አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ
2.06K subscribers
94 photos
36 videos
13 files
126 links
የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።
Download Telegram
የስላሴ ምሳሌዎች ሲፈተሹ —2
**********************

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ።

በክፍል አንድ የስላሴ ምሳሌዎችን መፈተሽ ጀምረናል ቀደም ብለን ያየነው፣ ስላሴን በጠጣር ፣በፈሳሽ እና በጋዝ የተመሰለበትን ከስላሴ ጋር እንደማይሄድ አይተናል። በዚህ ክፍል ሌላኛውን ምሳሌ እንፈትሸዋለን።

ምሳሌው ሲብራራ—
**********

"The Trinity is Like a Man who is a Father, Husband, and Son,The trinity is Like a man who is a father, husband, and son. Although he is one he has different roles to different people. The trinity is like this man."

ስላሴ ማለት ልክ እንደ ወንድ ነው። ይህ ሰው አባት ነው፣ባልም ነው፣ ልጅም ነው። ሰውየው አንድ ሲሆን ሶስት የተለያየ ድርሻዎችን ያከናውናል ይህ ሰው እንደዚሁ የስላሴ ተምሳሌት ነው " ብለው ያስረዳሉ።

ችግሩ ምንድ ነው?
***********
ይህኛው ምሳሌ አንድ ወንድ ሶስት አይነት ሚና ይጫወታል እነሱም #ለልጆቹ አባት ነው ፣#ለሚስቱ ባል ነው ፣#ለእናቱ (ለአባቱ )ልጅ ነው።

በዚህ ምሳሌ ሰውየው አንድ ሲሆን ሚናው ግን ሶስት ነው።በተመሳሳይ መልኩ ሶስት ሰው እንደማንለው ሁሉ እኛም ሶስት አምላክ ሳይሆን የምናመልከው አንድ አምላክ ነው ይላሉ።

የዚህ አመክንዮ ችግር "ወንድ" ተብሎ የተገለፀው አካል በዚህኛው አረዳድ አንድ ሲሆን የሚሰራቸው ስራዎች ግን ሶስት ነው ነገር ግን እነዚህ ሶስት ሚናዎች ለአንድ ሰው ሳይሆን #ለተለያየ #ሰው ነው። ይህ ማለት:—

* ለልጆቹ አባት
*ለሚስቱ ባል
*ለእናቱ/ለአባቱ ልጅ

1)ስለዚህ ይህ በስላሴ የተመሰለው "ወንድ" ሚናውን ከሚያጋጥመው ሁኔታ(Mode)አንፃር ይቀያየራል ማለት ነው። አምላክ የሆነ ነገር ሲገጥመው "አብ" ፣ሌላ ነገር ሲገጥመው "ወልድ" አሁንም ሌላ ሲገጥመው "መንፈስ ቅዱስ " ይሆናል ማለትን ያሲይዛል(ያመለክታል)።

2)በተጨማሪ አብን ወልድን እና መንፈስቅዱስን በስላሴ ቦታ ተክተን ለመረዳት ስንሞክር ። የስላሴ አምላክነት የሚሆነው /የሚገደበው በዝምድና ላይ ብቻ ይሆናል።

ለምሳሌ ይህ "ወንድ "ተብሎ የቀረበው አካል ለእኔ ምኔም አይደል!! ወይ ለእኔ አባቴ አልሆነ /ወይ ለእህቴ ባል አልሆነ / ወይም ለእናቴ ልጅ አልሆነ ምንም ዝምድና ከሌለን ለእኔ አምላኬ ሊሆን አይችልም።

3) ሌላኛው ይህ ምሳሌ አንድ ወንድ የባልና የአባት ሚናውን የሚወጣው ሲያገባ ነው ።ካላገባ ይህን ሚና መጫወት አይችልም።

4) ይህን ምሳሌ በሴቷ ያልተገፀበትስ ምክንያት ምንድ ነው ?ልክ እንደ ወንዱ አንዲት ሴት
#እናት, #ሚሰት,# ልጅ መሆን ትችላለች። "አምላክ" ወንድ ሆኖ መጣ ብላቹ ስለምታስቡ ይሆን?

አምላክን ውስብስብ በሆነ ምሳሌ እየገለፃችሁ መከራችሁን አትብሉ!!

@abuyusra3