ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
34.8K subscribers
21.7K photos
185 videos
21 files
536 links
The best fiction is far more true than any journalism

📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ

👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56



👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Download Telegram
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች

                    

       ኤቨርተን 2-0 ሊቨርፑል
    ማን ዩናይትድ 4-2 ሼፊልድ
     ክሪስታል ፓላስ 2-0 ኒውካስትል
       ዎልቭስ 0-1 በርንማውዝ

ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio                       
#ዳጉ_ጆርናል
የሊጉ ተፎካካሪዎች

ሚኬል አርቴታ 🤝 ፔፕ

#ዳጉ_ጆርናል
16 ሰው አሳፍሮ ከመቐለ ከተማ በመነሳት ወደ ውቕሮ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ አደጋ ማጋጠሙ ተነገረ

ቶዮታ ሚኒባስ ወይንም ሀይሩፍ በመባል የምትታወቅ ተሽከርካሪ በትናንትናው እለት ሚያዝያ 16 ቀን 16 ሰዎችን አሳፍራ ከመቀለ ከተማ በመነሳት ወደ ውቅሮ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳለ አጉላዕ ተብሎ በሚታወቅ ስፍራ ባለ ቁልቁል መግቢያ ላይ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል።

አደጋው የደረሰው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን ተሳፋሪዎቹ ላይ ይህ ነው የሚባል ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እና ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸውም ተሳፋሪዎች በውቅሮ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል ።

የአደጋው መንስኤ ይፋ ያልተደረገ ቢሆንም ከተሳፋሪዎቹ በተገኘ መረጃ መሰረት የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ሊሆን ይችላል ተብሏል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጵያ ፤ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።

Via ዋልታ
#ዳጉ_ጆርናል
በአርጀንቲና መንግስት ለትምህርት የሚያደርገዉን ድጎማ በማቋረጡ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ

በመላው አርጀንቲና የትምህርት ወጪ መቀነስን በመቃወም ታላቅ ሰልፎች ተካሂደዋል።የፕሬዚዳንት ጃቪየር ሚሌ አክራሪ የቁጠባ እርምጃዎች በህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናዉያን ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ከሀገሪቱ ኃያላን የሰራተኛ ማህበራት እና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመቀላቀል ተቃዉሞ አሰምተዋል።

የቀኝ አክራሪው ፕሬዝደንት በታህሳስ ወር ስልጣን ከያዙ በኋላ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ተከታታይ ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆኑ የአሁኑ በተገኘዉ ህዝብ ብዛት ትልቁ ነዉ ተብሏል፡፡አስተባባሪዎች ዩንቨርስቲዎችን የመዝጋት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ያሉትን የበጀት ቅነሳን ለመቃወም ጥሪ አቅርበዋል።

የቦነስ አይረስ ዩኒቨርሲቲ በዋና ከተማው ብቻ በተቃውሞው ላይ ከ500 ሺ በላይ ሰዎች መሣተፋቸውን ገልጿል።ሚሌ በምርጫ ዘመቻው ወቅት የህዝብ ወጪን ለመቀነስ እና የመንግስትን ከባድ የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመፍታት እየሰሩ ይገኛል፡፡ኢኮኖሚውን ለማስተካከል የተወሰኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን መዝጋት፣ የባህል ማዕከላትን ከጥቅም ውጪ ማድረግ፣ የመንግስት ሰራተኞችን ማሰናበት እና ድጎማዎችን ማቋረጠ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል ናቸዉ፡፡

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
ባለፉት 9 ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ 392 ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል

በአደጋዎቹም  56 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባና አካባቢዋ በዘጠኝ ወራት ውስጥ  392 አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በአደጋውም 670 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን  የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዢን ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ ከ11.5 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳንም ተችሏል።

የሞት አደጋ ካጋጠማቸው ውስጥ ሁለቱ ብቻ በእሳት አደጋ ሲሆን የሀምሳ አራቱ ህይወት ያለፈው በኮንስትራክሽን አደጋ፣ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተዉና ዉሀ በአቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ እንዲሁም ምክንያታቸዉ በፖሊስ እየተጣራ ባሉ ጉዳዮች መሆናቸውን  አቶ ንጋቱ ጨምረውም  ተናግረዋል።

ህይወታቸዉ አልፎ የተገኙትን  የሀምሳ አራቱን ሰዎችን አስከሬን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በደረሱት አደጋዎች የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት 39 ሰዎችን ከእሳት አደጋ 85 ሰዎች ደግሞ ከሌሎች ድንገተኛ በድምሩ 125 በአደጋ ዉስጥ የነበሩ ሰዎችን ማትረፍ መቻሉን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከደረሱት የእሳት አደጋዎች ዉስጥ 41 የመኖሪያ ቤት 35 የንግድ ቤቶች ላይ የተከሰተ ሲሆን ሀያ ሁለቱ የጎርፍ አደጋዎች ናቸዉ ተብሏል። በዘጠኝ ወሩ የደረሱ አደጋዎች ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የንብረት ወድመት መጠን በ37 ሚሊየን ብር የቀነሰ ሲሆን የአደጋ ቁጥር በ4 ጨምሯል።

በትግስት ላቀዉ
#ዳጉ_ጆርናል
አሜሪካ ዩክሬንን ለመርዳት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በድብቅ መላኳ ተነገረ

ዩክሬን ዩናይትድ ስቴትስ በድብቅ የሰጠችውን የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ወራሪ ሃይሎች ላይ መጠቀም መጀመሯን የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። መሳሪያዎቹ በመጋቢት ወር በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፀደቀው የ300 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ጥቅል አካል ሲሆኑ በዚህ ወር ዩክሬን ደርሰዋል። በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬን ግዛት ክሬሚያ ድራስ ኢላማዎችን ለመምታት ቢያንስ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋ።

ባይደን በተመሳሳይ አሁንም ለዩክሬን የ61 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ፓኬጅ ፈርመዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም ለዩክሬን መካከለኛ ክልል የሚደርሱ የጦር ሃይል ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም አቅርባ ነበር። ነገርግን የበለጠ ኃይለኛ የጦር መሳሪያዎችን ለመላክ ፍቃደኛ ሳትሆን የቀረች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በከፊል የአሜሪካን ወታደራዊ ዝግጁነት ለመጉዳት ያሳስባል በሚል ነበር። ሆኖም ባይደን በየካቲት ወር እስከ 300 ኪ.ሜ የሚተኮሱ የረዥም ርቀት የሚሳኤል ስርዓትን ለዩክሬን ለመላክ አረንጓዴ መብራትን በድብቅ መስጠታቸው ተነግሯል።

የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓቴል "ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤል መሳሪያብ በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ መመሪያ እንደሰጠች አረጋግጠዋል። ከመሳሪያዎቹ ውስጥ ምን ያህሉ እንደተላከ ግልጽ ባይሆንም የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ዋሽንግተን ተጨማሪ ለመላክ አቅዳለች ብለዋል።

ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በክራይሚያ የሚገኘውን የሩሲያ አየር መንገድ ለመምታት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ስማቸው ያልገለጻቸውን የአሜሪካ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። አዲሶቹ ሚሳኤሎች ማክሰኞ እለት በሞስኮ በተያዘችው የዩክሬን የወደብ ከተማ በርዲያንስክ ውስጥ በሩሲያ ወታደሮች ላይ በተሰነዘረ ጥቃትም ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

በቅርብ ወራት ኪየቭ የጥይት ክምችቷ በመሟጠጡ እና ለሩሲያ ይህ ሁኔታ ቀጣይነት ያለው ትርፍ ስለሚያስገኝ በሚል ለምዕራቡ ዓለም የእርዳታ ጥሪዋን እያጠናከረች ትገኛለች።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ጎማ የተገጠመለት ተንቀሳቃሽ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ በ29 ሺ የአሜሪካን ዶላር ገደማ መሸጡ ተሰማ

ጎማ የተበጀለት የአስክሬን ሳጥን በተሽከርካሪ መልክ መቅረቡን ተከትሎ በ28,750 የአሜሪካን ዶላር የተሸጠ ሲሆን ያልተለመደው የሳጥኑ ቅርፅ መኪና ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

እኤአ በ1965 ለእይታ ይቀርብ ከነበረው የቴሌቭዥን ተከታታይ ዘ ሙንስተር ትዕይንት ላይ ድራግ-ዩ-ላ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ መነሳሻ ሆኖ እንደተሰራም ተሰምቷል።ይህ ያልተለመደ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ የሳጥን-ፍሬም እና ስምንት የፋይበርግላስ ሳጥን በመጠቀም ስራ ላይ ውሏል። የሹፌሩ መቀመጫ የተበጀለት ሲሆን ለተመለከተው በሙሉ እውነተኛ አስክሬን የጫና እንዲመስል ሆኖ ተሰርቷል።

የተሟላ ሰፊ የኋላ ጎማዎች በእሽቅድምድም ተንሸራታች ተደርገው የተሰሩ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ የጭስ ማውጫ ቱቦዎች እና የፋኖስ አይነት መልክ ያላቸው መብራት የተሞላው ይህ የሬሳ ሳጥን መኪና ከትክክለኛው ለመንገድ ብቁ ነው ከሚባለው ተሽከርካሪ ይልቅ ለፊልም የሚውል ንድፈ ሀሳብ ይመስላል። ነገር ግን ይህው የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ በኒውዮርክ ተመዝግቧል። በምዝገባውም በ1928 ፎርድ እና ትክክለኛ የሰሌዳ ቁጥር ተሰጥቶታል።

የሹፌሩ ክፍል በሬሳ ሣጥኑ የኋላ ክፍል ላይ የሚገኝ ሲሆን አነስተኛ መቀመጫ በሰማያዊ ጨርቃ ተሸፍኗል። ቼቭሮሌት ቪ8 ሞተር በሻሲው ማእከሉ ወደ ኋላ ተቀምጧል። ባለአራት በርሜል ካርቡረተር፣ የኤደልብሮክ ማስገቢያ መያዣ እና ሪብብ ቫልቭ አሉት። የማርሽ ሳጥኑን በተመለከተ አውቶማቲክ ሲሆን በወርቅ ቀለም በተቀባ የጽጌረዳ ዘዬዎች ተቀርጿል።

የነዳጅ ማጠራቀሚያው ወደ ተሸከርካሪው አፍንጫ አቅጣጫ ላይ ተቀምጧል ።ጎልቶ እንዲታይ ለማድረግ በወርቅ ቀለም የተቀባ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ሌሎች ጎልተው እንዲታዩ የሚገባቸው የተሽከርካሪው ክፍል አካል ሲሆን ለምሳሌ እንደ መቃብር ላይ ሀውልት ከፊት ለፊት ያለው የመቃብር ድንጋይ እና ግዙፍ የጭስ ማውጫዎች ለማመሳሰል ተሞክሯል።ልዩ የሆነው ተሽከርካሪ ኦዶሜትር የተገጠመለት ስላልሆነ አጠቃላይ የኪሎሜትር ርቀት አይታወቅም።

በሰዓት በምን ዓይነት ፍጥነት እንደሚጓዝ ምንም አይነት መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ነገር ግን ተሽከርካሪው የውድድር መኪና እንዳልሆነ ይታወቃል ተብሏል።የአስክሬን ሣጥን መኪናው ባለፈው ሳምንት በ28,750 ዶላር የተሸጠ ሲሆን፥ መኪናውን በተለያዩ ዝግጅቶች ጨረታ በማሸነፍ እና ልዩ ልዩ ምርቶችን በመሰብሰብ የሚታወቅ ድርጅት የግሉ አድርጎታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ስልክ እያነጋገሩ ያሽከረከሩ ከ6 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸው ተነገረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመነት ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ ከ25 ሺህ በላይ  አሽከርካሪዎችን መቅጣቱን አስታውቋል ።

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ በ33 መንገዶች ላይ ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ 25 ሺህ 888 አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ያላሰሩ 3 ሺህ 800 አሽከርካሪዎች በደንብ መተላለፍ መቀጣታቸው ተገልጿል ።

በተጨማሪም 204 ሞተረኞች የግጭት መከላከያ ቆብ ወይም ሄልሜት ሳያደርጉ ፣ 6504 አሽከርካሪዎች ስልክ እያነጋገሩ በመገኘታቸው በደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት ቅጣት እንደተጣለባቸው ተጠቁሟል ።

በዚህም የተነሳ የሞት አደጋ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ6 ነጥብ 34 በመቶ  መሻሻል መታየቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣኑ ያገኘው መረጃ ያመላክታል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
ቬትናም የለስላሳ መጠጦች ባለሀብትን በ40 ሚሊየን ዶላር የማጭበርበር ወንጀል በስምንት ዓመታት እስራት ቀጣች

የቬትናም ከፍተኛ የለስላሳ መጠጦች ባለሀብት ሐሙስ እለት በ40 ሚሊየን ዶላር የማጭበርበር ወንጀል ለስምንት አመታት በእስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

የቬትናም መንግስት በቅርቡ በከፈተው የሙስና ዘመቻ ላይ ታዋቂው የቢዝነስ ሰው ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል። የኮሚዩኒስት ሀገር የሆነችው ቬትናም ያለውን የሙስና ሰንሰለት ለማጥፋት በከፈተችው ሰፊ ዘመቻ ከ4,400 በላይ ሰዎች የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ባለሥልጣት እና ከፍተኛ የንግድ ተቋማትን ጨምሮ የክስ ሂደት ተጀምሮባቸዋል።

በመዲናዋ ሆቺ ሚን ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ በ2019 እና በ2020 በተሰጡ ብድሮች ባለሀብቶችን በማጭበርበር የለስላሳ መጠጦች ባለ ሃብቱን ትራን ኪ ታን እና ሁለቱን ሴት ልጆቹን ጥፋተኛ ብሏቸዋል። የ71 አመቱ የመጠጥ ግሩፕ ሊቀመንበር ታን ሂፕ ፋት በብድር ላይ ዋስትና ተብሎ በተዘጋጀው ተገቢ ንብረት ላይ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል ሲሉ የቬትናም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ተበዳሪዎች ገንዘቡን በወለድ ሲከፍሉ እንኳን ታህህ በተለያዩ ምክንያቶች ንብረቶቹን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆን የመግዛት መብታቸውን ሳይቀር ጥሰዋል ብሏል።

ፍርድ ቤቱ የታንህን የ 43 ዓመቷ ሴት ልጃቸውን ትራን ኡየን ፑኦንግ የኩባንያው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ስትሆን በአራት አመት እስራት እንድትቀጣ ወስኗል።የ40 ዓመቷ ታናሽ እህቷ ትራን ንጎክ በገደብ የሶስት አመት እስራት ተቀጥታች። ታን ሂፕ ፋት በታሸገ ሻይ እና በሃይል መጠጦች ከሚታወቁ የቬትናም ተቋማት መካከል ትልቁ የመጠጥ ኩባንያ ነው።አዛውንቱ ባለሃብት ታንህ በፍርድ ቤት በሰጡት የመጨረሻ ቃል በተፈጠረው ነገር ተጸጽቻለሁ እናም ሀላፊነቱን ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ ብለዋል።

ለቀጣይ ስራዬ እና ታማኝነቴ በቅርቡ ወደ ህብረተሰቡ እንድመለስ እድል እንዲሰጠኝ እፈልጋለሁ ሲሉ ታንህ ጠይቀዋል።አንዳንድ የቬትናም በጣም ስኬታማ የንግድ መሪዎች በሙስና ማጽጃ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል። በታሪክ ውስጥ ከታዩት ትልቅ የማጭበርበር ክሶች በአንዱ የንብረቱ ባለጸጋ ትሩንግ ማይ ላን በ27 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ያስከተለውን ማጭበርበር በማቀነባበር የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል። ከላን ጋር  85 ሌሎች ከፍተኛ የባንክ ባለስልጣናትን ጨምሮ ጉቦ በመቀበል እና ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም እንዲሁም የባንክ ህግን በመጣስ ክሶች ተፈርዶባቸዋል።

በመጋቢት ወር የሃኖይ ፍርድ ቤት የቅንጦት ንብረት ባለፀጋ ዶ አንህ ዱንግ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለሃብቶችን በ355 ሚሊዮን ዶላር የቦንድ ማጭበርበር በሚል ክስ በስምንት አመት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው። ለሶስት አመታት በእስር ላይ የሚገኙት ዱንግ እና ልጃቸው 355 ሚሊየን ዶላር መክፈላቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ከወላይታ ሶዶ - አዲስ አበባ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ታወር ብረትን የሰረቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን  በሁልባራግ ወረዳ በዋጮ ሆቢሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰላም መሊቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከወላይታ ሶዶ - አዲስአበባ የኤሌትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ታወር ብረትን የሰረቀዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል።

ነሰሩ ወርቀ - ነጋ የተባለው ግለሰብ  ዋሚያዚያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ሆን ብሎ በህገወጥ መንገድ በአቋራጭ  ለመበልፀግ በማሰብ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሆነ  ከወላይታ ሶዶ -ገለን ወደ አዲሰ አበባ የተዘረጋውን ዋና የኤሌክትሪክ ኃይል 400 ኪሎ ዋት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ሰርቆ እጅ ከፍንጅ መያዙን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
                
ግለሰቡ ግምቱ እስከ 100 ሺህ ብር ሊያወጣ የሚችል የኤሌክትሪክ ሽቦ መሸከሚያ  ታወር ብረት ሰርቆ ለመውሰድ እያዘጋጀ እያለ  በአካባቢው ህብረተሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ  ለሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን ፖሊስም ተከሳሹንና የተሰረቀውን ንብረት በኢግዝቢትነት በመያዝ ቃል ከመቀበል ጀምሮ  አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን  ማስረጃዎች በማሰባሰብና ምርመራ  በማጣራት  መዝገብ  አደራጅቶ ለሁልባራግ ወረዳ  ዐቃቤ ህግ  አቅርቧል።

ዐ/ህግም ተከሳሹ  በ1996  ዓ/ም  የወጣውን የኢፌዲሪ  የወንጀል  ህግ አንቀጽ  669(1)(ለ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ በፈጸመው  የስርቆት ወንጀል ክስ መስርቶ ለሁልባራግ ወረዳ ፍ/ቤት አቅርቧል። ፍ/ቤቱም ከዐ/ህግ የቀረበለትን  ይህንን የስርቆት ወንጀል  ክስ ከተገቢ ማስረጃዎች ጋር አገናዝቦ ከመዘነ በኋላ  በተከሳሹ ላይ  የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት የሁልባራግ  ወረዳ  ፍ/ቤት  ሚያዚያ 16 ቀን 2016  ዓ/ም  ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ነስሩ ወርቀነጋ ላይ የ5 አምስት ዓመት ከ6 ወር ጽኑ  ወስኖበታል ሲሉ የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
ጀርመን በፍቅር ስም ሲያጭበረብር የነበረ የናይጄሪያ የማፍያ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች

የጀርመን ፖሊስ በማፍያ ቡድን ውስጥ ከፍተኛ  በፍቅር ስም የማጭበርበር ድርጊቶችን ያቀነባበሩ 11 ናይጄሪያውያንን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ይህው የብላክ አክስ የተሰኘው ቡድን በአለም አቀፍ ደረጃ "በርካታ የወንጀል ድርጊቶች" ውስጥ ይሳተፋል ሲል የባቫርያ ፖሊስ ባወጠው መግለጫ ገልጿል። በጀርመን ውስጥ ድርጅቱ የሚያተኩረው በፍቅር ቀጠሮ ማጭበርበር እና በገንዘብ ማጭበርበር ላይ ነው ሲል ሃይሉ አክሏል።

መግለጫው “የውሸት መታወቂያዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎቹ ለምሳሌረ ለማግባት ፍላጎት እንዳላቸው በማሳየት ለተጨማሪ ግንኙነት በተደጋጋሚ በተለያዩ ሰበቦች ገንዘብ ይጠይቃሉ” ብሏል።በአለም አቀፍ ደረጃ የወሮበሎች ቡድን ዋና ዋና የስራ ቦታዎች "የሰዎች ህገወጥ ዝውውር፣ ማጭበርበር፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የወሲብ ንግድ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር" ናቸው።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ሁሉም የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው እና ከ29 እስከ 53 ዓመት እድሜ ያላቸው እንደሆኑ ተመላክቷል። ከሁለት አመት በላይ የፈጀውን የፖሊስ ምርመራ ተከትሎ በተያዘው ሳምንት ማክሰኞ በባቫሪያ ክልል በተደረገው የፖሊስ ዘመቻ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል ።

እ.ኤ.አ. በ 2021 በብላክ አክስ ላይ በተደረገው ምርመራ ቡድኑ ናይጄሪያ ውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ዘልቆ በመግባት የግድያ ዘመሻ እንደፈጸመ የሚያሳይ ማስረጃ መገኘቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበው የነበረ ቢሆን የተወሰደበት እርምጃ ግን የለም።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ

ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል።

ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል።

በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም።

Via Addis Maleda
#ዳጉ_ጆርናል