ህይወት ጥበብ ፍልስፍና
70 subscribers
1.55K photos
19 videos
9 files
8 links
Qዳማዊw ነው ሰላምታዬ ማንኛውንም የስዕል ስራ ለመግዛት ወይም
ለማሳል ከፈለጉ ይደውሉ
👇👇👇👇
0935647014
አላማችንሰአሊዋችንማበረታት

Lift ባለማለት ተባበሩን🙏 @zolaarts
Download Telegram
ከአንበሳ ፊት በጣም ብዙ ገንዘብ እና ትንሽዬ ስጋ ብታስቀምጥ ስጋውን ይመርጣል ምክንያቱም ገንዘብ ከአስቀመጥክለት ስጋ በላይ ሌላ ስጋ እንደሚገዛለት ስለማያውቅ!

አብዛኛው የአለማችን ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ ወይም ቢዝነስ እና በመንግሥት አልያም በግል ድርጅት የወር ደመወዝ መካከል ምርጫውን ብትጠይቁት ወርሃዊ ደሞዙን እንጂ እሚፈልግ ትንሽዬ የግሉን ቢዝነስ አይደለም። ምክንያቱም የፈለገው ትንሽም ቢሆን የግል ስራ ወይም ቢዝነስ ከወርሃዊ ደመዎዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወቱን የሚቀይረው ከዎርሃዊ ደመወዙ ይልቅ ይህ ትንሽዬ ቢዝነስ እንደሆነ ስለማያውቅ ነው።

የአለማችን ሰዎችን ለድህነት ከሚጋለጡባቸው አንዱ ምክንያት የግል ስራ ወይም ቢዝነስ የሚመጡትን እድሎች ማዬት አለመቻላቸው ነው። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ምክንያት በህይዎት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው።

ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል። በርግጥ የወር ደመወዝ ከድህነት ይጠብቅህ ይሆናል ነገር ግን በፍፁም ሃብት እንድታገኝ አያደርግህም። እስኪ በወር ደመወዝ ሃብታም የሆነ ሰው ንገሩኝ? ምን አልባት በጎን ሃገር እየሸጠ ካልሆነ አንድም ሰው በወር ደመወዝ ሀብታም የሆነ አታገኙም።

ሃብታም እና ሁሉም ነገር እንዲኖርህ ከፈለክ መጀመሪያ አስተሳሰብህን ቀይር። ተምረህ ስራ ለመቀጠር ሳይሆን መሮጥ ያለብህ ያንተ የሆነን ነገር ማቋቋም ላይ ነው መህን ያለበት። መማርህ አስተሳሰብህን ማስፋት መቻል እንጂ መሆን ያለበት ማጥበብ አይደለም እንደማንኛውም ሰው ተምረህ ስትጨርስ የመንግስት ስራ ወይም የግል ድርጅት ለመቀጠር አትሯሯጥ።

የፈለገ ትንሽም ብትሆን የአንተ እና የአንተን የግል ስራ ጀምር። አውቃለሁ አብዛኛው ሰው የግል ስራ ለመጀመር ገንዘብ ያስፈልጋል ያ ገንዘብ ከየት ይመጣል እንደሚል ነገር ግን ይሄ በፍፁም ችግር አይሆንም አንድ ብለህ መጀመር ትችላለህ ከመቶ ብር ጀምረህ የራስህን ቢዝነስ መጀመር ትችላለህ ዋናው የአንተ ተነሳሽነት ነው።

ትምህርትን ለዕውቀት እንጂ መማር ያለብህ እንደ ማንኛውም ሰው ተቀጥሮ ለመስራት አይሁን። በቅጡ እንኳን ሆድህን መሙላት ለማይችል የወር ደመወዝ እራስህን አታስገዛ ምንም ትንሽ ብትሆንም የራስህን ቢዝነስ ጀምር ያኔ የሃብት ጉዞ ትጀምራለህ!!
ቸር ሌሊት ተመኘሁላችሁ🙏
✍️ @zolaarts
እኔ እና ሕልውና (Me and Existentialism)??

ህይወትህን እንዴት ትመራለህ?በህይወትህስ ደስተኛ ነህ?ህይወት ምንድነው?እኔስ ማነኝ?ደስታ ምንድነው?ሞት፣እውቀት፣ስነስርአት ፣እውነት፣እምነት ፈጣሪ፣ማህበረሰብ፣ግለሰብ ፣መንግስት፣ሳይንስ፣ ፍልስፍና ፣ሀይማኖት፣ ባህል......ምንድነው?ጠይቀህ/ሽ ታውቃለህ/ሽ?ከነዚህ በፊት ግን ቀዳሚ የሆነ መጠየቅ ያለበት ነገር አለ እንላለን፤ <<ምን?>>ካልከኝ አልበርት ካሙን ጠይቀው እልሀለሁ። እሱም ደግ ነው ይመልስልሀል፦

<<....ነገሮችን ከመጠየቃችን በፊት ዋናውና አንገብጋቢው ጥያቄ ልኑር ወይስ ልሙት ነው። ሌላዎቹ ጥያቄዎች ለመኖር ከወሰንኩ የምደርስባቸው ናቸው፡፡.....>> ይልሀል። ካሙ ጥያቄዎች በዋናነት መመለስ እና መጠየቅ ያለባቸው ስለ መኖር እና ሞት(Live and Death) ነው።ከዛ በኋላ ህልውናህን ካረጋገጥክ የጥንት እንዲሁም ዘመናዊው አለም መልስ የሚፈልግለትን ጥያቄ ማንሳት እንዲሁም ለመመለስ መጣር የተፈቀደ ይሆናል።
<<ህልውና(Existentialism)ምንድነው?>> የሚል ጥያቄ በአእምሮህ ከተጫረ ደግሞ የመጀመሪያው የህልውናን ፍልስፍና አስጀማሪ(First Existentialist) በመባል የሚታወቀው ሶረን ኬርጋርድ እንወስድሀለን። እሱም ፈገግ እያል<<Existentialism? I don’t know what that is!>>ብሎ ይሸኝሀል። የሕልውናዊያን ፍልስፍና እንቅስቃሴ ስሙን ያገኙት እነሱ በሚያቀነቅኑት መኖር ወይም ህልውና የተወሰ ነበር፤ ለዛ ነው <<ህልውና ምንድነው?>>ስትል <<ግለሰብነትን ማጎላት፣ነፃነት፣ምርጫ...>> የመሳሰሉ ትርጓሜ የሚሰጡት።

ወደ ዋናዬ ሀሳብ ልዝለቅ እነሱ ማለቂያ የላቸው!
በርግጥ ዛሬ ማንሳት የፈለኩት ሁላችንም በሚባል ሁኔታ ትርጉም አልባ እና ሀዘን የበዛበት የህይወት ባህር ውስጥ እየቀዘፍን ነው፤አንዳንዶቻችንን መውጫ አጥተን መውጫ እንፈልጋለን፣ሌሎች ደግሞ ለመውጣት ማሰቡ በራሱ አድክሞን እዛው እንዳክራለን፣ጥቂቶች ደግሞ ሰምጠን እንቀራለን። <<በዚህ ዘመን ማነው በመኖሩ ደስተኛ?>> የሚለው ጥያቄ እንደውም የፍልስፍና መርህ መሆን የነበረበት እስኪመስለን ድረስ በደስታ የሚኖሩ ሰዎች(ካሉ!¡) ጠይቀናል።ህልውናዊያን ደግሞ ከሁሉ የተሻለ በዚህ ጉዳይ "የተሻለ" ያሉትን መንገድ ይጠቁሙናል። እነሆ!

ከህልውናዊ ፈላስፎች መካከል እጅግ ታዋቂነት ካተረፉቱ አሳቢያን አንዱ አልበርት ካሙ ሲሆን በመግቢያችን ላይ እንደጠቀስነው የፍልስፍናም ሆነ የግለሰብ ጥያቄ በመኖሩና ባለመኖሩ (Surviving and Death) መጀመር እንዲሁም ማጠንጠን ይገባዋል ይለናል።ካሙ <<የሰው ልጅ የሚኖርበት ምክንያት ከሌለው 3 ነገሮችን ሊያደርግ ይችላል።
1]Suicide(ራስን ማጥፋት) ሲሆን በዚች አስቸጋሪ ህይወት ውስጥ የመገላገያ አንዱ መንገድ ነው።ከውቅያኖስ ውስጥ አንዲት ጠብታ ብትወሰድ ውቂያኖስ እንደማይጎድለው ሁሉ በዚህ አሰልቺ ጉዞ ራስን ማጥፋት የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም።
2]ፍልስፍናዊ ግድያ(Philosophical Suicide) ውስጥ ይገባል።ማለትም ካሙ እንደምሳሌ የሚያቀርብልን ሃይማኖተኞች ሲሆን ህይወት ትርጉም ባይኖራትም ትርጉም እንዳዘለች አድርጎ መመልከት እና ያለመጠየቅ መከተል ነው። (ሌላ ምሳሌ ስጨምርልህ ልክ ፈጣሪ ለህይወት ትርጉም ይሰጣታል በዛም ትርጎሜ አንተ ትገፋበታለህ!)

3]አብዘርድ(Absurd)ይለዋል፤አለምን ይጋፈጣል ማለትም እንደሁለቶቹ(ሃይማኖተኝነት ወይም ራስን ማጥፋት) ሳይሆን በችግር የተዘፈቀ የህይወት ጉዞውን በራሱ ህይወት የሚቃኝ ሰው ነው-አብዘርድ ጀግና ነው።ካለህበት እውነት(ሁኔታ) ጋር ላለመጋጨት ስትል ትርጉም አትሰጥም። የህይወት ትርጉም አልባነት በተረዳህ ቁጥር ሌላ ዝባዝንኬ ትተህ አሁን ትኖራለህ ይሄው ነው-Absurd hero።አሁን ነው የተሰጠህ ጊዜ....>>ኒቼ ደግሞ እውነተኛ አለም አደገኝነን ለአንተ ለማስረዳት<<l'm afraid of the real World>>በለው ብሎኛል።

አንዳንድ ጊዜ በውስጥህ ራስህን የማጥፋት ፍላጎት መጥቶብህ አያውቅም?እንዴትስ መለስከው?......የግድ እኮ ስጋህም ሆነ አእምሮህ ስራ ማቆም እና መተኛት አይጠበቅባቸውም፤ የቁም ሞትስ ሞተህ ታውቃለህ?!..እነዚህን ጥያቄዎች ይዘን ወደ ቀጣዩ ኤግዚስቴንሺያሊስት ጃን ፖል ሳርተር እንጓዝ።ሳርተር ደግሞ ጨዋታውን የሚያነሳልህ ከኃላፊነት በመጀመር ነው በፈረንጂኛ <<Responsibility>> ከሚሉት።

አንዳንድ ጊዜ ራሳችንን ነፃ አውጥተን ሌሎችን ተወቃሽ እናደርጋለን፤አንዳንዴም ደግሞ ሌሎች ላይ ለመፍረድ እና ጥፋተኛ ለማድረግ ይቃጣናል፤ሳርተር ይሄንን <<ክፉ እምነት(Bad faith)>> ይለዋና። ክፉ እምነት ጥፋተኝነታችንን በኋላ ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ የምንጓዝበት መንገድ ነው።የሆነ ነገር ውስጥ እጅህ ኖሮበት እና ያመጣው ውጤት የጥፋት ሲሆን<<ውይ! እኔ አደለሁም ሰይጣን አሳስቶኝ ነው!>>ትላለህ፤ደግሞ አንተ ተሳትፈህበት ነገሩ ወደ ክብርና ጀግንነት ሲቀየር ለነገሩ ሁሉ አንተ ፈላጭ ቆራጭ እንደነበርክ ትናገራለህ...እ..ያንነው ሳርተር <<ክፉ እምነት>> ያለህ!።እዚሁ ጋር ደግሞ ኒቼን ምን አለ መሰለህ<<ከውሸት ሁሉ የከፋው ውሸት ራስን መዋሸት ነው!>> ይልሀላ!። ሳርተርም ከካሙ ጋር የሚስማማ ርዮት ውስጥ ነው-የመጀመሪያው ጥያቄ ልኑር ወይስ ልሙት የሚለው የህልውና ጥያቄ ነው መሆን ያለበት በሚለው ነዋ።

ሳርተር እንደሚለው ሁላችንም የለበስነው ጭንብል አለ፤ለዛ ነገር ስንል እናስመስላለን።ምናልባት ጭንብሉ በፍላጎት ለብሰነው ሊሆን ይችላል ነገርግን በአብዛኛው ጊዜ ከማህበረሰቡ የሚሰጡን ናቸው።አንዱ ያይህና ጭምት፣ዝምተኛ፣ሰው አክባሪ እንደሆንክ ይነግርሀል ሌላው ይመጣና ደግሞ ውስጡ ሽሮ የፈላበት፣የሚናገረውን የማያውቅ እንደሆንክ ይነገርሀል....እንዲህ እያሉ ብዙ ጭንብል ያለብሰሀል አንተም ለልወደድ ይሁን እንጃ! ትተገብረዋለህ።ሳርተርም ይጨምርልሀል <<ሲኦል ማለት ሌሎች ሰዎች ናቸው!>>ሌላው ምን ይለኛል?ሌላው ምን ይሰማዋል?ሌላው....ሌላው ትላለህ።ይቺን ጨዋታ ከርቀት ሆኖ ሲሰማ የነበረው ላኦ-ቱዙ ደግሞ ምን አለ መሰለህ<<ሌላው ስለሚያስበው የሚገድ ከሆነ ሁሌም የነሱ እስረኛ ነህ!>>ጥቅስ ብቻ ባጃጅ የሆነ ህይወት! እረወዲያ!! ደና ሰንብት ወንድምአለም

በምርጡ ካህሊል ጅብራል አባባል ክፍል ፩ ላበቃ ካልደበረኝ ፪ ሁለትን እቀጥላለሁ!

<<ጭምብሌን የሰረቁ ሌቦች ለዘላለም ይባረኩ ....ይባረኩ....>>አዎ የተባረኩ ይሁኑ..

ተፃፈ ዞላ
ቢኒያም ግራ አዝማች:
#ድራማዊ_አሣሣል
- የገፀ-ባህሪያት ማንነት በታሪካችን ውስጥ የሚገለፀው በድራማዊ አሣሣል ነው።ድራማዊ አሣሣል ሲባል፣
ለምሳሌ:-አበበ ቸር ነው ብለን ከመናገር ይልቅ ቸርነቱን በድርጊት እንደ ማሳየት ለማለት ነው።

#የዋና_ገፀ_ባህሪያት_ማንነት_አሳሳል

የሰው ልጅ ውስጣዊ እና ውጪያዊ ማንነቶች አሉት።

- #ውጪያዊ ስንል ከአካላዊ መግለጫችን ይጀምር እና አካባቢያዊ ወይም ማህበራዊ ማንነታችን ላይ ያተኩራል።

- #ውሰጣዊ ስንል ደግሞ ሕሊናዊ ወይም ከስነ-ልቦናዊ ባህሪያችን ይጀምርና ለሰዎች የምናሳየውን ግብረገባዊ ፀባያችንን ያጠቃልላል።

1/ #አካላዊ_ማንነት_አሳሳል (Physical Personality):- አካላዊ ማንነት አሳሳል ማለት በድርሰታችን ውስጥ ያለው ገፀ-ባህሪ አካላዊ ጉዳዮች ማለት እንደ ውፍረት፣ቅጥነት፣ርዝመት፣እጥረት፣ጥቁረት፣ቅላት የመሳሰሉት አካላዊ ማንነት የሚገለፁ ማብራሪያዎች ማለት ነው።

ይህም ደራሲው በገፀ-ባህሪያት ንግግርና በሌላም መልክ ስለ አንድ የድርሰቱ ፍጡር የሚሰጠው ጥቆማ ይሆናል።

2/#ማህበራዊ_ማንነት አሳሳል(Sociological Personality):-ማህበራዊ ማንነት አሳሳል ማለት በድርሰታችን ውስጥ የምንፈጥረው ወጥ ገፀ-ባህሪ የት እንደተወለደ፣ቤተሰቦቹ እነማን እንደሆኑ፣የትምህርት ደረጃው፣የምን እምነት ተከታይ እንደሆነ፣ስራው፣የጋብቻ ሁኔታው ባጠቃላይ ማህበራዊ ኑሮውን የምናሳውቅበት ነው።

3/ #ስነ-ልቦናዊ_ማንነት አሳሳል(Psychological personality):- ስነ-ልቦናዊ ማንነት አሳሳል የወጥ ገፀ-ባህሪን ፍላጎትና ግብ የምንለካበት ነው።
ይህም ገፀ-ባህሪው ህይወትን የሚያይበትን መልክ ያሳየናል።

- የገፀ-ባህሪው አመለካከት፣ ገፀ-ባህሪው ህይወትን እንዴት ይመለከታል የሚለውን የምናሳይበት ነው።

4/ #ግብረ-ገባዊ ማንነት አሳሳል(Moral personalityi):-የአንድ ገፀ-ባህሪ ሞራላዊ ማንነት አሳሳል የገፀ-ባህሪውን መልካምነት ና መጥፎነት፣ፅድቅ እና ኩነኔ፣ቸርነት እና ንፋግነት የመሳሰሉትን የምናሳይበት ነው።

* #ደራሲው ይህን ለይቶ በመስቀመጥ ፍጡር ወይም ዋና ገፀ-ባህሪውን በዚህ መልክ እንዲታወቅ ያደርገዋል።

#መቼት

የፊልማችን ታሪክ የሚከናወንበት ቦታ ፣ጊዜ እና ነባራዊ ዕውነታ መቼት በመባል ይጠራል። 'መቼ' ና 'የት' እንደማለት ነው።

- የፊልሙ መቼት በቦታውና ጊዜው ያሉ ከአየር፣ ከመብራት ቀለም ከድምፅ እስከ ቅንጣት ጠጠር እስከ ትልቅ ግዑዝ የቤት ቁሳቁስ ሳር፣ቅጠል፣ሀይቅ፣መርከብ ያሉትን ያጠቃልላል።

#የመቼት_አላባውያን:-የሚሰኙት ድርጊቱ የተከናወነበት
👇👇👇

* #ቦታ:-ታሪኩ የተከናወነበት ቦታ ሲባል አህጉር፣ሀገር፣ከተማ፣ሰፈር እና ቤት ብሎም የቤቱ የትኛው ክፍል እንደሆን የሚነግረን መሆን አለበት።

* #ጊዜ:- ታሪኩ የተከናወነበት ጊዜ ሲባል :-ዘመን፣ክፍለ ዘመን፣ዓመታት፣ወራት፣ቀናት እና ሰዐታት ናቸው።

* #ነባራዊ_ዕውነታ:-አንድ ታሪክ ሲከናወን በስራው ላይ ያሉ ቁሳቁሶች ወይም በስፍራው ላይ የነበሩ የቦታው አጠቃላይ ማስዋቢያዎች ናቸው።

በእውነታው ዓለም ልዩ ልዩ የቦታና የጊዜ ለውጦች እንዳሉ፣ በድርሰት ዓለም ውስጥም የተለያዩ የቦታዎችና የጊዜያት ለውጦች አሉ።
በፊልም ውስጥ ቦታና ጊዜ በሁለት ተከፍለው ይታያሉ። #ውስጥ (interior) & #ውጪ(exterior). ጊዜ ደግሞ ቀን(day) & ማታ (night) ተብሎ ይከፈላል።

#በፊልማችን_ድርሰት_ውስጥ_መቼት_የሚገለፅበት_ስርዐት

#ውስጥ_ውጪ / #ቀን_ማታ
ድርጊቱ የሚከናወንበት ቦታ፣ ከቤት ውስጥ ወይም ውጪ ከሆነ፣ በሚከተለው መንገድ እስከነጊዜው ይፃፋል።

ትዕይንት 1. ውስጥ-መኝታ ቤት-ማታ

ዮናስና ሜላት መኝታ ቤት ተኝተው ይታያል።

ዮናስ፥
ሜሊዬ… የሚጣን ነገር ምን ብናደርግ ይሻላል?

ሜላት፥
እስኪ ጠዋት ሲነጋ… እንደሚሆን እናደርጋለን

ትዕይንት 2. ውጪ-ቅፅር ግቢ-ጠዋት

ውስጥ ወይም ውጪ የሚለው/Camera Placement/ ነው።
መኝታ ቤት የሚለው/Location/ ነው።
ቀን ወይም ማታ የሚለው/Time/ ነው።

*ከላይ በተመለከትነው መሰረት፣ በፊልም ፅሁፍ ውስጥ፣ መቼት ከድርጊትና ከንግግር በፊት ይገለፃል። መኝታ ቤት፣ሳሎን፣ መንገድ ላይ…ወዘተ እየተባለ የታሪኩ ቦታ ይገለፃል። ቀን፣ ማታ፣ ከአንድ ሰዓት በኋላ…ወዘተ እየተባለ ጊዜውም ይገለፃል።

#ልዩ_መቼት
ታሪኩ በተንቀሳቃሽ አካሎች ውስጥ የሚፈፀም ከሆነ በልዩ መቼት ይገለፃል።

ለምሳሌ፦ መኪና፣ ታክሲ፣ መርከብ…ወዘተ ሲሆን እንደሚከተለው ይፃፋል።

ትዕይንት 15. ውስጥ-መኪና-11ሰዓት

ተመስገን መኪና እያሽከረከረ፣ መሰረት ትስቃለች
.
መቼት ታሪኩን ደጋፊ ሆኖ ይፃፋል። የዶክተር ቤትና የመካኒክ ቤት አንድ ዓይነት አይደሉም። ከታሪኩ አንፃር ለሁለቱም የምንመርጥላቸው ቦታ ይለያያሉ።

በዚህ መሰረት ይፃፋል
👇👇👇👇👇

• ውስጥ-መኝታ ቤት-ማታ

ደገፋ አልጋው ላይ ተኝቷል። ዙሪያውን የወዳደቁ የመኪና መፍቻዎች ይታያሉ። ግርግዳ ላይ የተለጠፉ የመኪና ምስሎች ይታያሉ።
============

#ድራማዊ_ድርጊትና_የፊልም_ንግግር
.
#የፊልም_ንግግር
በፊልማችን ውስጥ እንዲናገሩ የምናደርጋቸው ገፀ-ባህርያት አነጋገራቸውና የቋንቋ አጠቃቀማቸው እንደምንሰጣቸው ማንነት ይለያያል። ለምሳሌ፦ ሚኒስቴር ከሆነ፣ ሚኒስቴሮች የሚጠቀሙበትን አነጋገርና ስብዕና ተጠቅመን እንፅፋለን። ልዩ ምክንያት ካልተፈጠረ በስተቀር ለዘበኛና ለሚኒስቴር ተመሳሳይ የንግግር ዘይቤ አንጠቀምምም።
.
#የገፀ_ባህርያት_አነጋገር
የፊልም ንግግሮች ከእውነታው ዓለም በተለየ፣ ሳይንዛዙና ከታሪካችን መስመር ሳይወጡ፣ ተመጥነው፣ ስሜት ሰጪ ሆነው፣ በድራማዊ አቀራረብ ይቀርባሉ።

#የፊልም_ድርጊት
ፊልምን 'አሳይ እንጂ አትናገር' እንደሚባለው፣ ታሪካችን ከድርጊት ይልቅ ወሬ ከበዛበት አሰልቺ ይሆናል። በተቻለ መጠን አብዛኛውን የታሪኩን ክፍል በድርጊት ማሳየት ይኖርብናል።

#credit_for: አቢላማ የፊልም እና የቴአትር ፕሮዳክሽን

#ከላይ_የቀጠለ👆👆👆👆👆👆

#ክፍል_ሦስት

#ሴራ
የተለያዩ ታሪኮች እርስ በር'ስ በምክንያትና ውጤት እየተሳሰሩ የሚሄዱበት ሰንሰለት 'ሴራ' ተብሎ ይጠራል።
• በአጠቃላይ ሴራ ማለት የታሪክ ግጭት-መሰናክል-ጡዘት እንደማለት ነው።

-> #ስድስቱ_የሴራ_ጥያቄዎች

-ምን?
-መቼ?
-የት?
-ለምን?
-ማን?
-እንዴት?
የፊልማችንን ፅሁፍ ከእነዚህ የሴራ ጥያቄዎች አንዳቸውን ሳናጎድል እየመለስን ማዋቀር ይኖርብናል። ነገር ግን ከነዚህ ጥያቄዎች አንዳቸው ከጎደሉ የሴራ ክፍተት መኖሩን ይጠቁመናል።

#የሴራ_መስመር

በአንድ ፊልም ውስጥ አንድ ብቻ አልያም ከአንድ በላይ የሴራ መስመሮች ተከትለው ይፃፋሉ።

- አንድ ብቻ የሴራ መስመር ባለነጠላ ሴራ ይባላል። በዚህ የተዋቀረ ፊልም በአንድ ታሪክ ላይ ብቻ በማውጠንጠን ሌላ ታሪኮችን ሳይጨምር ቀጥ ብሎ የሚሄድ ነው።
- ከአንድ በላይ የታሪክና ሴራ መስመር ሲዋቀር ደግሞ ባለጥምር ሴራ ተብሎ ይጠራል።

-> #አብይና_ገባር_ሴራ

- የፊልሙን ዋና ታሪክ እያሰናሰነ የሚሄደው አብይ ሴራ ይባላል።
- በፊልሙ ዋና ታሪክ ላይ ተደራቢ ታሪክና ሴራ በመሆን አብሮ የሚጓዘው ገባር ሴራ ይባላል።

#ጥብቅና_ልል_ሴራ
- የታሪኩ መስመር በጠንካራ ሰበብ-ውጤት ተሰናስኖ የተያያዘና የተመልካችን ቀልብ በከፍተኛ ሁኔታ የሚስብ ጥብቅ ሴራ ይባላል።
- ተመልካችን ለማዝናናት ተብለው ቀላል በሆነ ባልተወሳሰበ ሴራ የሚዋቀረው (የቀልድ ፊልሞች) ልል ሴራ ይባላሉ።

#ግጭት

ግጭቶች ካለመግባባት የሚመጡ ናቸው። የፊልም ፅሁፍ መሰረቱ ግጭት ነው። በፊልም የተመልካች ትኩረት የሚሳበው ልዩ ልዩ ግጭቶችን በመፍጠር ነው።
- ግጭቶች አካላዊና ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ።

#credit_for: አቢላማ የፊልም እና የቴአትር ፕሮዳክሽን

#ክፍል_አራት



1.#ክስተት_(ዱብዳ)_መፍጠር
...
አንድ የፊልም ድርሰት ጽሑፍ መታየት በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አበይት (ዋና) ታሪኩን ተሸክሞ እስከ ፍፃሜው ድረስ ሊያዘልቀው የሚችል ክስተት(ዱብዳ) መፍጠር ግድ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በታሪክ የጉዞ ሂደት ያልታሰበና ያልተጠበቀ ክስተት መፈጠር አበይትና ንዑሳን ታሪኮችን ወደፊት ከማራመድም በላይ ለፊልም ድርሰት ፅሁፍ ማማር ጥበባዊ ፍይዳው ላቅ ያለ ነው፡፡

2. #ታሪክን_ወደ_ፊት_ማራመድ
...
ግጭት የፊልም ድርሰት ፅሁፍ የጀርባ አጥንት በመሆኑ በታሪክ ሂደት ውስጥ ልዩ ልዩ ገፀ-ባህሪያት የሚያደርጉትን የእርስ በእርስ ግኑኙነት እንዲሁም ልዩነት መሠረት በማድረግ ታሪኩ ወደፊት እንዲራመድ ማድረግ ያሻል፡፡

3. #አበይትና_ንዑሳን_ገፀ_ባህሪያት
...
በታሪክ የጉዞ ሂደት መጫወት ያለባቸው ሚና ንዑሳን ገፀ-ባህርያት አበይት (ዋና) ባለታሪኮችን በማጀብና ሊገጥሟቸው በሚችሉ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ደጀን ሆነው መሰለፍ አለባቸው እንጂ ፊት አውራሪ ሊሆኑ አይገባም፡፡

#credit_for: አቢላማ የፊልም እና የቴአትር ፕሮዳክሽን
1. ከሰዎች ጋር ለመስራት ስትፈልግ ሶስት ነገሮቻቸውን ተመልከት፦ ብልህነት (intelligence)፣ ጉልበት (energy) እና ታማኝነት (integrity)፡፡ እና የመጨረሻው ከሌላቸው ስለ መጀመሪያዎቹ ሁለት ስብእናዎች አትጨነቅ!
☞ ምክንያቱም በእውነት (truth)፣ በሐቀኝነት (honesty) እና በስነ-ምግባር (ethics) ልኬቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ማንም ባይመለከታቸው እንኳ ልባቸውን ያዳምጣሉ፣ ትክክለኛውን ነገርም ያደርጋሉ ፡፡

2. ስኬታማ በሆኑና ያልተሳካላቸው ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ስኬታማ ሰዎች በማያስፈልጉ ነገሮች ላይ 'ምንጊዜም 'አይሆንም' (no) ስለሚሉ ነው።
☞ በየቀኑ ወደ እኛ አቅጣጫ ለሚመጡ አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ደግመን ደጋግመን 'አይሆንም' (no) ማለት እና አስፈላጊ ለሆኑ ጥቂት ነገሮች ትኩረት በመስጠት 'እሽ' ማለት አለብን።
ይህን መርህ በየትኛውም ነባራዊ ሁኔታ፣ በዕለት ተዕለት የውሳኔ አሰጣጥ መንታ መንገድ ላይ ስትደርስ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ይህን ካደረክ ህይወትህን ማቅለል ትችላለህ።

3. ከአንተ የተሻሉ ሰዎች ጋር ጊዜህን አሳልፍ!
☞ በባህሪያቸው ከአንተ የተሻሉ ጓደኞችን መምረጥ ከቻልክና ከእነሱ ጋር ጊዜህን ካሳለፍክ አንተም ወደዚያ አቅጣጫ መጓዝ ትችላለህ፡፡
ዕድሜህም ሆነ ያለህበት ደረጃ ምንም ይሁን ምን እንደ መሪ፣ የንግድ ሰው ፣ ሠራተኛ እና ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ የሚያደርግህን ጥበብ ፣ ልምድ እና ባህርይ የበለጠ ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች መማር አስፈላጊ ነው፡፡
.
4. ሀብታም ብትሆን ወይም የገንዘብ ነጻነት ቢኖርህ ልትሰራው የምትችለውን ስራ ለመስራት ወስን!
☞ ይህን ስታደርግ የምትወደውን እና የምትጓጓለትን ነገር መፈለግና ያንን የህይወትህ ዋና ተግባር እንድታደርገው ይረዳሃል።
ይህ ማለት በየቀኑ ልትሰራው የምትጓጓለት ስራ ስላለህ ከአልጋህ ዘለህ ትነሳለህ፣ ምንጊዜም አንድ ነገር ትማራለህ ይህም ደስታን ይሰጥሃል።

5. ዝናን ለመገንባት 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል ይህን ለማበላሸት ግን አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል ፡፡ ይህን ማስብ ከቻልክ ነገሮችን በተለየ መንገድ ማድረግ ትችላለህ።
☞ የማንኛውም ሰው ዝና ወይም እውቅና በአሸዋ እንደተገነባ ቤት በፍጥነት ሊወድቅ ይችላል። ስለሆነም በህይወት ጉዞህ የምትመራበትን ታማኝነት (integrity) በውስጣዊ የጂፒኤስ ስርዓትህ ውስጥ ሳትገነባ ከቀረህ መውደቅህ የማይቀር ነገር ነው፡፡

መልካም ቀን!
🌿#ለራስህ_ለመሆን_መጀመር_ያለብህ_5_ነገሮች

#ከትክክለኛ_ሰዎች_ጋር_ጊዜህን_ማሳለፍ_ጀምር - እነዚህ ሰዎች የሚያስደስቱህ ፣ የሚያደንቁህ ፣ የሚወዱህ እና እንድትሻሻል እና እንድትቀየር ጤናማ በሆነ መንገድ የሚያበረታቱህ ናቸው፡፡

#ችግሮችህን_ፊት_ለፊት_መጋፈጥ_ጀምር - አንተን የሚገልጽህ ችግርህ ሳይሆን ለችግሮችህ የምትሰጣቸው ምላሾች እና ከችግሮችህ ውስጥ ወጥተህ ማገገም የምትችልበት አቅምህ ነው፡፡ እርምጃ እስካልወሰድክባቸው ድረስ ችግሮችህ አይጠፉም፡፡ የምትችለውን አድርግ ለአደረግከውም ነገር እውቅና ስጥ፡፡

#ስለ_ሁሉም_ነገር_ከራስህ_ጋር_ግልጽ_መሆን_ጀምር - ትክክል ስለሆነው ነገር እና እንደዚሁም መቀየር ስላለባቸው ነገሮች ሀቀኛ እና ግልጽ ሁን፡፡ ማሳካት ስለምትፈልገው ነገር እና መሆን ስለምትፈልገው ሰው ግልጽ ሁን፡፡ ሁልጊዜም በሕይወትህ እያንዳንዱ ክፍል ላይ ሀቀኛ እና ግልጽ ሁን፡፡

#ለራስህ_ደስታ_ቅድሚያ_መስጠት_ጀምር - ፍላጎቶችህ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ለራስህ ዋጋ ካልሰጠህ ፣ ለራስህ ካልቆምክ፣ ራስህን ካልጠበቅክ ሆን ብለህ ራስህን ለማጥፋት ተነስተኻል ማለት ነው፡፡ አስታውስ በዙሪያህ ላሉት እየተቆረቆርክ እና እያሰብክ የራስህንም ፍላጎቶች ማሳካት ትችላለህ፡፡ አንድ ጊዜ ፍላጎቶችህ እንደተሟሉ ደግሞ የአንተ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የበለጠ መድረስ ትችላለህ፡፡

#በኩራት_እና_በሀቀኝነት_ራስህን_መሆን_ጀምር - ሌላ ሰው ለመሆን መሞከር አንተ የሆንከውን ሰው ማባከን ነው፡፡ ራስህን ሁን፡፡ ሌሎች አጠገቡ የማይደርሱበት ሀሳቦች ፣ ብርታቶች እና ውበት የያዘውን በውስጥህ ያለውን ያን ሰው ተቀበለው፣ እቀፈው፡፡

🎖 @zolaarts
ደስታን ከየት እናገኘዋለን?

ፍልስፍና

በዚህ ምድር ላይ እየኖረ ደስታን ለማግኘት የማይፈልግ ይኖራል ብሎ ለመገመት ይከብዳል፡፡ የሰው ልጆች በተፈጥሮ የሚያስደስታቸውን ነገሮች ለማግኘት ይጥራሉ ይህንን ደስታም ለማግኘት ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን ይሰዋሉ። ብዙዎች በብዙ ፍለጋ ውስጥ ሳያገኙት ደክመው ሲቀሩ፤ አንዳንዶች ግን ያገኙታል፡ መቼም፤ ከየትኛው ጎራ ለመሰለፍ ትፈልጋላችሁ ብንባል ከሚያገኙት እንደምንል | አያጠራጥርም። ዛሬ፤ በፍልስፍና ዐምዳችን፤ ደስተኛ ሆኖ ኖሮ ያለፈው የግሪክ ፈላስፍ ሶቅራጠስ ደስታን ስለ ማግኘት ያስተማረውን በጥቂቱ እንመለከታለን።
ይህንን ፈላስፋ ለማታውቁት ጥቂት ለማስተዋወቅ ያህል፤ ሶቅራጠስ በጥንታዊ ግሪክ የነበረ ፈላስፋ ነው። አባቱ የድንጋይ ጠራቢ፤ እናቱ ደግሞ የልምድ አዋላጅ ነበረች፡ ሶቅራጠስ በሃምሳዎቹ እድሜው ውስጥ ዛንቲፒ የተባለች ሚስት አግብቶ ይኖር ነበር ሦስት ልጆችም ነበሩት፡፡ ጠዋት ወጥቶ እለቱን በተመስጦ ሲያስብ፣ ካገኘውና ከሰማው ጋር ሁሉ በፍልስፍናዊ ጉዳዮች ሲወያይ ውሎ ወደቤቱ ይገባ ነበር። ይህ ለሀቅ የኖረ ነበር። በወቅቱ 'የግሪክን ወጣቶች ባልሆኑ አሳቦች አሳስቷል' ተብሎ ተከስሶ ሞት ተፈረደበት። ጓደኞቹ ለጠባቂዎቹ ጉቦ ከፍለው ሊያስመልጡት ሞክረው ነበር- ሶቅራጠስ ግን 'ወይ ፍንክች' አለ፤ ከተፈረደበት ፍርድ ሊሸሽ አልፈለገም፤ ሕሊናው እንደማይፈቅድለትና ለሀገሩ መታዘዝ የሞራል ግዴታው እንደነበር ለጓደኞች ነገራቸው። ሔምሎክ የተባለ መርዝ እንዲጠጣ ተደርጎም ሞተ፡፡
ሶቅራጠስ በሕይወት ዘመኑ ከተፈላሰፈባቸው ነገሮች አንደኛው ስለ ሰው ልጅ ደስታ ነበር። የሶቅራጠስ ተማሪ የነበረው ፕሌቶ (በግዕዙ አፍላጦን ተብሎ ይጠራል) በጻፈው ኢውቲዲመስ' በተሰኘ ሥራው ላይ፤ ሶቅራጢስ ስለ ደስታ ያስተምር የነበረ ጽፎልናል፡፡ ሶቅራጠስ እንደሚለው ከሆነ፤ ደስታ በውጫዊ ነገሮች ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ይህም ማለት ባለን ውበት፣ ገንዘብ፣ ሥልጣን...ወዘተ የሚመሠረት አይደለም፡፡ ገንዘብን ለጥበበኛ ብንሰጠው፤ መልካምን ያደርግበታል። ጥበብ ለሌለ የሰጠነው እንደሆነ ግን ከደካማ የገንዘብ አጠቃቀሙ የተነሳ ራሱን ወደባሰ መንገድ ሊከትት ይችላል፡፡ ውበትም ቢሆን፤ ጥበበኛ ያልሆነ ሰው ካለው፤ ውበቱን ተጠቅሞ ሰዎችን ለማሳሳት እና የሚፈልገውን ለማግኘት ሊጠቀምበት ይችላል። እውቀትን ብንወስድ ጥበበኛ ሰው እውቀትን ለልማት ሲጠቀም፤ ካልተማረ ተንኮለኛ ይልቅ፤ የተማረ ተንኮለኛ ጥፋቱ እጅግ ብዙ ነው። ሶቅራጠስ እንዲህ ያለውን እሳቤ ተመስር አንድ ሰው በውጫዊ ነገሮች ደስታን ለማግኘት ስንኳ አጠቃቀሙን ሊችልበት እንደሚገባ ማለትም የአጠቃቀም ጥበቡ ሊኖረው እንደሚገባ ያስተምራል። አላ ከሆኑ እንደ ገንዘብ፥ ውበት፥ ሥልጣን ባሉ ለነገሮች የሚመሠረት ደስታ ቶሎ| ይመክናል፥ ቁልፉ ያለው ከጥበብ ዘንድ መሆኑን ሶቅራጢስ ጠቆም ያደርገናል።
ሶቅራጠስ ተጨማሪ ምክርም አለው። ደስታን ለማግኘት የሚፈልግ ሰው ከሥጋው, ይልቅ ነፍሱን የሚያዳምጥ መሆን አለበት። ከሥጋው ምግብ ይልቅ ለነፍሱ ምግብ የሚጨነቅ መሆን አለበት። ይህ ማለት ምንድር ነው? ይህ ማለት ዘውትር ጥበብን የሚፈልግ፤ ነፍሱ የምትሳቀቅበትን ነገር (መዋሸት፣ የሌላውን መቀማት፣ ጉቦ መስጠትና መቀበል፣ ፍትሕን ማጓደል...ወዘተ) አለማድረግ ይኖርበታል፡፡ ነፍሳችን የምትጠየፋቸውን ነገሮች በማድረግ የሚመሠረት ደስታ፥ መጨረሻው የማያምር ይሆናል። ሶቅራጠስ እንደሚለን ከሁሉ በላይ መልካም እሴቶች Virtue) የተባሉ የሚፈልግ እና ያገኘ ሰው ደስታ የእርሱ ትሆናለች። የሰው ልጅ ከውጫዊ እውቀት፣ ንብረት፣ ውበት፣ ሥልጣን፣ ገንዘብ ደስታ መፈለጉን ትቶ፤ መልካም እሴቶችን ማለትም ጥበብን፣ ፍትሐዊነትን፣ ጽናትን፣ ደግነትን፣ እውነት ተናጋሪነትን፣ ትህትናን የራሱ በማድረግ ነፍሱን ከመገበ-ደስታ የእርሱ ትሆናለች፡፡ እነዚህን መልካም እሴቶች በመላበስ ይለናል ሶቅራጠስ - እውነተኛ ደስታን ማግኘት እንችላለን።


ማጣቀሻ፦ ኢውቲዲመስ፥ Happiness Strategies ድረገጽ ፥ Pursuit of Happiness ድረገጽ ፥ ጥበብ ከጲላጦስ መጽሐፍ ፥ Wikipedia የመረጃ ቋት

@zolaarts
🌿የአምላክ ፍቅር የአለምን ፍርሃት ሁሉ አውጥቶ ይጥላል::
-
ፍርሃት ትልቁ ሀጥያት ነው::
-
የፍቅር ተቃራኒም ጥላቻ ሳይሆን ፍርሃት ራሱ ነው::
-
ሰው የሚጥላው ስለሚፈራ ነው::ሀጥያትም የሚሰራው ፍርሃት ያሰረው ነው::
-
ፍርሃት የሌለው ፍቅር አለው::ፍቅር ካለው ደግሞ አምላክ አለው::
-
ፍርሃት አለምን የሚመሩ ሰዎች አይነተኛ መሳርያ ናት::
-
ይህቺ መጥፎ መንፈሳዊ ቅመም በህዝቡ ልብ ውስጥ ስትጨመር በቁም ያንቀላፋ ማህበረሰብን ትፈጥራለች::
-
ይህቺ ፍርሃት የተባለች መርዝ ሰውን ከራሱ: ከሰው : ከተፈጥሮ እና ከአምላኩ ትለያለች::
-
ይህም ምድርን ለሚመሩ ሰዎች ምቹ ሁናቴን ይፈጥራል::በቁም ያንቀላፋን እንደፈለጉት ለመምራት ይቀላል::
-
ሚዲያውን ብንመልከተው የሚነዛው ፍርሃት እንጂ ፍቅር አይደለም::ሆሊውድን ብናየው ግድያ እንጂ ህይወት አይደለም::
-
የተፈጥሮ አደጋ : ጦርነት: የኑሮ ውድነት: በሽታ: ስራ አጥነት: ወንጀል ....እና ሌላም አስፈሪ መረጃዎችን የአለም ሚዲያዎች ሲለቁ አጋጣሚ እንይደለም::ሆን ተብሎ ህዝቡን ለማስፈራራት ታስቦ ነው::
-
ለዜና ለዜናማ መተንፈሳችን ብቻ አስደናቂ ነበር::ችግር ካለበት ጥቂት ቦታ ሰላም ያለበት ብዙ ቦታ ያስገርም ነበር::እርሱን ማውራት ግን ማስፈራራት ስለማይሆን በዜና አይዘግብም::
-
አንተን ማስፈራራት አንተን ከፈጠርህ አምላክህ መለየት ነው::አንተን ማስፈራራት አንተን እንደአንተ ካሉ የአምላክ ልጆች መነጠል ነው::አንተን ማስፈራራት የውስጥህን አቅም እንዳታወጣ መገደብ ነው::አንተን ማስፈራራት ለሚያስፈራሩህ ሰዎች ባርያ እንድትሆን መፍቀድ ነው::
-
ፍቅርን ግን እነሱ ራሱ ይፈራሉ::የፀጋው ብርሃን ይጥላቸዋል::
-
ፍቅር ከኒውክሌር ቦንብ በላይ ሀይል አለው::የአለምን ፍርሃት ሁሉ ድምጥማጡን ያጠፋል::
-
የሚፋቀር ህዝብ እና ማህበረሰብ ከፍርሃት ባረነት ነፃ ይወጣል::ማንም እንደፈለገ አይፈነጭበትም::
-
ለራስህም ሆነ ለሰው ልጆች ስትል ፍቅርን ምርጥ::አምላክ እያለ አትፍራ::የፈጣሪን ፍቅር ሰዎች ውስጥ እይ::ጠላቶችህን ሳይቀር በፍቅር አይን ተመልከታቸው::ባንተ የፍቅር ብርሃን ውስጥ የእነሱ የክፋት ጨለማ ቦታ አይኖረውም::
-
ፍርሃት ትልቁ ሀጥያት ነው! ፍቅር ደግሞ የመጨረሻው ፅድቅ ነው::
-
የቱን ትመርጣለህ? ፍቅርን ወይስ ፍርሃትን??
@zolaarts
ማንም ከበታችነት ስሜት ጋር የተወለደ ወይም የሚወለድ ሰው የለም፡፡ የበታችነት ስሜት ተፈጥሮአዊ ሳይሆን በአካባቢ ተጽእኖ የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሰዎች ስለራሳቸው የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከአካባቢያቸው ይማራሉ፡፡ የተማሩትን ነገር ደግሞ ትተው አዲስ ነገር መማር ይችላሉ ማለት ነው።ስለዚህ የበታችነት ስሜት ሊለወጥ የሚችል አስተሳሰብ ነው።

እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ እንዲሁም ካደገበት አካባቢ አንጻር ልዩ በመሆኑ በበታችነት ስሜትን የሚሸነፍበት አንድ ወጥ የሆነ አካሄድ ሊኖር ይችላል።

በሌሎች ሰዎች አስተያየት ላይ ጥገኛ አለመሆን በልጅነት ወቅት አንድ ነገር ሰርተን ወላጆቻችን ወይም ትልልቆች ብለን የምናስባቸው ሰዎች ጥሩ ነው ትክክል ነው ጎበዝ እንዲሉን እንፈልጋለን በጎልማሳነት ጊዜ እንዲህ ያለውን የልጅነት ወቅት ባህርይን መተው አስፈላጊ ነው።

ከሰዎች ተገቢውን አስተያየት መጠየቅና ስራችንን መገምገም ጠቃሚ ቢሆንም፣ በእነርሱ አስተያየት ላይ ጥገኛ መሆን ዞሮ ዞሮ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ይጎዳል ራሳችንን ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መለየት በተቻለ መጠን ማንነታችንን በአእምሮአችን ውስጥ ከተከማቸው አሉታዊ አስተሳሰብ መለየት አለብን።
ከእኛ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆዩ ከሆኑ ከእነርሱ ጋር ዝምድና ስለፈጠርን በቀላሉና ቶሎ ላይሄዱ ይችላሉ።


ከእነርሱ ጋር ላለመኖር ከወሰንን ቀስ በቀስ ስፍራውን ይለቃሉ። በእነርሱ ስፍራ ደግሞ ተገቢ የሆኑ ሃሳቦችን እናስገባለን እነዚያ ቀስ በቀስ ገብተው ስፍራ እንደያዙ ሁሉ አዲሱና መልካም የሆነው አስተሳሰብም ዕድል ከሰጠነው ቀስ በቀስ ወደ አእምሮአችን ገብቶ ሥፍራውን ይይዛል።

በውድቀታችን ራሳችንን ከመኮነን ይልቅ ከውድቀታችን መማር እና ስህተታችንን ማዎቅ እና ድጋሚ ስህተት እንዳንሰራ መጠንቀቅ ነው እሚሻል ሰው ሆኖ ስህተት የማይፈጽም ሰው የለም። ዋነው ነገር የሰራነውን ስህተት መማሪያ ማድረግ ላይ ነው።

በስህተታችን ራሳችንን እየወቀስን የምንሄድ ከሆነ ራሳችንን ለመቀበል እንቸገራለን። ከስህተታችን ተምረን ወደፊት ማሻሻል የሚገባንን ነገር የምናስብ ከሆነ ደግሞ ራሳችንን ተቀብለን ወደፊት እንሄዳለን።

ስለሆነም በህይወታችን በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች በደረሰቡን ችግሮች ውድቀቶች፣ አለመሳካቶችና መልካም ያልሆኑ ነገሮች ሁሉ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን ከመኮነን ከክፉ ነገሮች መልካምን ነገር ተምረን ወደፊት መሄድ የተሻለ አማራጭ መንገድ ነው ሁሌም ወደ ፊት

ራሳችንን በፉክክር ውስጥ አለማስገባት
እያንዳንዱ ሰው ልዩ የሆነ ተፈጥሮ አለው በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው እምቅ ወይም ችሎታ አንድ ዓይነት አይደለም።

ስለዚህ ከሌሎች ጋር ሁልጊዜ መፎካከርና ራሳችንን ከሌሎች አንጻር ከመገመት ይልቅ እኛ ዘንድ ያለውን ማወቅና መጠቀም ነው እሚሻለው። ፀሀይን ከጨረቃ ጋር ካነፃፀርን ጨረቃ ምንም ብርሀን የላትም ማለት ነው አያችሁ ሁሉንም እንደተሰጠን ነው መጠቀም ያለብን ጨረቃ በጨለማ ስናያት ብዙ ብርሀን ትሰጠናለች ከፅሀይ ጋር ግን ማነፃፀር ግን ከንቱ ልፋት ነው
ከቀረበልን እንጀራ ላይ ቆመን የቀረበልንን እንጀራ እንደመፈለግ ነው በፍፁም እራሳችሁን ከማንም ጋ አታዎዳድሩ በቃ በዚህ አለም ትልቁ ነገር ከሌሎች መማርን መልመድ እና ስህተትን ማወቅ ነው...

የተሰጠንን ስጦታችንን በመለየት ማሳደግ እያንዳንዱ ሰው የተለያዬ ተሰጥኦ አለው።ስለዚህ በውስጣችን ያለውን እምቅ/ችሎታ ፍላጎታችንን እና ምቹ ሁኔታዎችን በመለየት ስጦታችንን በዕውቀትና በክህሎት ማሳደግ እንችላለን፡፡ ጎበዝ በሆንበት ወይም መስራትና መሆን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የበለጠ ዕውቀትና ክህሎትን በማጎልበት የበለጠ ፍሬያማ መሆን እንችላለን።

በችሎታችን ራሳችንና ሌሎች ሰዎችን መጥቀም ስንችል ደግሞ እርካታና ደስታን እናገኛለን። ለሰዎችም አንድ በጎ ነገር ማድረግ መቻላችን ደግሞ ስለራሳችንም በጎ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያግዘናል።

የበታችነት ስሜት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ ተገቢውን መፍትሔ ለመፈለግ እጅግ ያግዛል። ምክንያቶቹ ከሰው ወደ ሰው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ራሳችንን የማንቀበል ከሆነ እኛው ለራሳችን ጠላቶች ሆንን ማለት ነው። ሁልጊዜ ከራሳችን ጋር እንጣላለን። ጠላትን በውስጣችን ተሸክመን እንዞራለን ማለት ነው። ስለዚህ ራሳችንን በመቀበል በሰላም በመኖር የበታችነት ስሜትን ማስወገድ እንችላለን።

በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት እንዲሁም ስለራሳችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እንከን የለሽ ስራዎችን ለመስራት ጥረት ማድረግ የማይጠቅም አካሄድ ነው። ማንም ሰው በንግግሩና በስራው ፍጹም መሆን አይችልም። ስለዚህ ይህን ዓይነት መንገድ መከተል የበለጠ ራስን ለውድቀት ብሎም ለበለጠ የበታችነት ስሜት እንዲሰማን ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይሆናል።

በቅናት መንፈስ ውስጥ ሆኖ ከሌሎች ሰዎች በልጦ ለመገኘት ጥረት ማድረግ የበታችነት ስሜትን አያጠፋም። ጤናማ ያልሆነ ፉክክር በማሸነፍና በመሸነፍ ሚዛን ውስጥ ያስገባናል።

ብዙ ጊዜ በአሉታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ የበታችነት ስሜታችን እንዲኖር እንዲሁም እንዲያድግ ያደርጋል።ከሌሎች ሰዎች በችሎታ በብቃት በትምህርት ደረጃ በገንዘብና በሌሎች ነገሮች እኩል ብንሆን ስለራሳችን ያለን አስተሳሰብ በጎ እንደሚሆን ማሰብ ሁልጊዜ ትክክል አይደለም። ስለዚህ ትኩረት መደረግ ያለበት ደረጃን በማሻሻል ላይ ሳይሆን በማንኛውም ደረጃ ላይ ብንሆን ራሳችንን ተቀብለን መኖር መማር ላይ ነው።

@zolaarts
ሰው ለምን ይስቃል?

ዮጋ ንቃተ ሂሊናን ለሁለት ይከፍለዋል- እራሱን ያወቀና ያላወቀ። ነፍስ እያላቸው ነፍስ እንዳላቸው የማያውቁት ራሳቸውን ያላወቁ ናቸው። ይሁን እንጂ ራሳችንን ማወቅ የሚገባን እኛ እንኳን በብዙ መንገዶች እንደ እንስሳት፣ ዛፎችና ድንጋዮች ነን። ሰው የሆነው በጣም ጥቂቱ ክፍላችን ነው።
በዚህም ሳብያ ሰው እጅግ በጣም እረፍት አልባ ነው። እንስሳት እረፍት አልባ አይደሉም፤ እራሱን የሚገድል እንስሳ የለም። አንድ እንስሳ እራሱን ያጠፋ ግዜ ዝርያዉን ከእንስሳነት ወደ ሰብዓዊ ፍጡርነት እየተቀየረ መሆኑን እወቁ። ራሱን የሚያጠፋ አንድም እንስሳ የለም። እራሱን እንዲያጠፋ የሚያነሳሳ ስጋት አይፈጠርበትም። ከሰው በቀር አንድም እንስሳ አይስቅም።መንገዳችሁ ላይ አንድ በሬ ሲስቅና ሲገለፍጥ ቢያጋጥማችሁ በዛ መንገድ አታልፉም። የትኛውም እንስሳ አይስቅም። ምክንያቱም ሃዘንተኛ ስላልሆነ ሃዘኑን የሚያስረሳው ሳቅ አያስፈልገውም። ሳቅ የሀዘንና የደስታ አልባነት መደበቅያ ነው።

በአለማችን ደስታ እየጠፋ በመጣ ቁጥር የተለያዩ የመዝናኛ አይነቶች እየተፈጠሩ የመጡትም በዚህው ምክንያት ነው። ሲኒማ፣ ቲቪ፣ ሬድዮ፣ ዳንስ፣ ዘፈን ተፈጥረዋል። እነዚህ ሲሰለቹት ደግሞ ሰው ሌሎች አዳዲስ መዝናኛዎች እንዲመጡለት ይፈልጋል። በዚ ዘመን ሃምሳ በመቶ የዓለማችን ሃይል ለሰው ልጆች መዝናኛዎችን ለማቅረብ እየዋለ ይገኛል። በዚ ዘመን ሰውን ለማዝናናት የቻሉ ሁሉ በጣም ተፈላጊ ናቸው። የምትፈልጓቸው አልፍ ስለሚያዝናኗችሁ ነው። ስቃይ ስላላችሁ ትንሽ የሚያዝናናችሁ ሰው ስታገኙ በጣም አስፈልጊያችሁ ታደርጉታላችሁ።

ሳቅ ከውስጥ ያለን ውጥረት መቀነሻ ነው። እንስሳ የማይስቀው ውጥረትና ስጋት ስለሌለበት ነው!

ምንጭ©-: የንቃት ፀሐይ- ባግዋን ራጅኒሽ(ኦሾ)
@zolaarts
ማመን አለማመን

አለማመንን፣ከማመን ይልቅ ከባድ ሆኖ ነው ያገኘውት ሰው ሲያምን አንዴ ነው ያንን እምነት መጠበቅም ማበላሸትም እምነት የተጣለበት ሰው ኃላፊነት ነው ስለዚህ ያመነው ሰው ኑሮውንና ስራውን በሰላም መምራት ይችላል አለማመን ግን በየደቂቃውናበየቅፅበቱ ስጋትን የሚሚፈጥር፣ግንኙነትንና ፍቅርን የሚያቀጭጭ አረም ነው።

የማያምን ሰው የጥርጣሬውን ትክክለኛነት ለማረጋገኝ የሚያባክነው ጉልበትና ጊዜ ለስራ ቢውል ብዙ ውጤት ባስገኘ ነበር። በዚህም የተነሳ እምነት በጠፋበት ትዳር ቤተሰብና ኅብረተሰብ ውስጥ ብክነትና ክስረት ይበዛል ።

መተማመን ደግሞ የብልፅግናና የፍቅር መሰረት የደስታ ዛፍ የሰላም ልማትም ነው ከዚህ በተጨማሪም የጠፋን እምነት ለመመለስ የፈሰሰን ውሀ ለማፈስ ከመሞከር ያላነሳ ስለሚከብድ እምነትን በታማኝነት መጠበቁ የጠፋ እምነትን ለመመለስ ከሚከፈለው ዋጋ በሲ እጥፍ ያንሳል።ይህ ማለት ግን የተሰበረ እምነት አይጠገንም ማለት አይደለም።

የተቆለፈበት ቁልፍ { ዶ/ር ምህረት ደበበ @zolaarts
የተሻለ ሰው ለመሆን በህይወት ውስጥ ማሸነፍ የሚያስፈልጉ 6 ተግዳሮቶች
===========
ሕይወት እርግጠኛ ያልሆነ ሮለር ኮስተር ነው። እሱን ለመቀበል እና በጉዞው ለመደሰት መምረጥ ይችላሉ ፣ በመንገድ ላይ ካሉዎት ልምዶች በደስታ ይማራሉ ። ወይም በሁሉም የሕይወት ፈተናዎች ላይ ለማመፅ መምረጥ ትችላላችሁ, በእያንዳንዱ የጉዞዎ ቅጽበት ይናደዳሉ. የኋለኛው የትኛውንም እድገት ወይም እድገት ይዘርፋል ፣ የቀደሙት ግን ከእነዚያ ፈተናዎች ለመማር እና እነሱን ለመለማመድ ጥሩ ሰው ለመሆን እድሉን ይሰጥዎታል።
"የተሻለ" አንጻራዊ ሊሆን ቢችልም አንድ ነገር እርግጠኛ ነው - "የተሻለ" ማለት የተሻሻለ ማለት ነው. እራስህን የትም ብታገኝ፣ ሁልጊዜ መሻሻል ቦታ አለህ። አንድ መነኩሴ እንኳን በየቀኑ ራሱን ለማሻሻል ይጥራል፣ ሁልጊዜ የተሻለ ሰው ለመሆን ይጥራል።
በህይወት ውስጥ ያሉ ፈተናዎች ተሰጥተዋል, እና ለእርስዎ ጥቅም ሊጠቀሙበት ይችላሉ. እያንዳንዳቸው ለግል እድገት እና ራስን ማሻሻል እድል ናቸው. ዞሮ ዞሮ፣ ግቡ እያደጉ ሲሄዱ የተማራችሁትን ተጠቅማችሁ የራሳችሁ ምርጥ እትም መሆን ነው።
የተሻለ ሰው ለመሆን በመንገድዎ ላይ ሊያሸንፏቸው የሚገቡ 6 የተለመዱ የህይወት ፈተናዎች እዚህ አሉ፡-
1. ኪሳራ/ Loss
ስራዎን, እድልዎን, ወይም ግንኙነትዎን ያጡ - ማጣት የማይቀር የህይወት ክፍል ነው.
ምንም ይሁን ምን, ኪሳራ የህይወት ትልቁ ፈተናዎች አንዱ ነው. ድንገተኛ እና የሚረብሽ ስሜት ሊሰማው ይችላል. ነገር ግን፣ ኪሳራ ወደፊት ለመራመድ በእውነት አስፈላጊ በሆነው ነገር ላይ ለማሰላሰል እድል ይሰጥዎታል።
ያለዎትን ወይም የሚፈልጉት ነገር ማጣት እንኳን ደህና መጣችሁ የማንቂያ ጥሪ ሊሆን ይችላል። ማጣት እራስህን እንድትጠይቅ ያስገድድሃል፣ “የጠፋሁት ነገር ለእኔ ጠቃሚ ነበር?” እና "የምፈልገውን ለማግኘት ምን ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ?"
በነዚህ ጥያቄዎች መነፅር የእርስዎን ኪሳራ ለመፈተሽ መምረጥ የጠፋብዎትን ትክክለኛ ዋጋ እንዲገመግሙ ያደርግዎታል እንዲሁም ለምን ዋጋ እንደሚሰጡት ይወቁ። ስለምትሰጡት እና ለምን ዋጋ እንደምትሰጡት ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ማግኘቱ የተሻለ ሰው ለመሆን ቁልፉ ነው ምክንያቱም ቃላቶችዎ እና ድርጊቶችዎ ታማኝነትን ስለሚሰጡ ነው።
2. ውድቀት/ Failure/ ማለፍ
ውድቀት ያላጋጠመው አንድም ሰው በህይወት የለም። ለማደግ ውድቀት አለብህ። አለመሳካት በጉዞዎ ላይ ተፈጥሯዊ የፍተሻ ነጥብ ያቀርባል፣ ይህም ማሻሻያዎችን ለማድረግ የቅርብ ጊዜ የባህሪ ምርጫዎትን እንዲገመግሙ ያስችልዎታል። ሲወድቁ፣ አንድ አትሌት በጨዋታዎች መካከል የተቀረጸውን ቀረጻ እንደሚገመግም ውሳኔዎችዎን እና ባህሪዎችዎን ለመገምገም እድሉን ያገኛሉ።
ወደ ውድቀት የሚመሩዎትን ውሳኔዎችን እና ድርጊቶችን መገምገም በዋጋ ሊተመን የማይችል ልምምድ ነው። ያደረጓቸው ውሳኔዎች ወደ አንዳንድ ባህሪያት እና ድርጊቶች እንዴት እንዳመሩ መረዳቱ እንደገና ተመሳሳይ ስህተቶችን እንዳያደርጉ ይከላከላል። እንዲህ ዓይነቱ ግምገማ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመለጡዎትን ጠቃሚ ዝርዝሮች በሚቀጥለው ጊዜ የተሻለ እና የበለጠ መረጃ ያለው አካሄድ እንዲወስዱ ያስችልዎታል።
የውድቀት ልምድ ርህራሄን ፣ ርህራሄን እና ርህራሄን እንዲያዳብሩ ያደርግዎታል። የእርስዎ ልምድ ተመሳሳይ ልምድ ካጋጠመው ከማንኛውም ሰው ጋር የጋራ የሆነ ነጥብ ይሰጥዎታል። እነዚያ ሶስት ስሜቶች የተሻለ ሰው ለመሆን በሚያደርጉት ጉዞ ላይ አስፈላጊ መሳሪያዎች ናቸው ምክንያቱም ሌሎች ደህንነት እንዲሰማቸው እና በዙሪያዎ እንዲታዩ ስለሚያደርጉ ነው።
3. እንቅፋቶችን/ Setbacks/ ማሸናፍ
ብዙ ስሞች አሏቸው: የተሳሳቱ እርምጃዎች, የዝንጀሮ ቁልፎች, ያልተጠበቁ ሁኔታዎች. ነገር ግን የተሻለ ሰው ለመሆን በምናደርገው ጉዞ ላይ እንቅፋቶች አሉ።
ሁላችንም በጉዟችን ላይ የዘገየ ሂደት፣ እንቅፋት ወይም መዘግየት አጋጥሞናል። ተግዳሮቱ መዘግየቱ ለምን እንደተከሰተ መረዳት ነው። እድገታችን እንዲቀንስ ያደረገው ምንድን ነው?
በአእምሮህ ሁሉንም ማድረግ ወይም መናገር የሚገባቸውን ትክክለኛ ነገሮች ማወቅ ትችላለህ፣ነገር ግን ሰብአዊነትህ ከአንተ የሚሻልህ ጊዜዎች አሉ። የተሻልህ ሰው ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ብታደርግም በድንገት የምትጸጸትበትን ነገር ፈጸምክ ወይም ተናገር። ምናልባት ጥሩ ሰው ለመሆን ካለህ ፍላጎት ጋር አሉታዊ በሆነ መንገድ ምላሽ ትሰጥ ይሆናል። ችግር የለም!
መሰናክሎች የመማር እድሎች ናቸው። እድገትን የሚቀንሱትን የነገሮችን አይነት ጠንከር ያለ ግንዛቤ ማግኘታችሁ ሁለቱንም እንድታስወግዷቸው እና እንድታስቀድሙ ይፈቅድላችኋል።
ድክመቶችን የማሸነፍ አንዱ አወንታዊ ውጤት ማገገም ነው። የተሻለ ሰው ለመሆን የሚደረገው ጉዞ በአእምሮ ጠንካራ መሆንን ይጠይቃል። መሰናክሎች በድርጊትዎ ውስጥ አሁንም ታማኝነትን እየጠበቁ ያንን የአእምሮ ጥንካሬ ለመገንባት እና ሌሎች እንደሚታዩ የሚሰማቸውን ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን የሚያበረታታ ስሜታዊ ግንዛቤ ናቸው።
4. የሞራል ኮምፓስዎን ማቋቋም/ Establishing Your Moral Compass
ለራስህ ትክክልና ስህተት የሆነውን መለየት ምንጊዜም የአሁን የህይወት ፈተና ነው። ዛሬ ከአንዱ ርዕዮተ ዓለም ነገ ደግሞ ሌላ ሊስማሙ ይችላሉ። ሃሳብህን መቀየር መብትህ ነው፡ እና የት እንደቆምክ መወሰን የአንተ ሃላፊነት ነው። ሁለቱ እጅ ለእጅ ተያይዘዋል።
የተሻለ ሰው ለመሆን በመንገድዎ ላይ አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑትን መወሰን። ራስን ማሻሻል በራስዎ የግል ስሜት ትክክል እና ስህተት ነው.
ብዙ ሰዎች በእሴቶቻቸው እና በእምነታቸው መሰረት ይሰራሉ። እንደ ሰው ለማደግ ለራስህ ፍቃድ መስጠት ማለት ሁለቱንም እንደገና ለመመርመር ጊዜ ወስደህ ነው። የእርስዎ እሴቶች እና እምነቶች ከመጨረሻው ግብዎ ጋር የማይጣጣሙ መሆናቸውን ማወቅ ይችላሉ።
5. አእምሮዎን መቆጣጠር/ Mastering Your Mind/ መቻል
አእምሮህ የተሻለ ሰው ለመሆን በምትሄድበት መንገድ ላይ ብርቱ ተቃዋሚ ሊሆን ይችላል። ነገሮች ጥሩ በማይሆኑበት ጊዜ ሁሉንም ዓይነት አሉታዊ አስተያየቶችን ሊይዝ ይችላል፣ እና እርስዎን በጥርጣሬ እና በፍርሀት ሊያደናቅፍዎት ይችላል - ከፈቀዱት። አእምሮን መቆጣጠር ከሁሉም ትልቁ የህይወት ፈተናዎች አንዱ ነው።
አእምሮዎ እይታዎን ይቆጣጠራል፣ በዙሪያዎ ካለው አለም ጋር ያለዎትን ግንኙነት እንዴት እንደሚቀበሉ እና እንደሚያስተናግዱ ያሳውቃል። ከሌሎች ነገሮች በተለየ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ገዢ ለመሆን፣ አእምሮ ለመቆጣጠር የተወሰነ ዕድሜ ሊወስድ ይችላል። ተግዳሮቱ የእለት ተእለት አእምሮን የመቆጣጠር ስራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆን እና የዚህ ስራ ማለቂያ የለሽ ተፈጥሮ ሙሉ ግንዛቤ እያለው ማሳየት ነው።
የትም ብትሄድ እዚያ ነህ; ስለዚህ ከራስዎ መደበቅ የማይቻል ነው. አእምሮህ የማይታዘዝ እና ደግነት የጎደለው ከሆነ፣ በዋነኛነት ከራስህ የተሻልክ ስላልሆንክ የተሻለ ሰው ለመሆን ከባድ ይሆንብሃል።
እንደ እድል ሆኖ፣ አእምሮዎን የመቆጣጠር ስራ ለመጀመር እጅግ በጣም ብዙ መንገዶች አሉ። ዋናው ነገር እድገትን በሚያበረታታ ጤናማ መንገድ ከራስህ ጋር እንድትሆን ቦታ መፍጠር ነው። በትኩረት የግል ጊዜን ለማመቻቸት አንዳንድ የተለመዱ ዘዴዎች ቴራፒ, ማሰላሰል, ራስን ማሰላሰል, ጸሎት, ሆን ተብሎ ዝምታ, ጆርናል እና በተፈጥሮ ውስጥ መገኘት ናቸው.
ከትክክለኛ_ሰዎች_ጋር_ጊዜህን_ማሳለፍ_ጀምር - እነዚህ ሰዎች የሚያስደስቱህ ፣ የሚያደንቁህ ፣ የሚወዱህ እና እንድትሻሻል እና እንድትቀየር ጤናማ በሆነ መንገድ የሚያበረታቱህ ናቸው፡፡

#ችግሮችህን_ፊት_ለፊት_መጋፈጥ_ጀምር - አንተን የሚገልጽህ ችግርህ ሳይሆን ለችግሮችህ የምትሰጣቸው ምላሾች እና ከችግሮችህ ውስጥ ወጥተህ ማገገም የምትችልበት አቅምህ ነው፡፡ እርምጃ እስካልወሰድክባቸው ድረስ ችግሮችህ አይጠፉም፡፡ የምትችለውን አድርግ ለአደረግከውም ነገር እውቅና ስጥ፡፡

#ስለ_ሁሉም_ነገር_ከራስህ_ጋር_ግልጽ_መሆን_ጀምር - ትክክል ስለሆነው ነገር እና እንደዚሁም መቀየር ስላለባቸው ነገሮች ሀቀኛ እና ግልጽ ሁን፡፡ ማሳካት ስለምትፈልገው ነገር እና መሆን ስለምትፈልገው ሰው ግልጽ ሁን፡፡ ሁልጊዜም በሕይወትህ እያንዳንዱ ክፍል ላይ ሀቀኛ እና ግልጽ ሁን፡፡

#ለራስህ_ደስታ_ቅድሚያ_መስጠት_ጀምር - ፍላጎቶችህ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ለራስህ ዋጋ ካልሰጠህ ፣ ለራስህ ካልቆምክ፣ ራስህን ካልጠበቅክ ሆን ብለህ ራስህን ለማጥፋት ተነስተኻል ማለት ነው፡፡ አስታውስ በዙሪያህ ላሉት እየተቆረቆርክ እና እያሰብክ የራስህንም ፍላጎቶች ማሳካት ትችላለህ፡፡ አንድ ጊዜ ፍላጎቶችህ እንደተሟሉ ደግሞ የአንተ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የበለጠ መድረስ ትችላለህ፡፡

#በኩራት_እና_በሀቀኝነት_ራስህን_መሆን_ጀምር - ሌላ ሰው ለመሆን መሞከር አንተ የሆንከውን ሰው ማባከን ነው፡፡ ራስህን ሁን፡፡ ሌሎች አጠገቡ የማይደርሱበት ሀሳቦች ፣ ብርታቶች እና ውበት የያዘውን በውስጥህ ያለውን ያን ሰው ተቀበለው፣ እቀፈው፡፡ @zolaarts
ልጅ ሳለህ ገና ጎረምሳም ይህን አስተውል!
=========================

ሳተናው!
አንድ ወንድምህ በፈተና ተንጦ፣ በንባብ ረግቶ፣ በልምድም በስሎ ያገኛቸውን መራር ሐቆች በምክር መልክ አቅርቦልሃል፤ አንተ ግን በወደድከው ኑር!

በየዘመናቱ ያለውን ትውልድ የሚፈትኑ፣ በተፈጠረለት ልክ፣ ለተፈጠረለትም ዓላማ እንዳይኖር የሚያሰናክሉ ተግዳሮቶች አሉ።

እነዚህንም ተግዳሮቶች አስቀድሞ ለይቶና መርምሮ ትውልዱን ማሳወቅ፣ እነርሱን የሚገጥመበትና የሚረታበትንም ጥበብና ክሒሎት ማስታጠቅ የወላጆች በተለይም የአባቶች ሚና ነው።

አለበለዚያ ግን የማስተዋልና የማመዛዘን እድሜ ላይ እስኪደርስ ድረስ በቀላሉ በሚወድቅባቸው የፈተና ጉድጓዶች ውስጥ መቅረቱ መጎዳቱም የማይቀር ይኾናል።

ወንድምዓለም! ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፍ የነበረውን እውቀት በተለይም የአጼው ሥርዓት ከተለወጠ ወዲህ አባቶችን፣ ታላላቆችን፣ አዛውንቶችን መስማት ማክበርና ፈለጋቸውን መከተል እጅጉን እያሽቆለቆለ መጥቷል።

ዛሬም በእኛ ዘመን ጎረመስኩ፣ ደረስኩ፣ አወቅኩ የሚለው አባቱን በአክብሮት ስም ሳይኾን "ሼባው..." ብሎ መጥራት ወግ አድርጎታል። የሚያሳዝነው ግን የተሳለቀበት "ሼባነት" ላይ ሳይደርስ የሚረግፈው ወጣት ብዙ መኾኑ ነው።

የኾነው ኾኖ ታናሼ! አንተ ምክሬን እንድትሰማኝ፣ በተሳሳተ መንገድም ኾነ በልከኛው ሄጄ ያተረፍኩትን ጥበብ እንድታደምጠኝ አምናለሁ።

ደግሞም እኮ እወድሃለሁ! ቁጣዬም ኾነ ተግሳጼ ስለምወድህ እንጂ እንደ ወተት በሚጣፍጥ ቃል ማባበል ጠፍቶኝ አይደለም። ነገር ግን ጎርምሰሃልና አጥንትም መጋጥ ችለሃልና መራሩን ሐቅ መጋት መልመድ ስላለብህ እንጂ።

ሳተናው!
እድሜህ በአስራዎቹ መጨረሻ በሀያዎቹም አማካይ መካከል ከኾነ እነዚህን አስተውል፦

፩ኛ ሥነ-ሥርዓት አልተማርክ ከኾነ ራስክን አስተምር!
ሥነ-ሥርዓት ያንተን ሰብዓዊ እሴት፣ ዋጋ፣ ማንነት በከፍተኛ ደረጃ የሚሰቅል፣ የሚጨምርና የሚያገንም ነው። እርሱም ደግሞ በብዙዎቹ የዛሬ ወንዶች ላይ የማይታይና የማይገኝም ነው።

ሥነ-ሥርዓት ማለት ሥራዎችህን የምትሠራበት የታወቀ፣ የተገለጠ፣ ምክንያታዊ እና ቅደም ተከተላዊ መንገድ ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ የእንቅልፍ፣ የንባብ፣ የአመጋገብ፣ የጠዋት ንቃት፣ የእስፖርት፣ የጸሎት፣ የወሲብ... የሌሎችም ድርጊቶችህ አካሄድ አንተን ይቀርጹሃል።

ብዙውን ጊዜ የሥነ-ሥርዓት ሰው የሚያደርጉን ነገን ዐይተውልን ዛሬ ላይ በእኛ የሚጨክኑ አባቶቻችን ናቸው። ምንም እንኳ የዛሬው ትውልድ በእንደ እነዚህ ዓይነት አባቶች ባይታደልም።

ነገር ግን አንድ ብለህ ራስክ ላይ መሥራት ከደፈርክ ይቻልሃል። ምክንያቱም ባሰብከውና በምትሄድበት መንገድ ፈጣሪህ ካንተ ጋር እንደሚኾን ቃል ቀብቷልና።

ስለኾነም ስለወደድክ ስላልወደድክ ሳይኾን መሥራት ያለብህን ነገር ቦታና ጊዜ ሰጥተህ ሥራ። ይህም ደግሞ ማንም የማይወስድብህ ታላቅ ሀብት ሥነ-ሥርዓት ነው።

ነገ ለምትፈልገው የሕይወት ስኬት፣ ትዳርም ኾነ ለምትገነባት ሀገር ከክንድህም የማይለይ ምርጥ መሣሪያህ እርሱ ነውና።

@zolaarts
አለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም!!

ፍቅር በራችሁን አንኳኩቶ ያውቃል? በጭራሽ! ምክንያቱም ገና ፍቅር መስጠት አልቻላችሁም። ማስታወስ ያለባችሁ የሰጠነው ሁሉ ወደ እኛው ተመልሶ እንደሚመጣ ነው። ይህም ከህይወት ህጎች አንዱ ነው።

መላው ዓለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም። ጥላቻ እንሰጣለን፣ ጥላቻም ወደኛው ተመልሶ ይመጣል። ሌሎችን እንሳደባለን ከዛም ስድብ ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። እሾህ ስንሰጥ እሾህ ወደኛው ተመልሶ ይመጣል፡፡ የምንሰጠው ሁሉ በተለያዩ መንገዶች ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። ፍቅርን ካካፈልንም እንደዚሁ በተለያዪ መንገዶች ተመልሶ ወደኛው ይመጣል። ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ፍቅር ወደ እኛ ተመልሶ ካልመጣ ፍቅር እንዳልሰጠን ማወቅ አለብን፡፡

ፍቅር እምትሰጠው እንጂ እምትቀበለው አይደለም።

ኦሾ/osho @zolaarts
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 17 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 7 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.