አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
806 members
2 photos
1 video
1 file
6 links
የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።
Download Telegram
to view and join the conversation
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።

አላህ ሱብሐነሁ ወተአላ እስከፈቀደ ድረስ በዚህ ቻናል በእኔ የተዘጋጁ የንፅፅር አስተምህሮቶች እና ተዘማጅ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል።© አቡ ዩስራ

t.me/abuyusra3
ጠቃሚ የቴሌግራም ቻናሎች

💧ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል 💧

t.me/hidayaislam

💧ሒዳያ ንጽጽራዊ የውይይት መድረክ 💧

https://t.me/joinchat/Ez5a1EF-_IRPsLLoe6dFPg

💧ወሒድ የንፅፅር መድረክ 💧

t.me/tgvvyhb

💧ወሒድ የንፅፅር ማህደር 💧

t.me/Wahidcom

💧የየሕያ ኢብኑ ኑህ ትምህርቶች💧

t.me/Yahya5

💧የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች💧

t.me/abuhyder

💧የኦርቶዶክስ ቀኖናዎች ሲፈተሹ 💧

t.me/orthox

💧የኡስታዝ ሙሐመድ ከድር ግሩፕ 💧

https://t.me/joinchat/GSe6O0MJxo4-tLDh6Wj1wA
ኢየሱስ ዐሰ አልተሰቀለም ከተባለ በሱ ቦታ የተሰቀለው ማነው?

ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ማን ነው የተሰቀለዉ በሚለው ዙርያ ምን ይላሉ?

1. #ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰዉ ከሌሎቹ ወንጌል በተለየ መልኩ ዮሀንስ ላይ ( የሐ 19፡17 ) መስቀሉን እየሱስ እንደተሸከመዉ ተደረጎ የተፃፈዉ በግዜዉ ስም ዖን የቀሬናን በእየሱስ ቦታ ተሰቅሏል የሚል ዜናዎች ይሰራጩ ነበር./#Simon of Cyrene was #crucified #instead of #jeuses That Story was already in Circulation by the last decade of the 1st Century CE…./ የመፅሀፉን ፎቶ ለማየት ይህን ሊንክ ይጠቀሙ http://www.bilal.link/up/MzY3OA ስለዚህ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች እንኳን ‹‹ ሌላ ሰዉ ነው እያሉ ነዉ››!!( The History of heresies and their refutations)


2. የተለመደዉ የክርስትና አስተምህሮ እየሱስ በ3ኛዉ ቀን ከሞት ተነስቷል ቢልም የግኖስቲክ መፅሃፍት ናግ ሀማዲ እየሱስ ከስቅላት ተርፎ ስምኦን በስህተት በሱ ቦታ ተስቅሏል ብለዉ ያምናሉ፡፡ The Offical Christyan Version claims that Jesus was raised from death on the 3rd day but the Gnostic (Essences) text of Nag Hammadi claim that Jesus survived the crucifixion and #simon of #Cyrene was mistakenly Crucifed instead of jesus.( The quantum Vision of simon Kimbangu : Kintuadi in 3D P 23) ምስሉን ለማየት ይህን ይጫኑ http://www.bilal.link/up/MzY3OQ


3. የግኖስቲክ ዲክሽነሪ Simon of Cyrene በሚለዉ ስር ስምኦን በእየሱስ ቦታ ተስቅሏል ብሎ በአንደኛዉ ክ/ዘየነበሩ ባሲሊዲያንስ የተባሉ ክርስቲያኖች እንደሚያምኑ ያስቀምጣል/ In the Canonical Gosples, Simon carried the cross of Jesus when Jesus was unable to do so . Basilidis thought that Simon was Crucifed instead of Jesus.( Adictonery of Gnosticism P 2294) ምስሉን ለማየት ይህን ይጫኑ http://www.bilal.link/up/MzY4MA

4. እየሱስ ሳይን ስምኦን የቀሬናን ተገዶ መስቀሉን እንዲሸከም ተደርጓል በኋላም በእየሱስ ምስል ተመሰለ ሰዎችም ባለማወቅና በስህተት እየሱስ መስሏቸዉ እሱን ሰቀሉት እየሱስ ደግሞ የስምኦንን ምስል ይዞ ዳር ቆሞ ይስቅባቸዉ ነበር ይላል፡፡ (The Ante-Nicne Fathers Vo 1) ምስሉን ለማየት ይህን ይጫኑ http://www.bilal.link/up/MzY4MQ

#አሁን ይህን ካነበቡ ዘንዳ አላህ (ሱወ) ምን እንደሚል ያንብቡ
4፡157 «እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ (157)

http://t.me/abuyusra3
በክርስትና አስተምህሮ መሰረት ነብዩ ህዝቅኤል እየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት የነበረ ነብይ ነው። እግዝአብሔር እንዲህ አለኝ ብሎ ተናግሯል።

"የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ "ብሎ ከቁጥር አንድ ይጀምርና ማንም ልጅ በአባቱ ሓጢአት መጠየቅ እንደሌለበት ልጅም በአባት ሃጢአት መጠየቅ እንደሌለበት ያስተምራል ሁሉም በስራው እንደሚጠየቅ ይናገራል።

በመቀጠል ሃጢአትን ያደረገ ሰው የአምላክን ምህረት እንዲያገኝ ከሃጢአቱ መመልስ፡ የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ እንዲሁም ቅን ነገር ቢያደረግ በህይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም በማለት ይናገራል።

ኢየሱስ ወደ ምድር ሳይመጣ ነብዩ ህዝቄኤል ከእግዝአብሔር የሰማውን ይህን መልእክት የነገራቸው ሰዎች ከላይ የተቀመጠላቸዉን መስፈርቶች ካሟሉ ድነዋል ማለት ነው። እንዲያ ከሆነ የእየሱስ መሞት ለነዚያ ሰዎች ምን ይሰራላቸዋል ?


📌ትንቢተ ሕዝቅኤል 18:19-22

19 እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።20 ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤ ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም፤ የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የኃጢአተኛውም ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።21 ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።22 የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም፤ በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።

http://t.me/abuyusra3
መስካሪም በአላህ በቃ

ቁርኣን 4፡163-170

"እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ (163) ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውን መልክተኞች (እንደላክን ላክንህ)፡፡ አላህም ሙሳን ማነጋገርን አነጋገረው፡፡ (164) ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች የኾኑን መልክተኞች (ላክን)፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ (165) ግን አላህ ባንተ ላይ ባወረደው ይመሰክራል፡፡ በዕውቀቱ አወረደው፡፡ መላእክቱም ይመሰክራሉ፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡ (166) እነዚያ የካዱት ከአላህም መንገድ ያገዱት (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳቱ፡፡ (167) እነዚያ የካዱ የበደሉም አላህ የሚምራቸውና (ቅን) መንገድን የሚመራቸው አይደለም፡፡ (168) ግን በውስጧ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ የገሀነምን መንገድ (ይመራቸዋል)፡፡ ይህም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ (169) እናንተ ሰዎች ሆይ! መልክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ፡፡ እመኑም ለናንተ የተሻለ (ይኾናል)፡፡ ብትክዱም (አትጐዱትም)፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ (170)"

http://t.me/abuyusra3
የስላሴ ምሳሌዎች ሲፈተሹ —1
*******************

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ።

በክርስትናው አለም የአምላክን አንድነት እና ሶስትነትን ለሰው ልጆች ለማስረዳት የማይቆፈር ድንጋይ ፣የማይቦጠጥ ተራራ የለም። አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር እሱንነቱን እንዲያውቁት፣የሱን ትእዛዝ እንዲተገብሩ ነው።

ታዲያ መጀመሪያ ስለ እሱ አምላክነት ለመረዳት ሰዎችን እንዲህ አወዛጋቢ በሆነ ነገር ማንነቱን መግለፅ አለበትን? አብዛኛውን ግዜ ክርስቲያኖች ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ስላሴን ለማስረዳት የሚሰጡ ምላሾች ሰዎች የፈጠሩዋቸው ምሳሌዎች ሁሌም እንከን አይጠፋቸውም። ከእነዚህ ምሳሌዎች ለዛሬ አንዱን እንመለከት።

ስላሴን በ ውሃ/ Water/
****************

ይህ ምሳሌ ሲያዩት ትክክል የሚመስል ነገር ግን ትኩረት ከሰጡት ግን ውስጡ እንደሌሎቹ ምሳሌዎች በስህተት የተሞላ ነው።

ምሳሌውን ሲያብራሩ:—

"The trinity is like water. Water has three states: solid, liquid, and gas.Although the water changes forms it is still H2O. Just as water changes forms so too is the trinity.

"ስላሴ እንደ ውሃ ነው ።ውሃ በሶስት ቅርፅ ይገኛል በጠጣር (በረዶ),በፈሳሽ (ውሃ),በጋዝ (በእንፋሎት)። ምንም እንኳን ውሃ ቅርፁን ቢቀይርም ያው ውሃ ነው" በማለት ያስረዳሉ።

ችግሩ ምንድ ነው?
**********
አንድ የውሃ ሞለኪዪል (molecule) በአንድ ግዜ በሶስቱም ቅርፅ አይገኝም። ወይ ጠጣር /ፈሳሽ/ጋዝ መሆን አለበት ሶስቱንም ቅርፅ በተመሳሳይ ሰአት መያዝ አይችልም።

★በረዶ ሲቀልጥ ወደ ፈሳሽ
★ፈሳሹ ሲፈላ ወደ ጋዝ
★ጋዙ ሲቀዘቅዝ ወደ ፈሳሽ
★ፈሳሹ ሲቀዘቅዝ ወደ በረዶ

ከአንድ ይዘት ወደ ሌላ ይዘት ለመቀያየር የግድ ማሞቅ/ማቀዝቀዝ ይፈልጋል ይህ ካልሆነ በአንድ ግዜ ሊገኝ የሚችለው አንድ ቅርፅ ብቻ ነው።

ይህ ማለት አንዱ ቅርፅ ወደ አንዱ እየተቀየረ እንጂ ሶስት ሆኖ አይደለም። ምሳሌውን በስላሴ ስናደርገው ደግሞ አብ ወደ ወልድ ፣ወልድ ወደ መንፈስ ቅዱስ እየተቀያየረ እንጂ ሶስትም አንድም ናቸው የሚለው ምሳሌ ውድቅ ይሆናል።

እኛ ሲሞቅና ሲቀዘቅዝ ከአንዱ ወደ አንዱ የሚቀያየር አምላክ የለንም። አምላክን ውስብስብ በሆነ ምሳሌ እየገለፃችሁ መከራችሁን አትብሉ።

http://t.me/abuyusra3
የስላሴ ምሳሌዎች ሲፈተሹ —2
**********************

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ።

በክፍል አንድ የስላሴ ምሳሌዎችን መፈተሽ ጀምረናል ቀደም ብለን ያየነው፣ ስላሴን በጠጣር ፣በፈሳሽ እና በጋዝ የተመሰለበትን ከስላሴ ጋር እንደማይሄድ አይተናል። በዚህ ክፍል ሌላኛውን ምሳሌ እንፈትሸዋለን።

ምሳሌው ሲብራራ—
**********

"The Trinity is Like a Man who is a Father, Husband, and Son,The trinity is Like a man who is a father, husband, and son. Although he is one he has different roles to different people. The trinity is like this man."

ስላሴ ማለት ልክ እንደ ወንድ ነው። ይህ ሰው አባት ነው፣ባልም ነው፣ ልጅም ነው። ሰውየው አንድ ሲሆን ሶስት የተለያየ ድርሻዎችን ያከናውናል ይህ ሰው እንደዚሁ የስላሴ ተምሳሌት ነው " ብለው ያስረዳሉ።

ችግሩ ምንድ ነው?
***********
ይህኛው ምሳሌ አንድ ወንድ ሶስት አይነት ሚና ይጫወታል እነሱም #ለልጆቹ አባት ነው ፣#ለሚስቱ ባል ነው ፣#ለእናቱ (ለአባቱ )ልጅ ነው።

በዚህ ምሳሌ ሰውየው አንድ ሲሆን ሚናው ግን ሶስት ነው።በተመሳሳይ መልኩ ሶስት ሰው እንደማንለው ሁሉ እኛም ሶስት አምላክ ሳይሆን የምናመልከው አንድ አምላክ ነው ይላሉ።

የዚህ አመክንዮ ችግር "ወንድ" ተብሎ የተገለፀው አካል በዚህኛው አረዳድ አንድ ሲሆን የሚሰራቸው ስራዎች ግን ሶስት ነው ነገር ግን እነዚህ ሶስት ሚናዎች ለአንድ ሰው ሳይሆን #ለተለያየ #ሰው ነው። ይህ ማለት:—

* ለልጆቹ አባት
*ለሚስቱ ባል
*ለእናቱ/ለአባቱ ልጅ

1)ስለዚህ ይህ በስላሴ የተመሰለው "ወንድ" ሚናውን ከሚያጋጥመው ሁኔታ(Mode)አንፃር ይቀያየራል ማለት ነው። አምላክ የሆነ ነገር ሲገጥመው "አብ" ፣ሌላ ነገር ሲገጥመው "ወልድ" አሁንም ሌላ ሲገጥመው "መንፈስ ቅዱስ " ይሆናል ማለትን ያሲይዛል(ያመለክታል)።

2)በተጨማሪ አብን ወልድን እና መንፈስቅዱስን በስላሴ ቦታ ተክተን ለመረዳት ስንሞክር ። የስላሴ አምላክነት የሚሆነው /የሚገደበው በዝምድና ላይ ብቻ ይሆናል።

ለምሳሌ ይህ "ወንድ "ተብሎ የቀረበው አካል ለእኔ ምኔም አይደል!! ወይ ለእኔ አባቴ አልሆነ /ወይ ለእህቴ ባል አልሆነ / ወይም ለእናቴ ልጅ አልሆነ ምንም ዝምድና ከሌለን ለእኔ አምላኬ ሊሆን አይችልም።

3) ሌላኛው ይህ ምሳሌ አንድ ወንድ የባልና የአባት ሚናውን የሚወጣው ሲያገባ ነው ።ካላገባ ይህን ሚና መጫወት አይችልም።

4) ይህን ምሳሌ በሴቷ ያልተገፀበትስ ምክንያት ምንድ ነው ?ልክ እንደ ወንዱ አንዲት ሴት
#እናት, #ሚሰት,# ልጅ መሆን ትችላለች። "አምላክ" ወንድ ሆኖ መጣ ብላቹ ስለምታስቡ ይሆን?

አምላክን ውስብስብ በሆነ ምሳሌ እየገለፃችሁ መከራችሁን አትብሉ!!

@abuyusra3
የስላሴ ምሳሌዎች ሲፈተሹ —ክፍል 3
*******************
ስላሴን በእንቁላል
**
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ።

ቀደም ብሎ በሁለት ክፍሎች ሁለት የስላሴ (የውሃ እና በወንድ) ምሳሌዎችን አይተናል።በዚህ በሶስተኛው ክፍል የእንቁላልን ምሳሌ እንፈትሻለን።

ምሳሌው ሲብራራ:—
***
"One simple illustration of the Trinity is the egg. A chicken egg consists of a shell, a yolk, and an egg white, yet it is altogether one egg. The three parts create a unified whole"

"ቀላሉ የስላሴን አንድነት እና ሶስትነት የሚያሳየው እንቁላል ነው። የድሮ እንቁላል ሶስት ክፍሎች አሉት እነሱም:—(ቅርፊት:ነጭ አስኳሉ እና ቢጫው) ሶስት እንቁላል ብለን እንደማንጠራው ሁሉ ሶሰት አምላክ ብለን አንጠራውም" ይላሉ።

ችግሩ ምንድን ነው?
****

1) የመጀመሪያው ነገር አምላክህን በሚበሰብስ እና በሚበላሽ ነገር ምሳሌ ማደረግ አሳፋሪ ነው።

2) በምስሉ ላይ እንደምታዩት እንቁላል ሶስት የተለያዩ ክፍሎች አሉት ፣ሶስቱም አገልግሎታቸው የተለያየ ነው፣ ነጩና እና ቢጫው ለምግብነት ሲውል ቅርፊቱ ግን ይጣላል። በተጨማሪም የሶስቱም ይዘት በፍፁም የተለያየ ነው። ቅርፊት ጠጣር ሲሆን ሁለቱ ፈሳሽ ናቸው። በአገልግሎትም የተለያዩ ናቸው።

ይህን ምሳሌ ከወሰድን የአንድን እንቁላል #ቅርፊቱን #ነጩን እንዲሁም #ቢጫውን #እንቁላል ብለን እንደማንጠራው ሁሉ፣ አብን ,ወልድን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ለየብቻቸው #አምላክ ብለን መጥራት አንችልም።

3) ሌላኛው ነጥብ እንቁላል ሶስት ክፍል ብቻ መቼ አለውና? ከቅርፊቱ ስር ያለችው ስስ ከውስጥ የተለጠፈችው ነገር አራተኛ አይሆንምን? ከውስጥስ ጫጩቱ አድጎ እስኪፈለፈል ድረስ የሚጠቀመው ጫፍ ላይ የሚገኝ አየር Packed Air (የታመቀ አየር) አምስተኛ አይሆንምን?

4) በተጨማሪ አንድን እንቁላል መጥበሻ ላይ ሰብረን ቅርፊቱን ጥለን አንድ ህፃን ልጅ አምጥተን ይሄ ምንድ ነው ብለን ብንጠይቅ "እንቁላል" መባሉን አይቀይረውም ። ነገር ግን ቅርፊቱን— የስላሴ አንድ ክፍል የነበረውን ጥለንዋል።

5) እንቁላሉ ወደ ጫጩት ሲቀየር አሁንም ቅርፊቱ ተሰባብሮ ሲወድቅ ሁለቱ ግን ወደ ሌላ ህይወት ወዳለው ነገር ተቀየሩ? ይህም ሁለቱ ወደ ሌላ ነገር Transform ማድረግ ይችላሉ አንዱ ግን አይችልም ወደሚል እሳቤ ያመራል።

6) ከሁሉ የከፋው ደሞ አምላክን በሚገማ እና በሚበላሽ ነገር መመሰል እጅግ አሳፋሪ ነው።

Ash-Shura 42:11

فَاطِرُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِۚ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا وَمِنَ ٱلْأَنْعَٰمِ أَزْوَٰجًاۖ يَذْرَؤُكُمْ فِيهِۚ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ #የሚመስለው #ምንም #ነገር #የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡

አምላክን ውስብስብ በሆነ ምሳሌ እየገለፃችሁ መከራችሁን አትብሉ!!

@abuyusra3
የስላሴ ምሳሌዎች ሲፈተሹ —ክፍል 4
***************************
ስላሴን በዛፍ
********

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ።

ቀደም ብሎ በሶስት ክፍሎች የስላሴ (በውሃ ፣ በእንቁላል እና በወንድ) ምሳሌዎችን አይተናል።በዚህ በአራተኛው ክፍል የዛፍን ምሳሌ እንፈትሻለን።

ምሳሌው ሲብራራ:—

ስላሴን በዛፍ መውሰድ እንችላለን ለምሳሌ "‹‹.. ዛፍ ከላይ ቅርንጫፍ፤ ከመሃል ግንድ፤ ከታች ስር.. ስላለው ሶሰት ዛፍ እንላለን?… አንልም.. አንድ ዛፍ.. አንዱ ዛፍ ግን ስንት ነገር አለው?..ሶሰት… እግዚአብሄር ስንት ነው?.. አንድ… አንዱ አምላክ ግን ስንት አካል አለው?.. ሶስት.. ታድያ ይሄ ምን ይከብዳል..››ምንም። በማለት ለመሳረዳት ይጥራሉ።

ችግሩ ምንድን ነው?
************

1) አንድ ዛፍ አንድ ወጥ ሙሉ አካል አለው ይህ የዛፍ አካል የተለያዩ ክፍሎች አሉት ለምሳሌ ስሩ ብቻውን ዛፍ አይባልም፡፡ ግና የዛፉ አንድ ክፍል ነው ሚባለው ፡፡ ግንዱም ሆነ ቅጠሉም ዛፍ የሚባለው አንድ ወጥ አካል የተለያዩ ክፍሎች ናቸው፡፡ ለብቻቸው ዛፍ አይደሉም፡፡ ዛፍ የሚባሉት የሁሉም ክፍሎች ጥምረት የሚያስገኘው ድምር ውጤት ነው ይህን እውነታ ስር ቅጠሉ እንኳ ያውቀዋል፡፡ በምህረተ አብ ሎጂክ መሰረት አንዱ አምላክ ልክ እንደዛፍ ሁሉ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ አንድም አብ የሚባለው ክፍል ነው ሁለትም ወልድ ሚባለው ክፍል ሶስትም መንፈስቅዱስ የሚባለው ክፍል በመሆኑም ይህ አንዱ አምላክ የሚገኘው ሶስቱ ክፍሎቹ ሲደመሩ ነው ማለት ነው፡፡

2) ሁለተኛው ይህ ምሳሌ የሚያስረዳው እነዚህ የአንዱ አምላክ አካል ሶስቱ ክፍሎች ካልተደመሩ አምላክ ሊባሉ ወይም አንዱን አምላክ ሊሰጡ አይችሉም፡፡ ፡፡ ልክ ስር ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ግንዱ ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ቅርንጫፉም ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ሁሉ!!! አብ ብቻውን አምላክ አደለም ማለት ነው፡፡ ወልድም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ብቻቸውን አምላክ አይደሉም።

3) ስላሴን በዛፍ የምንመስል ከሆነ አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስን በመቁረጥ ( ቅጠላቅጠሉን) አብ እና ወልድን ማስቀረት እንችላለን ማለት ነው ይህ ደሞ መቼም አይነጣጠሉም የተባለቱን አካላት መለያየት ነው።

4) በተፈጥሮ ህግ መሰረት ቅጠሉ ከሌለ ( መንፈስ ቅዱስ ከሌለ) አብም ወልድም መኖር አይችሉም ምክንያቱም Photosynthesis
የሚካሄደው በቅጠሉ ነው። ቅጠሉ ከሌለ አብም ወልድም አይኖሩም።

Ash-Shura 42:11

فَاطِرُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِۚ جَعَلَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَٰجًا وَمِنَ ٱلْأَنْعَٰمِ أَزْوَٰجًاۖ يَذْرَؤُكُمْ فِيهِۚ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡ ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ #የሚመስለው #ምንም #ነገር #የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡

አምላክን ውስብስብ በሆነ ምሳሌ እየገለፃችሁ መከራችሁን አትብሉ!!

@abuyusra3
እባክዎትን ያንብቡት ...

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የሚሽነሪዎችን እንቅስቃሴ ለመመከት ታስቦ ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ በርካታ ስራዎችን በአላህ ፍቃድ ሰርቷል። ከእርዳታ ስራዎች በተጨማሪ የዳዕዋ ስራዎችም በማዕከሉ በሰፊው ተሰርተዋል። ከእነዚህም ውስጥ ለአብነት፦

❐ የተለያዩ ንፅፅራዊ የህትመትና የድምጽ ስራዎችን አዘጋጅቶ በተለያዩ አክፍሮተ ሀይላት በሚበዙባቸው አካባቢዎች በትኗል። በዚህም ብዙ ጥርጣሬ የነበረባቸው ሰዎች በቀላሉ የማዕከላችንን የሶሻል ሚዲያ አድራሻ በማግኘታቸው ወደኛ መጥተው እንዲማሩና ዲናቸውን እንዲረዱ አስችሏል።

❐ የመስጅድ እጥረት ባለባቸው ለኩፍር የተጋለጡ አካባቢዎች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የቆርቆሮ ማልበስ ስራዎችን ሰርቷል። በዚህም እስካሁን ስድስት የሚጠጉ መስጅዶችን ጨርሶ ለአካባቢው ህዝብ ክፍት አድርጓል።

❐ በመስለማቸው ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው የነበሩ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችንን በአቅማችን ለመደገፍ ችለናል። በዚህም በርካታ ወንድሞቻችንን ከነበሩበት ስቃይ በአላህ ፍቃድ መታደግ የቻልን ሲሆን ሌሎች በርካታዎችን በአነስተኛ መነሻ ራሳቸውን እንዲችሉ አመቻችተናል።

❐ በተለያዩ ቦታዎች ቋሚ ኡስታዞችን በመቅጠርና እንዲሁም ሌላ ቦታዎች ላይ ደግሞ ወጫቸውን በመሸፈን እየተንቀሳቀሱ የሚያስተምሩ ኡስታዞችን በመመደብ የገጠሩ አካባቢ ለኩፍር እንዳይጋለጥ ባለን ውስን አቅም እየታገልን እንገኛለን።

❐ ሚሽነሪዎች ከድረ ገፅ ጀምሮ በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ የሚሰሯቸውን ስራዎች ለመመከት ከተለያዩ የማስተማሪያ መንገዶች በተጨማሪ ቋሚ የኦንላይ ስልጠና በመስጠት ተተኪ የንፅፅር ዳዒዎችን ለማፍራት በትጋት እየጣርን እንገኛለን።

ለአብነት እነዚህን ጠቀስን እንጅ ስራዎቻችን እነዚህ ብቻ አይደሉም..! ይህም ቢሆን ግን ለነዚህ ስራዎች መስፋትና መጠናከር ከአላህ በታች የናንተ ድጋፍ ወሳኝ ነው። በጥቂት አቅም በሚሰሩ ስራዎች የሚሽነሪዎችን ጠንካራ እንቅስቃሴዎች መቋቋም እጅግ ፈታኝ ነው። ማዕከላችን ባለው አቅም እስካሁን እየተነሳ እየወደቀ የአቅሙን እየሔደ ነው። ይህንን ስራ በአቅም ማነስ ከመቋረጥ ይድን ዘንድ ግን የኛ ሀላፊነት ወሳኝ ነው። አደራ በዚህ የዳዕዋ ስራ ላይ አሻራዎትን በማሳረፍ መሠል ስራዎች በአቅም ማነስ ሳቢያ እንዳይቋረጡ የበኩልዎን ይወጡ..!

____

ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከልን በመቀላቀል ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ወንድምና እህቶች በሚከተለው ሊንክ በመጠቀም ወደ ግሩፑ መቀላቀል ትችላላችሁ።

https://chat.whatsapp.com/EqxP3r12nwvGe4ypjRz1fG

❐ በተጨማሪም በቴሌግራም

📌 t.me/Hidayacharity

ወደ ግሩፖች ሳይገቡ ቀጥታ ሊያገኙን ለሚፈልጉ የሚከተለውን ስልክ በመጠቀም በቀጥታ መደወል እንዲሁም በቴሌግራም ሊያገኙን ይችላሉ፦

+251901090095

ኑ ወገኖቻችን አብረን ከኩፍር እንታደግ..!
ጥንታዊ የእጅ ጹሁፎችን በተመለከተ
የሕያ ኢብኑ ኑህ
💥 የትምህርቱ ርዕስ 💥

💧 የጥንታዊ የእጅ ጹሁፎችን አስመልክቶ መጠነኛ ገለፃ💧

🎙 የሕያ ኢብኑ ኑህ
____

ተጨማሪ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን ለመከታተል

❐ በቴሌግራም t.me/yahya5

❐ በፌስቡክ facebook.com/yahyanuhe/

❐ በድህረ ገጽ www.ethio-islamic.org
Hidaya.apk
223.2 KB
የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ድህረ ገፅ የሆነውን የንፅፅር ዌብሳይት በአፕልኬሽን ማግኘት ከፈለጉ በሚከተለው አፕ አማካኝነት ያገኙታል..!
___

t.me/hidayaislam
ከ Hello papa God ወደ ሄሎ እየሱስ