#ሰሙነ ሕማማት
ማክሰኞ፡ የጥያቄ ዕለት
በዚህ ዕለት አይሁድ ለጌታችን የተለያዩ ጥያቄዎችን (ለምሳሌ፡ በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ?) በማቅረብ ሊያጠምዱት የሞከሩበት ዕለት በመሆኑ "የጥያቄ ዕለት" ይባላል። ጌታም በምሳሌዎች ትምህርት የሰጠበት ቀን ነው። ማቴዎስ 21፥23
©@Bezakulumedia

❤4😍1❤🔥1
✨ደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ..ባዝንም ባንቺ እጽናናለሁ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ....🤍
✨መጽሐፈ አርጋኖን
ማክሰኞ ምዕ ፫ : ፲ ✨
❤🔥3💘3😘1
#ሰሙነ ሕማማት
ረቡዕ፡ የምክር ቀን (መልካም መዓዛ ያለው ቀን፣ የዕንባ ቀን)
የአይሁድ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ የመከሩበትና የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ለመስጠት የተስማማበት ዕለት በመሆኑ "ምክረ አይሁድ" ይባላል።
"መልካም መዓዛ ያለው ቀን" ፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።
የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱

❤🔥3❤2🥰1
✨የሕይወት መድኃኒት መጀመሪያ ናትና የንጽሕናም የቅድስናም መሠረት የዓለም ሁሉ ጌጥ ፈርጽ የፍጥረትም መመኪያ ዘውድ ከዚህም እስከ ሰማይ የምታደርስ መሰላል ናት።🤍
G.N y'all😚💗
መጽሐፈ አርጋኖን ዘ ረቡዕ
ምዕ ፩:፲፰
G.N y'all😚💗
❤🔥5😘1
አየህ የኔ እግዜር ያንተ ልጅ እንዲህ ነኝ ሌላው አባቴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን በእድሜ በጤና ለዚህ አውዳመት ለትንሳኤህ ያደረስከኝ ብሎ የፍቅርና የደስታ እንባ ሲያለቅስ እኔም በተራዬ ጌታ ሆይ ምን አድርጌህ ነው ደሞ ለአሁኑ አውዳመት ያደረስከኝ 🥺 ከረከሰው ሞት ለኔ አተህ ነው ብዬ አማርራለሁ 😔
አየህ እኔ ልጅህ እች ሴት ነኝ
ትናንትም ዛሬም ነገም ደሞ ካልሞትኩኝ
የምማፀንህ ሰው እያልኩኝ ግደለኝ
ያንተ ልጅ እንዲህ ነኝ 🥺😔😔
አየህ እኔ ልጅህ እች ሴት ነኝ
ትናንትም ዛሬም ነገም ደሞ ካልሞትኩኝ
የምማፀንህ ሰው እያልኩኝ ግደለኝ
ያንተ ልጅ እንዲህ ነኝ 🥺😔😔
😍4❤1❤🔥1
Benena banchi mehal last seen menor neberebet woyyyyyy😔😔😔😫😫
@Topasion_11
@Topasion_11
😍3😢1❤🔥1
#ሰሙነ ሕማማት ሐሙስ
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ እግር ይባላል።
በዚህም ምሳሌ ካህናት አባቶቻችን በእለተ ሐሙስ በእውቀት፣ በእድሜ፣ በክብር፣ በስልጣል ትልቅ ነኝ ሳይሉ ከዲያቆናት እስከ ምዕመናን ድረስ ዝቅ ብለው እግር በማጠብ ክርስቶስን በተግባር ይሰብካሉ።
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።
የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።
የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
❤🔥5😍1
•ጌታችን አጎንብሶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግሥት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው፡፡ 'ወኀፀበ እግረ ይሁዳ አስቆሮታዊ ዘያገብኦ' ‹የሚያስይዘውን የአስቆሮቱ የይሁዳንም እግር አጠበ› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ)
•ከአንድ ቀን በፊት ክፋትን ለማሴር ወደ አይሁድ ካህናት ግቢ የሮጡትን የይሁዳን እግሮች ጌታችን አጎንብሶ አጠባቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሊያስይዘው ወደ አይሁድ የሚሮጥባቸውን እግሮች ፣ የሚይዙትን ወታደሮች እየመራ ወደ እርሱ የሚመለስባቸውን እግሮች አጠበለት፡፡ ምንም እንኳን በነገው ዕለት እግሮቹን እንዲቸነከር አሳልፎ የሰጠው መሆኑን ቢያውቅም ወዳጁ ክርስቶስ ግን የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመጨረሻ ጊዜ እግሩን አጥቦ ተሰናበተው፡፡
•እንደ ነቢዩ ዳዊት ‹አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ!› ከማለት በቀር በምን አንደበት ልንናገር እንችላለን? (መዝ. ፴፮፥፯) ‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ› ያለን ጌታ አሳልፎ የሚሰጠውን የይሁዳን እግር ሲያጥብ ከማየትስ በላይ በቂም በቀል ለሚቆስለው ልባችን ምን መድኃኒት ይኖር ይሆን?.....
ሕማማት
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ✨

✨ለመንጻቴ ማንን እጠራለሁ ቁስሌንስ ለመፈወስ ወደ ማን እጮሃለሁ የኃጥአን ዕዳ በደላቸው ንጹሕ መሆን የቁስለኞችም የቁስላቸው መፈወሻ ከምትሆን ካንቺ ሌላ...
ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጢአቴን የሚያስተሠረይልኝ አልፈልግም ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳም በደሌም ሁሉ ንጹሕ አድርጊኝ ። ከሥጋና ከነፍስ ቁስሌም ፈውሽኝ💘
G.N y'all pamily lob u betam😚💗

መጽሐፈ አርጋኖን ዘ ሀሙስ
ምዕ፩ : ፳-፳፩
G.N y'all pamily lob u betam😚💗
❤🔥5
#ሰሙነ ሕማማት
ዓርብ፡ ስቅለት (መልካሙ ዓርብ)
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ የተሰቀለበት ታላቅ ዕለት ነው። ቀድሞ የወንጀለኞች መቅጫ የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምሕረት ምልክት፣ የሕይወት ዓርማና የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው ዕለቱ "መልካሙ ዓርብ" ይባላል። በክቡር ሞቱ ለእኛ መልካሙን ሕይወት በቸርነቱ ስለሰጠን፣ ይህ ቀን የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቀበትና የሞት ፍርድ የተሻረበት የድኅነታችን መሠረት ነው።
ዛሬ እኛም የጌታን ሕማምና መከራ ስናስብ፣ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደሙ የሕይወታችን ብርሃን መሆኑን በማመን ነው። ጌታ ሆይ! ለእኛ ስትል የተቀበልኸው መከራና ስቅላት ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶናልና ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን።
"ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ...” ማቴዎስ 27:35
@Bezakulumedia

❤🔥4💋1😘1
እኔ ግን ምን ልቤን እንደሚነካው ልንገራችሁ
የማርያም ሀዘን🥺እንዲያ እያየች ልጇ ሲገረፍ ሲሰቀል
በእኛ በደል እሱ ሲጎሳቆል🥺
እንዲያ በውሃ ጥም ነዶ ስታየው ምንኛ አዝና ይሆን??🥺 ልቧስ ምንኛ ቆስሎ ይሆን??
የአንድ ቀን አይደለም እድሜ ልኳን ሁሉ
ማርያም እና ሀዘን ይተዋወቃሉ🥺💔

❤🔥5😍1💘1
ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ዎይ የንስሐ መዝሙር በ ሊቀመዘምራን ኪነ ጥበብ ወ/ኪሮስ
One Move
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በቸርነቱ ጠብቆ ለብርሃነ ትንሣኤውም በሰላም ያድርሰን ዘንድ የእርሱ መልካም ፍቃድ ይሁን 🙏🏽
❤🔥3❤1