Basic Computer Skills
1.9K subscribers
1.23K photos
100 videos
576 files
837 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
#The End!
📍ሳይንስን በስልካችን📍

- በእጆቻችን ላይ የሚገኙ ስማርት ስልኮቻችን ብዙ ነገሮችን እንድንከውን በሚያስችሉን ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች የተሞሉ ናቸው፡፡
- ታድያ ስልካችንን ለፎቶ ማንሳት እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ፍጆታ ከማዋል ባለፈ ተከታዮቹን መተግበሪያዎች ተጠቅመን ሳይንስን በተለየ መነፅር መመልከት እንችላለን፡፡

1. #eBird
- በስነ-አዕዋፍ (Ornithology) ጥናት ላይ በተሰማራ ቤተ-ሙከራ የሚተዳደረው ይህ መተግበሪያ የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንድናውቅና እንድንመረምር ከማስቻል ባለፈ ከዘርፉ ተመራማሪዎች ጋር ጭምር መረጃውን እንድንለዋወጥ ያደርገናል፡፡ በመተግበሪያው አድራሻችንን በማስገባት በዙሪያችን ያሉ ዝርያዎችን ማየት ስንችል የወፍ መገኛ ስፍራዎች ላይ በአጋጣሚ ከተገኘንም ያሳውቀናል፡፡ ታድያ ከበይነ መረብ ውጪም ስለሚሰራ ገጠራማ ቦታዎች ላይ አንቸገርም፡፡

2. #Star_Walk
- Star Walk በአመሻሹ ሰማይ ካሜራችንን ወደ ከዋክብት እንድናማትር በማድረግ ብቻ በእይታችን ስለገቡትን ከዋክብት እና ፕላኔቶች ገለፃ ያደርግልናል፡፡ ከማርስ የፀሐይ መውጫና መጥለቂያ ሰዓት አንስቶ እጅግ የበዙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ያቀብለናል፡፡

3. #NASA_Globe_Observer
- ይህ መተግበሪያ ከቀድሞዎቹ በተለየ ወደ ረጂነት ይለውጠናል፡፡ በዳመና ሽፋን፣ መሬት ሽፋን እና ወባ ትንኝ ዙሪያ መረጃን የሚሰበስብ ሲሆን እኛም ቢሆን የምንመለከተውን ዳመና ፎቶ በማንሳት ለናሳ እንድናደርስና የአየር ፀባይን በመረዳት ረገድ ሚና እንድንጫወት ያደርገናል፡፡

4. #MyShake
- ለምርምር ታስቦ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሰራ ሲሆን በዙሪያችን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴዎችን ያሳውቀናል፤ እኛ ላይ ቢከሰቱ ምን ማድረግ እንዳለብንም ይነግረናል፡፡ ሌላኛው የዚህ መተግበሪያ ስራ ስልካችን ላይ ተፅዕንዖ ሳያደርስ ያለንበትን ስፍራ የመሬት መንቀጥቀጥ ሁናቴ በመገምገም ምሁራኑ ግምቶችን እንዲያስተካክሉና ህይወትን እነዲያድኑ መረጃ ያቀብላል፡፡

5. #The_Elements (በክፍያ)
- iOS በሚጠቀሙ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲሆን Periodic Table ላይ የሚገኙትን ንጥረ-ነገሮች አካላዊ ቅርፅ ከመረጃ ደብሎ ያደርሰናል፡፡ ለምሳሌ እያንዳንዱን ንጥረ-ነገር ዙሪያውን ባሻን አቅጣጫ እንድንቃኝና ብሎም ስለ ይዘቱ፣ የግኝት ታሪኩ፣ ጥቅሙ፣ የገበያ ዋጋው ወዘተ… ጥልቅ ትንታኔ ይሰጠናል፡፡

6. #Wolfram_Alpha (በክፍያ)
- በድረ-ገፁ አማካኝነት የምናገኘው ይህ መተግበሪያ የፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ቀመሮችን፣ የቁሶችን ይዘት፣ የምድራችን ንብርብሮችን መረጃ፣ የከዋክብት ካርታን እና ሌሎች መረጃዎችን ያቀርብልናል፡፡ በተጨማሪም ውስብስብ የሂሳብ ኢኩዌዥኖችን የማስላትና የአየር ሁኔታንም የማሳወቅ ስራ ይሰራል፡፡

7. #Science_Journal
- ይህ የጎግል ምርት በዙሪያችን ያሉ ሁቴዎችን እንድንመዘግብ ያደርገናል፡፡ ለምሳሌ፡- የስልካችንን ሴንሰሮች በመጠቀም ብርሃን፣ ድምፅ፣ ግፊት፣ እንቅስቃሴን ያነባል፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት ከሌሎች ማሳሪያዎች ጋር በመቀናጀትም ይሰራል፡፡ ውጤቶችን በፎቶና ፅሁፍ ሲያስቀርልን እነዚህን መረጃዎች ወደ ሌሎች መሳሪያዎች በማስተላለፍ መጠቀም እንድንችልም ያደርገናል፡፡
     


Join and share 👇👇🏾👇🏿

🤲 Share for others

➡️Our channel

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

Tiktok: tiktok.com/@basiccomputerskills

Instagram: instagram.com/basiccomputerskills

YouTube: YouTube.com/@BasicComputerSkill

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
Google official የፍለጋ ውጤቶችን (search result) verify ማድረግ ሊጀምር ነው፡፡

አንድ ሰዉ Google ላይ መረጃ Search ሲያደርግ የተለያዩ የፍለጋ ውጤቶች ይመጡለታል። እነዚህ ውጤቶች በውስጣቸው ታማኝነት ያለው መረጃ ይኑራቸው አይኑራቸው ማወቅ አይቻልም። ይህን ለመለየት ይረዳ ዘንድ Google  ታዋቂ ድረ ገፆችን የፍለጋ ውጤት ላይ የVerity ምልክት () ለማድረግ ዕቅድ ይዟል።

በየዓመቱ ብዙ ሰዎች ተመሳሰለው በሚሰሩ ድረ ገፆች ይታለላሉ። በተለይ የonline Shopping ድረ ገፆች ለዚህ በጣም ተጠቂ ናቸው። ስለዚህ Google ይህን ነገር መጀመሩ የonline መጭበርበርን ለመከላከል ይረዳል።

ይህ ፊቸር ለጊዜው ሙከራ ላይ ያለ በመሆኑ መቼ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚሆን Google ያለው ነገር የለም።

source: #The_Verge
👍4