ASTU Network ®️
4.21K subscribers
1.49K photos
33 videos
292 files
356 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
#Library

የዩኒቨርስቲው ላይብረሪዎች በፊት የሚሰሩት ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ለሊቱ 11 ሰዓት እንደነበር ይታወቃል። ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በፊት ጀምሮ በሰራተኛ ምደባ አለመሟላት ምክንያት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ብቻ እየሰሩ ይገኛሉ።

አዳዲስ የተመደቡ ሰራተኞች ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ስራ ስለሚጀምሩ የላይብረሪዎቹ የስራ ሰዓት ቀድሞ ወደነበረበት ሊመለስ ይችላል።

አዲስ ነገር ካለ በፍጥነት እናሳውቃችኋለን።

@ASTU_Network
👍11
#Library

👉 ቤተመጻሕፍት የግላችሁን PC ስትጠቀሙ mouse መጠቀም የምትፈልጉ ተማሪዎች በመጀመሪያ ወደ ቤተመጻሕፍቱ ሰራተኞች በመሄድ እናም ፈቃድ በማስወጣት mouse መጠቀም ትችላላችሁ።
👉 ፈቃዱ ለማንኛውም የዩኒቨርስቲው ተማሪ ሊሰጥ ይችላል።
👉 Mouse መጠቀም በፈለጋችሁ ጊዜ ፈቃዳችሁን የሚያሳየውን ወረቀት ማሳየት ይኖርባችኋል።

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት


@ASTU_Network
#Library

ሴንተራል እና አፕላይድ ላይብረሪዎች የአዳር ፈረቃ እንዳልጀመሩ ይታወቃል። ይህ የአዳር ፈረቃ ቀጣይ ሳምንት የሚጀምር ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ ላይብረሪዎቹ የ24/7 አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ተብሏል።

|| @ASTU_Network
👍98👏3🤬2😭2
ASTU Network ®️
#Library ሴንተራል እና አፕላይድ ላይብረሪዎች የአዳር ፈረቃ እንዳልጀመሩ ይታወቃል። ይህ የአዳር ፈረቃ ቀጣይ ሳምንት የሚጀምር ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ ላይብረሪዎቹ የ24/7 አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ተብሏል። || @ASTU_Network
#Library

ዛሬም የአዳር ፈረቃ አገልግሎት አይሰጥም። ሁሉም ላይብረሪዎች ዛሬ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የሚዘጉ ይሆናል። የኢንተርኔት (WiFi) አገልግሎትም እስካሁን አልተጀመረም።

— መረጃውን ያገኘነው ከአፕላይድ ቤተመጽሐፍት ቢሮ ነው

|| @ASTU_Network
🤬166🤣5🤷‍♀4
ASTU Network ®️
#Library ዛሬም የአዳር ፈረቃ አገልግሎት አይሰጥም። ሁሉም ላይብረሪዎች ዛሬ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የሚዘጉ ይሆናል። የኢንተርኔት (WiFi) አገልግሎትም እስካሁን አልተጀመረም። — መረጃውን ያገኘነው ከአፕላይድ ቤተመጽሐፍት ቢሮ ነው || @ASTU_Network
#Library

የዩኒቨርስቲው ላይብረሪዎች እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ የአዳር ፈረቃ ፕሮግራም አይጀምሩም ተብሏል። በመሆኑም አገልግሎት የሚሰጡት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ብቻ ይሆናል።

በሌላ መረጃ ፣ የኢንተርኔቱን ጉዳይ በተመለከተ WiFi እየሰራ ያይደለው በ ICT Center የሚገኘው የዩኒቨርስቲው ዋናው የኢንተርኔት ማከፋፈያ ቦርድ ስለተቃጠለ መሆኑን ሰምተናል። በመሆኑም የኢንተርኔት አገልግሎቱ የሚጀመረው አዲስ ቦርድ ሲገዛ ይሆናል።

|| @ASTU_Network
😭30😁91💔1
🤷‍♀1
#ማስታወቂያ‼️
#Library

➲ የዩኒቨርስቲው የ24 ሰዓት የቤተመጽሐፍት አገልግሎት መሰጠት የሚጀምረው ቀጣይ ሳምንት ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም ፣ ሐሙስ ዕለት እንደሆነ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የቤተመጽሐፍት አገልግሎት አስታውቋል።

|| @ASTU_Network
🤬132🌚2😡1
ASTU Network ®️
#ማስታወቂያ‼️ #Library ➲ የዩኒቨርስቲው የ24 ሰዓት የቤተመጽሐፍት አገልግሎት መሰጠት የሚጀምረው ቀጣይ ሳምንት ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም ፣ ሐሙስ ዕለት እንደሆነ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የቤተመጽሐፍት አገልግሎት አስታውቋል። || @ASTU_Network
#Library #Update

ከዚህ በፊት የዩኒቨርስቲው ላይብረሪዎች በዛሬው ቀን የአዳር ፈረቃ አገልግሎት እንደሚጀምሩ ባሳወቅነው መሰረት የአዳር ፈረቃ አገልግሎቱ ዛሬ መጀመሩን አረጋግጠናል። በመሆኑም ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ማታ ማታ ላይብረሪ መጠቀም ትችላላችሁ።

እሁድ እለት ከዚህ በፊት የአዳር ፈረቃ አገልግሎት እንደማይሰጠው ሁሉ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ ይቀጥላል። ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት ማታ ማታ ላይብረሪ ክፍት ነው።

|| @ASTU_Network
👏153👍2🤗2
ASTU Network ®️
#Library #Update I just got informed that they're trying to fix the internet (WiFi) issues before the 24/7 service starts this Thursday. In fact, there are some changes, but now I see that they're working to resolve the network configuration issues and…
#Library #Update

የላይብረሪዎች የኢንተርኔት (WiFi) ችግር በተወሰነ ደረጃ ተስተካክሏል። ነገርግን ከዚህ በፊት እንደነበረው አይደለም እየሰራ ያለው። አሁን በላይብረሪዎች የኢንተርኔት (WiFi) አገልግሎት ቢኖርም ምናልባት እንደከዚህ በፊቱ ላታገኙት ትችላላችሁ። ለማንኛውም ሄዳችሁ ሞክሩ እና ተጠቀሙ።

|| @ASTU_Network
😭5👍2🤷‍♂11😐1
#Library

በነገው የገና በዓል ምክንያት በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ቤተ-መጽሐፍት ከዛሬ ምሽት ሁለት ሰዓት ጀምሮ የሚዘጉ ይሆናል። ቤተ-መጽሐፍቱ እስከ ሐሙስ እለት ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ።

በተጨማሪም ቤተ-መጽሐፍቱ ዛሬ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ስለሚዘጉ እንደሌላ ጊዜው ደብተር ፣ ላፕቶፕ እና የመሳሰሉትን እቃዎቻችሁን አስቀምጣችሁ እንዳትወጡ ሲል የዩኒቨርስቲው የቤተመጽሐፍት አገልግሎት ያሳስባል።

👁️‍🗨️ ASTU Network መረጃውን ያገኘው ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የቤተመጽሐፍት አገልግሎት ቢሮ ነው!

|| @ASTU_Network
😭16🤷‍♀32👍2💅1😘1
ASTU Network ®️
#Library በነገው የገና በዓል ምክንያት በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ቤተ-መጽሐፍት ከዛሬ ምሽት ሁለት ሰዓት ጀምሮ የሚዘጉ ይሆናል። ቤተ-መጽሐፍቱ እስከ ሐሙስ እለት ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ። በተጨማሪም ቤተ-መጽሐፍቱ ዛሬ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ስለሚዘጉ እንደሌላ ጊዜው ደብተር ፣ ላፕቶፕ እና የመሳሰሉትን እቃዎቻችሁን አስቀምጣችሁ እንዳትወጡ ሲል የዩኒቨርስቲው የቤተመጽሐፍት አገልግሎት ያሳስባል። 👁️‍🗨️
#Library #Update

ከዚህ በፊት በገና በዓል ምክንያት የዩኒቨርስቲው ቤተ-መጽሐፍት እስከ ሐሙስ እለት ማታ እንደሚዘጉ ከዩኒቨርስቲው የቤተመጽሐፍት አገልግሎት መረጃ እንዳገኘን ነግረናችሁ ነበር።

አሁን ግን ነገ ፈተና በመኖሩ ምክንያት ተማሪዎች እንዲያነቡ በማሰብ ቤተመጽሐፍቱ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደተወሰነ የቤተመጽሐፍት አገልግሎት ቢሮው አሁን ጠዋት አሳውቆናል።

በመሆኑም ተማሪዎች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ቤተ-መጽሐፍቱን መጠቀም ትችላላችሁ።

|| @ASTU_Network
👏75👍1