Al EHSAN አል_ኢህሳን
187 subscribers
417 photos
45 videos
2 files
653 links
የቻናሉ አላማ
1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ
2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት
3 ለወጣቶች ምክር
4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል።

ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን

ለአስተያት @S1u9l
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇
Download Telegram
የኢራን የውጭ ገዳይ ሚንስትር አሚር አብዶላሂ

“እራስን ለመከላከል በጽዮናዊው ወታደራዊ ሰፈሮችን ማጥቃት በተባበሩት መንግስታት ቻርተር የተረጋገጠ ህጋዊ መብት ነው

ኢራን ማንኛውንም ጥቃት በመጋፈጥ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና ብሄራዊ ጥቅም በፅናት ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ታረጋግጣለች

ማንኛውንም ጥቃት በመመከት ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተጨማሪ የመከላከያ እርምጃዎችን ከመውሰድ ወደ ኋላ አትልም
ራስን የመከላከል መብትን በመጠቀም የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰዳችን ለክልላዊ ደህንነት ያለንን ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ መሆኑን ያረጋግጣል


https://t.me/B1e9h
ልቤ ሆይ!!
~
ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ
ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ ያስፈራኛል - በጧትም በማታ
እጄ ሆይ ተመከር - "እጄን በ’ጄ" እንዳልል - በሚያስጨንቅ ቦታ
እግሬ እግር አታብዛ - ታዋርደኛለህ - በጭንቁ ቀን ለታ
አዋጅ ሰምቻለሁ - እጅግ የሚያስፈራ - ከሰማዩ ጌታ።

(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ) [النور 24]
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24]
ኢብኑ ሙነወር


https://t.me/B1e9h
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጀነትን ሽታ የማያገኙ ሴቶች

🦯ኡስታዝ አብዱረዛቅ አል-ሀበሺይ

https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎞  ትንሿ ዒድ!

🎙ኡስታዝ ኢብራሂም ሙሳ እና ኡስታዝ ጂብሪል አክመል

https://t.me/B1e9h
አስተማሪና መሳጭ ታሪክ!
~
በሰዑዲ የሚኖር የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ሄድን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5ሺ ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳ-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ፡ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡
ሹፌሩ፡ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
* “ከየት ነው ወንድም?”
- “ከየመን”
* “የት ነው የምትሄደው?”
- “የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ።”
* “ህጋዊ ነህ?”
- “አይደለሁም”
* “ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
- “ለዋስትና 2ሺ ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
* “እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
- “ስድስት ቀን!”
* “እየፆምክ አይደለም ኣ?”
- “አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
* “ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?”
- “ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!”
* “ለስራ ነው አመጣጥህ?”
- “በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
* “በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”
- “ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲጠይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ።”
* “ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡
- ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
* እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
* “የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
- “አዎ!” አለ፡፡
* “ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
- “ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
* “አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ ራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡
- “ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡
* ባልደረባዬ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡
ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡
* “ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
- “እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡
ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡
በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡
* “በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡
የተተረጎመ
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 25/2010)

https://t.me/B1e9h
ሲሳያችን ከሐላል ወይስ ከሐራም
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
👆👆👆
🔖 ሲሳያችን ከሐላል ወይስ ከሐራም

https://t.me/B1e9h
ከፈተናዎች መውጫ #1
ኢብኑ/ሙነወር
“ከፈተናዎች መውጫ”
ክፍል - 1
ሚያዚያ 14/2016 ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቀረበ

https://t.me/B1e9h
ከፈተናዎች መውጫ #2
ኢብኑ/ሙነወር
“ከፈተናዎች መውጫ”
ክፍል - 2
ሚያዚያ 14/2016 ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቀረበ

https://t.me/B1e9h
ሰለፊያ እውነታና ተግባር
ኢብኑ/ሙነወር
ሰለፊያ፡ እውነታና ጥንቃቄ
ኢብኑ ሙነወር

https://t.me/B1e9h
#አላህ የመልካም ሰሪዎችን ምንዳ በከንቱ አያስቀርም

#አባት ከአምስት #ሴት ልጆቹ ጋር ይኖራል ለትዳርም ስለደረሱ አባት ከታላቋ ጀምሮ በቅደም ተከተላቸው እንዲያገቡለት ይፈልጋል።

ታላቋ ግን አባቷን መንከባከብ በመፈለግ ማግባት አልፈቀደችም ታላቋ ብቻ ስትቀር አራቱ ልጆቹ አገቡ።እሷም አባቷ አጀሉ ደርሶ እስኪሞት ድረስ ተንከባከበችው ። አባት ከሞተ በኃላ ግን ይቺ ሴት ብቻዋን ቀረች ። የአባታቸውንም ኑዛዜ አገኙ እሱም " አደራ ራሷን መስዋዕት ያደረገችው እህታችሁ ሳታገባ ቤቱን እንዳትካፈሉ " የሚል ነበር...

ነገርግን አራቱ እህቶች የትልቅ እህታቸውን ጉዳይ ቦታ ሳይሰጡ ተሽጦ መከፋፈልን ፈለጉ ።

ትልቋ እህታቸው ቤቱን እንደሚሸጡት ስትረዳ ለመግዛት ለተስማማው ሰው በመደወል ከምትኖርበት ቤት ውጭ ሌላ እንደሌላትና ያለውን ሁኔታ አስረድታ ነገሮችን እስክታስተካክል ድረስ ጊዜ እንዲሰጣት አስፈቀደች ። ቤቱን የሚገዛውም ሰውም ፍቃደኝነቱን ገለፀላት። ቤቱ ተሽጦ ለአምስቱ እህቶች ተከፋፈለ።

ከተከፋፈለ በኃላ አራቱ ወደ ትዳራቸው ተመለሱ ታላቋ እህታቸው ከቤት ቀረች። ይቺ ሴት ወላጇን በመንከባከብ ባሳለፈችው ጊዜ አላህ ልፋቷን በዱንያም ከንቱ እንደማያስቀርባት ተማምና በአላህ ተስፋ አድርጋለች።

ወራት አለፉ ቤቱን ከገዛው ሰው ስልክ ተደወለላት ቤቱን እንድትለቅ መልክት እንደሚያስተላልፍ በመገመት በፍራቻ '#ይቅርታ እስካሁን ቤት አላገኘውም' አለችው። እሱም ችግር የለም! የደወልኩም ለሱ ሳይሆን ቤቱን '#መህር' አድርጌ እንድታገቢኝ ልጠይቅሽ ነው ፍቃድሽ ከሆነ ባልሽ እሆናለው ፍቃደኛ ካልሆንሽም ችግር የለም! ቤቱ ግን ያንቺ ነው አላት ። #አጂብ

ይህን ስትሰማ አለቀስች 😭😭
ተስማማችም አላህም የመልካም ሰሪዎችን ምንዳ ከንቱ አያስቀርምና በመልካም ተካሰች ። አባቷን በተንከባከበችበት ቤት ትዳር ይዛ ባሏን መንከባከብ ጀመርች 💍

ያ አላህ ! በየቤቱ ያንተን ተስፋ ብቻ የሚጠባበቁ እህቶች አሉና መልካምን ትዳር ወፍቃቸው🤲🤲🤲

ከአረብኛ የተተረጎመ

https://t.me/B1e9h
ዛሬ የመጽሐፍ ቀን ነው አሉ መሰል። አላማዬ ስለቀኑ ሳይሆን ኢስላማዊ መጽሐፍ ስለሚያቃጥሉት ጉዶች ነው።
ያቃጠሏቸውና ለማቃጠል ያዘጋጇቸው እንዲሁም በውሃ ሊዘፈዝፏቸው ያሰቧቸው መጽሐፍት "መንዙማ" የሚለው የሳዳት ከማል መፅሐፍ፣ "መውሊድ!፣ ኢብኑ ተይሚይያህ… ወዘተ የሚሉትን የኢብኑ ሙነወርን መጽሐፍቶች ነው። ለማቃጠል ያነሳሳቸው ከመጽሐፍቶቹ ጸሐፊዎች ጋር አለመግባባታቸው እንጂ መጽሐፍቶቹ ውስጥ ለመቃጠል የሚዳርግ መጥፎ መልዕክት ኖሮ አይደለም።

ይህን የፈጸሙት ሰዎች ሙስሊሞች ናቸው። ከሙስሊምም አልፈው ብቸኛና እውነተኛ "ሰለፊይ" ነን ብለው የሚሞግቱ ናቸው። እኔ እነዚህን ፌክ ሰለፊያ ነው የምላቸው። እነዚህ ትክክለኛውን የሰለፎች ጎዳና እና ትክክለኛ ሰለፊዮችን የሚያሰድቡና መንገዱን ሌሎች እንዲጠሉት የሚያደርጉ፣ የሚያወሩትንና የሚተገብሩትን የማያውቁ ጉዶች እንጂ ሰለፊይ ናቸው ማለት ይከብደኛል።

"መውሊድ" የሚለውን መጽሐፍ መውሊድ አክባሪ የሆኑ አሕባሾችና መሰል ቡድኖች እንኳ አቃጥለው ጀብዱ እንደሠራ ሰው አላሳዩንም። "መንዙማ" የሚለውን መጽሐፍ መንዙማ ወዳጆች አቃጥለው አላሳዩንም። ታዲያ መውሊድና መንዙማን እቃወማለሁ የሚል ሰው ደራሲውን በመጥላት ብቻ ተነሳስቶ መውሊድና መንዙማ የሚቃወሙ መጽሐፍትን ያቃጥላልን? እኔ እንዲህ አይነት ሰለፊይ ነኝ ባይ ሰምቼም አይቼም አላውቅም።
እነዚህ ስሜታቸውን ያላሸነፉ በእውር ድንበር የሚጓዙ ያልተገራ አንደበት ያላቸው ናቸው፤ አላህ ይምራቸው። ምክንያቱም ባቃጠሏቸው መጽሐፍቶች ውስጥ ያለን ሐዲሥና ቁርኣን አቃጥለዋል።

ሐሰን ታጁን ጠላሁ ብዬ የተረጎመውን የኢማሙ ነወዊይ ሪያዱ-ስ'ሷሊሒን ወይም የኢብኑ ሐጀርን ቡሉጙ-ል-መራም ወይም የሸይኽ ፈውዛንን አል-ኢርሻድ… በእሳት አላቃጥልም።

በዚህ አካሄዳቸው ሳዳትና ኢብኑ ሙነወር አላህ አግርቶላቸው ቁርኣንን ቢተረጉሙም ሊያቃጥሉት ነው ማለት ነው።
አሁን ይሄ እብደት ምን አይነት ሰለፊይነት ነው? ወላሂ ትክክለኛ የደጋግ ሰለፎች መንገድ ከነዚህ ስሜት ከጋለባቸው ሰዎች አካሄድ የጠራ ነው።
አላህ ወደ ትክክለኛው ሐዲድ ይመልሳቸው። ሚዛናዊነትን ያላብሳቸው፣ ካሉበት ጡዘትና እልህ ያብርዳቸው። እኛንም ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ይምራን።

https://t.me/B1e9h
☀️ قَالَ رَسُولُ اللهﷺ :


(أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ ، فمَن صلَّى عليَّ صلاةً صلَّى الله عليهِ عَشرًا)


📚 صحيح الجامع

✔️ የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:

በጁሙዓ ቀንና ለሊት በኔ ላይ ሶለዋት ማውረድን አብዙ, ምክኒያቱም በኔ ላይ አንድ ሶለዋትን ያወረደ ሰው አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋትን ያወርዳል።



https://t.me/B1e9h
🔹 የነቢዩላህ ዘከሪያ ዱዓ🔹
ነቢዩላህ ዘከሪያ አሏህ ወራሽ ልጅን እንዲሰጣቸው ዱዓ ባደረጉበት ሰዓት ላይ የተጠቀሙት ቃል ይደንቀኛል።

رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا
«ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡"

ይህን ካሉ በኃላ የዱዓቸውን መደምደሚያ እንዲህ አስከተሉ፦

وَأَنتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ
"አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ"

ኢማም አሉሲይ በዚህ አንቀፅ ተፍሲር ላይ እንዲህ አሉ:-
"የእሳቸው ንግግር ሲብራራ "ጌታዬ ሆይ! ወራሽ ልጅን ስጠኝ። ውሳኔህ ሆኖ የሚወርሰኝን ልጅ ባትሰጠኝም፤ አንተ ምድርና ሰማያትን የምትወርስ፤ ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ።" ማለት ነው።
ይህም ረቂቅ የሆነን የዱዓ አደብ ይዟል። ለምኜህ የምፈልገውን ባትሰጠኝ፤ ጉዳዬን ላንተ ጥያለሁ። አንተ በቂዬ ነህ። ካንተ መልካም የሆነን ምትክ እንጂ አላገኝም። ይህ የኢስላም አስኳል ነው። ይህ የኢማን መቅኔ ነው።


https://t.me/B1e9h
Forwarded from "ኡማ ቲቪ " Tv
እኚህ ሰው abdulmunaf yunusa sarina ይባላሉ ፡ እና በጠዋት ይነሱና በመኪና ለመጓዝ አስቸጋሪ የሆኑ ቦታ ላይ ያላቸውን የሩዝ እርሻ ለመጎብኘት ሞተር ሳይክላቸውን ይዘው ይወጣሉ ።
.....
በመንገዳቸውም ላይ የሚያገኟቸውን ሰወች ሰላም እያሉ ፡ በአካባቢው ያሉትን ገበሬዎች ፡ እርሻው እንዴት ሆነላችሁ ፡ ቤተሰብስ ሰላም ነው ወይ ብለው እየጠየቁ ፡ የታመመ ፡ ያዘነ ፡ ወይም የወለደች ሴት ካለች ገባ ብለው ጠይቀው ነው ወደ ስራቸው የሚሄዱት ።
.....
እና አሁን ደግሞ እኚህ ለመኪና አስቸጋሪ ቦታ በሞተር እየሄዱ ስራቸውን እየሰሩ ያሉት ፡ ኩራት የሚባል ጫፋቸው ሳይደርስ የወለደና የታመመን ሰው የሚጠይቁና የሚረዱ ሰው ማን ናቸው የሚለውን እንይ ።
......
abdulmunaf yunusa sarina በነዳጅ ዘይት እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ ናይጄሪያዊ ቢሊየነር ናቸው ። በአሁኑ ወቅት ፡ በመላ ናይጄሪያ ከ50 በላይ የነዳጅ ማደያዎች እንዲሁም በካኑ ግዛት ያለው ግዙፍ ዩኒቨርስቲ የሳቸው ነው ። ይህ ብቻ አይደለም ። አዝማን የሚባል አየር መንገድ የግል ንብረታቸው ነው ። በስሩም ሁለት ቦይንግ 747 አንድ ኤርባስ እና ሌሎች አውሮፕላኖች አላቸው ። አጠቃላይ የሀብታቸው መጠንም ወደ 3 ቢሊየን ዶላር ይጠጋል
...
ይህ ሁሉ ግን ለሳቸው ምንም አይደለም ። ይህ ሁሉ ንብረት እያላቸው ኩራት ጫፋቸው ደርሶ አያውቅም ። አሁንም በሞተር ይጓዛሉ ። አሁንም የታመመ ይጠይቃሉ ። ህይወታቸው ይሄ ነው ።
....
ሚሊየን ብሮች ያልቀየሩት ምርጥ ስብእና
©Wasihun tasefaya
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
እስኪ ዛሬ ለኔም ለእናንተም ኻሰተን ለእህቶቻችን ማነቀቃያ ትሆን ዘንድ በዘመናችን ካሉ ድንቅ የሴት ሸይኻህ በወፍ በረር አንዷን ልጠቁማቹ

ስሟ ሸይኻህ ዱክቱራህ ካሚለህ ቢንት መሃመድ ቢን ጃሲም ቢን ዐሊይ አል ጁሃሪል ከዋሪ ትባላለች ዱክቱራህ ካሚለቱል ከዋሪ በሚባለው በስፋት ትታወቃለች ኳታራዊ ነች እጅግ ድንቅ የሆነች የእውቀት ባለቤት ነች ፊቂህ ነህው ኡሱሉል ፊቂህ ተፍሲር እና ሌሎችም ፈኖች ላይ ያላት ተመኩን ዐጂብ ነው

የተለያዩ 17 በዑሉሙ ተፍሲር ፣ ዐቂዳህ ፣ ፊቂህ ፣ ኡሱሉል ፊቂህ ፣ ቀዋኢዱል ፊቂሂያህ ፣ ሲራህ ፣ ሉገህ ፣ መንጢቅ ፣ በላጋህ በመሳሰሉት ፈኖች ላይ ወሳኝ ኪታቦች ተእሊቃቶች እና ኢኽቲሳራቶች አሉዋት ከነሱም ውስጥ በከፊሉ

1ኛ፦ አል ሙኽተሰሩ ሚን ሸርሂል ሙምቲዕ፦ ይህ ኪታብ የኢብኑ ዑሰይሚኑን የዘመኑ የፊቂህ ኢንሳይክሎፒድያ ሚባለውን ግዙፉን ሸርህ አል ሙምቲዕን ያሰጠረችበት ኪታብ ነው የተለያዩ ፈዋኢዶችንም ጨምራበታለች በጃሚአዎች ውስጥ እንደ ዋና ማስተያያ ይወሰዳል ሸይኹ ከመዝሃባቸው ሃናቢላ ወጥተው ተርጂህ ሲያረጉ እሷ የተለያዩ ከመዝሃቡ ፈዋኢዶች ትጨምራለች

2፦ ተፍሲሩ ገሪቢል ቁርአን
3፦ አል ፈዋኢዱል መስጡራህ ፊ ሀሊ አልፋዚ ኪታቢ ኢዕላሚ ሱነቲል መንሹራህ(2 ሙጀለድ)
4፦ አልወሲጥ ፊ ነህው
5፦ አተጥቢቁል ኢዕራቢይ
6፦ አፍናኑ ሲያገቲ ፊ ሀሊ አልፋዚ ዱሩሱል በላገቲ
7፦ አደውኡል ባሂር ፊ ሀሊ አልፋዚ ረውደቱ ናዚር ወጀነቱል ሙናዚር
8፦ አል ዐዝቡል መዒን ፊ ሃሊ አልፋዚ ሚንሃጁ ሳሊኪን
9፦ ሸርህ ኪታቡ ተህቢሪ ፊ ዒልሚ ተፍሲር(2 ሙጀለድ)
10፦ ሸርህ ቀዋኢዱል ፊቂሂያህ
11፦ ቀድሙል ዐሊም ወተሰልሱሉል ሃዋዲስ በይነ ሸይኺል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ወልፈላሲፋህ መዐ በያኒ መን አኽጠአ ፊል መስአለቲ ሚነ ሳቢቂን ወልሙዐሲሪን

12፦ አል ተስሂሉል ሙቅኒዕ ፊ ሃሊ አልፋዚ ረውዲል ሙረቢዕ (4 ሙጀለድ)
14፦ አል ኹላሰቱ ፊ ኡሱሉል ፊቂህ
15፦ አል ሙጅላ ፊ ሸርሂ ቀዋኢዱል ሙስላ ፊ አስማኢላሁል ሁስና
16፦ ሸርሁ ኑኒየቲ ሸይኽ ዐኢድ ዐዒድአል ቀርኒ
17፦ አህካሙ ሰላቲል ኹሱፍ

ቡግየቱል ሙቅተሲዲ ሸርህ ቢዳየቱል ሙጅተሂድን ተዕሊቅ እና ተህቂቅ አርጋዋለች
አትደነቁምን? አትገረሙምን ?
©Abdulhafiz_Mitiku
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!

https://t.me/B1e9h
ከስደተኛ ሴት

እየተበደሉ ብዙ እየተከፉ መኖርን በሀሴት፡
ተምረህ ተለወጥ ከስደተኛ ሴት....፡

......ያች ስደተኛ....

ስራ እየበዛባት አይወልቅም ቀሚሷ፡
ግን ስትነጋገር ፈገግ ይላል ጥርሷ፡
ለብሶተኛ ወንድ ዐርዐያህ ነች እሷ፡

እባክህ ወንድ ሆይ፤
ተበደልኩኝ ብለህ አሏህን አታማር....
ህመም መደበቅን፤
ስቃይ መሸከምን ከሴት ልጆች ተማር


Nuredin

https://t.me/B1e9h