✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
16.5K subscribers
226 photos
22 videos
51 files
444 links
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮╭━─━─━─
ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት @Zemaryan
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯╰━─━─━─
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት ጥያቄ> creator ለማግኝት @kidanemiherat_bot
@yita21
@Binyam
https://youtu.be/Fz4JARE6-DI
Download Telegram
​​♦️ምስጋናው ይቀጥል♦️

ምስጋናው ይቀጥል ዝማሬው ይቀጥል
እግዚአብሔር ስላለ ከያዘ የማይጥል
በምናየው ነገር በምንሰማው ወሬ
እንዳይቆም ምስጋና እንዳይቆም ዝማሬ
#አዝ
የሰማእታቱ ደም የፈሰሰው በምድር
አይተናል ሲያስቀጥል የክርስትናን ዘር
እንድናምን ብቻ መች ተጠራን እና
በእሳቱም መካከል ቅኔ አለን ምስጋና
#አዝ
መች ማጥፋት ይቻላል እሳትን በእሳት
አይቆምም ማህሌት ቅዳሴ ሰዓታት
ከሰማዩም በላይ ከሰማዩም በታች
ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ነገም አለች
#አዝ
የዓለም ጨው ሆነን በዓለም የበዛነው
እየተደበደብን እየተገፋን ነው
በገደሉን ጊዜ ቁጥራችን ይበዛል
ከሞትም በኃላ ሂወት ይቀጥላል
#አዝ
የተስፋይቱን ምድር ተነሱ እንወርሳለን
በመዝሙር በእልልታ ቅጥሩን እያፈረስን
የሰላዮቹን ቃል ሰምታችሁ አትፍሩ
በሃይማኖት ጽኑ በእምነታችሁ ኑሩ
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
​​#የሰላም_እናት

የሰላም እናት የመዳኒዓለም
እመቤታችን ማርያም
ግቢ ከቤታችችን ከልባችን
ውዳሴ አለን ለአንቺ ድንግል እናታችን

#አዝ
ፀንተን እንኖራለን ግቢ ከቤታችን
የያዕቆብ መሰላል ድንግል ድልድያችን
አማልጂን ከልጅሽ ይፈር ጠላታችን
ዳዊትም ነግሮናል አንቺ ነሽ ተስፋችን
የብርሃን እናቱ ያለበሺን ግርማ
ሞገስ ሆኖን ድንግል ወጣን ከጨለማ
ስለዚህ ማርያም ሆይ እናገንሻለን
ምልጃሽን ተማምነን ስምሽን እንጠራለን

#አዝ
ጠቢቡ እንዳለሽ ነይ እርግብዬ
እመቤቴ ማርያም አንቺው ነሽ ተስፋዬ
ፅንሱ የዘለለው ስምሽ ሲጠራ
ለካ ስላለ ነው ጌታ ከአንቺ ጋራ
ከፍ ከፍ ያለ ነው ክብርሽ ከፍጥረት
የጌታዬ እናት መሰረተ ህይወት
ትውልድ ይህን አምኖ ያመስግን አንቺን
አንቺ ነሽ ምክንያቱ ከሞት እንዲድን

#አዝ
እሙ ለማስያስ ድንግል መፅናኛዬ
የማህፀኑ ስግደት ሆኗል መማርያዬ
ህይወት ያለሽ ሰማይ የጌታ ዙፋኑ
ምልጃሽ ያው ነው ዛሬም አንቺን ለታመኑ
መላዕክት በመንጦላይት የሚያመሰግኗት
ክብሯ የገነነው እመቤታችን ናት
እፁብ ነው የድንግል እረዳትነቷ
የዳነ ይዘምር በአማላጅነቷ

#አዝ
አዳም ስለዳነ በማህፀንሽ ፍሬ
ብፅይት ይላል ፍጥረት ደርሷልና ዛሬ
እኔም እንደ ያሬድ እንደ ሊቁ አባቴ
ማርያም ማርያም ስልሽ ጠግባለሁ እናቴ
ክብርሽን ልናገር ቃላቶች ቢያጥሩኝ
ዝመምታን መርጬ እፁብ ነሽ አልኩኝ
አከብርሻለሁኝ በኤፍሬም ውዳሴ
ቆሜ በማለዳ በሕርያቆስ ቅዳሴ

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
ተስፋ ቆርጠን ነበር
ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#ተስፋ_ቆርጠን_ነበር

ተስፋ ቆርጠን ነበር ኤማሁስ የሄድነው
በግፍ ስለሞተ ይቤዠናል ያልነው
ስልሳውን ምእራፍ በሓዘን ተራመድን
የሚያቃጥል ፍቅሩን/ሞቱን እያሰብን/(2)

በመንገዳችን ላይ አንድ እንግዳ መጥቶ
ጠየቀን በብርቱ መሃላችን ገብቶ
አለም የሰማውን ባያውቀው ደነቀን
እውነቱን ገለጽነው በእምነት ተናገርን
#አዝ
በስራና በቃል ብርቱ ነብይ ነበር
በአይሁድ ተገድሎ አደረ መቃብር
ይህ ሁሉ ከሆነ ሶስተኛ ቀን ሆነው
በምኩራባችን ላይ መምህሩን ካጣነው
#አዝ
ዛሬ በማለዳ አዲስ ነገር ሰማን
በመቃብር የለም ተነስታል ጌታችን
ሴቶች አስገረሙን ስጋው የለም ሲሉ
መላእክቱም ታዩ ህያው ነው እያሉ
#አዝ
መጻህፍትን ገልጾ በሚነግረን ነገር
ልባችን በሚስጢር ይቀልጥብን ነበር
አይናችን ተይዞ እኛ መች አወቅነው
ቀኑ መሽታል እና በቤት እደር አልነው
#አዝ
እንጀራውን ቆርሶ በእጃችን ሲሰጠን
ባይናችን ላይ ያለው አዚሙ ለቀቀን
እንዳላዋቂ ሰው ከኛ ጋራ ያለው
የትንሳኤው ጌታ ለካስ እየሱስ ነው(፫)

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
አልረሳውም ያንን እለት
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#አልረሳውም_ያንን_ዕለት

አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/

ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
#አዝ
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ
ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
#አዝ
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
#አዝ
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ

#ሼር
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃 ══════════★═╝
Audio
#ቅዱስ_ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል(፫)
ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ

አንተ ስለሆንክ - - - ሚካኤል
የአምላክ ባለሟል - - - ሚካኤል
ልመናህ ፈጥኖ - - - ሚካኤል
ከአምላክ ያቀርባል - - - ሚካኤል
የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው(፪)
ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው (፪)
#አዝ
ደዌ የጸናበት - - - ሚካኤል
ባንተ ይድናል - - - -ሚካኤል
በአደባባይህ - - - ሚካኤል
ምስክር ሆኗል - - - ሚካኤል
ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ(፪)
በቃል ኪዳንህ ህይወቱ ዳነ (፪)
#አዝ
ከአምላክ ተሰጥቶህ - - - ሚካኤል
ክብርህ ያበራል - - - ሚካኤል
ለጎስቋላው ሰው - - - ሚካኤል
መጠጊያ ሆኗል - - - ሚካኤል
ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ(፪)
ለምኖ አግኝቷል ከአምላክ በስሙ(፪)
#አዝ
በብሉይ ኪዳን - - - ሚካኤል
ከአምላክ ተልከህ - - - ሚካኤል
ሕዝበ እስራኤልን - - - ሚካኤል
ነጻ ያወጣህ - - - ሚካኤል
በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ(፪)
በተአምራትህ ትፈውሳለህ(፪)

ሊቀ መዘምራን ዲ.ን.ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
''ዘማሪት_ህይወት_ተፈሪ''
|@Z_TEWODROS
መድኃኔአለም

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው

አላስብም ነበር አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
#አዝ
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
#አዝ
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ
#አዝ
እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ

....ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን 👇
╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ 👆 ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ