Zemenbet/ዘመን ስፖርት ቤቲንግ
2.22K subscribers
1.08K photos
6 videos
1 file
642 links
Download Telegram
🗣 ፔፕ ጋርዲዮላ፡

"ኦስካር ቦብ ምናልባት እስከ ጥር ድረስ ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል።"

"ሲመለስ እጆቻችንን ዘርግተን እንቀበለዋለን ይህ ድል ለእርሱ ነው!"

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
እንኳን ለቡሄ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
“ ውጤቱ እንደ አሰልጣኝ አሳፍሮኛል “ አንቶኒዮ ኮንቴ

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ዋና አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ትላንት በሄላስ ቬሮና የደሰባቸውን የ 3ለ0 ሽንፈት “ እንደ አሰልጣኝ ያፈርኩበት ጨዋታ “ ሲሉ ገልጸውታል።

“ እሳፋሪ ውጤት ነው እንደ አሰልጣኝ አሳፍሮኛል “ ያሉት አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በተጨዋችም ሆነ አሰልጣኝነት እንደዚህ አይነት ውጤት ብዙም አይገጥመኝም ነበር ፣ ውስጤ እየደማ ነው።"ሲሉ ተናግረዋል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
የቀድሞ ተጨዋቾች የፕርሚየር ሊግ ግምት ምን ይመስላል ?

በተንታኝነት እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋቾች ጋሪ ኔቭል እና ጄሚ ካራገር የያዝነውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ዘመን ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

የጄሚ ካራገር ግምት ምን ይመስላል ?

- የሊጉ አሸናፊ :- ማንችስተር ሲቲ

- የሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊዎች :- ማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል ፣ ሊቨርፑል እና ቶተንሀም

- ማንችስተር ዩናይትድ አምስተኛ እንዲሁም አስቶን ቪላ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቅቃሉ።

- ወራጅ ክለቦች :- ሳውዝሀምፕተን ፣ ሌስተር ሲቲ እና ኖቲንግሃም

የጋሪ ኔቭል ግምት ምን ይመስላል ?

- የሊጉ አሸናፊ :- አርሰናል

- ወራጅ ክለቦች :- ሳውዝሀምፕተን ፣ ኢፕስዊች ታውን እና ሌስተር ሲቲ

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ሲቲ የተጫዋቹን ውል ማራዘም ይፈልጋል !

ማንችስተር ሲቲ የስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ለማራዘም አዲስ ውል እንዳቀረቡለት ተገልጿል።

ሮድሪ በአዲሱ ኮንትራት መሰረት ከማንችስተር ሲቲ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች መካከል አንዱ እንደሚሆን ዘ አትሌቲክስ አስነብቧል።

ማንችስተር ሲቲ የሮድሪን ክፍያ ከኬቨን ዴብሮይን እና ኤርሊንግ ሀላንድ ክፍያ ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ ማቀዳቸው ተዘግቧል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ፔድሮ ኔቶ የስተርሊንግን ሰባት ቁጥር ወስዷል !

ፖርቹጋላዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶ ራሂም ስተርሊንግ ይለብሰው የነበረው የሰባት ቁጥር ማልያ እንደተሰጠው ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ባለፈው ሳምንት ከዎልቭስ ቼልሲን የተቀላቀለው ፔድሮ ኔቶ በማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ወቅት የ 19 ቁጥር ማልያ ለብሶ መጫወቱ የሚታወስ ነው።

በክለቡ እንደማይፈልግ የተነገረው እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ በቀጣይ ሰማያዊዎቹን እንደሚለቅ ይጠበቃል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ኣሽንዳ ና ዓሚየ ና ዓሚየ
ተጋኒና ሎሚየ

ኣቲ ፅብቅቲ
ኣሸንዳ
ኣቲ ውቅብቲ
ኣሸንዳ
ትዘመን ናትኪ
ኣሸንዳ እንኳዕ ናብ ነፃነት ደቂ ኣንስትዮ ዝኮነት በዓል ኣሸንዳ ብሰላም ኣብፀሐክን!!!
“ ባሉኝ ተጨዋቾች እምነት አለኝ “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ተጨዋቾች አለማስፈረሙ እንደማያስፈራቸው ከእሁዱ የብሬንትፎርድ የሊግ ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ምን አሉ ?

- “ ተጨዋቾች አለማስፈረማችን አያስፈራኝም ምክንያቱም በቡድኑ እምነት አለኝ ፣ ጥሩ ቡድን ነው የተረከብኩት ተጨዋቾቹም ባለፈው ሳምንት አረጋግጠውልኛል።

- በአንፊልድ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታ ለማድረግ ጎጉቻለሁ ፣ ፍርሀት አይሰማኝም በቡድኑ እና ቴክኒካል ቡድኑ እምነት አለኝ።

- ጃሬል ኳንሳህ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል እሮብ ልምምድ አልሰራም ዛሬ ልምምድ መስራት ከቻለ እናየዋለን።

- በአሁን ሰዓት ያሉን ሁሉም ተጨዋቾች በክለቡ ይቆያሉ ብዬ እጠብቃለሁ።"ሲሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ጉንዶጋን ወደ ማንችስተር ሲቲ  ተመለሰ !

ማንችስተር ሲቲ ጀርመናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢልካይ ጉንዶጋን በድጋሜ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ ኢልካይ ጉንዶጋንን ከባርሴሎና በነፃ ዝውውር ማስፈረሙ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ሲቲ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ባካተተ የአንድ አመት ውል መፈረሙ ተነግሯል።

ጉንዶጋን ከፊርማው በኋላ “ ወደ ማንችስተር ሲቲ የመመለስ ተጨማሪ እድል ማግኘት ለእኔ ትልቅ ነገር ነው ፣ ሁሉም ሰው የአለም ምርጡን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን ያህል እንደማከብር ያውቃል።"ብሏል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
“ ዴሊትን የመጀመሪያ ምርጫዬ ነህ አላልኩትም “ ቪንሴንት ኮምፓኒ

የባየር ሙኒኩ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ማንችስተር ዩናይትድን ለተቀላቀለው ተከላካዩ ማትያስ ዴሊት " ነገርኩት ተብሎ የተዘገበው ሀሰተኛ ነው “ ብለዋል።

አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ማትያስ ዴሊት ባየር ሙኒክን ሲለቅ ውሳኔው የክለቡ እንደሆነ እና ባይለቅ የመጀመሪያ ምርጫቸው እንደሚያደርጉት እንደነገሩት ተዘግቦ ነበር።

“ በፍጹም እንደዛ ብዬ አልተናገርኩም “ ያሉት አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ እንደዛ ካልኩ ሞኝነት ነው ከቡድኑ ጋር ካለን እቅድ ጋር የማይሄድ ነው በሁሉም ቦታዎች ሁለት ተጨዋች ነው ያለን “ ብለዋል።

ለመልቀቅ ለተቃረበ ተጨዋች እንዴት እንደዛ ተብሎ ይነገራል መረጃው ብዙም ሚዛን የማይደፋ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
መድፈኞቹ ተከታታይ ድላቸውን አስመዘገቡ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከ አስቶን ቪላ ጋር ያደረገውን የሁለተኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ትሮሳርድ እና ቶማስ ፓርቴ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
“ እንደዛ ተጫውተን መሸነፋችን አበሳጭቶኛል “ ቴንሀግ 

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በዛሬው የቡድናቸው ሽንፈት መበሳጨታቸውን በመግለፅ የተቆጠሩባቸው ግቦች ቀላል እንደነበሩ ገልጸዋል።

“ ሊቆጠሩ የማይገባቸው ሁለት ቀላል ግቦች ተቆጥረውብናል " ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እንደ ቡድን የተሻለ ነገር ማሳየት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

የተመዘገበው ውጤት " የሚያበሳጭ ነው “ ሲሉ የገለፁት አሰልጣኙ በተለይ እንደዛ አብዛኛውን ጨዋታ ተቆጣጥረን መሸነፋችን ያበሳጫል ብለዋል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ቡናማዎቹ ቀጣዩን ዙር አልተቀላቀሉም !

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የወከለው ኢትዮጵያ ቡና ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ሳይችል ቀርቷል።

የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር የመልስ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከኬንያ ፖሊስ ጋር ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ከቀናት በፊት ኬንያ ላይ 0ለ0 የተለያዩት ቡናማዎቹ በድምር ውጤት 1ለ0 ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
በሁለተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ እና ሉዊስ ዲያዝ ማስቆጠር ችለዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከሰላሳ ሶስት አመታት በኋላ ተከታታይ ሁለት የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን ያሸነፉ የመጀመሪያው የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሆነዋል።

መሐመድ ሳላህ በአንፊልድ ባደረጋቸው 128 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች 128 የግብ አስተዋጽኦ ማድረግ ችሏል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ባርሴሎና ቪቶር ሮኪን በውሰት ሰጥቷል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ቪቶር ሮኪ ለላሊጋው ክለብ ሪያል ቤቲስ በውሰት መስጠቱን ይፋ ተደርጓል።

የ 19ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቪቶር ሮኪ ሪያል ቤቲስን ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ባለው የአንድ አመት የውስት ውል መቀላቀሉ ተገልጿል።

ሪያል ቤቲስ ሙሉ የተጫዋቹን ደሞዝ እንደሚሸፍኑ ሲገለፅ በቀጣይ የመግዛት አማራጭም እንዳላቸው ተነግሯል።

ቪቶር ሮኪ ባለፈው አመት 60 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ ዋጋ ወጥቶበት በረጅም ጊዜ ኮንትራት ከብራዚሉ አትሌቲኮ ፓራኔንስ ባርሴሎናን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ጁቬንቱስ በጄዶን ሳንቾ ውል ላይ እየሰራ ሲሆን የመግዛት ግዴታ ባለው የውሰት ውል ማስፈረም ይፈልጋል።

- Fabrzio Romano

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ሮናልዶ ጫማውን መቼ ይሰቀላል ?

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁን በሚጫወትበት አል ነስር ጫማውን ለመስቀል በማሰብ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ጫማውን ስለሚሰቅልበት ቀን የተጠየቀው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ “ በቅርቡ ይመስለኛል ከሁለት ወይም ሶስት አመት በኋላ እግርኳስ አቆማለሁ “ ብሏል።

በሰዑዲ ዓረቢያ እና በአል ነስር ቆይታው ደስተኛ መሆኑን ጨምሮ የገለፀው ሮናልዶ “ በአል ነስር ቤት ጫማዬን የምሰቅል ይመስለኛል “ በማለት ተናግሯል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ከፒኤስጂ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክስ አስነብቧል።

የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ዛሬ ወደ እንግሊዝ በማምራት ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል የሚያስችለውን የህክምና ምርመራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን 50 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እና ታይቶ የሚጨምር 10 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት እንደሚያስፈርሙት ተነግሯል።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን መሸጥ ይፈልጋል !

ሪያል ማድሪድ ስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ሴባዮስ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት መሸጥ እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ተጨዋቹ በክለቡ እንዲቆይ ጥረት እንደማያደርጉ እና ጥሩ የዝውውር ሒሳብ ከቀረበላቸው እንደሚሸጡት ዘ አትሌቲክስ ዘግቧል።

በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት በቂ የጨዋታ ጊዜ ያላገኘው ዳኒ ሴባዮስ የጨዋታ ጊዜን ለማግኘት ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ ከዚህ በፊት መዘገቡ አይዘነጋም።

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!
ጄሱስ ናቫስ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ በ 38ዓመቱ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

ጄሱስ ናቫስ ባለፉት አስራ አምስት አመታት ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት መስጠት ሲችል የአለም ዋንጫ ፣ አውሮፓ ዋንጫ እና ኔሽንስ ሊግ ያሸነፈ ብቸኛው ተጨዋች ነው።

ጄሱስ ናቫስ በብሔራዊ ቡድኑ ምን አሳካ ?

2️⃣ አውሮፓ ዋንጫ

1️⃣ አለም ዋንጫ

1️⃣ ኔሽንስ ሊግ

በዘመንቤት የተሻለ ኦዶችን እንዲሁም ዳጎስ ያለ ካሽ ባክ ያገኛሉ። www.zemenbet.com በመግባት ስፖርት ቡካችንን ይጎብኙ፤ አሸናፊነትን ያጣጥሙ!