✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
15.3K subscribers
226 photos
22 videos
51 files
444 links
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮╭━─━─━─
ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት @Zemaryan
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯╰━─━─━─
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ጥያቄ> creator ለማግኝት @kidanemiherat_bot
@yita21
@Binyam
https://youtu.be/Fz4JARE6-DI
Download Telegram
በዛሬው ዕለት ምእመናን ወደ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን /ግቢ ገብርኤል/ እንዳይገቡ ተከለከሉ።

የጸጥታና የደኅንነት ግብረ ኃይል ትናንት ምሽት ከንጋቱ 11:00 እስከ ረፋድ 4:00 ሰዓት ድረስ የተለያዩ የከተማዋ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ ተናግሮ ነበር።

የአጥቢያው ምእመናን ይህንን በማክበር ከሌሊት 10:00 ጀምሮ ወደ ደብሩ ቢሄዱም ከላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በማለት ፖሊሶች እንዳይገቡ ከልክለዋቸዋል።

የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ባጋራው መረጃም ምእመናን በሌሉበት ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተከናወነ ገልጿል።

@zemaryan
የይቅርታ ደብዳቤ


@zemaryan
@zemaryan
✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
የይቅርታ ደብዳቤ @zemaryan @zemaryan
ሰበር መረጃ!
አፈናው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ (ጋዜጠኛ እና ደራሲ) በጸጥታ ኃይሎች ታፍኖ ተወሰደ።

ዛሬ  ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ በሥራ ጉዳይ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ መካኒሳ አካባቢ ለጥያቄ እንፈልግሃለን የሚሉ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አፍነው ወስደውታል።

©ምንተ ንግበር

ዛሬ ምሽት ከ2፣30 ጀምሮ የሚተላለፍ ቃለ መጠይቅ ከብጹዕ አባታችን አቡነ አብርሐም ጋር ማድረጉን EOTC TV ዘግቧል።

#ኢንፈርህ_ሞተ
#ሞትን_አንፈራውም

“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2

ምዕመናን መረጃ ይደርሳቸውና ይነቁ ዘንድ ይሄን ሊንክ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አድርሱ ቀላል የሚመስል ግን ብዙ ጥቅም አለው አድርጉት።

በዚ ግዜ ለዚያልሆንን መቼ ልንታዘዝ ነው። 

#share #share #share 

@zemaryan
በኦርቶዶክሳዊ የጠበቆች ቡድን አማካኝነት የፌደራል ፖሊስ ዛሬ ችሎት ባቀረባቸው 12 ኦርቶዶክሳውያን ተጠርጣሪዎች ላይ ሰባቱ በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ።

የፌደራል ፖሊስ 'በሽብር ተግባር እና ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ፈጥረው ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ በሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናንን ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለችሎት ማቅረቡ ይታወሳል።

በወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ችግር ምክንያት በተቋቋመው  የጠበቆች ቡድን ዛሬ በተሰየመው አንድ ችሎት ብቻ 10 ጠበቆች መሟገታቸው ተገልጿል።

በእነዚህ የጠበቆች ቡድን ክርክር በመደረጉም ሰባት ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲለቀቁ ተደርጎል።
እንዲሁም መ/ር ምሕረተአብ አሰፋና ኪሩቤል አሰፋ ላይ የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ መቻሉን ተገልጿል።

በተመሳሳይ ክስ (የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ)  በሌላ መዝገብ  ፌቨን ዘሪሁን እና ብሩክታዊት ነብዩ እንዲሁም ፋሲል አግደው ላይ በአጠቃላይ  5 ሰዎች ላይ የ8 ቀን ጊዜ ቀጠሮ  መፈቀዱን ተነግሯል።

እንዲህ ዓይነት ትንኮሳዎች እየጨመሩ ሊመጡ ስለሚችል የሕግ ባለሙያዎች ሙያዊ አሥራታችሁን ለቤተ ክርስቲያን  ታበረክቱ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል ሲል የዘገበው አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው።
@zemaryan
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያዩ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ትናንት የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ከፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይተዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከቅዱስነታቸው ጋር ስለነበራቸው ውይይት አመስግነዋል::

@zemaryan
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መራር እውነት አባታችንን ስማቸው
ላናምነው ከልባችን ወቷል ስርአቱ።

@zemaryan
በሀገረ ሩሲያ አባቶቻችን ውይይቱን እየመሩ ነው። የሩሲያ ካህናትና ምእመናንም እኛን መስለው ድምፃችንን እየሰሙ፣ መከራችንን እየተካፈሉ ነው።
አስፈራርተው ወስደውኝ ነው

እንግዲህ ተመልከቱ ክርሰቲያኖች እሁድ እለት ወደ ቅድስት ቤ/ክ በይቅርታ የተመለሱት አባት ያን እለት ቪዲዮውን ያያችሁ አይታቹኋል።ዛሬ ደግሞ ወደ ሕገ ወጡ ሲኖዶስ በድጋሚ ተመልሰዋል።

@zemaryan
@zemaryan
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ቀጥታ ሥርጭት ከመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

https://www.youtube.com/live/wMgJaj5pn4o?feature=share

የEOTC TV YOUTUBE ቻናል SUBSCRIBE አድርጉት ሁላችሁም 1Million እናድርሰው
#ሰበር_ዜና

"ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡" ብፁዕ አቡነ አብርሃም

@zemaryan
ለ ሕጋዊ የሚድያ ተቋማት በሙሉ፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ያካበተቻቸውን መንፈሳዊ፣ ቁሳዊ፣ ታሪካዊ እና ኪናዊ ሀብቶቿን በተለያዩ የብዙኅን መገናኛ ተቋማት የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ጉልህ አስተዋጽኦ ስታበረክቱ መቆየታችሁ ይታወቃል።

ስለሆነም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከብዙኅን መገናኛ ድርጅቶች ጋር ተቀራርባ የምትሠራባቸው የተሻለ አሠራር መዘርጋት ትችል ዘንድ የብዙኋን መገናኛ ድርጅቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅና ተሰጥቷቸውና  ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ  ከቤተ ክርስቲያናችን የሚወጡ መረጃዎችን በኃላፊነት እና መርሕን ባከበረ መንገድ፤ ለተዛባ ትርጉም ሳይጋለጡ እንዲዘገቡ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሚዲያዎች መረጃዎችን በትክክል እንዲያደርሱ የግንኙነት መዋቅር መዘርጋት ይቻል ዘንድ የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

ስለሆነም ይህ ማሳሰቢያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የግል እና የመንግሥት ብዙኅን መገናኛ ተቋማት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥሪ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዐውደ ምሕረት እና የአደባባይ በዓላትን ለመዘገብ፤  ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየጊዜው የምትሰጣቸውን መግለጫዋች የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት፤ በየአብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ቅርሶችን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና በርካታ ሀብቶችን መሠረት ያደረገ የሚዲያ ሽፋን በመስጠትና  ልዩ ልዩ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመሥራት ወዘተ... የሚፈልግ ማንኛውም   የመንግሥትም ይኹን የግል ሚዲያዎች ከዛሬ የካቲት 9ቀን 2015 ዓ.ም እስከ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ  በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት  መምሪያ  በመገኘትና  የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት ምዝገባ እንድታካሂዱ እያሳሰብን አዲስ የሚመሠረት የሚዲያ ተቋምና ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ  ካልሆኑት  በስተቀር ማንኛውም  የሚዲያ ተቋም በእነዚህ ቀናት ተገኝቶ ምዝገባ በማከናወን ቤተ ክርስቲያናችን በምታዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ  ካልተካፈለ በምንም አይነት መንገድ  ለቅድስት ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት ጥያቄ ቢያቀርብ የማይስተናገድ መኾኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክጠቅላይ ቤተ ክህነት የህዝብ
ግንኙነት  መምሪያ
የካቲት 9 ቀን 2015


@zemaryan
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                †               


[ ሰበር መረጃ ! ]



ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ በከፊል !

@zemaryan
@zemaryan
         †               †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
24,300 ዶላር ደርሷል።

በመላው ዓለም የምትገኙ ቅድሚያ ለጋሾች እናተው ናችሁ!!

አገር ቤት ያለነው መልዕክቱን በማጋራት የተግባር ሰው እንኹን!

ብዙዎች በበጎ ይነሱ ዘንድ ስክሪን ሻት ላኩልን እናጋራለን!!

https://www.gofundme.com/f/eotc-charity-fundraiser-united-we-stand?utm_campaign=p_cf+share-flow-1&utm_content=undefined&utm_medium=copy_link&utm_source=customer&utm_term=undefined