ዝገት--thoughts
244 subscribers
2.79K photos
87 videos
26 links
Join & share 🙏
🌹🌹🌹🌹🌹
Download Telegram
አየህ የኔ እግዜር ያንተ ልጅ እንዲህ ነኝ ሌላው አባቴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን በእድሜ በጤና ለዚህ አውዳመት ለትንሳኤህ ያደረስከኝ ብሎ የፍቅርና የደስታ እንባ ሲያለቅስ እኔም በተራዬ ጌታ ሆይ ምን አድርጌህ ነው ደሞ ለአሁኑ አውዳመት ያደረስከኝ 🥺 ከረከሰው ሞት ለኔ አተህ ነው ብዬ አማርራለሁ 😔


አየህ እኔ ልጅህ እች ሴት ነኝ

ትናንትም ዛሬም ነገም ደሞ ካልሞትኩኝ

የምማፀንህ ሰው እያልኩኝ ግደለኝ

ያንተ ልጅ እንዲህ ነኝ 🥺😔😔
😍41❤‍🔥1
Benena banchi mehal last seen menor neberebet woyyyyyy😔😔😔😫😫
@Topasion_11
😍3😢1❤‍🔥1
#ሰሙነ ሕማማት ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦


ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ እግር ይባላል።
በዚህም ምሳሌ ካህናት አባቶቻችን በእለተ ሐሙስ በእውቀት፣ በእድሜ፣ በክብር፣ በስልጣል ትልቅ ነኝ ሳይሉ ከዲያቆናት እስከ ምዕመናን ድረስ ዝቅ ብለው እግር በማጠብ ክርስቶስን በተግባር ይሰብካሉ።

የምስጢር ቀን ይባላል፡-

ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-

መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-

ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
❤‍🔥5😍1
•ጌታችን አጎንብሶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግሥት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው፡፡ 'ወኀፀበ እግረ ይሁዳ አስቆሮታዊ ዘያገብኦ' ‹የሚያስይዘውን የአስቆሮቱ የይሁዳንም እግር አጠበ› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ)

•ከአንድ ቀን በፊት ክፋትን ለማሴር ወደ አይሁድ ካህናት ግቢ የሮጡትን የይሁዳን እግሮች ጌታችን አጎንብሶ አጠባቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሊያስይዘው ወደ አይሁድ የሚሮጥባቸውን እግሮች ፣ የሚይዙትን ወታደሮች እየመራ ወደ እርሱ የሚመለስባቸውን እግሮች አጠበለት፡፡ ምንም እንኳን በነገው ዕለት እግሮቹን እንዲቸነከር አሳልፎ የሰጠው መሆኑን ቢያውቅም ወዳጁ ክርስቶስ ግን የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመጨረሻ ጊዜ እግሩን አጥቦ ተሰናበተው፡፡

•እንደ ነቢዩ ዳዊት ‹አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ!› ከማለት በቀር በምን አንደበት ልንናገር እንችላለን? (መዝ. ፴፮፥፯) ‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ› ያለን ጌታ አሳልፎ የሚሰጠውን የይሁዳን እግር ሲያጥብ ከማየትስ በላይ በቂም በቀል ለሚቆስለው ልባችን ምን መድኃኒት ይኖር ይሆን?.....

ሕማማት
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
❤‍🔥5😍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኔ ውብ🥹🌴🩵
❤‍🔥4💋2
ፀሎተ ሐሙስ፤ ሕፅበተ እግር❤️‍🩹
❤‍🔥4🥰1
ላያዛልቀኝ ነገር ሲጋራዬን አስተወኝ😑😭
❤‍🔥3😍1
ለመንጻቴ ማንን እጠራለሁ ቁስሌንስ ለመፈወስ ወደ ማን እጮሃለሁ የኃጥአን ዕዳ በደላቸው ንጹሕ መሆን የቁስለኞችም የቁስላቸው መፈወሻ ከምትሆን ካንቺ ሌላ...
ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጢአቴን የሚያስተሠረይልኝ አልፈልግም ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳም በደሌም ሁሉ ንጹሕ አድርጊኝ ። ከሥጋና ከነፍስ ቁስሌም ፈውሽኝ💘

መጽሐፈ አርጋኖን ዘ ሀሙስ
ምዕ፩ : ፳-፳፩



G.N y'all pamily lob u betam😚💗
❤‍🔥5
#ሰሙነ ሕማማት

ዓርብ፡ ስቅለት (መልካሙ ዓርብ)

​ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ የተሰቀለበት ታላቅ ዕለት ነው። ቀድሞ የወንጀለኞች መቅጫ የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምሕረት ምልክት፣ የሕይወት ዓርማና የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው ዕለቱ "መልካሙ ዓርብ" ይባላል። በክቡር ሞቱ ለእኛ መልካሙን ሕይወት በቸርነቱ ስለሰጠን፣ ይህ ቀን የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቀበትና የሞት ፍርድ የተሻረበት የድኅነታችን መሠረት ነው።

​ዛሬ እኛም የጌታን ሕማምና መከራ ስናስብ፣ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደሙ የሕይወታችን ብርሃን መሆኑን በማመን ነው። ጌታ ሆይ! ለእኛ ስትል የተቀበልኸው መከራና ስቅላት ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶናልና ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን።

"ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ...”  ማቴዎስ 27:35


@Bezakulumedia
❤‍🔥4💋1😘1
እኔ ግን ምን ልቤን እንደሚነካው ልንገራችሁ
የማርያም ሀዘን🥺እንዲያ እያየች ልጇ ሲገረፍ ሲሰቀል
በእኛ በደል እሱ ሲጎሳቆል🥺
እንዲያ በውሃ ጥም ነዶ ስታየው ምንኛ አዝና ይሆን??🥺 ልቧስ ምንኛ ቆስሎ ይሆን??

የአንድ ቀን አይደለም እድሜ ልኳን ሁሉ
ማርያም እና ሀዘን ይተዋወቃሉ🥺💔
❤‍🔥5😍1💘1
አየኽልኝ አይደል የክፋቴን ጥልቀት.....🥀😔💔
😢42❤‍🔥1
ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ዎይ የንስሐ መዝሙር በ ሊቀመዘምራን ኪነ ጥበብ ወ/ኪሮስ
One Move
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በቸርነቱ ጠብቆ ለብርሃነ ትንሣኤውም በሰላም ያድርሰን ዘንድ የእርሱ መልካም ፍቃድ ይሁን 🙏🏽
❤‍🔥41
ወገን እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ልንል ፩ ቀን ቀረን🥹
3❤‍🔥2
Network የያዘኝን ያህል ፀላይ እራሱ አይዘኝም🥺😭mtsm 😭
❤‍🔥1😘1
ቀዳም ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)

​ይህች ዕለት "ቀዳም ሥዑር" የተባለችው የተሻረች ቅዳሜ በመሆኗ ነው። በቤተክርስቲያን ሕግ ቅዳሜና እሁድ አይጾሙም፤ ነገር ግን ይህች ቅዳሜ ጌታችን በመቃብር የነበረባት ዕለት በመሆኗ፣ መከራውን በማሰብ በጾም ታስባ እንድትውል በሥርዐት ተደንግጓል።

በዚህም ምክንያት ከሌሎቹ ቅዳሜዎች በተለየ የደስታና የዕረፍት ቀንነቷ ተሽሮ በጾምና በሐዘን ስለምትታሰብ ሥዑር (የተሻረች) ተብላለች።

በተጨማሪም ዕለቱ "ለምለም ቅዳሜ" ይባላል፤ ካህናቱ ለምእመናን ቄጤማ የሚያድሉበትና የትንሣኤውን ብርሃን በናፍቆት  የሚጠባበቁበት የምሥራች ቀን ነው። ይህ ቄጤማ ርግብ ለኖኅ የጥፋት ውሃ መጉደሉን ያበሰረችበትን ቅጠል የሚያስታውስ ሲሆን፣ ዛሬም ለእኛ የኃጢአት ውሃ መጉደሉንና በክርስቶስ ሞት ነፃ መውጣታችንን የምናስብበት ነው። ጌታችን በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ለነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን የሰጠባት "ቅዱስ ቅዳሜ" በመሆኗ ታላቅ ክብር አላት።



@Bezakulumedia
❤‍🔥3😘1
​​​​👉 ቅዳሜ

ቀዳም ስዑር ትባላለች

ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

ለምለም ቅዳሜ ይባላል

ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቄጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል

ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።
❤‍🔥31
ቤተክርስቲያን ማደር💆‍♀❤️‍🩹

ደህና እደሩልኝ አበባዎቼ💘
❤‍🔥5😘1
ያቀባብራል ወይ በናፍቆት ወዳጅን ቢሰጡት ፈተና 🥺🎧
❤‍🔥1😘1
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ
ተሃፂባ በደመ ክርስቶስ🥰❤️
እልልልልልልልልልል
❤‍🔥2😘1
💘
❤‍🔥3😘1