✴️ ቨርቹዋል ሪያሊቲ -1-
🚩ምናባዊ ምስለ-እውነታ - ቨርቹዋል ሪያሊቲ (Virtual Reality)(VR)
🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ማለት አሁን ካለንበት የገሀዱ ዓለም አውጥቶ ወደ ሌላ የዲጅታል ዓለም የሚዘፍቅ (Immerse) አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው።
🚩ለምሳሌ እናንተ ቤታችሁ ውስጥ ናችሁ እንበል ወይም ቢሮ ውስጥ ወይም ታክሲ ውስጥ ናችሁ...ወዘተ....ባጭሩ አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በህይወታችሁ "ባየሁት!" ወይም "ባደረኩት!" ብላችሁ ወደ ምትመኙት ዓለም መጓዝ ብትመኙስ? ወይም
🚩አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በአራዊቶች የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ መሆን ብትፈልጉስ? ሜድትራኒያን ባህር ውስጥ ከሻርኮች ጋር መዋኘት ብትመኙስ?....ወይም ደግሞ አውሮፕላን ማብረር ብትፈልጉ...
🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ካላችሁበት ዓለም ሳትንቀሳቀሱ ወደ ተመኛችሁት ዓለም የሚወስድ እጅግ አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው። ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት እንደ መነፅር ዓይናችን ላይ የምናጠልቀው መሳሪያ (Head-mounted Device) ያስፈልገናል።
Part 1
════❁✿❁ ═════
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍 ተስፋ
✅ ከዊልቸር ሌላ መንቀሳቀሻ አማራጭ የሌላቸው ህጻናት እንዲራመዱ ለማስቻል እየተሰራበት ስለሚገኘው ቴክኖሎጂ ጥቂት እናካፍላችሁ፡፡

📍 ንስር
✅ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምን መፍትሔ ይኖረው ይሆን?

✳️ የሰዎችን ድምጽ በማዳመጥ በልብ ድካም የመጠቃት እድልን የሚያሰላው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት
🚩በተዘጉ የደም ቧንቧዎች ምክንያት ከፍ ያለ ቀጭን ድምጽ ያላቸው ሰዎች የልብ ችግሮች ሊገጥሟቸው እንደሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓትን ተመስርተው ተመራማሪዎች አሳወቁ፡፡
🚩ተመራማሪዎቹ የልብ ደም ስሮቻቸውን ሁኔታ ለመገንዘብ ኤክስ ሬይ የታዘዘላቸውን መቶ ስምንት ታማሚዎች በመመልመል ቮካሊስ ሄልዝ በተባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የስልክ መተግበሪያ ላይ የሰላሳ ሰከንድ የድመጽ ናሙና እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡
🚩በሦስት የተለያዩ ደረጃዎች ወደመተግበሪያው የሚቀዱት የድምጽ ናሙናዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ ተተንትነው ከውጤት አመላካች ጋር ይቀርባሉ፡፡
🚩አስር ሺህ የድምጽ ቅጂዎች ሥርዓቱን ለማሰልጠን አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት በዘገባው አመላክቷል፡፡
🚩ሥርዓቱ ሰማንያ አይነት የድምጽ ሁኔታዎችን መገንዘብ እንደሚችልና ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ የልብ ደም ስር መዘጋት ችግርን አመላካች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
🚩በተመራማሪዎቹ ገለጻ የሰው ልጆች ጆሮ እና አዕምሮ የማይለይለዩትን የድምጽ ሁኔታ ቴክኖሎጂው በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት ሊቆጠሩ ወደሚችሉ የውጤት መግለጫዎች በመቀየር ማስቀመጥ እንደቻለ አብራርተዋል፡፡
🚩በአሜሪካ የማዮ ክሊኒክ ባልደረባ እና ምርምሩን የመሩት ዶ/ር ጃስክንዊል ሳራ እንደተናገሩት ምርምሩ ሐኪሞችንም ሆነ በተግባር ላይ ያሉ የልብ ምርመራ መንገዶችን ለመተካት ያሰበ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከተለመዱት መንገዶች ጋር አጣምሮ ለመጠቀም ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ነው፡፡
#የቴክኖሎጂ_ዜና
#Technology_News
©Technology Master Page
════❁✿❁ ═══════

በጽሁፍ ውስጥ የተደበቁ ስሜቶችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመግለጽ ብልሀት
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና የስልተ-ቀመሮች ዕውን መሆን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አድካሚ የዳታ ትንተና ሂደቶችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል ሴንቲሜንት አናሊስስ #SentimentAnalysis ይጠቀሳል፡፡ ይህ ሥርዓት በአገልግሎት እና ምርት አቅራቢነት ወይም ከደምበኞች ጋር በተለያየ ምክንያት የሚያገናኝ ሥራ ያላቸው ተቋማት የደምበኞቻቸውን ግብረ-መልስ እውነተኛ ትርጉም ወይም ስሜት የሚረዱበት አንዱ መንገድ ነው፡፡
ሥርዓቱ ናቹራል ላንጉዌጅ ፕሮሰሲንግን ከማሽን ለርኒንግ ጋር አሰባጥሮ በመጠቀም በጽሁፍ የሰፈረ ግብረ-መልስ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ይተነትናል፡፡
ሴንቲሜንት አናሊስስ በሦስት መንገዶች ይከወናል፡፡ አንደኛው ቀድመው በተቀመጡ ሕግጋት ወይም የቋንቋው መዝገበ ቃላት መሠረት የሚተገበር ነው (Rule or Lexicon based approach) ፡፡ ሌላኛው በጊዜ ሂደት ከዳታ በሚማር የማሽን ለርኒንግ ስልት ይከወናል (Automated or Machine Learning approach)፡፡ ሦስተኛውና ተመራጩ እንዲሁም በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ሁለቱን በጥምረት የሚጠቀመው ነው (Hybrid approach)፡፡
በዚህም መሠረት በኢሜል፣ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና መሰል መድረኮች ደንበኞች ካሰፈሯቸው ተቋሙን የተመለከቱ ያልተደራጁ ጽሁፎች ውስጥ ጠቃሚ እይታዎች ይጠናቀራሉ፡፡
እንደ ቴክታርጌት ትንተና ይህ ሥርዓት በዓረፍተ ነገር፣ በሐረግ፣ በአንቀፅ እና ከዛም ደረጃ በላይ በሚገኙ ጽሁፎች ላይ መተግበር ይችላል፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.mr/TechnologymasterPage

በፓርኪንሰንስ በሽታ የተጠቁ ሴሎችን ድብቅ ባሕርያት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት መለየት ተቻለ፡፡
ተመራማሪዎች ከፓርኪንሰንስ ተጠቂዎች የተወሰዱ የቆዳ ሕዋስ ናሙናዎችን አዳዲስ ባሕርያት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን በማጣመር መለየት መቻላቸው ተገልጿል፡፡
ከዘጠና አንድ የበሽታው ተጠቂዎች እና ጤናማ ሰዎች የተወሰዱ ከሚሊዮን የተሻገሩ የቆዳ ሕዋስ ምስሎችን በመጠቀም ውጤቱ እንደተገኘ ተዘግቧል፡፡
በኒው ዮርክ ስቴም ሴል ፋውንዴሽን በበለፀገው የሮቦቲክ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከሕመምተኞቹ የተወሰደውን ናሙና በመተንነተን እስካሁን ያልታወቁ አዳዲስ ባሕርያት መገኘታቸው ታውቋል፡፡
NYSCF Global Stem Cell Array ተብሎ የሚታወቀው የፋውንዴሽኑ እጅግ ዘመናዊ የሮቦት ሥርዓት ብዛት ያላቸውን የሕዋስ ምስሎች ለመለየት አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ በውጤቱ የተገኙ የሕዋስ ምስሎችን ለዚሁ ወደተዘጋጀ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በማስገባት የጋራ ባሕርያቸውን ለመለየት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡
የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱዛን ኤል. ሶሎሞን እንደተናገሩት እንደ ፓርኪንሰንስ ላሉ ውስብስብ በሽታዎች በተለመደው መንገድ መድኃኒት ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አመርቂ አይደለም፡፡ ነገር ግን በምርምሩ የተደረገው ጥረት ውጤታማ የሆነ አዲስ መድኃኒት ለማግኘት መሠረት እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡
ኔቸር ኮምዩኒኬሽንስ ተብሎ በሚታወቀው ጆርናል ላይ ለሕትመት የበቃው ምርምር የኒው ዮርክ ስቴም ሴል ፋውንዴሽን እና የጉግል የምርምር ክፍል ውጤት መሆኑን ኒውሮሳይንስ ኒውስ ድረ-ገጽ ዘገቧል፡፡

ስማርት ስልክዎን ለበሽታ ምርመራ የማዋል ሂደት
ጉግል በጤናው ዘርፍ ያሉ መሰናክሎችን ለመቅረፍ ስማርት ስልኮች እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመሰሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ምርምሩ የስልኮቹን የድምጽ ማዳመጫ እና ካሜራ በመጠቀም የሕመም ምልክቶች መኖር አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ የዩሮ ኒውስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ለአብነትም የስልኮቹን የድምጽ ማዳመጫ እና መነጋገሪያ (ማይክሮፎን) ደረት ላይ በማስቀመጥ የልብ ምት እንዲሁም ተያያዥ ድምጾችን በማዳመጥ የሕመም ምልክቶችን አስቀድሞ ለመለየት ያገለግላል፡፡
በሌላ በኩል የስልኮቹን ካሜራ በመጠቀም የተወሰዱ የዓይን ምስሎችን መሠረት አድርጎ የስኳር በሽታ ምልክቶችን ሳይረፍድ ለመለየት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡
በአዋቂዎች ዘንድ ለአይነ ስውርነት አንዱ ምክንያት የሆነው ይህ በሽታ ሬቲና ተብሎ በሚታወቀው የዓይን ክፍል የደም ስሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ይታወቃል፡፡
የጉግል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓትን በመጠቀም በሕንድ እና ታይላንድ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ዳያቤቲክ ሬቲኖፓቲ በተባለው በዚህ በሽታ ተጠቂ የሆኑ መቶ ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን መለየት እንደቻሉ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡
ሆኖም እስካሁን ባለው ሂደት ጥቅም ላይ የዋሉት በጤና አገልግሎት ተቋማት የሚገኙ ሌሎች ካሜራዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ይህን ሂደት በስማርት ስልኮች ለመተካት እየተሰራ ያለው ምርምር ከጅምሩ አመርቂ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

✴️ዓለም አቀፍ የትርጉም አገልግሎት ማቅረብ የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት
⚡️ሜታ ኩባንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማገልገል የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትርጉም ሶፍትዌር የማበልፀግ እቅዱን ይፋ አደረገ፡፡
⚡️"ሰዎች በዓለም ላይ ከሚገኝ የትኛውም ግለሰብ ጋር በየትኛውም አይነት ቋንቋ የመግባባት አቅምን ለዘመናት ሲያልሙት ኖረዋል፡፡ ይህ ሕልም አሁን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት ዕውን ይሆናል፡፡" ሲል የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ መግለጹን ዘቨርጅ አስነብቧል፡፡
⚡️እንግሊዘኛ፣ ማንድሪን እና ስፓኒሽን የመሳሰሉ ቋንቋዎች ገበያ ላይ ባሉ የትርጉም ሥርዓቶች በሚገባ እየተስተናገዱ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ ሆኖም ሃያ በመቶ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በመሰል የትርጉም ሥርዓቶች ውስጥ የተካተቱ ቋንቋዎችን እንደማይናገር የኩባንያው መግለጫ ይጠቅሳል፡፡
⚡️ለቋንቋዎቹ ችላ መባል አንዱ መንስኤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትርጉም ሥርዓት ለማሰልጠን ጥቅም ላይ የሚውሉ የፅሁፍ እና የንግግር ሰነዶች በቀላሉ ተደራሽ አለመሆን እና አንዳንዴም መደበኛ የሆነ የጽሁፍ ሥርዓት እስከነጭራሹ አለመኖር በተግዳሮትነት ተጠቅሰዋል፡፡
⚡️ሜታ ይህን ተግዳሮት አዲስ የማሽን ለርኒንግ ስልቶችን ተግባር ላይ በማዋል ለመፍታት ነው እቅዱ ፡፡ አንደኛው ስልት በጥቂት ምሳሌዎች መማር የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት መገንባት ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ ምንም አይነት የጽሁፍ ግብዓት ሳያስፈልገው በቀጥታ አሁናዊ ትርጉሞችን ማቅረብ የሚችል ሥርዓት ማበልፀግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
⚡️እቅዱ መቼ ዕውን ይሆናል የሚለው በኩባንያው አለመገለፁን ዘገባው አስፍሯል፡፡

በቅርቡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ በያዝነው አመት 2022 ሊኖሩ ስለሚችሉ ለውጦች ብዙ አለም አቀፋዊ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የባለሙያዎች አስተያየት በስፋት ተንሸራሽሯል፡፡ ከነዚህ በርካታ ጽሁፎች እና አስተያየቶች የተወሰኑትን በሁለት ክፍል ወደናንተ ልናደረስ ወደናል፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ በ2022 ሊኖሩ የሚችሉ ለውጦችን የዳሰሱ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የባለሙያዎች አስተያየት ክፍል ሁለት፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሳተላይቶች ወደ ህዋ ሲመጥቁ ዋንኛ ተግባራቸው የምድር ሁኔታ የሚያሳዩ እጅግ ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን በማንሳት መላክ ነው፡፡ የዛሬው ጥንቅር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ግኝት ሳተለያቶች እንዲያስቡ ያደረገ በፈጣን መንገድም የመረጃ መላላኩን በቅጽበት እንዲካሄድ ያደረገ ነው፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
t.me/TechnologyMasterPage
ለጥንታዊ የሥነ-ጽሁፍ ቅርሶች ጥበቃ መፍትሔ የሆነው ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸውን አስራ ሁለት ጥንታዊ መዛግብት ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ታሪካዊ እና ጥንታዊ ሰነዶች ይገኛሉ፡፡
ሆኖም እነዚህን በቁም ጽሕፈት (Calligraphy) የተከተቡ ጥንታዊ መዛግብት ለጥናት እና ምርምር ሥራዎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ለትውልድ ጠብቆ ለማቆየት ሰነዶቹን ከኮምፒዩተር ጋር ማወዳጀት ለነገ የሚባል አይደለም፡፡
ይህን ለማድረግ ከሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል አንደኛው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት እየተሰራበት የሚገኘው #OpticalCharacterRecognition (OCR) ተብሎ ይታወቃል፡፡
ቴክኖሎጂውን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በማጣመር በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉና በሕትመት መልክ የሚገኙ መዛግብትን ስካን በማድረግ አሊያም ፎቶ በማንሳት በቀላሉ ኮምፒውተር ወደሚረዳው እንዲሁም የአርትኦት ሥራን ለማከናወን ወደሚያስችል የጽሁፍ አይነት (ቴክስት) መቀየር የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡
በሀገራችን የሚገኙ ጥንታዊ መዛግብቶች ለትውልድ የሚኖራቸውን አበርክቶ የተረዳው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም የቁም ጽሁፎች፣ የቆዩ የሕትመት ውጤቶች እና በእጅ የተጻፉ ሰነዶች ላይ ትኩረት አድርጎ ይህን ቴክኖሎጂ ለትግበራ ለማብቃት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

❤1
✅ እግራቸው ለማይንቀሳቀስ ሰዎች እንዲራመዱ የረዳው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት
📍የሥርዓተ ነርቭ አለመታዘዝ እክል ገጥሟቸው መራመድ የማይችሉ ሰዎች እጅግ ዘመናዊ በተባለ ሕብለ ሰረሰር ላይ በሚገጠም አነስተኛ መሣሪያ አማካኝነት መራመድ፣ መዋኘት እና ሳይክል መንዳት መቻላቸው ተገለፀ፡፡
📍ግለሰቦቹ ሆድ ውስጥ በሚቀበር ተጨማሪ አጋዥ መሣሪያ ላይ የተጫነው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ሕብለ ሰረሰር ላይ የሚገጠመውን አነስተኛ መሣሪያ ይቆጣጠራል፡፡
📍በዚህም የእግር ጡንቻዎችን የሚያዘው የሕብለ ሰረሰር አካባቢን የነርቭ ሕዋሶች በማነቃቃት እና ወደስራ እንዲገቡ በማስቻል የእግር ጡንቻዎች መታዘዝ እንዲችሉ አድርጓል ሲል ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡
📍በሞተር ሳይክል አደጋ ምክንያት ከአራት ዓመታት በላይ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲያሳልፍ ተገዶ ለነበረ ግለሰብ ቴክኖሎጂው ዳግም የመራመድ እድልን አጎናፅፎታል፡፡
📍 የስዊዘርላንዱ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውጤት የሆነው ይህ ቴክኖሎጂ ለታማሚዎቹ ከተገጠመ ከአንድ ቀን በኋላ ግለሰቦቹ መቆም፣ መራመድ፣ ሳይክል መንዳት፣ መዋኘት እና አካላቸውን መቆጣጠር መቻላቸው ተመላክቷል፡፡
#የቴክኖሎጂ_ዜና
#Technology_News
@TechnologyMasterPage

🖥 የኮምፒዩተር ኮድ በመጻፍ ከሰዎች ጋር የሚፎካከረው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት
✅ አልፋኮድ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶችን በመጻፍ በተደረገ ውድድር አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡
✅ ሥርዓቱ ኮድፎርስ ተብሎ በሚታወቀው የኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ የውድድር መድረክ ላይ ከሰዎች ጋር በመፎካከር ጥሩ ውጤት ካስመዘገቡት ሃምሳ አራት በመቶ ቀዳሚ ተፎካካሪዎች ውስጥ መካተት መቻሉን የዲፕ ማይንድ ድረ-ገፅ አስነብቧል፡፡
✅ በመድረኩ በተመረጡ አስር ፉክክሮች ላይ የተሳተፈው አልፋኮድ በመካከለኛ ሁኔታ በሚመደብ የተፎካካሪነት ደረጃ መገኘት መቻሉ ተገልጿል፡፡ ይህም ለፉክክር የበቃ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮድ አመንጪ ሥርዓት እንደሚያደርገው ዘገባው ያስረዳል፡፡
✅ ይህ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶቹን ለማመንጨት ትራንስፎርመር ቤዝድ ላንጉዬጅ የተባለውን ስልት እንደሚጠቀም መረጃው ጠቁሟል፡፡
✅ ሥርዓቱ የበለፀገው በጉግል ባለቤትነት በሚተዳደረው ዲፕማይንድ ኩባንያ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ይህ መድረክ በጥልቀት ማገናዘብን፣ አመክንዮን፣ ስልተቀመሮችን፣ ኮድ እና ተፈጥሯዊ ቋንቋን አዋህዶ መረዳትን ይጠይቅ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

❤3

✍ ©️ ©️
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
tiktok.com/@basiccomputerskills
instagram.com/basiccomputerskills
Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
✅ አልፋኮድ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶችን በመጻፍ በተደረገ ውድድር አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ፡፡
✅ ሥርዓቱ ኮድፎርስ ተብሎ በሚታወቀው የኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ የውድድር መድረክ ላይ ከሰዎች ጋር በመፎካከር ጥሩ ውጤት ካስመዘገቡት ሃምሳ አራት በመቶ ቀዳሚ ተፎካካሪዎች ውስጥ መካተት መቻሉን የዲፕ ማይንድ ድረ-ገፅ አስነብቧል፡፡
✅ በመድረኩ በተመረጡ አስር ፉክክሮች ላይ የተሳተፈው አልፋኮድ በመካከለኛ ሁኔታ በሚመደብ የተፎካካሪነት ደረጃ መገኘት መቻሉ ተገልጿል፡፡ ይህም ለፉክክር የበቃ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮድ አመንጪ ሥርዓት እንደሚያደርገው ዘገባው ያስረዳል፡፡
✅ ይህ ሥርዓት የኮምፒዩተር ኮዶቹን ለማመንጨት ትራንስፎርመር ቤዝድ ላንጉዬጅ የተባለውን ስልት እንደሚጠቀም መረጃው ጠቁሟል፡፡
✅ ሥርዓቱ የበለፀገው በጉግል ባለቤትነት በሚተዳደረው ዲፕማይንድ ኩባንያ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ይህ መድረክ በጥልቀት ማገናዘብን፣ አመክንዮን፣ ስልተቀመሮችን፣ ኮድ እና ተፈጥሯዊ ቋንቋን አዋህዶ መረዳትን ይጠይቅ እንደነበር ተመላክቷል፡፡
#የቴክኖሎጂ_ዜና
#Technology_News
✍ ©️ ©️
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
tiktok.com/@basiccomputerskills
instagram.com/basiccomputerskills
Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
✴️ ቨርቹዋል ሪያሊቲ -1-
🚩ምናባዊ ምስለ-እውነታ - ቨርቹዋል ሪያሊቲ (Virtual Reality)(VR)
🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ማለት አሁን ካለንበት የገሀዱ ዓለም አውጥቶ ወደ ሌላ የዲጅታል ዓለም የሚዘፍቅ (Immerse) አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው።
🚩ለምሳሌ እናንተ ቤታችሁ ውስጥ ናችሁ እንበል ወይም ቢሮ ውስጥ ወይም ታክሲ ውስጥ ናችሁ...ወዘተ....ባጭሩ አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በህይወታችሁ "ባየሁት!" ወይም "ባደረኩት!" ብላችሁ ወደ ምትመኙት ዓለም መጓዝ ብትመኙስ? ወይም
🚩አሁን ካላችሁበት ቦታ ሳትንቀሳቀሱ በአራዊቶች የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ መሆን ብትፈልጉስ? ሜድትራኒያን ባህር ውስጥ ከሻርኮች ጋር መዋኘት ብትመኙስ?....ወይም ደግሞ አውሮፕላን ማብረር ብትፈልጉ...
🚩ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ካላችሁበት ዓለም ሳትንቀሳቀሱ ወደ ተመኛችሁት ዓለም የሚወስድ እጅግ አስደናቂ ቴክኖሎጂ ነው። ቨርቹዋል ሪያሊቲ(VR) ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት እንደ መነፅር ዓይናችን ላይ የምናጠልቀው መሳሪያ (Head-mounted Device) ያስፈልገናል።
Part 1
════❁✿❁ ═════
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
tiktok.com/@basiccomputerskills
instagram.com/basiccomputerskills
Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════

👏1
በጽሁፍ ውስጥ የተደበቁ ስሜቶችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመግለጽ ብልሀት
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና የስልተ-ቀመሮች ዕውን መሆን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አድካሚ የዳታ ትንተና ሂደቶችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል ሴንቲሜንት አናሊስስ #SentimentAnalysis ይጠቀሳል፡፡ ይህ ሥርዓት በአገልግሎት እና ምርት አቅራቢነት ወይም ከደምበኞች ጋር በተለያየ ምክንያት የሚያገናኝ ሥራ ያላቸው ተቋማት የደምበኞቻቸውን ግብረ-መልስ እውነተኛ ትርጉም ወይም ስሜት የሚረዱበት አንዱ መንገድ ነው፡፡
ሥርዓቱ ናቹራል ላንጉዌጅ ፕሮሰሲንግን ከማሽን ለርኒንግ ጋር አሰባጥሮ በመጠቀም በጽሁፍ የሰፈረ ግብረ-መልስ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ይተነትናል፡፡
ሴንቲሜንት አናሊስስ በሦስት መንገዶች ይከወናል፡፡ አንደኛው ቀድመው በተቀመጡ ሕግጋት ወይም የቋንቋው መዝገበ ቃላት መሠረት የሚተገበር ነው (Rule or Lexicon based approach) ፡፡ ሌላኛው በጊዜ ሂደት ከዳታ በሚማር የማሽን ለርኒንግ ስልት ይከወናል (Automated or Machine Learning approach)፡፡ ሦስተኛውና ተመራጩ እንዲሁም በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ሁለቱን በጥምረት የሚጠቀመው ነው (Hybrid approach)፡፡
በዚህም መሠረት በኢሜል፣ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና መሰል መድረኮች ደንበኞች ካሰፈሯቸው ተቋሙን የተመለከቱ ያልተደራጁ ጽሁፎች ውስጥ ጠቃሚ እይታዎች ይጠናቀራሉ፡፡
እንደ ቴክታርጌት ትንተና ይህ ሥርዓት በዓረፍተ ነገር፣ በሐረግ፣ በአንቀፅ እና ከዛም ደረጃ በላይ በሚገኙ ጽሁፎች ላይ መተግበር ይችላል፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና የስልተ-ቀመሮች ዕውን መሆን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አድካሚ የዳታ ትንተና ሂደቶችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል ሴንቲሜንት አናሊስስ #SentimentAnalysis ይጠቀሳል፡፡ ይህ ሥርዓት በአገልግሎት እና ምርት አቅራቢነት ወይም ከደምበኞች ጋር በተለያየ ምክንያት የሚያገናኝ ሥራ ያላቸው ተቋማት የደምበኞቻቸውን ግብረ-መልስ እውነተኛ ትርጉም ወይም ስሜት የሚረዱበት አንዱ መንገድ ነው፡፡
ሥርዓቱ ናቹራል ላንጉዌጅ ፕሮሰሲንግን ከማሽን ለርኒንግ ጋር አሰባጥሮ በመጠቀም በጽሁፍ የሰፈረ ግብረ-መልስ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ይተነትናል፡፡
ሴንቲሜንት አናሊስስ በሦስት መንገዶች ይከወናል፡፡ አንደኛው ቀድመው በተቀመጡ ሕግጋት ወይም የቋንቋው መዝገበ ቃላት መሠረት የሚተገበር ነው (Rule or Lexicon based approach) ፡፡ ሌላኛው በጊዜ ሂደት ከዳታ በሚማር የማሽን ለርኒንግ ስልት ይከወናል (Automated or Machine Learning approach)፡፡ ሦስተኛውና ተመራጩ እንዲሁም በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ሁለቱን በጥምረት የሚጠቀመው ነው (Hybrid approach)፡፡
በዚህም መሠረት በኢሜል፣ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና መሰል መድረኮች ደንበኞች ካሰፈሯቸው ተቋሙን የተመለከቱ ያልተደራጁ ጽሁፎች ውስጥ ጠቃሚ እይታዎች ይጠናቀራሉ፡፡
እንደ ቴክታርጌት ትንተና ይህ ሥርዓት በዓረፍተ ነገር፣ በሐረግ፣ በአንቀፅ እና ከዛም ደረጃ በላይ በሚገኙ ጽሁፎች ላይ መተግበር ይችላል፡፡
#Technology_News
#የቴክኖሎጂ_ዜና
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
👍2
የጤና ምርመራዎችን ለማድረግ ድምጽን የሚጠቀመዉ የሰዉሰራሽ አስተዉሎት ሥርዓት
ጉግል ኩባንያ ሳንባ ነቀርሳ እና ሌሎች ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ የጤና እክሎችን ድምጽን በመጠቀም መለየት የሚያስችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አበልጽጓል።
ሞዴሉ ሄልዝ አኮስቲክ ሪፕረዘንቴሽንስ (Health Acoustic Representations) ይሰኛል። ምርመራ ለማድረግም ሳል፣ ንግግር፣ አተነፋፈስ እና መሰል ከሰዉነት የሚወጡ ድምጾችን ይጠቀማል።
ሞዴሉ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የድምጽ ናሙናዎች ላይ የሰለጠነ ሲሆን የበሽታዎችን የመጀመሪያ ምልክቶች ለመለየት ይረዳል። ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማትም አዳዲስ መሰል ሞዴሎችን ለማበልጸግ እንደ ማስተማሪያነት ይገለገሉበታል።
የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እደሚያሳየዉ በየዓመቱ 10 ሚሊዮን ሰዎች በሳንባ ነቀርሳ ይጠቃሉ። እ.ኤ.አ 2023 ብቻ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታዉ ምክንያት ሕይወታቸዉ አልፏል።
ሄልዝ አኮስቲክ ሪፕረዘንቴሽንስ ሞዴል በዓለም አቀፍ ደረጃ የቲቢ በሽታን ለማከም በሚደረገዉ ጥረት ተጨባጭ የሆነ ለዉጥ ለማምጣት እንደሚያስችል ጉግል በድረ ገጹ ያወጣዉ መረጃ ያመላክታል።
#የቴክኖሎጂ_ዜና
#Technology_News
EAI
══════════════
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇
Join our channel
➊ t.me/Grade1_4Info
❷ t.me/Grade5and6Info
➌ t.me/Grade7Info
❹ t.me/Grade8Info
❺ t.me/Grade9Info
❻ t.me/BasicComputer_Skills