ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
50K subscribers
12.5K photos
346 videos
31 files
7.7K links
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Download Telegram
እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ሚያዝያ ቡሩክ፤ አመ ፲ወ፱፦

ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኀኒነ ክርስቶስ
ተዝካረ ዳግም ትንሣኤ

✞ወበዓለ ቅዱሳን ፦

✿አበዊነ ሐዋርያት ንጹሐን
✿ቶማስ ሐዋርያ (ዘሕንደኬ)
✿ስምዖን ሰማዕት (ዘአርማንያ)
✿፻ወ፶ ሰማዕታት (ዘሃገረ ፋርስ)
✿ጽርሐ ጽዮን ቅድስት

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

https://t.me/zikirekdusn
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ሚያዝያ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=

✞ ሰማዕቱ በብኑዳ ✞

+ቅዱስ በብኑዳ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ በምድረ
ግብፅ ተባሕትዎን መርጦ የሚኖር ገዳማዊ አባት ነው::
በበርሃ
በጾምና በጸሎት ተወስኖ ለእግዚአብሔር የምስጋናን
መስዋዕት እየሠዋ አገልግሏል::

+በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያኖች በግፍ ሲገደሉ ቅዱሱ
ሰው በበርሃ ውስጥ ነበር:: አንድ ቀን የእግዚአብሔር
መልአክ መጥቶ
ሰማዕት እንዲሆን መከረው:: እርሱም ነጭ በነጭ ለብሶ
አምሮበት ወደ ንጉሡ ሔደ:: በፊቱም ቀርቦ በክርስቶስ
ስም ታመነ::
ብዙ ጸዋትወ መከራም ተቀበለ::

+ንጉሡ (መኮንኑ) "አመጣጥህ ወደ ሞት ሳለ ምነው
እንዲህ እንደ ሠርገኛ ማጌጥህ?" ቢለው "እኛ
ክርስቲያኖች ትልቁ
ሠርጋችን ሞታችን ነው:: ልንሔድ ከክርስቶስም ጋር
ልንኖር እንናፍቃለንና" ብሎታል::

+ቅዱስ በብኑዳ ብዙ ተሰቃይቶ: ተአምራትን ሰርቶ በዚሕች
ቀን ተሰይፏል:: የጽድቅን አክሊል ከሰማዕትነት ጋር ደርቦ
አግኝቷል::

❖ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ በረከትን ያካፍለን::

❖ሚያዝያ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ በብኑዳ (ሰማዕት ወጻድቅ)
2.ቅዱስ ቄርሎስ: ሚስቱና 12 ልጆቹ ሰማዕታት (ከቅዱስ
በብኑዳ ጋር የተገደሉ)

በ 20 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
6.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት
 

++"+ በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን
ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ
ብጹዓን ናችሁ::
ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ:: አትናወጡም:: ዳሩ ግን
ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: በእናንተ
ስላለ ተስፋ
ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር
የተዘጋጃችሁ ሁኑ:: ነገር ግን በየውሃነትና በፍርሃት
ይሁን:: +"+ (1ዼጥ.3:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn
#Feasts of #Miyazia_20

✞✞✞On this day we commemorate the departure of the Righteous Martyr Saint Babnuda (Paphnute)✞✞✞

✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞

✞✞✞Babnuda (Paphnute) the Martyr✞✞✞
=>St. Babnuda was a monastic father that chose the ascetic life and lived in the 3rd century in the land of Egypt. He served in the desert devoted to fasting and prayer offering praise to God.

✞During the Era of Persecution when Christians were brutally being slaughtered the Saint was in the desert. One day an angel of the Lord came to him and advised him to become a martyr. Hence, he clothed himself in white and went to the governor. He stood before him and testified the name of Christ. And he received much affliction.  

✞And when the governor asked the martyr, “While you have come to die, why are you adorned in such a way like a Groom?” the Saint replied, “For us Christians our death is our ultimate nuptials because we desire to depart and live with Christ.”

✞St. Babnuda was slain on this day after enduring many afflictions and performing several miracles. He has received the crowns of righteousness and martyrdom together.

✞✞✞May the Good God grant us from the Martyr’s blessings.

✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 20th of Miyazia
1. St. Babnuda (Paphnute) the Martyr
2. St. Cyril, his wife and his twelve children martyrs (Slain with St. Babnuda)

✞✞✞ Monthly Feasts
1. Honorable Saint Mar Theodore the Martyr
2. St. John Colobos (the Short)
3. St. Kloag (Bagoug)/ Aklog/Eclogius, the Priest
4. The Emperor St. Kaleb the Righteous (Emperor of Ethiopia)/St. Elesbaan
5. Abba Ammonius of Tounah/ Tona
6. St. Sades the Meek

✞✞✞ “And who is he that will harm you, if ye be followers of that which is good? But and if ye suffer for righteousness' sake, happy are ye: and be not afraid of their terror, neither be troubled; But sanctify the Lord God in your hearts: and be ready always to give an answer to every man that asketh you a reason of the hope that is in you with meekness and fear:”✞✞✞
1Pet. 3:13-15

✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞

(Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)

https://t.me/zikirekdusn
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!

🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑

5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
    1, 🛑አላማ

    2 ,🛑እምነት

    3,🛑ጥረት

    4 🛑ጥንቃቄ

     5🛑ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️

👉ሃይማኖት
👉ጾም
👉ጸሎት
👉ስግደት
👉ምጽዋት
👉ፍቅር
👉ትህትና
👉ትዕግስት
👉የዋህነት

ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።
        (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

🛑በቴሌግራም👉
https://t.me/zikirekdusn
Audio
"" እንብላ፥ እንጠጣ፤ "" (፩ ቆሮ. ፲፭:፴፫)

"የዘመነ ትንሣኤ ትምህርት" (ክፍል ፪/2)

(ሚያዝያ 15 - 2017)
https://t.me/zikirekdusn
እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ሚያዝያ ቡሩክ፤ አመ ፳፦

✞ወበዓለ ቅዱሳን ፦

✿በብኑዳ ገዳማዊ ወሰማዕት (ዘሃገረ ደንደራ)
✿ቄርሎስ ወብእሲቱ ወወለቱ (ሰማዕታት)
✿፲ወ፪ቱ ውሉዱ (ሰማዕታት)

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

https://t.me/zikirekdusn
የ፬ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ፦

የኔታ አባታችን፦
በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ስለርስዎ ትንፍሽ ብዬ አላውቅም፡፡ ጻድቃን በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ክብራቸውን የሚገልጽባቸውን አይወዱምና፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሰማያዊው ሠርግ ቤት (በሰሙነ ሕማማት) ተጠሩኮ መባሉን ሰማሁ፡፡

ያ ገራገር ተማሪዎ መጥቶ፤ "የንታንኮ አሟቸዋል፤ ገብረመስቀል ብለህ ዳዊት ድገም" ሲለኝ የቁርጥ አልመሰለኝም፡፡ ብጸልይስ በረከትዎን ስሻ እንጂ፤ ሌላ ምን ሙያ እዘጋለሁ!

ቁርጥ ሆነ እንግዲህ! ብዙ አበውን ቢወልዱም፤ እርስዎን የተካ ግን እስካሁን አላየሁም። ከቅኔና ቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅነትዎ የጻድቃንን ሕይወት መኖርዎ ይልቅብኛል፡፡ (ሃገሬ የተማረም አላጣች! የሚያስተምረውን የሚኖር እንጂ!)

ክቡር አባቴ ሆይ! የጸሎተ እግዝእትነ ማርያሙስ ነገር እንዴት ሆነ? (ከርስዎ ዘንድ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን ወድቆ አስደግሞ የፈቀደውን ያላገኘ ማን አለ!)

ስንት ዋርካ ቀረ ሲባል፤ "ከዋኖቹስ የተረፈ አንድ ብቻ ነው ያለ" የምንለው ነገር ዛሬ አከተመ፡፡

ጨንቆት ለሚመጣ፤ ምስጢር ለተጠማ፤ ለሃገር ምሰሶ ሆኖ መኖሩ አከተመ፡፡ (ሌላ ጽኑ ሐዘን!)

ግን ደግሞ ለስንት አሠርት ዓመታት የተሸከሙትን መከራ ሳስብ፤ ለርስዎ ደስ ይለኛል! ተገላገሉት!

ኦ እግዚኦ! አዕርፍ ነፍሰ አቡነ፡ ወመምህርነ ገብረ መስቀል! (ዘውእቱ ወላዴ አእላፍ፡ ወርዕሰ አበው የኔታ ጥበቡ ታዬ)

https://t.me/zikirekdusn
††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ብሩታዎስ †††

††† ሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የውዳሴ ማርያም ደራሲ ነው::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሙቶ ከተነሳ ከ8 ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ያምናል:: ባመነ በ6 ዓመቱ (ማለትም ከክርስቶስ ዕርገት 14 ዓመታት በኋላ) እየሰበከ ግሪክ አቴና /ATHENS/ ደርሶ ብዙ ፈላስፎችን ወደ ክርስትና ሲያመጣ አንዱ ይህ ቅዱስ ብሩታዎስ ነበር::

ቅዱስ ብሩታዎስ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: ሐዋርያትን ተከትሏቸው: እነሱም ቅስና ሹመውታል:: ጵጵስና እንሹምህ ቢሉት በፊታቸው ተንበርክኮ አልቅሷል:: አይገባኝም ማለቱ ነበር::

ታዲያ ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያት ስለ ድንግል እመቤታችን ሲጨዋወቱ እየሰማ "መቼ አይቻት" እያለ በፍቅሯ ይቃጠል ነበር:: አንዴ ግን ወሰነ:: "እመቤቴን ሳላያት እንቅልፍ አላይም" ብሎ በሽማግሌ እግሮቹ ከግሪክ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ::

የሚገርመው እርሱ እሥራኤል (ጽርሐ ጽዮን) የደረሰው በ49 ዓ/ም ጥር 21 ቀን እመቤታችን ልታርፍ ሰዓታት ሲቀራት ነበር:: ቅዱሱ ሽማግሌ እመቤታችንን በአካለ ሥጋ ስላያት በፊቷ እንደ እንቦሳ ዘለለ:: እየሰገደም አመሰገናት:: እመ ብርሃንም በንጹሐት እጆቿ ባረከችውና ዐረፈች::

ይሕን ጊዜ ምሥጢር ተገልጦለት ዜማና ቅኔ ያለውን የመጀመሪያውን ውዳሴ ማርያም ዕለቱኑ ደርሶ ለሐዋርያት ሰጣቸው:: እነርሱም ከምስጋናው ጣዕም የተነሳ ተደነቁ:: ከሐዘናቸውም ተጽናኑ::

ይሕ ድርሰት በዘመነ ሰማዕታት በመጥፋቱ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አምልቶና አጉልቶ ደርሶታል::

ቅዱስ ብሩታዎስ ግን ብዙ ሃገራትን በሐዋርያነት አዳርሶ በመልካም ሽምግልና አርፏል::

††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ብሩታዎስ ላይ ያሳደረውን የድንግል እናቱን ፍቅር በእኛም ላይ ያሳድርብን::

††† ሚያዝያ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያዊ
2.አባ ዕንባቆም ጻድቅ ሰባኬ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ (በትውልድ የመናዊ በጸጋና አገልግሎት ግን ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው:: ደራሲ : ሰማዕት : ባሕታዊና ሊቀ ምኔትም ነበሩ::)
3.ቅዱስ አካክሪስ
4.ቅዱስ ይወራስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1፡ እግዝእትነ ማርያም
2፡ አበው ጎርጎርዮሳት
3፡ አባ ምዕመነ ድንግል
4፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
5፡ አባ አሮን ሶሪያዊ
6፡ አባ መርትያኖስ
7፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል

††† "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሠጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና:: ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል . . . ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለት እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፯-፲፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
#Feasts of #Miyazia_21

✞✞✞On this day we commemorate the departure of the Saint Hierotheos (Berutawos) of Athens✞✞✞

✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞

✞✞✞Saint Hierotheos (Berutawos)✞✞✞
=>The Apostle St. Hierotheos was the first Theotokia (Hymns to Mary) author in the Era of the New Testament. If asked how that was, it was as follows.

✞8 years after our Lord Jesus Christ died by His own will and rose, St. Paul the Apostle believed. And 6 years after he converted (14 years after the ascension of Christ), he converted many philosophers to Christianity when he went preaching to Greek, Athens. And one of the converts was this Saint, Hierotheos. 

✞After St. Hierotheos believed in Christ and was baptized, he followed the Apostles. And they ordained him a priest. Thereafter, when they asked to appoint him a Bishop, he wept kneeling before them. It was him saying, “Certainly not”.

✞St. Hierotheos used to burn with the love for our Lady, the Virgin, saying, “When will I see her?” when he used to hear the Apostles discuss about her. And one day he decided. He said, “I will not sleep until I see my Lady” and went from Greek to Jerusalem with his aged legs.

✞What was amazing was that, he reached Israel (at the Upper Room) on Tir 21 (January 29) in 49 E.C (57 A.D) only hours before our Lady departed. The elderly Saint leaped in joy like a calf before our Lady because he saw her in the flesh (physically). He praised her with prostrations. And our Lady blessed him with her pure hands and departed.

✞At that moment, a mystery was revealed to him and he authored the first Theotokia that had melody and was poetic. He then gave it to the Apostles and they were amazed of the tang of the hymn and were consoled of their grief.

✞Because this hymn was lost during the Era of Persecution, St. Ephraim the Syrian wrote it later wholly and with greater emphasis.

✞St. Hierotheos departed in good old age after having reached many countries as an apostle.

✞✞✞May our Lord Jesus Christ indwell in us the love for the Virgin, His mother, which dwelt in St. Hierotheos.

✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 21st of Miyazia
1. St. Hierotheos (Berutawos) the Apostle
2. Abba Enbaqom (Habakkuk) Righteous, the Preacher of Faith of Debre Libanos (He was a Yemeni in lineage but an Ethiopian father in grace and service. He was an author, a martyr, a hermit and an abbot/Ichege of Debre Libanos). 
3. St. Akarkes
4. St. Yeweras

✞✞✞ Monthly Feasts
1. Our Lady, the Holy Virgin Mary (Theotokos)
2. The Gregories
3. Abune Memene Dingel (Ethiopian)
4. Abune Amde Selassie (Ethiopian)
5. Abba Aron/Aaron the Syrian
6. Abba Martinianus (Marcian) the Righteous
7. Abune Betselote Michael

✞✞✞ “But the manifestation of the Spirit is given to every man to profit withal. For to one is given by the Spirit the word of wisdom . . . to another divers kinds of tongues; to another the interpretation of tongues: But all these worketh that one and the selfsame Spirit, dividing to every man severally as he will.”✞✞✞
1 Cor. 12:7-11

✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞

(Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)

https://t.me/zikirekdusn