Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
✴️ዓለም አቀፍ የትርጉም አገልግሎት ማቅረብ የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

⚡️ሜታ ኩባንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማገልገል የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትርጉም ሶፍትዌር የማበልፀግ እቅዱን ይፋ አደረገ፡፡

⚡️"ሰዎች በዓለም ላይ ከሚገኝ የትኛውም ግለሰብ ጋር በየትኛውም አይነት ቋንቋ የመግባባት አቅምን ለዘመናት ሲያልሙት ኖረዋል፡፡ ይህ ሕልም አሁን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት ዕውን ይሆናል፡፡" ሲል የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ መግለጹን ዘቨርጅ አስነብቧል፡፡

⚡️እንግሊዘኛ፣ ማንድሪን እና ስፓኒሽን የመሳሰሉ ቋንቋዎች ገበያ ላይ ባሉ የትርጉም ሥርዓቶች በሚገባ እየተስተናገዱ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ ሆኖም ሃያ በመቶ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በመሰል የትርጉም ሥርዓቶች ውስጥ የተካተቱ ቋንቋዎችን እንደማይናገር የኩባንያው መግለጫ ይጠቅሳል፡፡

⚡️ለቋንቋዎቹ ችላ መባል አንዱ መንስኤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የትርጉም ሥርዓት ለማሰልጠን ጥቅም ላይ የሚውሉ የፅሁፍ እና የንግግር ሰነዶች በቀላሉ ተደራሽ አለመሆን እና አንዳንዴም መደበኛ የሆነ የጽሁፍ ሥርዓት እስከነጭራሹ አለመኖር በተግዳሮትነት ተጠቅሰዋል፡፡

⚡️ሜታ ይህን ተግዳሮት አዲስ የማሽን ለርኒንግ ስልቶችን ተግባር ላይ በማዋል ለመፍታት ነው እቅዱ ፡፡ አንደኛው ስልት በጥቂት ምሳሌዎች መማር የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት መገንባት ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ ምንም አይነት የጽሁፍ ግብዓት ሳያስፈልገው በቀጥታ አሁናዊ ትርጉሞችን ማቅረብ የሚችል ሥርዓት ማበልፀግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

⚡️እቅዱ መቼ ዕውን ይሆናል የሚለው በኩባንያው አለመገለፁን ዘገባው አስፍሯል፡፡


#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና

t.me/TechnologyMasterPage
🖥️ፍላት ስክሪን ቲቪዎችን የሚያበላሹ 5⃣ ነገሮች

1⃣. ቮልቴጅ

⚠️ሁሉም እቃዎችን የሚያበላሸው የተለመደው የቮልቴጅ መጨመር እና መቀነስ ነው😡 አብዛኛው ቲቪዎች የራሳቸው መቆጣጠሪያ ስለሌቻው
ቦርዳቸው ቶሎ ለመቃጠል ይዳረጋል ስለዚህ 500 V Stabilizer ገዝተው ይጠቀሙ።

2⃣. የቲቪ የጀርባ መብራቶች (Backlight) መቃጠል

⚠️ላይቶቹ ሚቃጠሉበት ወቅት ቲቪዎቹ ምስል ማሣየት አቁመው ድምፅ ብቻ ማሠማት ይሆናል ይህ ነገር እሚከሠተው የባክ ላይቶቹ እድሜ (life span) ሲያልቅ እና ከፍተኛ ሀይል ሲመታቸው ይቃጠላሉ በቶሎ ማስቀየር ያስፈልጋል።

3⃣. ፅዳት

⚠️ስክሪኑ ላይ Spray
ረጭቶ ማፅዳት በፍፁም ሊደረግ እማይገባ ነው። ስክሪኑ በጣም Sensitive ስለሆነ ውስጥ ውሀ ገብቶ በቀላሉ ይበላሻል። ለማፅዳት ሲፈልጉ በንፁ ለስላሣ ጨርቅ ላይ ስፕሬውን በትንሹ በመርጨት ማፅዳት ይችላሉ።

4⃣. ኬብል

⚠️በክረምት ወቅት HDMI ኬብል አይጠቀሙ መብረቅ በዲሹ ኬብል አልፎ በHDMI አማካኝነት ቲቪዎን ቀጥታ ያገኘዋል

⚠️በዚ ጊዜ Av ጃክ መጠቀም የተሻለ ነው።

5⃣. የስክሪን መሰበር ነው።

⚠️በተለያዩ አጋጣሚዎች ስክሪን ይሰበራል ይሰነጠቃሉ ማሰቀየር በጣም_ውድ ነው፤ ስለዚህ ልንጠነቀቅላቸው ይገባል።

⚠️ቲቪዎን ከፍ አርጎ ግድግዳ ላይ መስቀል ያስፈልጋል።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

━━━━━━━━━━━━━━━
📢:
t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌
Share📌▬▬▬▬▬
✳️ Cloud Storage

▫️ ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

▫️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

▫️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

▫️ ባክአፕ ክላውድ በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

▫️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

▫️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

━━━━━━━━━━━━━━━
📢:
t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌
Share📌▬▬▬▬▬
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ በያዝነው አመት 2022 ሊኖሩ ስለሚችሉ ለውጦች ብዙ አለም አቀፋዊ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የባለሙያዎች አስተያየት በስፋት ተንሸራሽሯል፡፡ ከነዚህ በርካታ ጽሁፎች እና አስተያየቶች የተወሰኑትን በሁለት ክፍል ወደናንተ ልናደረስ ወደናል፡፡

#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና

t.me/TechnologyMasterPage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ በ2022 ሊኖሩ የሚችሉ ለውጦችን የዳሰሱ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የባለሙያዎች አስተያየት ክፍል ሁለት፡፡

#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና

t.me/TechnologyMasterPage
በብርኃን ቅምሻ

እስቲ ይሞክራት - ፀሐይን ለማጥፋት
እኔ ነኝ ብርኃን የሚል - ፀኃይን ለመተካት
እፈካለሁ የሚል - በኮኮቦች ድምቀት
እነግሳለሁ የሚል - ለብርኃን ፍካት
እኮ የሚችል ካለ - ይምጣና ይሞክራት።
እንሞክራለን የሚል ካለ
ሰውም እንዲህ ይላል፣
አረ እነሱ አብደዋል፣
ፀኃይን እኮ - እናጠፋታለን ብለዋል።
አረ ጎበዝ በዚህ - የድንቁርና ያለ
አረ ድንቁርናም ያፍራል- የማንሰማው የለ።
ከዚህ ነው ከማዶ - የምንሰማው ጉድ፣
ከሰው ነው ከሮቦት - የየነው እብድ፣
ፀሀይ በላ ግኝት - አረ ኬት ነው ከወዴት።

ሲለምኑ ኖረው - ሁሌ በልመና፣
ሲቃዡ ከርመው - ሁሌ በደፈና፣
ስያበላሹ መጥተው - መስሏቸው እርድና፣
ሰውነታቸውን አፍታተው- በራሷም ተጣዱና፣
የጨለመች መሰላቸው - ብትሸፈን በዳመና።

ሲፈልጉ ይመራመሩ - ወጥተው ይውረዱ፣
ድንጋይ ይፈንቅሉ - ሲያሻቸው ይበዱ፣
ጠጥተው ከሆነ - ከስክርናቸው ሲበርዱ፣
ተቃጥለው ይቀበራሉ - ሲታያቸው ጉዱ።

በምድር ላይ የተሰለፈው - ፊቱን ወደ ፀሐይ አዙሮ፣
በእሪታ ሲቀልጥ - የተቃጠልኩኝ እሮሮ፣
አምላኬ ይላል - ከፀሐይዋ ጓሮ።
አረ ክፋት ሲዘሩ ያኔ - ያልታያቸው አምላክ፣
እናጠፋለን ሲሉ - ትዝ ያላላቸው አምላክ፣
እና አሁን ከምኔው - ወዴትስ በርከክ!

ወይ እህል ሲዘሩ - ወይ ሲያርሱ እርሻ
ውሸት ሲያርሙ - ለሆዳቸው ጉርሻ
ወይ እውነት ሲታያቸው - የክፉነታቸው ድርሻ
ሲጦልግ ያያሉ - በብርኃን ቅምሻ።

በረሻድ ሙዘሚል

ቀን፦ ሚያዝያ 29/2014[May 7/2022]


t.me/SharpSwords
ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን።
ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ!
ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች #Like #shear ይደረግ።


t.me/TechnologyMasterPage
አንዳንድ የኮምፒውተር ክፍሎች ማብራሪያ
1. RAM (Random Access Memory)
ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል::
(1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል::
:
2. ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot)
ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን::
:
3. Heat_sinker
ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም
Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል::
:
4.Fan
ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው::
CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን::
:
CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው CPU በተባለ Divice ነው::ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው::
CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም
:
1. Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው::
:
2. Arthmatic and logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል::
:
3. Regster
ይሄ ደግሞ Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::ይሂም
Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው::
Port (ፓርት)
:
port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው:: መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ::
የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ ኤሌክትሪክ ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው::
Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል)
power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው:: የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል::
ሞደም (Modem):-ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው::
:
ኪቦርድ Keybord:-መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት.ቁጥሮች.ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።


━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage

━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
1
💻 ለስራዎ ምቹ የሆነ ላፕቶፕ እንዴት ይገዛሉ?

በአሁኑ ወቅት ላፕቶፕ ለመግዛት ሲታሰብ ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ያሉት ላፕቶፖች በሙሉ የራሳቸው የሆነ ጥሩና መጥፎ መገለጫ ቢኖራቸውም ላፕቶፕ ሲገዙ ቢንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መገለጫዎችመመልከት በጣም አስፈላጊ ነው

1ኛ. የስክሪን ስፋት እና የላፕቶፕ ክብደት (Screen size and weight)

የላፕቶፕ ስክሪን በአብዛኛው ከ9-17 ኢንች (ከ23-43 ሳንቲ ሜትር) ድረስ ይሆናል፡፡ የስክሪን ስፋቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የላፕቶፑም ክብደት ይጨምራል፡፡ እዚህ ላይ ላፕቶፑን ለምን እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ የላፕቶፑ መጠን እየጨመረ በሔደ ቁጥር ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ከባድ ላፕቶፖችን አዘውትሮ መሸከም በሰውነታችን ቅርጽ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ልዩ ልዩ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ስለዚህ ስራችን ብዙ እንቅስቃሴ ያለበት ከሆነ ክብደታቸው አነስተኛ የሆኑና በቀላሉ ልናንቀሳቅሳቸው የምንችላቸውን መርጦ መግዛት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰፊ ስክሪን ያላቸው ላፕቶፖች የባትሪ ቆይታ ጊዜያቸው አነስተኛ ነው፡፡

2ኛ. CPU (የላፕቶፑ አእምሮ)

በአለማችን ሁለት የታወቁ የCPU አምራች ኩባንያዎች አሉ፡፡ እነዚህም Intel እና AMD ናቸው፡፡ Intel ገበያውን የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በጨመር ሲቆጣጠረው፤ AMD ደግሞ ተወዳዳሪ የሆኑ ሞዴሎችን በአነስተኛ ዋጋ ያቀርባል፡፡ እዚህም ላይ ኮምፒውተሩን ለምን ስራ እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ የግራፊክስ ባለሙያ ከሆኑ ኤዲተር ከሆኑ ጥንድ ኮር (Dual-core CPU) ቢጠቀሙ የተሸለ የመፈጸም ብቃት አለው፡፡ ከዚህ ውጭ ለመሰረታዊ የኮምፒውተር አገልግሎት የሚፈልጉት ከሆነ ነጠላ ኮር (single-core CPU) ያለውን ላፕቶፕ ቢገዙ ከዋጋም አንጻር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

3ኛ. RAM

ኮምፒውተርን ለመደበኛ አገልግሎት ማለትም ለቤትከሆነ ውስጥ እና ለቢሮ ወይም ለጉዞ የሚጠቀሙት ከሆነ ከ 2-4 GB ያላቸውን መጦ መግዛት የተሻለ ነው፡፡ የግራፊክ አርቲስት ከሆኑ ወይም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች የሚያዘጋጁ ከ4 GB እስከ 8 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መርጦ መግዛት ውጤታማ ያደርጋል፡፡

ተማሪዎች የቤት ስራቸውን ለመስራት፣ ለኢሜይል ወይም የጠለያዩ ድረ ገፆችን መጎብኘት የመሳሰሉ ተግባራትን ለመከወን ግን 1 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መግዛትም ይቻላል።


t.me/TechnologyMasterPage
✴️ ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን

🔆 ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ  wifi በመጠቀምም በዋየርለስ ወይም ያለ ኬብል ፕሪንተራችንን ከኮምፒውተራችን ጋርም ማስተዋወቅ እንችላለን።
🔆 እኔ ግን ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ያለምንም wifi እና software ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር እንዴት ማስተዋወቅ እንደምንችል ነው።
🔆 ኮምፒውተራችንን እንዴት ከፕሪንተራችን ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን።
1⃣ control panel ውስጥ በመግባት device printer እንመርጣለን ወይም start ን በመንካት search box ላይ device and printer ብለን እንፅፋለን።
ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማያያዙን እንዳንረሳ።
2⃣ በመቀጠል add printerን  እንመርጣለን ።search እስኪጨርስ እንጠብቃለን።
3⃣ add alocal printer የሚለውን መርጠን next እንለዋለን።
4⃣ በመቀጠል ፕሪንተራችንን ያያዝነው በኬብ ስለሆነ ከሚመጣልን ምርጫ የመጀመሪያውን USB portን እንመርጣለን።next እንለዋለን
5⃣ አሁን ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የፕሪንተራችንን ስም በመፈለግ መርጠን next ቀጥሎም next እንለዋለን።
6⃣ በመጨረሻም print a test page የሚል ይመጣልናል click አርገን test እናደርግና finish ብለን እንጨርሳለን።
ለወዳጆ ያጋሩ

ለጥቆማና ለአስታያየት
@ReshadMuzemil

t.me/TechnologyMasterPage
✳️ የGoogle አስገራሚ እውነታዎች፡

◽️ Googleን ከቀኝ ወደ ግራ ገልብጠን ብንፅፍ elgooG ይሆናል፡፡
elgooG.im ብለን የገፀ ድር አድራሻ ላይ ብንፅፍ የተገለበጠ የጎግል መፈለጊያን ማየት እንችላለን፡፡

◽️ Zerg rush ብለን ጎግል ላይ ሰርች ብናደርግ አስገራሚ ነገር እናያለን፡፡

◽️ አሁን የሚጠራበት ጎግል የሚለው ስያሜ በስህተት የቀረበ መሆኑን ያውቃሉ ካልሆነ ይህ መጠሪያው ትክክለኛው ሳይሆን በአጋጣሚ የመጣ መጠሪያው ነው። ይህ የሆነው መስራቾቹ Googol ብለው ለመጻፍ በማሰብ በስህተት Google ብለው ከሰየሙት በኋላ ነው፤ ይህ መጠሪያ ደግሞ በሂሳብ ከኋላው 1 መቶ ዜሮዎችን የሚያስከትል 1 ቁጥርን ይወክላል።

◽️ የጎግል ሰራተኞች Googlers የሚል መጠሪያ ሲኖራቸው አዲስ ተቀጣሪዎች ደግሞ Nooglers ይባላሉ።

◽️ የጎግል የመጀመሪያው ትክክለኛ መጠሪያ Backrub ይባል ነበር፤ ይህ የሆነው ደግሞ በማፈላለጊያ ገጹ ላይ ለሚፈለጉ አድራሻዎች በሚሰጠው አድራሻ እና ደረጃ አማካኝነት ነው።

◽️ ወደ ገጹ ገብተው ምናልባት “ራሴን ማጥፋት እፈልጋለሁ" I want to commit suicide የሚል ቃልን ቢጽፉ ይህን እንዳያደርጉ እና እርዳታ
የሚያገኙባቸውን በሚገኙበት አካባቢ እርዳታን እንዲያገኙ የሚያስችሉ ቁጥሮችንና መርጃ መንገዶች ያቀርብልዎታል።

◽️ ዘና ማለት ካሰኘዎት ደግሞ በጎግል ምስል መፈለጊያ ላይ ገብተው Atari breakout ብለው ይፈልጉና በሚመጣልዎት ጨዋታ ዘና ማለት ይችላሉ።

◽️ በመፈለጊያ አድራሻው ላይ የፈለጉትን ያክል ቁጥር እስከቻሉት ድረስ ይጻፉ ጎግል በፊደል እያስደገፈ ያቀርብልዎታል።

◽️ ጎግል ለፈለጉት ነገር ትክክለኝነት ማረጋገጫ 28 የተለያዩ ማረጋገጫ እና አምስት ማስጠንቀቂያ መንገዶችን ይከተላል።

◽️ አይበለውና አንድ የድርጅቱ ሰራተኛ ከዚህ አለም በሞት ቢለይ የሟቹ የፍቅር ወይም የትዳር አጋር፥ በየወሩ ከደሞዙ 50 በመቶውን ለ10 አመት ያክል መውሰድ ይችላል። ምናልባት ሟቹ ልጅ ካለው ደግሞ ልጁ 19 አመት እስከሚሞላው/ላት ድረስ በየወሩ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል።

◽️ ከሚኖሩበት ምድር ወደ ላይ አልያም ወደ ላይ ከፍ ብለው ሰማየ ሰማያት ላይ ምን እንዳለ ማወቅ ከፈለጉ ደግሞ
www.google.com/sky . ከፍተው ይመልከቱ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት አልያም የከዋክብት ስብስቦችን ይመልከቱ።

◽️ Google Maps ደግሞ የሚኖሩባትን ምድር የተለየ ገጽታ ማየት ያስችልዎታል።

◽️ ማወቅ አይከፋምና ወደ Google Mars ገብተው ስለ ቀይዋ ፕላኔት የፈለጉትን መረጃ ከየትኛውም ቦታ በተሻለ መልኩ ማግኘትም ይችላሉ።

◽️ እንዴት ነው የሚከፈላቸው የሚለው እንዳለ ሆኖ ግን፥ ይህ ኩባንያ ጎግል ማፕን ተጠቅሞ የበረሃን እይታ ለደንበኞቹ ለማድረስ ለዚህ ስራ ብቻ የሚያገለግል ግመልም ቀጥሯል። እናም ለተጠቃሚዎቹ እርካታ ጎግልም የበረሃዋን ግመል ቀጥሮ ያሰራል፤ እርሷም ደሞዝ ተከፋይ የጎግል ሰራተኛ ናት።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage
t.me/TechnologyMasterPages
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቅርቡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ በያዝነው አመት 2022 ሊኖሩ ስለሚችሉ ለውጦች ብዙ አለም አቀፋዊ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የባለሙያዎች አስተያየት በስፋት ተንሸራሽሯል፡፡ ከነዚህ በርካታ ጽሁፎች እና አስተያየቶች የተወሰኑትን በሁለት ክፍል ወደናንተ ልናደረስ ወደናል፡፡

t.me/TechnologyMasterPage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በተመለከተ በ2022 ሊኖሩ የሚችሉ ለውጦችን የዳሰሱ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የባለሙያዎች አስተያየት ክፍል ሁለት፡፡

t.me/TechnologyMasterPage
ዓለም ከኮምፒውተር ጋር ከተዋወቀ በርካታ ዓመታት ቢቆጠሩም የብዙዎች የኢንተርኔት አጠቃቀም መስመርን የሳተ ነው።

ከመረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ የትየለሌ እሮሮዎች በተደጋጋሚ የሚሰሙትም ከአጠቃቀም ስህተቶች ጋር በተያያዘ ነው።

የኢንተርኔት አጠቃቀም ስህተት ለአካላዊ ወይም አእምሯዊ ጉዳት እንደሚያጋልጥ
ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

በስፔን የሚገኘው የበይነ-መረብ ደህንነት ተቋም ኢንተርኔት ሰክዩሪቲ ኦፊስ (ኢኤስኦ) በተደጋጋሚ የሚሰሩ ስህተቶችን ይፋ አድርጓል።

ከኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ራሳችሁን ለመታደግ ስህተቶቹን ከመፈጸም ተቆጠቡም ብሏል።

የማይታወቁ_ማስፈንጠሪያዎች

የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ሰዎችን ከሚያጠምዱባቸው መንገዶች አንዱ የተሳሳቱ ማስፈንጠሪያዎች መላክ ነው። ሰዎችን በቀላሉ ማማለል የሚችሉ 'የዋጋ ቅናሽ' ወይም 'በነጻ የሚታደሉ ምርቶች' ማስታወቂያ ይጠቀሳሉ።

ማስፈንጠሪያዎቹ ቫይረስ ወደተሸከሙ ገጾች ስለሚወስዱ የተጠቃሚዎችን የመረጃ ደህንነት አደጋ ውስጥ ይጥላሉ።

ኢኤስኦ "ማስፈንጠሪያዎች ከመከተልዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ" ይላል።

ያረጁ_ሶፍትዌሮች

በስልክ ወይም በኮምፒውተር የሚጫኑ ሶፍትዌሮች በየግዜው መታደስ አለባቸው። ሳይታደሱ ከቆዩ የኮምፒውተር ወንጀለኞች በየግዜው ለሚሰሯቸው አደገኛ ቫይረሶች ያጋልጣሉ።

አጠራጣሪ_መተግበሪያዎች

መተግበሪያዎችን (አፕ) ከተለያዩ ድረ ገጾች መጫን ለደህንነት አስጊ ነወ። ትክክለኛ የሚመስሉ
ነገር ግን ለቫይረስ የሚያጋልጡ መተግበሪያዎች ብዙ ናቸው።
ብዙዎችም ያለማወቅ ይጭኗቸዋል።

ቀላል_የይለፍ_ቃል

የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለመስረቅ የይለፍ ቃላቸውን ይሰብራሉ።

ስለዚህም ኢኤስኦ "ጠንካራ የይለፍ ቃል ይኑራችሁ" ይላል። ምክንያቱም በቀላሉ
የሚገመቱ የይለፍ ቃሎች በርካቶችን ለአደጋ አጋልጠዋል።

የመረጃ_ቅጂ_አለማስቀመጥ

በኮምፒውተር ወይም በስልክ ላይ ያሚገኙ መረጃዎችን ቅጂ አለማስቀመጥ ሌላው ችግር
ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች የግል መረጃ ካገኙ ለባለቤቱ ለመመለስ ገንዘብ ይጠይቃሉ።

ተጠቃሚዎች የመረጃቸው ቅጂ ካላቸው ግን ከመዝባሪዎች ጋር መደራደር
አያስፈልጋቸውም።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
👍1
☑️All Mobiles Secret👁‍🗨 Codes AdFree
All Mobiles Secret Codes AdFree v1.3 @ApkManagerBot.apk
2.2 MB
#በጣም ብዙ የሆኑ Codes(ኮዶችን) ይዛለች!

●የያንዳንዱ ኮድ ስልካችንን ኦርጂናል ነው ወይስ ፎርጂት የሚለውን ነገር እንድናውቅ ይረዳናል!!

#ረሻድ_ሙዘሚል