጆች ውጤት ሲቀንስባቸው ቤት ውስጥ የሚኖረው መሸማቀቅ (ፍርሃት) ለቀጣይ ውድቀት ይዳርጋቸዋል። ከስህተት መማር እንደሚቻል ማሳየት ያስፈልጋል። በተለይም ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ባለው የዕድሜ እርከን (በተለይ ወደ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ሲጠጉ) የራሳቸው የሆነ ስሜታዊ ሽግግርና የጓደኛ ግፊት ውስጥ ስለሚገቡ፣ ወላጅ "አዛዥ" ከመሆን ይልቅ "አማካሪ እና ጓደኛ" መሆን አለበት። ልጆቻችሁን "ለምን አልመጣህም?" ብላችሁ ከመውቀሳችሁ በፊት፣ "ለማጥናት ምን ጎደለህ/ሽ? ምን የሚያስጨንቅሽ ነገር አለ?" ብላችሁ በጥበብ ጠይቁ።

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ እኔን የሚያየኝ እንደ "አስፈሪ ዳኛ" ነው ወይስ እንደ "አጋዥ ደጋፊ"?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ በሳምንት አንድ ቀን ከትምህርት ውጪ በሆነ ጉዳይ ላይ ከልጃችሁ ጋር ብቻችሁን ጊዜ አሳልፉ።

ክፍል 10፦ የቴክኖሎጂ እና የስክሪን አስተዳደር
​በአሁኑ ዘመን የወላጆች ትልቁ ፈተና ቴክኖሎጂ ነው። ስልክ፣ ጌም እና ቴሌቪዥን የልጆችን ጊዜና ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ ይሰርቃሉ። ነገር ግን ቴክኖሎጂን ከማጥፊያነት ወደ ማሳደጊያ መሣሪያነት መቀየር ይቻላል። ለምሳሌ ለጥናት የሚረዱ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን እንዲያዩ በማድረግ በሥርዓት እንዲጠቀሙ መምራት ያስፈልጋል። ቴክኖሎጂን ያለ ገደብ መልቀቅ የልጆችን ተፈጥሯዊ የመማር ፍላጎት ያደነዝዛል።

⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የቤቴ ቴክኖሎጂ ልጆቼን እያሳደጋቸው ነው ወይስ ትኩረታቸውን እየሰረቀ?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጆች ስክሪን የሚያዩበትን ሰዓት ገደብ በማውጣት፣ ከትምህርት ጋር የተገናኙ ጠቃሚ ይዘቶችን ብቻ እንዲከታተሉ መምራት።
Basic Computer Skills
Photo
ክፍል 11፦ ማጠቃለያና የነፍስ ቃል
​ውድ ወላጆች፤ ልጆቻችን የአላህ አማናዎች ናቸው። በትምህርት ቤታችን የተሰጠው የጥናት መርሐ ግብር (Schedule) እናንተን ለማገዝ የተዘጋጀ "ካርታ" ነው። ይህን ካርታ በፍቅር፣ በትዕግስትና በእምነት ተጠቀሙበት። የልጆቻችሁን ልዩ ተሰጥኦ እዩላቸው፣ ጥረታቸውን አድንቁላቸው። ዛሬ የምታሳዩአቸው ርህራሄና የምትሰጧቸው ማበረታቻ፣ ነገ ለሚገነቡት ታላቅ ስብዕና ዋነኛው ግብዓት ነው።

​➤ የድርጊት ቃል ኪዳን፦ ይህን መልዕክት ካነበባችሁ በኋላ፣ ዛሬውኑ ማታ ከልጆቻችሁ ጋር አዲስ የፍቅርና የክትትል ምዕራፍ ጀምሩ።


🌸 አላህ ይርዳችሁ እና ትምህርታችሁንም ይባርክላችሁ። ዛሬ የምታደርጉት እያንዳንዱ ትንሽ ጥረት ነገ ብሩህ ስኬት ይሆናል! 🌸 🤲  🤲

━━━━━━━━━━━━━━
📢 ለልጆቻችን ስኬትና ብሩህ ተስፋ!

ይህ መመሪያ በአላህ ፈቃድና እገዛ የልጆቻችንን ሁለገብ ስኬት ለማገዝ የቀረበ አነስተኛ ጥረት ነው። ሁሉም ስኬት የሚገኘው በአላህ ፈቃድ ነውና፣ ይህ መልዕክትም ለልጆቻችን እድገት ሰበብ እንዲሆንልን እንመኛለን።
መልዕክቱ 11 ወሳኝ ክፍሎችን የያዘ በመሆኑ ረዘም ሊል ይችላል፤ ሆኖም እያንዳንዱ ነጥብ ለልጆቻችን ስኬትና ሥነ-ምግባር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ የታሰበ ነው። ኢንሻአላህ!!

💡 ትኩረት ለልጆቻችን ስኬት፦ እነዚህን ነጥቦች በአግባቡ ለማደራጀትና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ረጅም ሰዓታት ቢፈጁም፤ እናንተ ለልጆቻችሁ ስኬት ሲባል ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥታችሁ አስራ አንዱንም ክፍሎች ብታነቧቸው፣ በአላህ ፈቃድ ለትልቅ ለውጥ መነሻ ይሆናል።

መልካም ንባብ!
━━━━━━━━━━━━
🌈✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈
ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App
FLEX PDF READER

🔶 Group PDF files together
🔶 Table of contents
🔶 Merge multiple PDFs
🔶 Split PDF
🔶 Add watermark
🔶 Images to PDF
🔶 PDF to Image
🔶 Lock PDF
🔓 PDF
🔶 Create Bookmarks
🔶 Search PDFs
🔶 Dark and light mode

Install 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.smartpdf.reader
4
ጥቆማ
=====
✍️ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ! ማለፍ የሌለባችሁ ወርቃማ የስታርታፕ ዕድል!

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) በአይነቱ ልዩ የሆነውን የስታርታፕ (Startup) ድጋፍ 2ኛ ዙር ምዝገባ ይፋ አድርጓል።

ባለፈው በመጀመሪያው ዙር የገቡት ከ200 በላይ ልጆች ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑና በወረቀት ላይ የነበረ ሃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ቢዝነስ እንደቀየሩ አይተናል። አሁን ደግሞ ይበልጥ ሰፍቶ እና አዳዲስ ድጋፎችን አካቶ መጥቷል።

እንደ ወንድም ልምከራችሁ፡- ምናልባት "ገና እኮ ሞዴል ትሬይን (Train) አድርጌ አልጨረስኩም" ብላችሁ ወደኋላ እንዳትሉ። ማቅረብ ያለባችሁ ፕሮጀክት ከኤአይ (AI) ጋር የተያያዘ መሆን አለበት እንጂ፣ የግድ የተጠናቀቀ ሞዴል
ይዛችሁ ቅረቡ አይባልም። ከሃሳብ እና ከፕሮቶታይፕ (Prototype) ጀምሮ ይዛችሁ መግባትና መወዳደር ትችላላችሁ።

መድረኩን ካገኛችሁ በራስ መተማመን ሃሳባችሁን በሚገባ አስረዱት (Pitch it well)፤ በደስታ ነው የሚቀበሏችሁ።

ይሄ ፕሮግራም ዝም ብሎ ማዳመጥ ብቻ አይደለም፤ ከሃሳብ ጀምሮ፣ እውን አድርጋችሁት፣ ከዛ ጋር የተያያዘ ፈንድ (Funding) አግኝታችሁ፣ ተግባር ላይ የሚውል ፕሮዳክት እስኪሆን ድረስ አብረዋችሁ ሆነው ያግዟችኋል።

በተለይ ይሄ እድል ለነማን ነው አሪፍ? በኤአይ (AI) ዘርፍ ላይ ፈጠራ አስባችሁ ነገር ግን መስሪያ ቦታ (Workspace)
ላጣችሁ ስታርታፖች፣ የኤአይ ሞዴሎችን ትሬይን የምታደርጉበት አቅም ያለው ኮምፒውተር/ጂፒዩ (GPU) ለሌላችሁ፣ እንዲሁም
ለዲፕሎይመንት (Deployment) ለተቸገራችሁ ወጣቶች... ይሄ እድል ፈፅሞ ሊያመልጣችሁ አይገባም!

🎯 የትኞቹ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ይቻላል? በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በሮቦቲክስ፣ በኤ.አይ ኤጀንት
(AI Agent)፣ እንዲሁም በቨርችዋል እና ኦግመንትድ ሪያሊቲ (VR/AR) ዘርፎች ላይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ ሁሉ መሳተፍ ትችላላችሁ።

የምዝገባ ጊዜ፡- ከሚያዚያ 15፣ 2018 እስከ ግንቦት 06፣ 2018 ብቻ! (ቀኑ እየሄደ ነው ቶሎ በሉ)

🔗 ለማመልከት፡- ይህን ድረ-ገፅ ይጠቀሙ ▶️ aistartup.aii.et

የፈጠራ ሃሳብዎን ወደ ተጨባጭ ምርት፣ ህልምዎን ወደ እውነታ የሚቀይሩበት ጊዜ አሁን ነው። በድጋሚ እላለሁ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ!

ለሌሎች ጓደኞቻችሁም እንዲደርሳቸው ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!

||

©️ STEMwithMurad
3
Claude AI ያለVPN መስራት ጀምሯል መጠቀም ትችላላችሁ።
አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም።

Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።
Basic Computer Skills
Photo
🌟 የተስፋ ኃይል፡ የፍርሃትን ገበያ የሚያከስረው "አንዱ" ምክንያት! 🌟

🔶 የፍርሃት ገበያ ላይ ተስፋ ለመቁረጥ ሺህ ምክንያቶችን ልናገኝ እንችላለን... ነገር ግን ተስፋ ላለመቁረጥ አንድ ምክንያት በቂ ነው!!

​በዙሪያችን ያለው ዓለም አንዳንዴ "የፍርሃት ገበያ" ይመስላል። በዚህ ገበያ ውስጥ ውድቀት፣ ጥርጣሬ፣ ሰነፍ ጓደኞች እና "አትችሉም" የሚሉ ድምፆች በብዛት ይቸበቸባሉ። ተስፋ እንድንቆርጥ የሚያደርጉ ሺህ ምክንያቶች እንደ ሸቀጥ ተደርድረው "ግዙን" ይሉናል። ነገር ግን እኛ በዚህ ገበያ ውስጥ ገብተን ተስፋ መቁረጥን አንገዛም!
​ታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) የልብንና የተስፋን ሚዛን እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል፦

​"ልብ ወደ አላህ በሚያደርገው ጉዞ ልክ እንደ ወፍ ነው፤ አላህን መውደድ ጭንቅላቱ ሲሆን፣ ፍርሃትና ተስፋ ደግሞ ሁለት ክንፎቹ ናቸው።"

​ወፍ በአንድ ክንፍ መብረር አትችልም። ፍርሃት ብቻውን ሲነግስ ሽባ ያደርገናል። ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ክንፋችንን ሰብሮ መሬት ላይ ይጥለናል፤ ጉዞአችንንም ያሰናክላል። ስለዚህ በሺህ የፍርሃት ምክንያቶች መካከል ያችን "አንዲት" የተስፋ ክንፋችንን አጥብቀን መያዝ አለብን።
​ያች ተስፋ እንዳንቆርጥ በቂ የሆነችው "አንዲት ምክንያት" ምንድን ናት? እርሷማ ከአላህ ዘንድ የሚመጣው ድልና እገዛ ናት! አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርኣኑ ውስጥ የፍርሃታችንንና የጭንቀታችንን ግንብ እንደ ሚሳኤል ግቡን በሚመታ ቃል እንዲህ ይፈታዋል፦

​"ከችግርም ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።" (አሽ-ሸርህ፡ 5)

​ይህ አንቀፅ የሚነግረን ችግርና ምቾት አይለያዩም፤ አብረው ናቸው። ፈተናው ሲመጣ መፍትሄውም አብሮ ተልኳል። ይህን ካወቅን ተስፋ ለመቁረጥ ሺህ ምክንያቶች ቢደረደሩልንም፣ "አላህ ከመከራው ጀርባ ድልን ደብቆልናል" በሚል አንዲት ምክንያት ሁሉንም እናሸንፋለን።
​ለስኬታችን ደግሞ እንደ ሰይፍ የሳለ እና ተግባራዊ ሰዎች የሚያደርገንን የአላህ መልክተኛ (ﷺ) መመሪያ እንያዝ፦

​"የሚጠቅምህን ነገር ለማግኘት ጉጉት ይኑርህ፣ በአላህም ተመካ፣ አቅመ-ቢስም አትሁን (ተስፋ አትቁረጥ)።" (ሶሂህ ሙስሊም)

​ይህ ሀዲስ ዝም ብለን ለተቀመጥን ሰዎች አይደለም። የሚጠቅመንን (ትምህርታችንን፣ ስራችንን፣ ራዕያችንን) ለማሳካት እንደ ውሃ ጠጥተነው በውስጣችን ሊሰርፅ የሚገባ የጥንካሬ ቀመራችን ነው። "አቅመ-ቢስ አትሁን" የሚለው የአላህ መልክተኛን (ﷺ) ቃል ተስፋ መቁረጥንና መሸነፍን ሙልጭ አድርጎ የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።
​ብዙዎቻችን ፈተና ሲበዛብን አላህ የረሳን ይመስለናል። ነገር ግን ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

​"ፈተናዎች ወደ አላህ የሚያቃርቡህ ከሆነ ካንተ የተሰወሩ ፀጋዎች ናቸው።"


🚀 ከፍርሃት ገበያ ወደ ተስፋ ሜዳ የምንሸጋገርባቸው 3 እርምጃዎች፦

​አሁን ካለንበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ወጥተን ወደ ስኬት ጎዳና ለመመለስ እነዚህን ሦስት ተግባራዊ ነጥቦች በጋራ እንተግብራቸው፦

❶ ​ልባችንን እንጠግን፦ በየቀኑ ፈጣሪያችንን በማውሳት (ዚክር) የፍርሃትን ድምፅ እናጥፋው። አላህ እንዲህ ይላልና፦ "ልቦች አላህን በማውሳት ይረካሉና።" (አር-ራዕድ፡ 28)። የልብ መርጋት የተስፋ መጀመሪያ ነው።

❷ ​አካባቢያችንን እንመርምር፦ ሁሌም "አይቻልም" የሚሉንንና ተስፋችንን የሚሰርቁንን "የፍርሃት ነጋዴዎች" እንራቃቸው። በተስፋ ከሚሞሉን፣ ራዕይ ካላቸውና አብረውን ከሚተጉ ሰዎች ጋር እንቀላቀል።

❸ ​በትንሿ እርምጃ እንጀምር፦ ትልቁን ተራራ አይተን አንደንግጥ፤ ዛሬ መራመድ የምንችላትን አንዲት እርምጃ ብቻ እንራመድ። ግቡ ላይ ለመድረስ ሺህ ኪሎ ሜትር መጓዝ ካለብን፣ በዛሬዋ አንዲት እርምጃ መጀመር ግድ ይለናል። የተቀረውን ለፈጣሪያችን እንተው!

♦️​የመጨረሻ መልዕክታችን፦
ትላንት የተሳሳትንባቸው ስህተቶች፣ ዛሬ የገጠሙን መሰናክሎች እና ነገ የሚመጡት ስጋቶች በሙሉ የፍርሃት ገበያ ሸቀጦች ናቸው። እኛ ግን ከእኛ ጋር ያለውን ጌታ፣ ውስጣችን ያለውን አቅም እና ከፊታችን ያለውን ብሩህ ቀን እናስብ። ያ "አንዱ ምክንያት" ሺህ የፍርሃት ሰራዊትን ለማሸነፍ በቂ ነው!

​ተስፋ አንቁረጥ! ጉዞአችንን እንቀጥል!
━━━━━━━━━━━━
🌈✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈
3
ስለClaude AI ሙሉ ኮርስ በነፃ መውሰድ ከፈለጋችሁ (በተለይ ዴቨሎፐሮች) በዚህ link ተመዝግባችሁ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ።
https://anthropic.skilljar.com/claude-101


©️
📚በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ል የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ሴሚስቴር ሞዴል ፈተና ፕሮግራም!

🔴 የ6ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 ዓ.ል ይሰጣል!

🔴 የ8ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እና 11
/2018 ዓ.ል ይሰጣል!

🔴 የ12ኛ ክፍል: ግንቦት 10 እስከ 12/2018 ዓ.ል የሚሰጥ ይሆናል!


መልካም  ፈተና!!

━━━━━━━━━━━━
ከእያንዳንዱ ጥረት ጀርባ የስኬት አሻራ አለና ጥረታችሁን መቼም አታቁሙ።

🤲 አላህ ይርዳችሁ፤ ብሩህ ስኬትን ይወፍቃችሁ! 🤲