የሳይበር ጥቃት ይደርስብን ይሆን?
አለም ተቀይሯል! የየለቱ ህይወታችንም ቢሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ የመጣ ነገር ነው። የዚህ ሁሉ ስር መሰረት ቴክኖሎጂ ነው!
ቴክኖሎጂ ሲባል የግድ ስልክ፣ ኮምፒዩተር፣ ኢንተርኔት፣ ሮባቲክስ፣ እና የመሳሰሉት ብቻ አይደለም፣ ምንም እንኳ እነሱ ትልቁን የቴክኖሎጂ ዝና እና እውቅና ቢያገኙም። ቤታችን ውስጥ ያሉ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ማንኪያ... ጭምር የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው!
ስለዚህ፣ ሰዎች በቀላሉ ነገሮችን ከዚህ በፊት ሲጠቀምቧቸው ከነበረው መንገድ ይልቅ፣ በአዲሱ ሻል ባለው መንገድ በቀላሉ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ሁሉ ቴክኖሎጂ እንልዋለን።
አለም ተቀይሯል ስንል፣ ቴክኖሎጂ አለምን ቀይሮታል ማለታችን ነው።
በህክምናው ዘርፍ፤ በትምህርት ዘርፍ፤ በፋይናንስ ዘርፍ፤ በግብርናው ዘርፍ፤...እና በወታደራዊው ዘርፍ ጭምርም።
በወታደራዊ ዘርፍ ስንል፣ ዛሬ ላይ እንደ ጥንቱ የጦርነት #battle መርጠህ ፊት ለፊት ወታደሮችህን አዝምተህ ጦርነት የምትከፍትበት ፋሽን እየቀረ የመጣ ነገር ነው። ይህም ቴክኖሎጂ ምንያህል በወታደራዊ ዘርፉ ላይ ተጽዕኖ እንዳሳረፈበት የምናይበት ጥሩ ምሳሌ ነው። ከሚሰሩበት ቢሮዋቸው እንኳ ሳይወጡ በሰው አልባ ጄት/አውሮፕላን የሚፈለገውን ታርጌት በአመርቂ ሁኔታ(99%) መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ አሁን በምንኖርበት አለም እየተተገበረበት ይገኛል።
ለዚህ ቴክኖሎጂ ቀዳሚዋ ሀገር፣ Russia፤ US፤ China፤ Israel እና አብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራትን ያካትታል። ወደፊት ታቅዶ እየተሰራበት የሚገኘው ደሞ ጦርነትን ምንም የሰው ደም ሳይፈስ በሮቦትች ብቻ የሚከናወን ይሆናል።
የዘመኑን ቴክኖሎጂ ስናነሳ ስለ ሳይበር ደህንነት ሳያነሱ መሄድ ትንሽ ይከብዳል። ቴክኖሎጂ ባደገ ቁጥር፣ የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችም እያደጉ እየመጡ ይገኛሉ። የሳይበር ጥቃት በወታደራዊ ዘርፍ ላይ ከተፈጸመ፣ ውጤቱ እጅግ አስከፊ ይሆናል! ምሳሌ ብንወስድ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን/ድሮን እንደሚታወቀው በኔትወርክ ግንኙነት መሰረቱን አድርጎ ነው የሚሰራው፣ ማለትም አዲስ አበባ ባለው ቢሮ ኮምፒዩተር ድሮኑ በኔትወርክ ይገናኙሉ(ይህ ኔትወርክ አይነት ሳተላይት አማካኝነት ሊሆን ይችላል)፣ ኮምፒዩተሩን የያዘው ሰውዬ በኮምፒዩተር ስክሪኑ እየታገዘ ድሮኑን ወደፈለገበት አቅጣጫ እያበረረ ይቆጣጠረዋል(ልክ ጌም እንደመጫወት)። እንበለንና ድሮኑን የሚቆጣጠረው ሰውዬ ድሮኑ ከሱ ቁጥጥር ስር ቢወጣስ? የተሳሳተ ሰው እጅ ጋር የድሮኑ ቁጥጥር ቢያደርግበትስ? ጥቃቱ የታለመለት ኢላማ ጋር ሳይሆን ወደራሳቸው ቢሮ ይሆናል ማለት ነው። አየህ ይህ ምን ያህል የከፋ እንደሚያደርገው?
ጥሩ ዜና ግን እንዲው በቀላሉ ማንም ሰው ተነስቶ የድሮንኑ ቴክኖሎጂ ሰብሮ ገብቶ መጥለፍ አይችልም! በጣም ጠንካራ #Encryption #Algorithm ነው የሚጠቀሙት!
💠የሳይበር ጥቃት Vs ቴክኖሎጂ
አብዛኛውን ጊዜ የሳይበር ጥቃት በቴክኖሎጂው ክፍተት(vulnerability) በኩል ሆኖ የሚፈጽመው ጥቃት እምብዛም ነው፣ ምክንያቱም ከጊዜ ወደጊዜ የቴክኖሎጂው ድርጅት ሲስተማቸውን ከዘመኑ ቴክ ጋር ስለሚያዘምኑ(update)፣ በዚህም ሳቢያ እንብዛም ጥቃት አይፈጸምባቸውም።
ባጭሩ፣ ቴክኖሎጂ የሳይበር ጥቃት መንስዔ የሚሆንበት ምክንያት በጣም(በጣም) አናሳ ነው!
💠እንደዛ ከሆነ ታዲያ...?
አዎ፣ የሳይበር ጥቃት ይፈጸማል፣ እያየናቸው፣ እየሰማናቸው ጭምር እንገኛለን። ግን አጥቂዎቹ(hackers) ቀጥታ ሲስተሙን ሳይሆን፣ #social_engineering ዘዴ በመጠቀም ኢላማ ያደረጉትን የድርጅት ሲስተም ቅጥረኛ/ሰራተኛ ማጥመድ ነው!(phishing)፣ ይህን ዘዴ ነው በብዛት የሚጠቀሙት።
ጠመዳውን በሚያከናውንበት ሰዓት እንዲው ከመሬት ተነስተው አይደለም። ስለሰወዬው ጸባይ፣ ባህሪ፣ ስንት ልጅ እንዳለው፣ የሚወደው ነገር... ምናለፋህ አጠቃላይ ግላዊ ነገሮችን በጥልቀት ጊዜ ሰተው ያጠናሉ ይህም #Social_Engineering ይባላል።
ጥናታቸውን ካጠናቀቁ በዃላ፣ ወደሚፈልጉት ሰው ጠመዳቸውን ይጀምራሉ: ምሳሌ:-
#scenario
-------------
"የ X ዩኒቨርስቲ የ Y Department ሀላፊ የሆነው አቶ 'አበበ ይርጋ'፣ ከታች የተቀመጡትን የተለያዩ ማሻሺያዎችን መፈጸም ይችላል (ብለን እናስብ):-
💎 የተማሪዎችን ውጤት ማስቀመጥ፤ ማጥፋት፤ ማስተካከል
💎 ተማሪዎችን መመዝገብ፤ ማባረር
💎 የዲፓርትመንት ሽግግር ማድረግ
..."
-----------
ይሄን ሰውዬ('አበበ') አጥቂዎች(hackers) በሚገባ ካጠኑት በኋላ ጠመዳቸውን ይቅጥላሉ ማለት ነው፣ ምሳሌ:- ወደ አበበ email መልዕክት ላኩለት:-
-----------
"ይደረስ ለአበበ ይርጋ፣ የ X ዩኒቨርሲቲ Y ዲፓርትመንት ሀላፊ፣ ባለፉት ሶስት ቀናት ወደ አንተ አካውንት ለመግባት ጥረት እያደረጉ ያሉ የመረጃ መንታፊዎች እንዳሉ ደርሰንባቸዋል። ስለዚህም የዩንቨርስቲያችንን ዲፓርትመነት ሀላፊዎችን ደህንንነት የማስጠበቅ ግዴታ ስላለብን የይለፍ ቃልህን ከታች በላክልንህ ማስፈንጠሪያ ገብተህ በፍጥነት አሁንኑ ወደ ጠንካራ የይለፍ ቃል እንድትቀይር ስንል በጽኑ እናሳስባለን። የዩንቨርስቲው ሬጅስትራር ጽህፈት ቤት ዋና ሀላፊ፣ አቶ ገመቹ ሀጎስ።"
ፊርማ፣ ማህተብ...
----------------
'አበበ' በዚህ ሰዓት የተባለውን ለማድረግ ማስፈንጠሪያውን ተጭኖት፣ ሀከሮቹ ባዘጋጁለት ተመሳሳይ ገጽ ይገባል፣ የይለፍ ቃሉን ይቀይራል:
>Old Password
>New Password
>Re-Type New Password
>>Reset Password>>
boom!😎 አበበ ተበላ!
💠 የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ ምን ማድርግ አለብኝ
💎 ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም፣ እንዴታ!😎
ይህም የ brute force ጥቃት ከባድ ያደርገዋል
💎 በemail የሚላከውን ማንኛውንም ሊንክ አለመክፈት ሳታረጋግጥ አትክፈት።
🙄ለ phishing ፍትሁን መድሀኒት ነው
💎 የይለፍ ቃልህን በወረቀት፣ በዲያሪ እና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ አለመጻፍ፣ ይልቁኑ በተለያዩ ፓስወርድ ማናጀር ቱሎች ማስቀመጥ።
💎 በመጨረሻም #Mute ያደረጋችሁ #UnMute(ይሄ የሳይበር ደህንነትን አያስጠብቅም 😂)
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
▪︎●●●◇●●●◇●●●◇●●●◇●●●◇●●●▪︎
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
Our channel
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
Tiktok: tiktok.com/@basiccomputerskills
Instagram: instagram.com/basiccomputerskills
Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil

👍3