ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
49.9K subscribers
12.5K photos
346 videos
31 files
7.69K links
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Download Telegram
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!

🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑

5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
    1, 🛑አላማ

    2 ,🛑እምነት

    3,🛑ጥረት

    4 🛑ጥንቃቄ

     5🛑ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️

👉ሃይማኖት
👉ጾም
👉ጸሎት
👉ስግደት
👉ምጽዋት
👉ፍቅር
👉ትህትና
👉ትዕግስት
👉የዋህነት

ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።
        (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

🛑በቴሌግራም👉
https://t.me/zikirekdusn
🛑<<< በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን:: >>>

<< 🛑በበዓለ ሃምሳ ንስሃ ለምን ተከለከለ? 🛑>>

=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያለ ምክንያት የሚደረግ : ያለ ምሥጢርም የሚከወን ምንም ነገር የለም:: የሃይማኖትን ትምህርት አብዝተን በተማርን ቁጥር የምናውቀው አለማወቃችን ነውና ምንም ያህል ብንማር : የአዋቂነት መንፈስም ቢሰማን ከመጠየቅ ወደ ጐን አንበል:: መጠየቅ ለበጐ እስከሆነ ድረስ ሁሌም ሸጋ ነው:: ግን ልብን እያጣመሙ ቢያደርጉት ደግሞ ገደል ይከታል::

+ወደ ጉዳዬ ልመለስና ሁሌ የሚገርመኝ የትውልዱ አመለካከት ነው:: ጾም ሲመጣ "ለምን? . . . አልበዛም? . . ." ዓይነት ቅሬታዎች ይበዛሉ:: በዓለ ሃምሳ ሲመጣ ደግሞ "እንዴት ይህን ያህል ቀን ይበላል? . . ." ባዩ ይከተላል::

+ቤተ ክርስቲያን ግን ሁሉን የምትለን ለጉዳይ : ለምክንያትና ለእኛ ጥቅም ነው:: ለምሳሌ:- በዓለ ሃምሳ ድንገት እንደ እንግዳ ደርሶ : እንደ ውሃ ፈሶ የመጣ ሥርዓት አይደለም:: ይልቁኑ ምሳሌ ተመስሎለት በብሉይ ኪዳንም ሲከወን የነበረ እንጂ::

+እንደሚታወቀው እስራኤል ከግብጽ ባርነት በ9 መቅሰፍት : በ10ኛ ሞተ በኩር ወጥተው : በ11ኛ ስጥመት ጠላት ጠፍቶላቸው ወደ ምድረ ርስት ተጉዘዋል:: ቅዱስና የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ከእግዚአብሔር እየተቀበለ ብዙ ሥርዓቶችን ለቤተ እስራኤል አስተምሯል::

+እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ ለሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ድኅነት ጥላና ምሳሌዎችም ነበሩ:: በኦሪት ዘሌዋውያን ላይ ጌታ እንዲህ ይላል:-
". . . ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቁጠሩ:: እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቁጠሩ:: አዲሱንም የእህል ቁርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ::" (ዘሌ. 23:15)

+ይህም "በዓለ ሰዊት (የእሸት በዓል)" የሚባል ሲሆን ከፋሲካ 7 ሱባኤ (49 ቀን) ተቆጥሮ : በሰንበት (ቅዳሜ) ማግስት (እሑድ ቀን) በዓለ ሃምሳ ይውላል:: በዓሉ በግሪክኛው "ዸንጠቆስቴ (Pentecost)" ይባላል:: "በዓለ ሃምሳ" እንደ ማለት ነው::

+ለዚያም ነው ቅዱስ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በዚህ ቀን መሰጠትን ሊነግረን ሲጀምር "ወአመ ተፈጸመ መዋዕለ ዸንጠኮስቴ . . ." የሚለው:: (ሐዋ. 2:1) በዓለ ሃምሳ (50ው ቀናት) በብሉይ "የእሸት በዓል" ቢባሉም ለሐዲስ ኪዳን ግን "የሰዊት (እሸት) መንፈሳዊ" ዕለታት ናቸው::

+ጌታ መድኃኔ ዓለም ስለ እኛ መከራ ተቀብሎ : ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ 50 ያሉት ቀናት የዕረፍት : የተድላ : የመንፈሳዊ ሐሴት ቀናት ናቸው:: በእነዚህ ዕለታት ማዘን : ማልቀስ : ሙሾ ማውረድ : ንስሃ መግባት ወዘተ. አይፈቀድም::

=>ለምን?

1.ለእኛ ካሣ በጌታችን መፈጸሙን የምሰናስብባቸው ቀናት ናቸውና:: በእነዚህ ዕለታት ብናዝን "አልተካሰልንም" ያሰኛልና::

2.በዚህ ጊዜ መስገድ : መጾም "ክርስቶስ በከፈለልን ዋጋ ሳይሆን በራሴ ድካም (ተጋድሎ) ብቻ እድናለሁ" ከማለት ይቆጠራልና::

3."ፍስሐ ወሰላም ለእለ አመነ - ላመን ሁሉ ደስታና ሰላም ተደረገልን" ተብሎ በነግህ በሠርክ በሚዘመርበት ጊዜ ማዘን . . . ሲጀመር ካለማመን : ሲቀጥል ደግሞ "ደስታው አይመለከተኝም" ከማለት ይቆጠራልና::

4.50ውም ቀናት እንደ ዕለተ ሰንበት ይቆጠራሉና:: መጾምና መስገድ በዓል ያስሽራልና::

5.ዋናው ምሥጢር ግን እነዚህ 50 ዕለታት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት (የሰማያዊው ዕረፍት) ምሳሌዎች ናቸው::

ስለዚህ በእነዚህ ቀናት መጾም : መስገድ "መንግስተ ሰማያት ውስጥ ከገቡ በሁዋላ ድካም : መውጣት መውረድ አለ" ያሰኛልና ነው::

+በዚያውም ላይ "ኢታጹርዎሙ ጾረ ክቡደ (ከባድ ሸክም አታሸክሙ)" የተባለ ትዕዛዝ አለና ቅዱሳን አበው በጾም የተጐዳ ሰውነት ካልጠገነ ወጥቶ ወርዶ : ሠርቶ መብላት ይቸግረዋልና ሰውነታችን እንዲጠገን : ይህንን በፈሊጥ ሠርተዋል::

+ስለዚህም:-
"ሐጋጌ አጽዋም እምስቴ::
ወሠራዔ መብልዕ በዸንጠኮስቴ::" እያልን አበውን እናከብራለን:: (አርኬ)

+ስለዚህ በበዓለ ሃምሳ ጾም : ስግደት : ንስሃ : ሐዘን : ልቅሶ . . . የለም:: አይፈቀድምም::
<<ግን ይህንን ተከትሎ 50ውን ቀን ሙሉ ሆድ እስኪተረተር ከበላን ጉዳቱ ሥጋዊም : መንፈሳዊም ይሆናል!!>>

+አበው እንደነገሩን "እንደ ልባችሁ ብሉ" ሳይሆን የተባለው "ጦም አትዋሉ" ነው:: ለምሳሌ:-

1.በልቶ ጠጥቶ ከሚመጣ ኃጢአት : ክፋትና ፈተና ለመጠበቅ 50ውን ቀናት ጥሬ የሚበሉ አሉ::
2.ጠዋት ተመግበው ከ24 ሰዓት በሁዋላ ጠዋት የሚመገቡ አሉ::
3.መጥነው ጥቂት በልተው አምላካቸውን የሚያመሰግኑ አሉ::
4.ነዳያንን አጥግበው እነርሱ ከነዳያን ትራፊ የሚቀምሱ አሉ::

+እኛም ከእነዚህ መካከል የሚስማማንን መርጠን ልንከውን : በተለይ ደግሞ በጸሎት ልንተጋ ይገባል:: አልያ ብሉ ተብሏል ብለን ያለ ቅጥ ብንበላ : ብንጠጣ እኛው ራሳችን የሰይጣን ራት መሆናችን ነውና ልብ እንበል:: ማስተዋልንም ገንዘብ እናድርግ::

"እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና:: እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ::
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና:: ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው::
ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና:: ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና:: መገዛትም ተስኖታል::
በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም::" (ሮሜ. 8:5)

=>አምላከ ቅዱሳን ማስተዋሉን ያድለን::

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
Dn Yordanos Abebe
https://t.me/zikirekdusn
🛑ዕለተ ዐርብ🛑

በእውነት አብያተክርስቲያናትን ቸሩ ይጠብቅልን በቸርነቱ ይማረን።

እንኩዋን ለዕለተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለነፍሳተ ብሉይ ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

=>ከትንሳኤ ሳምንት ቀናት ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን አንድም ነፍሳት በመባል ትታወቃለች::

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:-
¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት
¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት
¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት
¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል::

††† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :-
¤በመጸነሱ ተጸንሳ
¤በመወለዱ ተወልዳ
¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ
¤በጥምቀቱ ተጠምቃ
¤በትምሕርቱ ጸንታ
¤በደሙ ተቀድሳ
¤በትንሣኤው ከብራ
¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ
¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች::

ድንገት የተመሠረተች ሳትሆን ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና የታሠበች: በዓለመ መላእክት የተወጠነች ናት:: በአማን ጐልታ: ግዘፍ ነስታ የተመሠረተችው ግን በደመ ክርስቶስ ተቀድሳ: በትንሳኤው ከብራ: ንጽሕትና ጽሪት ባደረጋት ጊዜ ነው:: መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን ሕልውና አይኖራትም ነበርና ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትከበራለች::

ነፍሳት

=>በብሉይ ኪዳን የነበሩና ለ5,500 ዓመታት በሲዖል የተጋዙ ሰዎችን ያመለክታል:: እነርሱም ከአባታችን አዳም ጀምሮ በዓመተ ኩነኔ የነበሩ ሰዋች ሲሆኑ ደመ ክርስቶስ ቀድሷቸው: የትንሳኤው ብርሃን ደርሷቸው ወደ ገነት ስለ ገቡ በዚሁ ቀን ይታሠባሉ::

=>እግዚአብሔር ከአባቶች ነፍስና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን::

=>+" መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ: ተቀበረም:: መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነስቷል...  ከዚያም በሁዋላ ለያዕቆብ: ሁዋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ:: ከሁሉም በሁዋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ:: እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና:: የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብየ ልጠራ የማይገባኝ: ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ:: "+ (1ቆሮ. 15:3-10)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

✝️✝️✝️Resurrection Week - Pascha Week✝️✝️✝️

+*"❇️Resurrection Friday – Day of the Church and Souls [of the Saints of the Old Testament]❇️ "*+

=>From the days of Resurrection Week, this day, Friday, is called Church and also Souls.

+*"❇️The Holy Church❇️ "*+
=>The Holy Church before the world was created was thought of in the heart of God and after being seen in the world of the angels
*The Fathers hoped for Her
*The Prophets foretold of Her
*They counted ages/jubilees for Her
*And lived creating typologies of Her.

✝️✝️✝️And when the time came,
*By the Conception of Jesus Christ, our God, She was conceived
*By the Nativity of Jesus Christ, our God, She was born
*She grew with Him in wisdom and favor
*By His Baptism being baptized
*By His instruction being preserved
*By His Blood being sanctified
*By His resurrection being glorified
*By His ascension maintaining Her heavenliness
*And by the descent of the Holy Spirt on Pentecost for Her, the Church was given publicly to Her children.

✝️The Church was not established haphazardly rather It was thought by God before the world and formed in the world of the angels. Nevertheless, It truly became vivid and assumed physicality when It was sanctified by the Blood of Christ, honored by His resurrection when He made Her pure and flawless. Since, if the Holy Savior was not, the Church would have not existed, this day, Thursday of Resurrection Week, is commemorated as the Church. 

+*"❇️Souls [of the Saints of the Old Testament]❇️ "*+
=>It indicates to the people that lived during the Old Testament and were in hell for 5,500 years. And they were from Adam to people that lived the Era of Damnation who being sanctified by the Blood of Christ, receiving the light of the resurrection have entered paradise, they are remembered on this day.

=>May God not detach us from the blessings of the Souls of the Fathers and His Holy House.

+"+For I delivered unto you first of all that which I also received, how that Christ died for our sins according to the scriptures; And that he was buried, and that he rose again the third day according to the scriptures . . . After that, he was seen of James; then of all the apostles. And last of all he was seen of me also, as of one born out of due time. For I am the least of the apostles, that am not meet to be called an apostle, because I persecuted the church of God. But by the grace of God I am what I am+"+
(1 Cor. 15:3-10)

<<<Salutations to God>>>
እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ሚያዝያ ቡሩክ፤ አመ ፲ወ፯፦

ተዝካረ ትንሣዔሁ ለመድኀኒነ ክርስቶስ

✞ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦

✿ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ (ዓምደ ሐዋርያት)
✿ወለተ ጴጥሮስ ዘሬማ (ኢትዮጵያዊት)
✿ቅድስት ቤተ ክርስቲያን (ማኅደረ መላእክት ትጉኃን)
✿ነፍሳተ ጻድቃን ንጹሐን (እምአዳም እስከ ዘካርያስ)

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

https://t.me/zikirekdusn
✞ ሚያዝያ 18 ✞

✞ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "አባ ዼጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

*+" ጻድቅና ሰማዕት አባ ዼጥሮስ "+*

=>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል
የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው
ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል::
ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት
ነው::

+ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል::
የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ
ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ
መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

+እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ
ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ
ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን
የሚመለከት ሕግ የለውም::

+እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን
መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ.
5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና
በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም
የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ
ይመጣል::

+በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል
ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን
እንድንጸና ነውና::

❖ቅዱስ አባ ጴጥሮስም ከዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች አንዱ
ነው፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን (3ኛው መቶ ክ/ዘ) ግብፅና
ሶርያ በብዙ መከራ ውስጥ ሳሉ በርካታ ቅዱሳን
ተሰውተዋል፡፡ በተለይ በግብፅ ደግሞ ብዙ ንጹሐን አበውና
ቅዱሳት አንስት መከራውን ታግሠው ለክብር በቅተዋል፡፡

❖ከእነዚሁ አንዱ የሆነው አባ ጴጥሮስ ገና ከልጅነቱ
ጣዕመ ክርስትናን የተማረው ከአሳዳጊው (ከአክስቱ)
ነበር፡፡ በፍፁም ልቡ የሚወደው ወንድም እና ባልንጀራም
ነበረው፡፡ ስሙ ደግሞ አባ ብሶይ ይሰኛል፡፡ ሁለቱም በበጎ
ምግባር ተኮትኩተው ፡ ዓለምንም ንቀው በርሃ ገብተው ፡
በጾም በጸሎት ተወስነው ብዙጊዜ ኑረዋል፡፡

❖በመከራው ዘመን ደግሞ ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ
ተከሰው ታስረዋል፡፡ ተገርፈው ተደብድበዋል፡፡ ጭንቅ
ስቃይንም በትእግስት አሳልፈዋል፡፡ በፍጻሜውም አባ
ጴጥሮስ በዚህች ቀን ተሰውቶ ለክብር አክሊል በቅቷል፡፡
ወዳጁና ወንድሙ ቅዱስ ብሶይም በክብር ገንዞ
ቀብሮታል፡፡

=>አምላከ ሰማዕታት ከጸናች ገድላቸው ፡ ከበዛች
ትእግስታቸው ፡ ከፍጹም በረከታቸው ያሳትፈን፡፡

=>ሚያዝያ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት
2.አባ ዼጥሮስ ሰማዕት
3.ሰማዕታተ ጠርሴስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

=>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር:
አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት:
ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ
ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . .
የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ
የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ
11:23)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn
#Feasts of #Miyazia_18

✞✞✞On this day we commemorate the departure of the Righteous Martyr Abba Peter✞✞✞

✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞

✞✞✞Righteous Martyr Abba Peter✞✞✞

=>Martyrdom is the highest price a Christian pays for his/her faith. A person can subdue his body in the service of God or give away his wealth and property. However, the greatest gift is offering oneself. 

✞Giving oneself is possible in matrimony or asceticism. Nonetheless, its peak is martyrdom. As Saint Ephraim the Syrian said, “…the martyrs rejected the desire of this world, and poured out their blood for God, and have endured bitter death[s] for the sake of the kingdom of heaven”, martyrdom means enduring unpleasant death for the love of God. [Theotokion of Thursday]

✞Did not our Redeemer, Christ, while being the Lord of heaven and earth endure the humiliation of the Cross and die for us! Many religions in the world speak about killing directly or indirectly. But Christianity does not have a rule that puts forward or indicates killing [others as an option].

✞That is because He Himself told us, “Love your enemies, bless them that curse you, do good to them that hate you, and pray for them which despitefully use you, and persecute you” (Matthew 5:44). But if we do not nourish ourselves with faith and virtues daily, Christianity is not a belief where one becomes perfect in a day hence there might come failures in trials.

✞Particularly, we the Christian youths of today should give due attention, since the chronicles of the youth martyrs of the past are articulated to us in order that we steadfast. 

[Let’s see the account of Abba Peter in short for today.]

✞Abba Peter was one of the fruits of the Era of Persecution. In those days of tribulation (the 3rd century), because Egypt and Syria were in much adversity, many saints were martyred.  Particularly in Egypt, many pure fathers and holy mothers, enduring the afflictions, were glorified [in martyrdom].

✞And one of them was Abba Peter who learned the tang of Christianity while he was a child from his caretaker (his aunt).  He had a brother and a friend that he loved dearly. And his name was called Abba Bishoy. Both after being raised ethically, despised the world, entered the desert and lived for many years devoted to prayer and fasting. 

✞And during the Era of Persecution, they were accused and imprisoned for just worshipping Christ. They were lashed and were beaten. They have also endured in patience excruciating pains.  In the end, Abba Peter was martyred on this day and was glorified. And his friend and brother Abba Bishoy honorably shrouded and buried him. 

✞✞✞May the God of the martyrs let us partake from their diligent strife, their much longsuffering, and their perfect blessing.

✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 18th of Miyazia
1. St. Eusebius (St. Arsenius) the Martyr (Slave of St. Sousnyous)
2. St. Peter the Martyr
3. Martyrs of Tarsus

✞✞✞ Monthly Feasts
1. St. Philip the Apostle
2. Abune Ewostatewos/Eustathius/Eustathios, preacher of faith
3. Abune Anorios/ Honorius of Debre Tsegaga
4. Mar James of Egypt

✞✞✞ “I am more; in labours more abundant, in stripes above measure, in prisons more frequent, in deaths oft . . . In weariness and painfulness, in watchings often, in hunger and thirst, in fastings often, in cold and nakedness. Beside those things that are without, that which cometh upon me daily, the care of all the churches.”✞✞✞
2 Cor. 11:23-28

✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞

(Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)

https://t.me/zikirekdusn
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ✞✞✞

✞ አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) ✞

ልዩ ስሟ አምዓዳ በምትባል ሀገር በሉፊ አውራጃ በሮም አገር አንድ ጽኑ ክርስቲያን ነበር፡፡

ይህ ክርስቲያን ስሙ አብርሃም ይሰኛል፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከአንዱ አገር ወደ ሌላ አገር ሲሰደድ የኖረ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለሰው ሁሉ በጎን የሚያደርግ ለነዳይና ለምስኪን ባልቴቶች እናት አባት ለሞቱባቸዉ ልጆች ምጽዋትን የሚሰጥ ነበር፡፡

እንዲሁም እንደርሱ ደግ የሆነች ስሟ ሐሪክ የምትባል ደግ ሚስት ነበረችው የስሟ ትርጉምም  በክርስቶስ የታመነች ማለት ነው፡፡ 

እነዚህ ሁለት ደግ ክርስቲያኖች ታዲያ ልጅ አልነበራቸውም ነገር ግን
ልጅ ባይኖራቸውም እለት እለት እግዚአብሔርን ከማመስገን በቀር አማረው አያውቁም ነገር ግን ለቤተ እግዚአብሔር  አገልጋይ የሚሆን አንድ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ በአንቃዕድዎ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ ነበር፡፡

አንድ ቀን መልዐከ እግዚአብሔር ለዚህ   ደግ ሰው ተገልፆ ይኽ ፍሬ የአንተ ነው እርሱም ወደ እኔ የሚቀርብ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ፈቃዱንም የሚፈፅም ያማረ መባዕ ነው ብሎ እጅግ መልካም ፍሬን በእጁ ሰጠው፡፡

ይኽ ደግ ሰው አብርሃምም ከእንቅልፉ ተነስቶ ይህንን  በህልሙ የሰማውንና የአየውን ነገር ኹሉ ለሚስቱ ሐሪክ ነገራት እርሷም ታላቅ ደስታ ተደሰተች ልዑል እግዚአብሔርን በአንድነት አመሰገኑ፡፡ሚስቱ ሐሪክም ፀነሰች፡፡

ይኽቺ ሚስቱ ሐሪክ በፀነሰች ጊዜም በቤታቸው መካከል ሁለንተናው መልካምና ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉ ላይ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈ ጽሕፈትን አዩ ጽሕፈቱም በጽዮን አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ቅዱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቡላ የሚል ነው፡፡

ከዚህም በኀላ ሐሪክ መልከ መልካምና ከብርሃናት ይልቅ ፊቱ የሚያበራ ወንድ ልጅን ወለዱ፡፡እናቱና አባቱ ይህንን በአዩ ጊዜ ታላቅ ደስታ ተደስተው ለነዳያን ምጽዋትን ለአብያተ ክርስቲያናት የሚገባውን በወርቅና በብር ያጌጡ የነዋየ ቅድሳት አልባሳትን ሰጡ ስሙንም ቡላ ብለው ሰየሙት፡፡ትርጓሜውም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው፡፡

እናትና አባቱም በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት አሥር አመት በሆነው ጊዜም በመጀመሪያ አባቱ አብርሃም አረፈ ከትንሽ ቀናት በኀላ እናቱ ሐሪክ አረፈች፡፡

በዚያን ዘመን ታዲያ ንጉሡ ቤተ ክርስቲያንን እንዲዘጉ እና ቤተ ጣዖት እንዲከፍቱ ክርስቲያን ሁላቸው የምስጋና ባለቤት ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን (ሎቱ ስብሐት) እንዲክዱ የሚል ወደዚያች አገር ደረሰ፡፡

ይህ የተባረከ ብላቴና ቡላም ይህንን በሰማ ደጋጎች ክርስቲያንም ሲሰቃዩ ባየ ጊዜ ስለ ክርስቶስ በሰማዕትነት ይሞት ዘንድ ጨክኖ ሕዝብን ሰማዕትነት ለመቀበል በወዲህም በወዲያም ያሉትን ሕዝቡን እየገፋ ሄዶ ንጉሥ አቅሮጵስ ካለበት ቀርቦ ያፈርክና የተዋረድክ የረከስክ የጽድቅ ሁሉ ጠላት የዲያቢሎስ መልእክተኛ አንተና ንጉስክ የተነቀፋችሁ የምታመልኳቸው ጣዖታትም የተዋረዱና በምድር የረከሱ ናቸው አለው፡፡

ንጉሡም ሰምቶ ይህንን ወጣቱ ቡላን አስረው ከፊቱ ያቆሙት ዘንድ አዝዞ ተመልከቱ የእሊክ ክርስቲያን ልቦናቸው የጸና ነው ትንሽ ብላቴና ሆኖ ሳለ ምንም አልፈራም ይልቁኑም እንድቀጣው ይቃወመኛል እንጂ አለ፡፡

ይህንንም ብሎ በሚቆራርጥ ብረት ሠንሰለት አሰሩት ጀርባውን በአለንጋ እንዲገርፉት ሰውነቱም እየለያዩ እየቆራረጡ የውስጥ አንጀቱን በተቆለፈ ብረትና በስለታማ መጋዝ እጆቹንና እግሮቹን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡

በእንዲህ ባለ መከራ ቢያሰቃዩትም ተመልሶ በእግሩ ይቆማል እንጂ አልሞተም ንጉሡ እሊህ ክርስቲያን መተታቸውን ተመልከቱ አለ፡፡

እንዲሁም አባ ቡላ በአሥራ አምስት አመቱ ከሌላ ንጉሥ ጋር እንደ ቀድሞ ለረከሱ ጣዖቶች አልሰግድም በማለቱ ብዙ ስቃይ አሰቃየው በመጨረሻም አንገቱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ብጹዕ ጻድቅ ቡላም ራሱን ከመቁረጣቸው አስቀድሞ ከመዝሙረ ዳዊት ሳምኬት ዐማፅያንን ጠልቼ ሕግህን ተከተልኩ ረዳቴና መጠጊያዬ አንተ ነህ በቃልህም አመንኩ የአምላኬን ትዕዛዝ እፈፅም ዘንድ  ዐማፅያን ከእኔ ራቁ በሕይወት እኖር ዘንድ እንደ ቃልህ ተቀበለኝ ተስፋዬንም አታስቀርብኝ ርዳኝ አድነኝ ሁል ጊዜ ሕግህን እናገራለሁ ከትእዛዝህ የሚርቁ ሁሉ ምኞታቸው አመፃ ነውና አዋረድኻቸው እሊኽ በምድር ያሉ ኃጥአን ከዳተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህም አምልኮተ ሕግህን ወደድኹ፡፡ከሕግህ የተነሣ ፈርቻለሁና በአንተ መታመንን ከሰውነቴ ጋራ አስማማ፡፡ የሚለውን ጸሎት ጸለየ፡፡

የእግዚአብሔር አገልጋይ ቡላም በዚህች ቀን በሚያዝያ 18 አንገቱን ተቆረጠ በዚህን ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ወርዶ ራሱን ወስዶ ከሥጋው ቢያገናኘው እንደነበረ ሆኖ ተነሣ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም አይዞህ አትፍራ እመን ጽና እግዚአብሔር ይረዳሃል ፡፡በሃገሪቱ ዳረቻ ወደ አለዉ ገዳም ሂድ እኔ የምሰጥህ በእጄ ያለች ልብስህ ሁል ጊዜ ይህች ናት ጌታችን ከወዳጆቹ ቅዱሳን መነኮሳት ጋራ ተሳታፊ እንድትሆን አዝዞኻል ብሎ የብርሃን መስቀል ምልክት ያላት አስኬማንም ሰጥቶት ከእርሱ ዘንድ ተሰወረ፡፡

ጻድቁ አባታችን አቡነ አቢብ(ቡላ) ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መፍቅሬ ሰብእ (ሰውን ወዳጅ) አምላካቸውን አርአያ ያደረጉ ለሰው ያላቸውን ፍቅር አድንቆ ከማዕድ በኀላ ስብሐት ተብሎ የተረፈውን በእንተ አቡነ አቢብ ብሎ ሦስት ጊዜ የተመገበውን ሰው ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ እምርልሃለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡

የንዑድ ክቡር ጻድቁ አባታችን አቡነ አቢብ (ቡላ) ጸሎታቸዉና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኹን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ✞

(በዮሐንስ ዘሐረር - ዝክረ ቅዱሳን)

ምንጭ፡ ገድለ አቡነ አቢብ

https://t.me/zikirekdusn
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!

🛑 ዝክረ ቅዱሳንን ላልደረሳቸው  እናድርስ እናስፋ ስለ ሀገራችን እንጸልይ ንስሐ እንግባ!!🛑

5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
    1, 🛑አላማ

    2 ,🛑እምነት

    3,🛑ጥረት

    4 🛑ጥንቃቄ

     5🛑ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

❇️9ኙ የቅድስና መንገዶች❇️

👉ሃይማኖት
👉ጾም
👉ጸሎት
👉ስግደት
👉ምጽዋት
👉ፍቅር
👉ትህትና
👉ትዕግስት
👉የዋህነት

ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።
        (ቅዱስ መቃርስ )   ንስሐ ግቡ።

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

🛑በቴሌግራም👉
https://t.me/zikirekdusn
እንኩዋን ለእናቶቻችን "ቅዱሳት አንስት" ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ቅዱሳት አንስት "*+

=>ከትንሳኤ ሳምንት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" (የተቀደሱ ሴቶች) ተብላ ትጠራለች::

+በወቅቱ በኢየሩሳሌምና ዙሪያዋ ከተከተሉት ሴቶች ጌታችን 36ቱን መርጧል:: እነዚህ እናቶች ከዋለበት ውለው : ካደረበት አድረው : የቃሉን ትምሕርት ሰምተዋል:: የእጁንም ተአምራት አይተዋል:: ፈጽመውም አገልግለውታል::

+መጽሐፍ "አንስተ ገሊላ ኩሎን::
አዋልዲሃ ለጽዮን::
አስቆቀዋሁ ለመድኅን::
ከመ ዖፈ መንጢጥ እንዘ ይሤጽራ ገጾን::" ይላልና በዕለተ ዐርብ ፊታቸወውን እየነጩ : ደረታቸውን እየደቁ : እንባቸውም እንደ ጐርፍ እየፈሰሰ አብረውት ውለዋል::

+ጌታም ፍጹም ፍቅራቸውን ተመልክቷልና ከሁሉ አስቀድሞ ትንሳኤውን ለእነሱ ገለጠላቸው:: እነርሱም ትንሳኤውን በመፋጠን አብሥረዋል:: "ሰበካ ትንሳኤ፡ አዋልዲሃ ለጽዮን" እንዳለ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት "ቅዱሳት አንስት" ተብላ ትከበራለች::

=>አምላካችን በፍቅርና በቅድስና ጌጥ ካጌጡ እናቶቻችን በረከትን ያድለን::

=>+"+ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው:- 'እናንተስ አትፍሩ:: የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና:: እንደተናገረ ተነስቷልና በዚሕ የለም:: የተኛበትን ሥፍራ ኑና እዩ:: ፈጥናችሁም ሒዱና ከሙታን ተነሣ: እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማቹሃል:: በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሯቸው' . . . እነሆም ኢየሱስ አገኛቸውና ደስ ይበላችሁ አላቸው:: እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት:: +"+ (ማቴ. 28:5-10)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝️✝️✝️Resurrection Week - Pascha Week✝️✝️✝️

+*"❇️Resurrection Saturday – Day of Holy Women❇️ "*+

=>From Resurrection Week, this day, Saturday, is named Holy Women.

✝️Our Lord, during the time He ministered, chose 36 women from Jerusalem and the surroundings. And these mothers heard His teachings staying where He did. They saw the miracles made by His hands and served Him completely.
  
✝️As text states,
“All women of Galilee
And the daughters of Zion
Cried for the Savior
Like a swallow bird that grazes its face” they, on Great Friday, scratching their face, beating their chest and their tears falling like a flood spent the day with Him.

✝️And our Lord as He has seen their perfect love, revealed His resurrection before anyone to them. And they announced His resurrection hurriedly as Saint Yared had said, “The daughters of Zion, preached the resurrection.” And for this reason, this day, Resurrection Saturday, is commemorated as Holy Women.

=>May our God grant us from the blessings of our Mothers who are adorned with love and holiness.

+"+And the angel answered and said unto the women, Fear not ye: for I know that ye seek Jesus, which was crucified. He is not here: for he is risen, as he said. Come, see the place where the Lord lay. And go quickly, and tell his disciples that he is risen from the dead; and, behold, he goeth before you into Galilee; there shall ye see him . . . behold, Jesus met them, saying, All hail. And they came and held him by the feet, and worshipped him.+"+
(Matt. 28:5-10)

<<<Salutations to God>>>

https://t.me/zikirekdusn