አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
2.07K subscribers
94 photos
36 videos
13 files
126 links
የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።
Download Telegram
የስላሴ ምሳሌዎች ሲፈተሹ —ክፍል 3
*******************
ስላሴን በእንቁላል
**
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ።

ቀደም ብሎ በሁለት ክፍሎች ሁለት የስላሴ (የውሃ እና በወንድ) ምሳሌዎችን አይተናል።በዚህ በሶስተኛው ክፍል የእንቁላልን ምሳሌ እንፈትሻለን።

ምሳሌው ሲብራራ:—
***
"One simple illustration of the Trinity is the egg. A chicken egg consists of a shell, a yolk, and an egg white, yet it is altogether one egg. The three parts create a unified whole"

"ቀላሉ የስላሴን አንድነት እና ሶስትነት የሚያሳየው እንቁላል ነው። የድሮ እንቁላል ሶስት ክፍሎች አሉት እነሱም:—(ቅርፊት:ነጭ አስኳሉ እና ቢጫው) ሶስት እንቁላል ብለን እንደማንጠራው ሁሉ ሶሰት አምላክ ብለን አንጠራውም" ይላሉ።

ችግሩ ምንድን ነው?
****

1) የመጀመሪያው ነገር አምላክህን በሚበሰብስ እና በሚበላሽ ነገር ምሳሌ ማደረግ አሳፋሪ ነው።

2) በምስሉ ላይ እንደምታዩት እንቁላል ሶስት የተለያዩ ክፍሎች አሉት ፣ሶስቱም አገልግሎታቸው የተለያየ ነው፣ ነጩና እና ቢጫው ለምግብነት ሲውል ቅርፊቱ ግን ይጣላል። በተጨማሪም የሶስቱም ይዘት በፍፁም የተለያየ ነው። ቅርፊት ጠጣር ሲሆን ሁለቱ ፈሳሽ ናቸው። በአገልግሎትም የተለያዩ ናቸው።

ይህን ምሳሌ ከወሰድን የአንድን እንቁላል #ቅርፊቱን #ነጩን እንዲሁም #ቢጫውን #እንቁላል ብለን እንደማንጠራው ሁሉ፣ አብን ,ወልድን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ለየብቻቸው #አምላክ ብለን መጥራት አንችልም።

3) ሌላኛው ነጥብ እንቁላል ሶስት ክፍል ብቻ መቼ አለውና? ከቅርፊቱ ስር ያለችው ስስ ከውስጥ የተለጠፈችው ነገር አራተኛ አይሆንምን? ከውስጥስ ጫጩቱ አድጎ እስኪፈለፈል ድረስ የሚጠቀመው ጫፍ ላይ የሚገኝ አየር Packed Air (የታመቀ አየር) አምስተኛ አይሆንምን?

4) በተጨማሪ አንድን እንቁላል መጥበሻ ላይ ሰብረን ቅርፊቱን ጥለን አንድ ህፃን ልጅ አምጥተን ይሄ ምንድ ነው ብለን ብንጠይቅ "እንቁላል" መባሉን አይቀይረውም ። ነገር ግን ቅርፊቱን— የስላሴ አንድ ክፍል የነበረውን ጥለንዋል።

5) እንቁላሉ ወደ ጫጩት ሲቀየር አሁንም ቅርፊቱ ተሰባብሮ ሲወድቅ ሁለቱ ግን ወደ ሌላ ህይወት ወዳለው ነገር ተቀየሩ? ይህም ሁለቱ ወደ ሌላ ነገር Transform ማድረግ ይችላሉ አንዱ ግን አይችልም ወደሚል እሳቤ ያመራል።

6) ከሁሉ የከፋው ደሞ አምላክን በሚገማ እና በሚበላሽ ነገር መመሰል እጅግ አሳፋሪ ነው።

Ash-Shura 42:11

فَاطِرُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِۚ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا وَمِنَ ٱلْأَنْعَٰمِ أَزْوَٰجًاۖ يَذْرَؤُكُمْ فِيهِۚ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ #የሚመስለው #ምንም #ነገር #የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡

አምላክን ውስብስብ በሆነ ምሳሌ እየገለፃችሁ መከራችሁን አትብሉ!!

@abuyusra3