Al EHSAN አል_ኢህሳን
176 subscribers
409 photos
44 videos
2 files
629 links
የቻናሉ አላማ
1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ
2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት
3 ለወጣቶች ምክር
4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል።

ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን

ለአስተያት @S1u9l
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፀሐይና ጨረቃ ዘላለም ቢኖሩ ከዘመኑ ጋር አይሄዱም እናዘምናቸው ተብሎ ይታሰባል? በጭራሽ!
ኢስላምም እንዲሁ ነው። እስከ እለተ ቂያማ በሚኖር ህዝብ ልክ የተሰፋ የዘመነ ዲን ነው

ሂጃብ ማለት ፀጉር መሸፈኛ ብጣሽ ጨርቅ ሳይሆን ሴቶች ውበታቸውን ለባዕድ ወንዶች ላለማሳየት የሚሰተሩበት፣ የሚሸፈኑበት፣ የሚከለሉበት ተግባር ነው።  ተግባሩ ከራስ እስከ ጥፍር በሰፊ ልብስ መሸፈንን፣ ተግባሩ ባዕድ ወንዶች ባሉበት አለመገኘትን/አለመቀላቀልን፣ ተግባሩ በሚዲያ አለመታየትን፣ ወዘተ ያካተተ የአላህ ትዕዛዝ ነው

ስለሂጃብ ምንነት ያልገባቸው ወይም ሊነግዱበት የፈለጉ ሰዎች ሚስ ሂጃብ የሚል ፀረ-ሂጃብ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የእንቅስቃሴው promoter ደግሞ ሚንበር ቲቪ ነው። ለኢስላም በኢስላም ስም የተቋቋመ አንድ ሚዲያ በዚህ መልኩ ኢስላምን የሚሸረሽር ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደማየት የሚያሳዝን ተግባር የለም ሚዲያውን በቅርብ ለሚያቀው ብዙ የከፍ ተግባትን ሲሰራ ነበር ዛሬ ደሞ ኢሄው በሴት ሀያእነት ስለ ሒጅብ ሊያስተምሩን ሚስ ሒጃብ መጡ!!

ምንኛ የከፋ ንግድ ነው!
ሰወቹን በቅርበት ለሚያቃቸው ጥቅም ያስገኝ እንጂ ሌላም ነገር ቃላቸውን አሳምረው መምጣታቸው አይቀርም ሀራም ሀራም ነው ኸምርን ስም ብቀይርት ያው አስካሪ መጠጥ ነው!!

https://t.me/B1e9h
ከፍ በል በኢስላም!
~
አለባበሳችንን፣ አነጋገራችንን፣ የፀጉር ቁርጣችንን፣ የሜካፕ አጠቃቀም፣ የልብስ ምርጫችንን፣ ... ለመወሰን በወቅታዊ ፋሽን መሸነፍ አይገባም። ሸሪዐው ሲያዝ አሻፈረኝ ብለን የዘመኑ ፋሽን ሲሆን የምንንበረከክ ልፍስፍሶች መሆን የለብንም። እኛ በኢስላማዊ እሴቶቻችን ፈፅሞ የማንሸማቀቅ ኩሩዎች እንጂ የተሸነፈ ስነ ልቦና የያዙ ደካሞች ልንሆን አይገባም። ደግሞም ለራሳችንም ዋጋ መስጠት መልካም ነው። አላህ በኢስላም ካከበረን በኋላ፣ 0ቅልን ያክል ኒዕማ ከሰጠን በኋላ ከሰውነት ወለል ወርደን የልብስ መስቀያ፣ የፋሽን ማሳያ አሻንጉሊት ልንሆን አይገባም።
IbnuMunewor

https://t.me/B1e9h
የሸዋል ወር ሊያልቅ 6 ወይም 7
ቀን ብቻ ስለቀረው ስድስቱን የሸዋል ፆም ያላጠናቃችሁ ወንድምና እህቶች ሳያመልጣችሁ ተሽቀዳደሙ ባረከሏሁ ፊኩም።

https://t.me/B1e9h
'ተጽእኖ  መፍጠር' የሚለው በህይዎታችን ላይ ተጽእኖ እንዳይፈጥርብን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን !
ሶሻል ሚዲያ በባህሪው የምናስተላልፈውን ነገር ሰዎች ግብረ-መልስ የሚሰጡበት  ላይክ፣ኮመንት፣ፎሎው የሚያደርጉቡት ፕላት ፎርም ስለሆነ ተጽእኖው ከፍተኛ ነው ። ዛሬ  አብሃኞቻችን ሌሎች ተጽእኖ ለመፍጠር እንጨነቃለን፣እንጠበባለን ። ሳናስበውም በራስ ፍቅር መውደቅ  እና ከፍ ሲልም ሳይታወቀን በራስ አምልኮ እንጠመዳለን ። ራሳችንን ለመሸጥ በምናደርገው ግፊያ  ራሳችንን እናጣለን !
መጥፎ በሆኑ ነገሮች ተጽእኖ መፍጠር እና ለሌሎች መጥፎ አርአያ መሆን ከባድ የሆነ ክስረት የመሆኑን ያህል መልካም ስራ እየሰራንም በዚሁ መፈተናችን አይቀርም ። ምን ጊዜም እንደ ሙስሊም ራስን መለስ ብሎ መቃኘት፣ሁሉን ነገር አላህ በሚወደው መልኩ ማድረግ፣ነፍስን መርመር ያስፈልጋል ።
ብዙ ሰው ስለተከተለን ታላቅ ደረጃ ላይ የደረስን፣ወይም  ደግሞ ሪአክሽኑ ሲያንስ የወደቅን የሚመስለን ከሆነ ከባድ የስነ-ልቦና ስብራት ያጋጥመናል ።
ሁሌም ቢሆን አላህን ማስታወስ፣ያገኘነውንም ተጽእኖ ፈጣሪነት በቻልነው ሁሉ ወደ እሱ ማስጠጋት በሱው መንገድ መትጋት ያስፈልጋል ።
በተለይ ከኸይር ስራ ከኢባዳ ጋር የተያያዙ ነገሮቻችን በሶሻል ሚዲያ ውሏችን እና አካሄዳችን ላይ ተጽእኖ እንዳይፈጥሩ መጠንቀቁ  መልካም ነው ።፡ በማንኛውም መልኩ ሁልጊዜ ከራስ ጋር ሂሳብ ማድረጉ ተገቢ ነው ብየ አስባለሁ !
ወሏሁ አእለም ! ሁላችንንም አላህ ቅኑን መንገድ ይምራን !
©አብዱረሂም አህመድ

https://t.me/B1e9h
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
~
﴿إذا سَبَّكَ رجلٌ بِما يَعلَمُ مِنكَ، فلا تَسُبَّهُ بِما تَعلَمُ مِنهُ، فيَكونُ أجرُ ذلكَ لكَ ووبالُهُ عليهِ﴾

ሰውዬው ስለአንተ በሚያውቀው ጉዳይ አንስቶ ክብርህን ለማጉደፍ ከሰደበህ(ከወነጀለህ) ፤ አንተ መልስህ ስለሱ ባወከው ነገር ላይ አትስደበው(አትወንጅለው)
በተሰደብክበት ነገር ላንተ ምንዳ ሲኖርህ ውንጀላው ደግሞ ወደራሱ ይሆናል።”


📚ሶሂህ አልጃሚ: 594

https://t.me/B1e9h
👆👆👆👆👆👆👆👆
እንደዚህ አይነት ሱራ(ስዕል) ያለበትን ነገር መግዛትም ይሁን መጠቀም በዲናችን በጥብቅ የተከለከለ ነገር(ሀራም) ነው ለልጅም ብሆን ያው ነው አይፈቀድም
🔅ስዕል ያለበትን ቤት መላኢካ አይገባም ተብሎዋል በሀድስ
🔅ታድያ ከቤታችን መላኢካዎች እንዲሸሹ ነው የምንፈልገው? መላኢካዎች ካልቀረቡን ልቀርበን የምችለው ማን እንደሆነ ግልፅ ነው
🔅 ነብዩ ለአልይ ስዕልን ካገኘሀው ቀደሀው ብሆን እንጂ እንዳተወው ነበርኮ ያሉት እኛ ግን በገዛ ገንዘባችን ገዝተን የነብዩን መመሪያ መጣስ፣መላኢካዎችን ከቤታችን ማባረር ሆነ ተግባራችን
🔅የቂያማ ቀን አላህ ዘንድ በጣም የተጠሉ ሰዎች ማለት ህይወት ያለበትን ስዕል የምስሉ ሰዎች እንደሆኑ ተነግሯል ሆኖም እኛ ምርታቸውን እየገዛን እናስተዋውቅላቸዋለን አላህን ልንፈራ ይገባል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እዚህ ተግባር ውስጥ ያለን ሰዎች በግዜ ተውበት አድርገን ወደ አላህ እንመለስ @ለብዙ ስህተት የምንዳረገው ድንኑን ምያስተምር ጠፍቶ ሳይሆን ከኡለማዎች ጠጋ ብለን ለመማር ያለን ፈላጎት የወረደ በመሆኑ ነው የምንሰራውን መልካል ስራ በሌላ በኩል እራሳችን መልሰን የምናበላሸው
አላህ ማስተዋሉን ይወፍቀን

https://t.me/B1e9h
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ2 ሰዎችን አስክሬን እየፈለግን ነው " - የዞኑ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

ከሰው ህይወት መጥፋት ባለፈ በአዝእርትና በብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ  መፍጠሩ ተነግሯል።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊው አቶ ሸምሰዲን ጉታጎ ፥ " ሁኔታዉ እጅግ አስደንጋጭ ነው " ብለዋል።

በጎርፍ አደጋው የ5 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁንም በጎርፍ ተወስደዉ ከሞቱት 5 ወገኖች መካከል የሁለቱን  አስክሬን ማግኘት አልቻልንም " ብለዋል።

የአስከሬን ፍለጋው ሻላ ሀይቅ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን እና የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተለይ ዋናተኞች እያገዟቸዉ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም አደጋው በርካታ የግለሰብ ቤቶችን እንዲሁም ዌራ ወረዳ ያለን ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ ከስራ ዉጭ እንዳደረገው ገልጸዋል።

በዞኑ በበርካታ ቦታዎች ላይ የተፈጠረው የመሬት መሰንጠቅም በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ መፍጠሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Al EHSAN አል_ኢህሳን
" የ2 ሰዎችን አስክሬን እየፈለግን ነው " - የዞኑ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከሰው ህይወት መጥፋት ባለፈ በአዝእርትና በብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ  መፍጠሩ ተነግሯል። በጉዳዩ…
👉ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ እንመለስ
የእኛ ትልቁ ችግራችን ከሌሎች አለመማር ነው በሌሎች የሙስሊም ሀገራት ላይ የምደርሰው እልቂት ለማሳሌ፦
ዱባይ ቱርክ፣ሰዑዲ፣ሱዳን፣ሶማሊ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ ፣አውሎ ንፋስ መከሰት፣ በጦርነት መብዛት የምደርስባቸው መከራ ለኛ ለሙስሊሞች ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደውል ነበር ከተማርንበት
ግን ችግሩ እኛን በቀጥታ እስካነካን ድረስ እኛን አይመለከትም አይነት ነገር ነው ምላሻችን
የሰሞኑን ጎርፍ ተመልከቱ አድስ አበባ 4 ሰው ጎረቤት አላባ 5 ሰው በጎርፍ ተወሰደ እየተባለ ነው ሀላባ ለይ የመሬት መሰንጠቅ ጭምር ነው የተከሰተው ከዚህ በላይ ምን ይሁን የምያስደነግጠን ሰዎች?
አሁንም እድሉ ያለን እኛ በግዜ ወደ አላህ እንመለስ ለማንም ሳይሆን ለራሳችን ስንል መጥፋት የአንድ ቀን ክስተት ነው ሁለተኛ ዬለውም

https://t.me/B1e9h
እያስተዋልን ወገኖቼ!

በጎረቤት ሀገር #ኬንያ ለሳምንታት በዘለቀ ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 228 መድረሱን የኬንያ የሀገሪር ውስጥ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ደብዛቸው የጠፋ በርካታ ሰዎች እንዳሉም ተነግሯል።
https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጫት ከሌሎች ዘርፎች የተሻለ ትርፍ እንዳለው ይታወቃል። የጫት ንግድ ማለት ለወገን ገዳይ መርዝ እየሰጡ በምትኩ ገንዘባቸውን መውሰድ ነው። ይሄ ንግድ በወገን ህይወት ላይ መጫወት ያለበት እርኩስ ንግድ ነው። ትርፉ ሳያማልላችሁ ኣኺራችሁን በማስቀደም እንዲህ አይነት ውሳኔ የወሰናችሁ ጀግኖች ኒያችሁን፣ ልፋታችሁን አላህ ይቀበላችሁ። ለሌሎች ምሳሌ ያድርጋችሁ። ለዱንያም ለኣኺራም የሚጠቅማችሁ የተሻለ ሐላል ሪዝቅ ይስጣችሁ። የበዛ፣ የጣፈጠ በሆነ የጀነት ሲሳይ ያንበሻብሻችሁ። በዚህ ውሳኔ ላይ ድርሻ ያላችሁን ሁሉ አላህ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመንዳችሁ።
በነገራችን ላይ
ጫት በመብላትም፣ በማብላትም፣ በማጓጓዝም፣ በመነገድም፣ ለጫት ንግድ በማከራየትም የተሰማራችሁ ሁሉ ወንጀል ላይ ናችሁ። አላህን ፈርታችሁ ከድርጊታችሁ ታቀቡ።

https://t.me/B1e9h
"ሁሉም ሰው በፖለቲካ ተጠምዷል። ፖለቲከኞች ሲቀሩ። እነሱ ግን በንግድ ነው የተጠመዱት።"
* ዐብዱል መሊክ አልኢብቢ *
·
·
መሪር ሐቅ!! አብዛኞቻችን የፖለቲካው ማእበል ወስዶን ከዚያ ከዚህ እያላጋን ነው። አንዳንዱማ ከሃይማኖቱ በላይ ዘሩን እያስቀደመ የቆሻሻ ፖለቲካ ጎርፍ ወስዶታል።
ፖለቲከኞቹስ? አብዛኞቹ የሞቀ ንግድ ላይ ናቸው። እንጀራቸውን ሊያበስሉ ተፍ ተፍ እያሉ ነው። ከመንግሥት በተቃዋሚ ስም፣ ከህዝብ በነፃነት ትግል ስም፣ ከውጭ በሰብአዊ መብት ቅስቀሳ ስም ከያቅጣጫው ይዘርፋሉ። ለምስኪን ተፈናቃዮች የተሰበሰበን እርዳታ ይነጥቃሉ።
በነሱ የፖለቲካ ጦስ የሚሞተው፣ የሚፈናቀለው፣ የሚጎዳው ግን ፖለቲከኞቹ ሳይሆኑ ህዝቡ ነው። ለዘመናት ተዋልዶ፣ ተጋምዶ የኖረ ህዝብ የፖለቲከኞች ድግምት ከተደገመበት በኋላ ፍፁም በማይታሰብ መልኩ አንዱ ሌላውን ያርዳል፤ ይሰቅላል፤ ያቃጥላል፤ ይወግራል፤ በጅምላ ያፈናቅላል። ፖለቲከኞቹ ግን በህዝብ እልቂት ገበያቸው ይደራል። በህዝብ መፈናቀል ንግዳቸው ይደምቃል። በኛ ስም በጮሁ ቁጥር ለኛ የተቆረቆሩ እየመሰለን ጆሯችንን እንሰጣቸዋለን። "ማንም በክፉ አይንካቸው" እንላለን። ፎቷቸውን አሳትመን እንለብሳለን፤ እንለጥፋለን፤ እንሰቅላለን። ግና ህዝብ እየከሳ እነሱ ይደልባሉ። ህዝብ እየተፈናቀለ እነሱ ለአይን ከሚያሳሳ ሰገነት መግለጫ ይሰጣሉ። የህዝብ ልጅ ወደ ትግል፣ የነሱ ልጆች ወደ ውድ ትምህርት ተቋማት። ህዝብ ወደ ታች እነሱ ወደ ላይ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 9/2011)

https://t.me/B1e9h
የሴት ልጅ መስተካከል የማህበረሰብ መስተካከል ነው!!

📌 ሸይኽ ፈውዛን ሀፊዘሁሏሁ እንዲህ ይላሉ:
ሴትን ልጅ በተጨባጭ ካየናት ለማህበረሰቡ እንደ መርህ ልታገለግል የምትችል አካል ነች እሷ ቀጥ ካለች ከተስተካከለች ማህበረሰቡ ይስተካከላል እሷ ከተበላሸች ማህበረሰቡ ይበላሻል።

ምንጭ: (التعليق القويم على كتاب إقتضاء الصراط المستقيم )

📌 ይህን ያሉበትን ምክንያት ካየን ልጆችን አንፃ ምታሳድገው አብራቸው ምትውለው ሴት ልጅ ነች ከአላህ በታች የነገው ትውልድ እጣ ፋንታ የወደቀው በሴት ልጅ እጅ ነው  እና የሴት ልጅ ስነ-ምግባሯ ተበላሸ ማለት ዲንን ሀገርን የሚረከበው ትውልድ ተበላሸ ማለት ነው ስለዚህ ሴት ልጅ እራሷን ችላ የቆመች አንድ መድረሳ ነች ማለት እንችላለን ይህ መድረሳ የተበላሸ ከሆነ ላሸክ ከዚህ መድረሳ ተመርቀው ሚወጡትም ተማሪዎች የተበላሹ ስለመሆናቸው የቀደምቶችንም ታሪክ መለስ ብለን ካየን አሁን ላይ አኢማዎች ብለን ምንጠራቸው የመልካም እናቶች ውጤት ናቸው እነ ኢማሙ አቡ ሐኒፋን እነ ኢማሙ ሻፊኢን እነ ኢማሙ አህመድን እነ ኢማሙል ቡኻሪን ይመስል ሌሎችም
📌 እና ሴት ልጅ የያዛችው(የተሸከመችው) ሀላፊነት ከባድ ነው ሀገርን አለምን ነው መገንባት የያዘችው ነገር ግን አንዳንድ ዘምነናል የሚሉ የተፈጠሩበትን አላማ የዘነጉ ፌሚኒዝም በሚለው ልክፍት የተለከፋ ሴት ልጅ እቤቷ ቁጭ ብላ ልጆቻን መንከባከቧ ማነፃ እንደ ሗላ ቀርነት የሚያዩ አካላቶች አሉ ይህ ከእስላም አስተምህሮ ፍፁም የማይገናኝ አስተሳሰብ ነው ሗላ ቀር ማለት የተፈጠረለትን አላማ የዘነጋ ሰው ነው እና እህቶች ያለባችሁን ትልቅ ሀላፊነት በማወቅ ሀላፊነታቹን በተገቢው መልኩ ልትወጡ እና አላህንም በዚህ ነገር ላይ እንዲያግዛቹ ልጠይቁት ይገባል።

አቡ ዐብዱ-ር'ረሕማን


https://t.me/B1e9h
መራር እውነታ!
ጓደኛህ ማነው?
~
ጓደኛህ ወደ ተሻለ የምትወስደው ወይም ወደተሻለ የሚወስድህ ይሁን። ካልሆነ ግን ወይ ያጠፋሀል። ወይ ታጠፋዋለህ። ወይ ተያይዛችሁ ትጠፋላችሁ።
ሰው ውሎውን ይመስላል። ውሎህ የት ነው? ከማን ጋር? ሰዎች ጠጪ የሚሆኑት በጓደኛ ሰበብ ነው። ቃሚ፣ አጫሽ የሚሆኑትም በጓደኛ ተፅእኖ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም "ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ" የሚባለው።
ከመጥፎ ሱስ መውጣት፣ ባህሪህን መግራት ትፈልጋለህ? ከልብህ ከሆነ ውሎህን አስተካክል። ልጅህ ከመጥፎ አዝማሚያ እንዲመለስ፣ መስመር እንዲይዝልህ ትፈልጋለህ? ሰበብ ሳታደርስ ጠዋት ማታ አትጨቃጨቅ። ይልቁንም ውሎው ላይ አጥብቀህ ስራ። ካልሆኑ ጓደኞች ጋር ገጥሞ ከሆነ የምትችለውን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለህ ለየው።
ለብዙዎች በዲንም ይሁን በዱንያ መቃናት መልካም ጓደኛ ትልቅ ድርሻ አለው። እስኪ በህይወት ጉዟችሁ ላይ አነሰም በዛ ላገኛችሁ ስኬት ወይም መልካም ለውጥ አስተዋፅኦ ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ለአፍታ አስቧቸው። በተቻለ መጠን ውለታ መላሽ ሁኑ። እሱ ቢቀር አመስጋኝ ሁኑ። ከዚያም በላይ በዱዓእ አስታውሷቸው።
ጓደኝነት ኣኺራን ከነጭራሹ ሊያጨልም፣ ኩ. ፍ. ር ላይ ሊጥል ይችላል። በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ለተረዱት እውነት እጅ መስጠት አቅቷቸዋል?! በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ውስጣቸው እያወቀ እምነት ቀይረዋል? ስንት ወንዶች ሴት ተከትለው፤ ስንት ሴቶችም ወንድ ተከትለው ዘላለማዊ ህይወታቸውን አጨልመዋል?! የተሰጠን እድል ከእጃችን ሳያፈተልክ፣ ነፍሳችን ሳትሾልክ በፊት ሳይመሽ እናስብበት። እንወስን በጊዜ። ነገ ፀፀት እንዳይበላን። ጌታችን እንዲህ ይላል:-
{ وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا (27) یَـٰوَیۡلَتَىٰ لَیۡتَنِی لَمۡ أَتَّخِذۡ فُلَانًا خَلِیلࣰا (28) لَّقَدۡ أَضَلَّنِی عَنِ ٱلذِّكۡرِ بَعۡدَ إِذۡ جَاۤءَنِیۗ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِلۡإِنسَـٰنِ خَذُولࣰا (29) }
{በዳይም፡ «ምነው ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)። «ዋ ጥፋቴ! ምነው እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ። (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)። ሰይጣንም ለሰው በጣም ለውርደት አጋላጭ ነው።} [አልፉርቃን፡ 27-29]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 2/2016)

https://t.me/B1e9h
Forwarded from ተውሒድ የሁሉም ነብያቶች ጥሪ ነው። (Bint Mohammed አላህ ከዐርሹ በላይ ነው።)
አሠላምአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ውድና የተከበራችሁ እህት ወንድሞች ይች እህታችን ስሟ ተምሬ አራጋው ጎቸል ትባላለች ከፓስፖርቱላይ እንዳለው በጠለብ ከአራትና አምስት ወር በፊት ሳኡድ ጂዳ ከተማ ገብታ ነበር እናም አሰሪዋ መንገድ ላይ ጥላታለች አሉን። አእምሮዋም ትክክል አይደለም ቪዶወውላይ እንደምታዩት።የቀረጿትም ልጆች ልንወስዳት ስንል ሴትየዋ እምቢአለችን አሉ በሰአቱ ዘወር ብለው ሲመለሱም ከቦታው እንዳላገኙዋት ነው የተናገሩት እና ጂዳ አካባቢ ያላችሁ በተለይ እባካችሁ ይችን እህታችንን ያያት ካለ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

አላህ ሁላችንም ይጠብቀን እሷንም ያስገኛት!!

እኔ የሰፈሯ ልጂ ነኝ ካገኛችኋት

0532053175 Bint Mohammed በዚህ ቁጥር በዋሳብም ወይም በመስመር ያገገኙኛል ይደውሉ የሠማችሁም አደራ ሸር አድርጉልኝ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሱፊያው ዓለም በርካታ የሚመለኩ ቀብሮች አሉ። ቀብሮቹ ዘንድ በመሄድ ልጅ፣ ዝናብ እና የተለያዩ ሐጃዎችን ይማፀናሉ። የሞተ ሰው እንኳን የነሱን ጉዳይ ሊፈፅም ከራሱ፣ ከተሰራለት ዶሪሕ እንኳ መከላከል አይችልም። ይሄው ይሄ "ወሃቢ" የሆነ ጎርፍ ዶሪሑን ነቅሎ እየወሰደው ነው።
{ أَیُشۡرِكُونَ مَا لَا یَخۡلُقُ شَیۡـࣰٔا وَهُمۡ یُخۡلَقُونَ (191) وَلَا یَسۡتَطِیعُونَ لَهُمۡ نَصۡرࣰا وَلَاۤ أَنفُسَهُمۡ یَنصُرُونَ (192) }
"ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን? ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)?" [አልአዕራፍ፡ 191-192


https://t.me/B1e9h