ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
34.6K subscribers
21.5K photos
183 videos
20 files
529 links
The best fiction is far more true than any journalism

📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ

👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56



👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Download Telegram
አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል። በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን  ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡

እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም  ከረፋዱ 5 ሰዓት  ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6  በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ  መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና  እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል።

ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል። ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የዋስትና ጥያቄያቸውን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ነጥቦችን ጠቅሶ ተከራክሯል።

ሰበር ሰሚ ችሎት ዋስትናን በልዩ ሁኔታ ሊከለክል የሚችልባቸው ነጥቦች ማለትም በተደራራቢ ክስ መከሰሳቸውን እና የተከሰሱት ድንጋጌ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስጥል ከሆነ ዋስትና ሊያስከለክል ይችላል በማለት ተከራክሯል።

የተከሳሽ ጠበቆችም ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጣቸው ዋስትናን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ድንጋጌዎች ተከሳሹ ላይ በቀረበው ክስ የሚመለከቱ አለመሆናቸው ጠቅሰው መልስ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም  ህጻን ልጃቸውን ጥለው የታሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጠው የሕጻናት መብት ታሳቢ ተደርጎ በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል።

አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው÷በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል።

ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል። ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱም  በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።

ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via FBC
#ዳጉ_ጆርናል
የቡርኪናፋሶ ጦር በ223 ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዱን የሰብዓዊ መብት ድርጅት አስታወቀ

በተያዘው አመት ከ220 በላይ ንፁሀን ዜጎች፣ ቢያንስ 56 ህፃናት በቡርኪናፋሶ ጦር በአንድ ቀን ተጨፍጭፈዋል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል።

በሰራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ለመበቀል ጦረ በሶሮ መንደር 179 ሰዎች ሲገድል 44 ሌሎች  ሰዎች ደግሞ በአቅራቢያው በሚገኘው ኖንዲን መንደር ውስጥ መገደላቸውን የመብት ተሟጋች ቡድሙ ያደረገው ምርመራ አረጋግጧል።የጅምላ ግድያው "በሀገሪቱ ከአስር አመታት ወዲህ ከተከሰቱት እጅግ የከፋ የጦር ሰራዊት ጥቃት" ሲል ገልጿል።

የቡርኪናፋሶ ባለስልጣናት በሪፖርቱ ላይ አስተያየት እስካሁን አልሰጡም። ባለፈው ወር የህዝብ አቃቤ ህግ አሊ ቤንጃሚን ኩሊባሊ ከጅምላ ግድያው ጀርባ ያለውን ቡድን ለመለየት ምስክሮች እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በወቅቱ የሟቾችን ቁጥር 170 አድርሶታል። ከጥቃቱ የተረፉ መንደርተኞች ለሂውማን ራይትስ ዎች እንደተናገሩት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንዳለፉ  ከ30 ደቂቃ በኋላ ወታደራዊ ኃይሉ ወደ ኖንዲን መንደር መውረዱን ተናግረዋል።

ወታደሮቹ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ነዋሪዎችን ከቤታቸው እያባረሩ ወንጀሉን ፈፅመዋል ሲሉ ተደምጠዋል። በመቀጠል 5 ኪሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሶሮ መንደር ደርሰው ከአንድ ሰአት በኋላ በመንደሩ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ከጥቃቱ  የተረፉት እማኞች ገልጸዋል። በሁለቱም መንደሮች ወታደሮቹ ለመደበቅ ወይም ለማምለጥ በሞከሩ ሰዎች ላይ መተኮሳቸውን እማኞቹ አክለዋል። የጅምላ ግድያው በወታደሮች የተወሰደው በታጣቂ ቡድን ለተፈፀመባቸው ጥቃት የበቀል እርምጃ ነው ተብሎ ታምኖበታል።

የመንደሩ ነዋሪዎች የታጠቁ ተዋጊዎችን ይረዱ ነበር በሚል ተከሰዋል። በሰሜናዊ ያትንጋ ግዛት አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ካምፕ ላይ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ሰንዝረዋል።የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር ቲራና ሃሰን እንዳሉት በኖንዲን እና በሶሮ መንደር የተፈፀመው እልቂት የቡርኪናፋሶ ወታደሮች በፀረ-ሽምቅ ዘመቻቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙት የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
ኬቨን ደ ብረይነ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያውን የግምባር ኳስ በመግጨት አስቆጥሯል 😲

ሁሉንም ማሳካት ተችሎታል...

ብራይተን 0-4 ማን ሲቲ

ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio

#ዳጉ_ጆርናል
የቲክ ቶክ ቻይና ዋና ድርጅት መተግበሪያውን የመሸጥ እቅድ እንደሌለው አስታወቀ

የቲክ ቶክ የቻይና እናት ኩባንያ ባይትዳንስ ዩናይትድ ስቴትስ በጣም ተወዳጅ የሆነውን የቪዲዮ መተግበሪያ እንዲሸጥ ወይም በአሜሪካ ውስጥ እንዲታገድ የሚያስገድድ ሕግ ካወጣች በኋላ ንግዱን የመሸጥ ፍላጎት የለኝም ሲል ኩባንያው አስታውቋል። "ባይት ዳንስ ቲክ ቶክን ለመሸጥ ምንም እቅድ የለውም" ሲል ኩባንያው በያዘው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ቱቲያኦ ላይ በይፋ መለያው አጋርቷል።

ቴክቶክ ከመገናኛ ብዙሃን አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ቲክ ቶክ “ህገ-መንግስታዊ ያልሆነውን” ህግ በፍርድ ቤት እንደሚቃወም ተናግሯል። የባይትዳንስ መግለጫ የመጣው ቲክ ቶክን ከሚሰጠው ስልተ ቀመር ውጭ ለመሸጥ አማራጮችን እያፈላለገ መሆኑን መገናኛ ብዙሃን ከዘገቡ በኋላ ነው።

ባይትዳንስ ቲክ ቶክን እንደሚሸጥ የውጭ መገናኛ ብዙሃን እያጋሩት ያሉት ዘገባዎች እውነት አይደሉም ብሏል ኩባንያው። ባይት ዳንስ ቲክ ቶክን ለመሸጥ ምንም እቅድ የለዉም ”ሲል ኩባንያው በማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም ቱቲያኦ ላይ በይፋ መለያው ላይ ለጥፏል። ቲክቶን በአሜሪካ የማገድ እርምጃ በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረቡዕ እለት ተፈርሟል። ቲክ ቶክ የተጠቃሚውን መረጃ ለቻይና መንግስት ጋር ሊያጋራ ይችላል በሚል ስጋት በአሜሪካ የተወነጀለ ሲሆን ኩባንያው ግን ውንጀላውን የሀሰት ሲል አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ከኢትዮ ቴሌኮም እውቅና ውጪ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ስልክ ሲያስደውል የነበረ ግለሰብ ተያዘ

በሀረሪ ክልል ጀኒላ ወረዳ ጆራ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከኢትዮ ቴሌኮም እዉቅና ውጪ በህገወጥ መንገድ  ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወደ ውጪ ሀገር በማስደወል ህገ ወጥ ተግባር ሲፈፅም የነበረው ግለሰብ ከግብራበሮቹ ጋር ከነ ቁሳቁሶቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የጅኒላ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሙፍቱ ከድር ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት  በተጠርጣሪነት የተያዘው ግለሰብ ከኢትዮ ቴሌኮም እውቅና ውጪ የስልክ መስመሮችን በመዘርጋት የኢትዮ ቴሌኮምን በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ እና ኪሳራ ላይ የሚጥል ተግባር ፈፅሟል።

ግለሰቡ በድብቅ ሰዎችን ወደ ውጪ ሀገር በማስደወል የግል ጥቅሙን በህገ ወጥ መንገድ ሲያካብት እንደነበር እና በዚህ ተግባር ላይ እያለም እጅ ከፍንጅ መያዙን ተናግረዋል።ለዚህ ተግባር አገልግሎት እንዲሁም በህገወጥ ተግባር ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባቸው ብዛት ያላቸው የዋይፋይ ሳጥኖች፣ የተለያዩ ኬብሎች ፣ፍላሾች ፣ አንቴናዎች፣ሲም ካርዶች እና ሞባይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

በዚህ ተግባር በተባባሪነት ከአንደኛው ተጠርጣሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ እና በቀጣይ ጊዜያት የምርመራ መዝገባቸው ተጠናቆ ለሚመለከተው የፍትህ አካል እንደሚላክ ኮማንደር ሙፍቱ ከድር ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
በጋዛ የጅምላ መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ 'ግልጽ' ምርመራ እንዲደረግ እስራኤልን ጠየቀች

ዋይት ሀውስ በእስራኤል ከበባ ከወደሙ የጋዛ ሆስፒታሎች የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን ተለትሎ ከእስራኤል ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንደሚፈልግ አስታውቋል።ከ300 በላይ ሰዎች በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸው የተረጋገጥው በካን ዮኒስ ናስር ሆስፒታል ተቀበሩ የተባሉ ከ300 በላይ ሰዎች እስካሁን ድረስ በመገኘታቸው ነው።በሰሜናዊው አል-ሺፋ ሆስፒታል ውስጥ ሌሎች የጅምላ መቃብሮችም ይገኛሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ እንፈልጋለን ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።በተጨማሪም ይህንን በጥልቀት እና በግልፅ መመርመር እንፈልጋለን ሲሉ አክለዋል።በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር በኑሴይራት ውስጥ የሃማስ ‘ስናይፐር ሴል’ አጠፍቻለሁ ሲል አስታውቋል።የእስራኤል ጦር ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ጋዛን የሚከፍለው በኔትዛሪም ኮሪደር አቅራቢያ በርካታ ተዋጊዎችን በመግደል እና ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን በማውደም በአካባቢው ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል።

ወታደሮቹ በሰሜን በሻቲ የሚገኘውን የሃማስ ማስጀመሪያ ቦታዎችን በመምታታቸው በማዕከላዊ ጋዛ ኑሴይራት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚገኘውን የቡድኑን “ስናይፐር ሴሎች” አንዱን “በትክክለኛ የአየር ድብደባ” በማውደም ላይ መሆናቸውን ጦሩ አስታውቋል።በአጠቃላይ ባለፉት 24 ሰዓታት የእስራኤል ጦር በወሰደው ዘመቻ 30 የሃማስ ኢላማዎችን መምታቱንም አክሏል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ የእስራኤል የመጨረሻ የጦር ማዕበል በሆነችው በራፋህ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ቢያንስ አምስት ሰዎችን መግደልን ጨምሮ በሲቪል ዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ሲል የፍልስጥኤሙ ዋፋ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በሰምሃል አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል
የበዓል ቅርጫ ቤትዎ ድረስ ብናመጣልዎትስ?
አጋፔ online ቅርጫዎች ነን።


ለገና በዓል እምነት የጣሉብን ደንበኞቻችን ሁሉ አስደስተናል!ለመጪው ፋሲካ ደግሞ ከቀድሞው በላይ ተዘጋጅተናል።የበዓል ቅርጫ በአቅራቢያዎ ካላገኙ
የስራ ሁኔታዎ ለሊት ተነስቶ በቅርጫ ስራ ለመሳተፍ ካልፈቀደልዎ
ሳይደክሙና እንቅልፎን ሳያጡ
ድካምና ጊዜዎን ቆጥበን ማለዳ ከወፏ ዜማ ቀድመን ትኩስ ስጋ ከቤትዎ እናደርሳለን።

ውጪ ሀገር ሆነው አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቾን በአውድ ዓመት ቅርጫ ሰርፕራይዝ ማድረግ ከፈለጉም ይዘዙን!
ለመመዝገብ

☎️ 09-20-80-98-21
09-20-72-91-52
ወይም
0913552085 ይደውሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ደግሞ የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://t.me/+HRT-JSbRFPQ3MzVk

#ዳጉ_ጆርናል
ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት እና መታወቂያ በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር  ዋለ

ረቡዕ ሚያዚያ 16/2016ዓ.ም  በየካ ክፍለ ከተማ  በሀሰተኛ  ማስረጃ  አገልግሎት  ለማግኘት የሞከሩ አራት ደንበኞች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን  የአዲስ አበባምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሁለት ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው አገልግሎት ለማግኘት የቀረቡ ተገልጋዮችን ጨምሮ  ሌሎች ሁለት በወንጀል ተግባሩ የተጠረጡ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አግልግሎት ኤጀንሲ  ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ ዓለማየሁ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል  ።

አንደኛው ግለሰብ ሃሰተኛ የመታወቂያ እና ያላገባ ህገ ወጥ ማስረጃ በመያዝ ለጽ/ቤቱ ሰራተኛ ጉቦ በመስጠት አገልግሎት ለማግኘት የሞከረ ሲሆን   ከዓመታት በፊት ማስረጃውን በሌላ አገናኝ ደላላ ያገኘው መሆኑን ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም  ደላላው እና  ሁለተኛው ተጠርጣሪ የቂርቆስ ክ/ከተማ ነዋሪነት መልቀቅያን አስመስሎ በማሰራት አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ ሲያደርግ ሃሰተኛ ሰነዱን ካዘጋጀው አስመዝጋቢ የቤት ባለቤት ነዋሪ ግለሰብ ጋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአንደኛው ወንጀል የተጠረጠረው የጽ/ቤቱ ሰራተኛ ከዚህ ቀደም በወንጀል ተጠርጥሮ በኤጀንሲው ታግዶ የፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ያለ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡  ሁለተኛው  ድርጊት ሃሰተኛ መልቀቅያ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ነዋሪነት ስም አስመስሎ ለመገልገል ሲቀርብ በማስረጃው ላይ በጽ/ቤቱ ጥርጣሬ በማደሩ  የቂርቆስ ክ/ክተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ድርጊቱ ለፖሊስ እንዲተላለፍ በየካ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት  ጽ/ቤት መደረጉን አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረውም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
የሜክሲኮ የምግብ አቅራቢ የአይጥ መረቅን ከ50 ዓመታት በላይ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታወቀ

በሜክሲኮ ሜርካዶ ሪፐብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ በሚሰኘው ገበያ ውስጥ በርካታ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይቻላል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልዩ የሆነው የአይጥ ስጋን በመሸጥ የሚታወቅ የቆየ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ታዋቂ ነው።

ለበርካታ የዓለም ህዝብ የአይጥ ስጋ በፍፁም የማይለመድ እና ነውር ቢሆንም በሜክሲኮ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ክልል ውስጥ ግን ለየት ያለ ጣዕሙ እና ለመድኃኒትነት ይውላል በሚል ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአይጥ ሥጋ የሚሸጡባቸው ሱቆች እና አከፋፋዮች ከአካባቢው ገበያ እየጠፉ ይገኛል።

በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ ግን አንዱ አከፋፋይ አሁንም ሁለቱንም ማለትን ጥሬ የአይጦች ስጋ እና የአይጥ መረቅ ከተለያዩ አትክልቶች እና ቅመማ ቅመም ጋር አዋህዶ መሸጡን ቀጥሏል። እያንዳንዱ የአይጥ መረቅ አንድ ሙሉ ሳህን የሚይዘው  በ100 የሜክሲከ ፔሶ ወይም በ5.80 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል።በሜርካዶ ሪፑብሊካ የመጨረሻው የአይጥ ስጋ ሻጭ ሆሴ ሬሜዲዮስ ሄርናንዴዝ "ካሚሎ" በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየችው ወላጅ እናቱ ይህንኑ ንግድ ወርሷል።

በአንድ ወቅት በገበያው ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይጥ ስጋ ሻጮች እንደነበሩ ያስታውሳል፣ ነገር ግን ሁሉም ጡረታ ወጥተዋል አልያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሁን ላይ በገበያው ውስጥ ብቸማ አቅራቢ ሆኖ ቀጥሏል። ስራው እየተቀዛቀዘ በርካቶች ከዘርፉ ቢወጡን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰብን ንግድ ለመተው እቅድ የለኝም ሲል ይናገራል። ይህው የቤተሰቡ ንግድ ለ52 ዓመታት ዘልቋል። በተቻለም መጠን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ለማድረግ የአቅሜን ያህል መስራቴን እቀጥላለሁ ሲል ይደመጣል።

ካሚሎ የሚያቀርበውን የአይጥ ሾርባ ለማዘጋጀት  በሳን ሉዊስ ፖቶሲ ዙሪያ ካሉ የከተማ አካባቢ እና በዙሪያው ክሚገኙ ገጠራማ ስፍራዎች ተይዘው ይመጣሉ። የአይጥ ሥጋ በተለይ የደም ማነስ፣ የስኳር በሽታ ወይም ካንሰር ላለባቸው ሰዎች ጠቃሚ ሲሆን የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር እና የምግብ ፍላጎትን ለመጨመር ይረዳል ተብሎ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ይታመናል።

በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ በሚገኘው ካሚሎ ሁለቱንም የአይጥ መረቅ በ100 ፔሶ የሚሸጥ ሲሆን ጥሬ አይጥ ገዝተው ቤት ይዘው ለሚሄዱ በ90 ዋጋ ይቀርባል።የስጋውን ጣዕም በትክክል ለማሟላት በአትክልቶችና ቅመማ ቅመሞች ለማብሰል ይመክራል ሲሉ የሬስቶራንቱ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 244 የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ ሰራተኞቹን መቅጣቱን እና በህግ ተጠያቂ ማደረጉን ገለፀ

👉 አገልግሎቱ አመራሮቹ እና ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ሰራተኞቹ ሀብታቸዉን እንዲያስመዘግቡ አድርጓል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎትከዚህ በፊት ይነሳበት የነበረዉን የሙስና ተግባር ለመከላከል የተለያዩ ለዉጦችን እየከወንኩኝ እገኛለሁ ማለቱን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ለዚህም በማሳያነት በባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከወናቸዉን ተግባራት በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል።

በተመሳሳይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የስነምግባር ጥሰት የፈጸሙ 244 ሰራተኞቹን ከስራ እንዲታገዱ ፣ ከሀላፊነት እንዲነሱ እና በህግ እንዲጠየቁ ማድረጉንም አሳዉቋል።

አገልግሎቱ ይህንን ያለዉ በዛሬዉ እለት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የ2016 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸምን በገመገመበት ወቅት ነዉ።

የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የኢ - ፓስፖርት (E-passport) ለመቀየር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየከወነ መሆኑንም ብስራት ከሪፖርቱ ሰምቷል። በተመሳሳይ በዉጪ የሚታተመዉን ፓስፖርት በሀገር ዉስጥ ለማድረግ የዲዛይን ስራዎች ተጠናቅቀዋል የተባለም ሲሆን ህትመቱን ከሚሰራዉ ተቋም ጋር ዉል መታሰሩን እና ህትመቱን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ለመጀመር ማቀዱንም ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ስራዎቹን ለመከወን እንዳልቻለ የገለጸ ሲሆን በአንጻሩ በትግራይ ክልክ ተቋርጦ የነበረዉን አገልግሎት ለማስጀመር የዳሰሳ ጥናት መስራቱን አስታዉቋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
የኬንያ አየር መንገድ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሰራተኞቼ ላይ ተፈፅሟል ያለውን እስር ተቃወመ

የኬንያ አየር መንገድ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ሰራተኞቼ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ቢወስንም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሁለት ሰራተኞቹን በቁጥጥር ስር አውሏል ሲል ከሷል።

ሁለቱ የአየር መንገዱ ሰራተኞች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደራዊ መረጃ ክፍል ባለፈው አርብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን “በጣም ጠቃሚ” ጭነት ላይ ያለ የጉምሩክ ሰነድ ጠፍተዋል በሚል ነው ሲል የኬንያ አየር መንገድ በመግለጫው ገልጿል። አየር መንገዱ ጭነቱን ወደ ኪንሻሳ ያላነሳው ባልተሟላ ሰነድ የተነሳ ነው ብሏል።

"የኬንያ አየር መንገድ የጭነት ንብረቱ ያልተሟላ ሰነድ ስለ መኖሩ ለወታደራዊ መኮንኖች ለማስረዳት የተደረገው ጥረት ሁሉ ከንቱ ሆኖ ተገኝቷል" ሲል አክሏል። ወታደራዊ መኮንኖቹ የኬንያ ኤምባሲ ባለስልጣናት እና የአየር መንገዱ ቡድን ለአጭር ጊዜ ሁለቱን ሰዎች እንዲጎበኟቸው የተፈቀደላቸው እስከ ማክሰኞ ድረስ ብቻ ነው።

ሐሙስ እለት የኬንያ አየር መንገድ እንደገለፀው ፍርድ ቤት ሰራተኞቹ ላክ ምርመራ እንዲጥል በመወስን ከእስር እንዲፈቱ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሏል። "ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ቢሰጥም የወታደራዊ መረጃ ክፍል አሁንም በድብቅ እንደያዛቸው ይገኛል፣ ሆኖም እነዚህ በወታደራዊ መረጃ ተቋም ውስጥ የታሰሩ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው" ሲል አየር መንገዱ አክሎ ተናግሯል።

በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የሰራተኞቹ ስልኮች መያዛቸውን የኬንያ አየር መንገድ ገልጿል። የተጠቀሰው ጭነት ምን እንደያዘ ግልፅ ያልተደረገ ሲሆን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለስልጣናት ዘንድ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ አስተያየት የለም ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ውስጥ ከ230 ኩንታል በላይ ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፅ እንዲወገድ ተደረገ

በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ በቁጥጥር ስር የዋለ ከ230 ኩንታል በላይ የሚገመት ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ እፅ እንዲወገድ መደረጉን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል።የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዶ/ር ደረጄ ኢተና በሻላ ወረዳ በተለያዩ ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ 230 ካናቢስ ከፍተኛ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ተናግረዋል::

በአርሲ ዞን እንደ ሻላ ያሉ ጥቂት ወረዳ ውስጥ አርሷአደሩ ከበቆሎ እና ከማሽላ ምርቶች ጋር አደንዛዥ እፅን እንደሚያመርት የጠቀሱት ኃላፊው ህብረተሰቡ በተለያዩ ጊዜያት መድረክ በመፍጠር አስፈላጊውን የግንዛቤ ማስጨበጫ  ትምህርት በመስጠት የምርቱን ስፋት በሂደት መቀነሱን ተናግረዋል።

የአደንዛዥ እፅ ንግድ እና ዝውውር የተደራጀ የቡድን ሰንሰለት ያለው በመሆኑ በከፍተኛ ገንዘብ በመደለል በድብቅ የሚመረት የሚደረግ ቢሆንም የተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ተቋማት ጋራ በመስራት የአደንዛዥ እጹን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፀዋል።በቅርቡ በተደረገ የተቀናጀ አሰሳ በሻላ ወረዳ ላይ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲወገድ መደረጉን ገልፀዋል።

አደንዛዥ እፅ የወጣቶችን አዕምሮ ለወንጀል ድርጊት የሚያነሳሳና ሀገር ተረካቢ የሆነውን ወጣት ለሞራል መላሸቅ እንዲገጥመው እና ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር የሚያገልጥ በመሆኑ የአደንዛዥ እፅ ዝውውር እና ንግድ ላይ ከመስራት ባሻገር በዚህ ተግባራት የተሰማሩ በርካታ ግለሰቦችን ለፍትህ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ረ/ኮሚሽነር ደረጄ ኢተና ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል