ዘገየ ዘኦርቶዶክስ
149 subscribers
323 photos
9 videos
19 files
36 links
የአማልክት አምላክ ቅድስት ሥላሴ ሆይ፦ ሁልጊዜም በሃይማኖት በዕምነት እና ምግባር እንድንበረታ ቅዱስ ፈቃዳችሁ ይኹንልን።

የጌቶች ጌታ፣ የነገሥታት ሁሉ ንጉስ፣ የአማልክት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእውነት የዓለም መድኃኒት ነኽ እኮን፤ ሁልጊዜም አንተን በማመን አጽናን፡፡

እመቤታችን ስለ ፍቅርሽ የምንቆምበትን ቅዱስ ፍቅርሽ እንደ ትናንቱ ዛሬም ይብዛልን።
@yeaskulij
ለመንፈሳዊ ጥያቄ
Download Telegram
የጋስጫ መጽሐፍት መደብር!

ጋስጫ
የንባብ ጥም መቊረጫ
የጸሐፊያን እና የአንባቢያን ተቀዳሚ ምርጫ

እኛጋ መጥተው የሚያጡት መጽሐፍ የለም ይሉናል። የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጻችንንም ይከታተሉ....

አዲስ አበባ፣ አምስት ኪሎ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ጋር፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ፊት ለፊት፣
ወይም በስልክ ቁጥር 0910657637 ይደውሉ።

ያንብቡ እናንብብ!

የፌስቡክ ገጻችን

https://www.facebook.com/gasichabooks/

ሲሆን...

በቴሌግራም ለመሳተፍ ደግሞ

https://t.me/gasichabooks

ይቀላቀሉን
ከጾም የሚገኘው ጥቅም...
©
ከጾም የሚገኘው ጥቅም...
©

"ብዙ ሰዎች አንዳቸው ለሌላቸው 'የጾሙ ግማሽ አለፈ፣ ግማሹን ጾም ፈጽመናል' ሲባባሉ እመለከታለሁ። እኔ ግን እንዲህ ያሉት ሰዎች የጾሙ ግማሽ በማለቁ በዚህ እንዳይደሰቱ እመክራቸዋለሁ። ከዚህ ይልቅ በጾማቸው የኃጢአታቸው ግማሽ ተወግዶ ስለ መሆኑ እንዲያስቡና በእርግጥ በጾማቸው እንደዚህ ዓይነት ጥቅም አግኝተው ከሆነ ያን ጊዜ ቢደሰቱ መልካም ይሆናል። ልናስብበት የሚገባው ነገር ይህ ነውና፤ ጾሙን ስንጨርስ ልክ ስንጀምር እንደ ነበርነው ዓይነት ሰዎች ሆነን ሳይሆን ከኃጢአታችን የነጻን ሰዎች ሆነን እንድንጨርሰው መሆንን ነው። ...የክረምት ጠቀሜታው የበለጠ የሚታወቀው ወቅቱ ካለፈ በኋላ ነውና። ያን ጊዜ የአበባዎች ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ የዛፎች መለምለም፣ እነዚህ ሁሉ በመታየታቸውና በመውጣታቸው ከክረምቱ ያገኙትን ጠቀሜታ በግልጽ ይናገራሉ። በእኛም እንዲሁ ይሁን። በጾም ወራት ያገኘነው መንፈሳዊ ጥቅም ጾሙ ካለፈ በኋላ በእኛ ላይ በሚያፈራው መልካም ፍሬ ጠቀሜታው ግልጽ ሆኖ እንዲታይ ይሁን። እንዲህ ካደረግን ጾሙ እንደገና ተመልሶ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን። ...ከጾም የሚገኘውን ጥቅም በትክክል የተረዳነውና በጾማችን ወቅት ያንን ጠቀሜታ የምንቀምሰው ሆነን ቢሆን ኖሮ ጾሙ በየቀኑ እንዲመጣ በተመኘን ነበር። እንዲህ ሆኖም የጾሙን መምጣት መናፈቃችንንና ለጾም ያለንን ጉጉትና ናፍቆት መቀነስ የለብንም፣ እርሱን በማሰብ መፍራትና መጨነቅም አይኖርብንም።"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ትምህርት በእንተ ምክንያተ ሐውልታት 18፣ ቁ. 1-2)
"አሳ ያለ ውሃ መዋኘት እንደማይችል፣ ወፍ ያለ አየር መብረር እንደማትችል ሁሉ ክርስቲያንም አንዲት እርምጃ እንኳ ያለ ክርስቶስ መሻሻል አይችልም።"

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
የቅድስት ሥላሴ ድንቅ ተአምር!
(ለብዙዎች እንዲደርስ #ሼር ይደረግ)
©
በሐምሌ 7 ቀን 2013 ዓም በ4 ኪሎ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዲስ አበባ ታቦቱ ቆሞ የተሰጠ ምስክርነት!

መስካሪዋ እናት ናቸው። የሁለት ልጆች እናት። ሁለተኛው ልጃቸው የአራት አመት ልጅ ሆኖ በድንገት ራሴን ወጋኝ አይኔንም አቃጠለኝ ብሎ አለቀሰ።ልጁ ህመሙ ጸናበት በአራተኛው ቀን ሁለት አይኖቹ ታወሩ። ሁለት ጆሮቹም ደንቆሩ። ከዚህ ይሰውረን! ጤነኛ ልጅ ወልዶ በአንድ ጊዜ እንዲህ አይነት ችግር ውስጥ መውደቅ ያሳዝናል። አሜሪካን አገር የሚኖረው የዳንኤል አባት ፍጹም ሀዘን እና ጭንቀት ውስጥ ወደቀ። እናት ሥራቸውን ለቀቁ በርካታ ገንዘብ እየተከፈለ የዳንኤል ህክምናው በየአቅጣጫው ቀጠለ። አልተሳካም። ወላጅ እናት ሕጻን ዳንኤልን ይዘው በየጠበሉ ጉዞ ሆነ። አራት አመት ሙሉ በጸሎት ታገሉ በጠበል ታገሉ በእምነት ታገሉ። ለአራት አመታት ሙሉ ልጅ ዳንኤል አይኑ እንደታወረ ጆሮውም መስማት እንደተሳነው ኑሮ ቀጠለ። የአባት እና እናት ጸሎትና ተማጽኖ ቀጠለ። ከትላንት ወዲያ ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓም እናት ልጅ ዳንኤልን በመኪናቸው ይዘው አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጡ። ቅዳሴ የተቀደሰበትን እምነት ግቢው ውስጥ ባለው የቅድስት ሥላሴ ጠበል በጥብጠው ልጃቸው ዳንኤልን በሥመ ሥላሴ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ብለው የታወሩ አይኖቹን በእምነቱ ለቀለቋቸው። ሁለት ጆሮቹን እምነቱን ለቀለቋቸው። እንዲህ ብለውም ተማጸኑ፦ አጋዕዝተ አለም ሥላሴ እርዱኝ ልጄ ቢያንስ ድምጼን ስምቶ እንድንግባባ ባይሆን ጆሮውን እንኳን ክፈቱልኝ ብለው ተማጸኑ። ከዚያም ልጃቸውን ይዘው መኪናቸውን እየነዱ ወደቤታቸው ሄዱ።ሌሊቱን ሐምሌ 6 ቀን 2013 ከሌሉቱ 7:00 ሰዓት ላይ ህጻን ዳንኤል በአልጋው ሆኖ እናቱን ተጣራ። ምነው ልጄ ደሞ አዕምሮውን ታመመብኝ ይሆን በሌሊት የሚጠራኝ ብለው ወደ ህጻኑ ሄዱ።እማዬ አይታይሽም? አይታይሽም? አይታይሽም? ብሎ ጮኸ ህጻን ዳንኤል። የሚሰማኝ ይመስል ምንድነው ሥለው ልጄ ዳንኤል ድምጼን ሰማኝ! እማ እማ አለ.....ጆሮው ተከፍቶ ድምጼን ሰምቶ! እይው እይው... ያንን መስቀል አለኝ።ለእኔ የሚታየኝ ነገር አልነበረም ፈዝዤ ቀረሁ። እይው የሚያበራ መስቀል እና መስቀሉ ላይ ያሉትን ሦስት ትልልቅ ሰዎች እያቸው እያቸው እያቸው አለኝ። እነዚህ ሦስት ሰዎች መስቀሉ ላይ ሆነው አይኔን አበሩልኝ ጆሮዬንም አዳኑኝ ብሎ ተናገረ።እናት እ እ እ... ልጄ..ድምጼን እየሰማህ ነው? እእእ እኔ እኔ እታይሃለሁ አዎ አዎ እማዬ።እናት እንዲህ አሉ...ልብስ ደረብኩ እና ምን አይነት ልብስ ነው የለበስኩት? አልኩት ልጄን እናቴ ነጭ እኮ ነው ብሎ በትክክል ነገረኝ። እናትና ልጅ ተቃቅፈው በለቅሶ ተዋጡ። ከአራት አመታት በኋላ ልጅ የእናቱን ድምጽ ሰማ! የእናቱን ፊት አየ..... ወዲያው እናት እና ልጅ ልብሳቸውን ለብሰው ሌሊቱን እናት መኪናቸውን እየነዱ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጡ። ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ልጅ የቅድስት ሥላሴን ስዕል አየ። እማዬ እነዚህ ናቸው እኮ ማታ መስቀሉ ላይ ያየዋቸው! እነዚህ ናቸው እኮ ያዳኑኝ ብሎ በገሀድ ተናገረ። እልልታ እና ለቅሶ ቀጠለ.... ምሥክርነቱ ተሰጠ። ደግሞ ከ40 ደቂቃ በፊት ታቦቱ ዞሮ እንደቆመ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደቆሙ እኛ ሁላችን እንደቆምን ምስክርነቱ በገሃድ ለህዝበ ክርስቲያን ታወጀ። አይኖቻቸው በእንባ የረጠቡ አዕላፍ ምዕመናን በማያቋርጥ እልልታ ግቢውን አናጉት። እልልልልልልልልልልልል እልልልልልልልልልልልልል እልልልልልልልልልልል........የደስታ እንባ ከሁላችንም አይኖች ፈሰሰ....ምን ልበላችሁ!?! እባካችሁ ወገኖቼ በእምነታችሁ ጽኑ! ምሥጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ! ይህንን ተአምር ታቦቱ ፊት ቆሜ እንደሰማሁ ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ላይ ጻፍኩት። የሥላሴ ቤተሰቦች ደስ ይላችሁ ዘንድም ለሁላችሁ አጋራኋችሁ። ሥላሴን አመስግኑ!

Mebatsion

ትክክለኛው የቴሌግራም ቻናላችን ነው አሁኑኑ ይቀላቀሉ.... https://telegram.me/theholyfathers
አባቶች "የሚሰጥ ለእግዚአብሔር ያበድራል" እንዲሉ ይኽቺን የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በተቻለን አቅም የቻልነውን እንርዳ።
አባቶች "የሚሰጥ ለእግዚአብሔር ያበድራል" እንዲሉ ይኽቺን የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በተቻለን አቅም የቻልነውን እንርዳ። ወደ ሥፍራው አሁን ካለሁበት የ1 ሰዓት የመኪና ጉዞና የ1 ሰዓት የእግር ጉዞ ይፈጃል፣ ቦታው በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ይገኛል። በብዛት ምእመናንን በመሰብሰብ እና የበኩላችንን ለማድረግ እንጥራለን።


በታህሳስ 24/2013 የአቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓልን ለማክበር በሄድንበት አካባቢው ማብራት ባለመኖሩ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ሊጠቅማቸው የሚችል solar እና ሌሎች ነገሮች ያስፈልጋቸዋል። በዚህ ፍልሰታ ሰሞንም ቅዳሴ እንደሚቀደስም እንጃ! በሥፍራው ሄደን እንድንረዳ ሁላችሁም ተሳተፉ።

ቤተክርስቲያኗን በቅርቡ ከዚህች ትንሽ ከፍ በምትል ቤት ለማደስም ታስቧል፣ ያን ጊዜም የአቅማችንን እናደርጋለን። የአቅማችሁን ለማድረግ የምትፈልጉ እህት ወንድሞቼ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000390755687
"ለዘኢይሰቲ ወይነ ምንትኑ ሕይወቱ። ሲራክ ይቤ እስመ ትፍሥሕተ ልብ ውእቱ። ለተአምርኪ ማርያም ዘይጥዕም እምነ ዝንቱ። ወስብሐተ ፍቅርኪ ጽጌ ዘያስተፌሥሕ ሥነ ርእየቱ። ለዘያስተሐቅር በመንኖ ሕይወት አልቦቱ።" አባ ጽጌ ድንግል
ያድምጡት!
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል
ዓውደ ወራዙት
"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል"

ጸሐፊ በረከት ንጉሴ
ንባብ በረከት ንጉሴ


የወጣቶች ክርስቲያናዊ ህይወት
ዓውደ ወራዙት
ይቀላቀላሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Awdewerazut
@Awdewerazut
@Awdewerazut
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ለማንኛውም አስተያየት👉 @Bekila123
1,ሰው ከመጠመቁ በፊት ሐይማኖቱ ምንድን ነው ?
2,ሰው ሲፈጠር ሐይማኖቱ ምንድን ነው?
ሁላችንም ከመጠመቃችን በፊት ሐይማኖታችን ኦርቶዶክስ ነው።
ይህን ያልኩት እንዲሁ በደፈናው አይደለም ምክንያት አለኝ።
# ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው ትርጉሙ
እውነተኛ ፣ ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት ማለት ነው።
ማስረጃ አለኝ ኤር 6÷16 " እግዚአብሔር እንዲህ ይላል
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ
መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርስዋም ላይ ሒዱ
ለነፍሳችሁም መድሐኒት ታገኛላቹ" ይላል መንገድ ማለት
ሐይማኖት ማለት ነው ማስረጃ ማቴ 7÷13 " በጠባቢቱ
በር ግቡ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር ሰፊ መንገድም አለችና
ወደ እርስዋ የሚገቡ ብዙዎች ናቸው። ወደ ሕይወት
የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገድዋም ቀጭን ናትና
የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው"
ኤርሚያስ የቀደመችውን መንገድ ጠይቁ አለ በእርስዋ ለይም
ተመላለሱ አለ
ክርስቶስም መጣ ወደ ጠበበው ደጅ ግቡ አለ በጠበበው
መንገድ ላይ ወደ ሕይወት የሚወስደው እርሱ ነው ግቡ አለ
የጠበበው መንገድ የቱ ነው ብለህ ስትጠይቅ መልሱ
ኦ....ር...ቶ...ዶ...ክ...ስ ነው ጥበቱንም ፆም ፣ ስግደት ፣ ቀኖና ፣ ንስሐ ፣ ስጋ ወደሙን መቀበል ፣
ቆሞ ማስቀደስ ፣ ፀበል መጠጣት ፣ መጠመቅ ........ እነዚህ
ሁሉ የኦርቶዶክስን ደጅ ያጠቡታል።
ሰፊው መንገድስ ካላችሁኝ
እንደመንገዱ ስፋት ማንም የሚገባበትና የሚወጣበት
የማይፆምበት፤ የማይሰገድበት የክርስቶስ ወዳጅ የሆኑ ቅዱሳንና
ቅዱሳት የማይከበሩበት የክርስቶስ ስጋና ደሙ የማይፈተትበት
ለአለባበስ፤ለአነጋገር እና ለአምልኮ ስርአት የሌላቸው ማንም ሰው
እንደልብ የሚቦርቅበት የሚጨፍርበት............በአጠቃላይ
ሉጋም የሌለበት መንገድ ሁሉ ሰፊው መንገድ ነው እላለው።
ኦርቶዶክስ ግን ሉጋም አላት ይህም በፆም፦
ገና ፆም ይገባል ነፍሳችንን እያበረታን ስጋችንን እናደክማለን
ከዚያም ይፈታል። ስጋ ሊበረታ ሲል እንደገና
የነነዌ ፆም ይገባል ስጋችንን አድክመን ነፍሳችን እናበረታለን
ይፈታል ስጋ አረፍኩ ሲል አብይ ፆም ይገባና ስጋችን 0
ይሆናል ነፍሳችን ትበረታለች ስጋ ሲዝል 50 ቀን ይፈልታ
50 ቀን ስጋችን ተደሰትኩ ሲል ሰኔ ፆም ይገልባል ስጋ
ይደክማል እንዲ እንዲያ እያልን ስጋን እያደከምን ነፍሳችንን
ወደ ገ....ነ....ት ስለዛ ጠባቧና እውነተኛዋ መንገድ
ኦ......ር....ቶ....ዶ...ክ..ስ.....ናት
ከአለም ሕዝብ እኛ ብቻ ልንፀድቅ ነው አላችሁ ?
አዎና በደንብ ከአለም ሕዝብ እኮ 8 ሰው ብቻ ነው የዳነው በኖህ
መርከብ እኛ ከ 8 አንበልጥም እንዴ
በእርስዋ ላይ ቁሙ ብዙ ሰው አይፈልጋትም አለ ክርስቶስ
ስማችን ኦርቶዶክስ ነው ክርስቲያን ስማችን አልነበረም
ያወጣልን ጠላት ነው
የሐዋ ሥራ 11÷26 "ደቀመዛሙርቱም መጀመሪያ በአንፆኪያ
ክርስቲያን ተብለው ተጠሩ"
የክርስቶስ ተከታዮች ናቸውና በክርስቶስ አማካይነት
ክርስቲያን ሲሏቸው እነርሱም "ይህ ስም ተስማምቶናል" አሉ
ሞትን አሸንፎ የተነሳው እርሱ ስለሆነ በእርሱ ስም መጠራት ፈለጉ
በመጠራታቸውም አላፈሩም ህዝቡም ለማስታወስ እንዲመቻቸው
በክርስቶስ አያያዙና ክርስቲያን አሏቸው ከዚያም ክርስቲያን መባል
መጣ
በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛቹ የሚባለውም ለዚሁ ነው።
ሥማችን ኦርቶዶክስ ነበር የቀደመችዋ ቀጥተኛዋ መንገድ
ይቺ ቀጥተኛ መንገድ ከማን መጣች ኦርቶዶክስ የማን ሐይማኖት ናት ካልችሁኝ ደግሞ
ከአዳም ጀምሮ የመጣው ሐይማኖት ኦርቶዶክስ ነው
እላለው እንዴት አትሉኝም?
ቆያ ላብራራላችሁ። ይኸውልህ ፦የአዳም ሐይማኖት ተጠምቆ መፈጠር ነው።
ማስረጃው
ዘፍ 1÷1 "በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ
ምድርም ባዶ ነበረች አትታይም ነበር የተዘጋጀችም አልነበረችም
ጨለማም በውሃ ላይ ነበር የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃ ላይ
ይንሳፈፍ ነበር" ይላል
ከውሃ ውስጥ የብሱ ይገለጥ ብሎ ምድርን ፈጠረ ( አፈርን )
ማለት ነው ከአፈር አዳምን ፈጠረ ከአዳም ሔዋንን
ፈጠረ ከሔዋንና ከአዳም እኛ ተፈጠርን ሔዋን ከአዳም አዳም ከአፈር አፈር ከውሀ ያ ውሀ የእግዚአብሔር
መንፈስ አለበት
የአዳም አባት አፈር አያቱ ውሃ ያ ውሃ
የእግዚአብሔር መንፈስ አለበት ስለዚያ አዳም በጥንት አያቱ
ተጠምቆ የተፈጠረው የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ
ተዘፍቆ ተፈጠረ ።
አይደለም አዳምና ሔዋን የሰው ዘር ቀርቶ ሰማይና ምድር ጭምር በውሃ ተጠምቀው ነው የተፈጠሩት
የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ። ምነው?ገረማችሁ? ልንገራችሁ
2ኛ ጴጥ 3÷5 ምን ይላል መሰላችሁ " ነገር ግን እነዚያ ሰዎች
ሰማያት ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው
እንደሚኖሩ መሬትም በውሃ መካከልና በውሃ እንደተሰራች ሆን
ብለው ይክዳሉ" በዚያን ጊዜ የነበረው አለም በውሃ ሰጥሞ ጠፉ።
በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች ለምን ጠፉ? ቢባል ሰማይና ምድር ከውሃ እንደተፈጠሩ ሆን ብለው ይክዳሉ ስለዚህ ጠፉ
በውሃው ጥምቀት ያመኑ ኖህና ቤተሰቦቹ ዳኑ በውሃው
ጥምቀት ያላመኑ የኖህ ዘመን ሕዝቦች ጠፉ
በውሃው ጥምቀት ያመኑት እስራኤል ዘስጋ ዳኑ በውሃው
ጥምቀት ያላመኑት ፈርኦንና ሰራዊቱ ጠፉ
1ኛ ቆሮ 10÷1 መስረጃ
"ወንድሞቻችን ሆይ አባቶቻችን ደመና እንደጋረዳቸው ሁሉም
በባህር መካከል አልፈው እንደሔዱ ልታውቁ እወዳለሁ ሁሉንም
ሙሴ
በደመናና በባህር አጠመቃቸው "
ስለዚህ አይደለም አዳምና ሔዋን ሰማይና ምድርም
የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ ተጠምቀው ነው የተፈጠሩት
የአዳም ሐይማኖት የእግዚአብሔር መንፈስ ካለበት ውሃ
ተጠምቆ መፈጠር ነው ።
ያ ውሃ በሰይጣን ተበላሽቶ ተቋረጠ
ከዛም ክርስቶስ መጣ ለ ኒቆዲሞስ እንዲህ አለው
ዮሐ 3÷5 " እውነት እውነት እልሀለሁ ዳግመኛ ከውሃና
ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት
ሊገባ አይችልም" አለው።
ያ የድሮ ውሃ ተበላሽቶ ክርስቶስ መጣና ያንን ውሃ ቀደሰው
ስለዚህ ድጋሚ አዳም ከተወለደበት ውሃ ተወለዱ ከዛ ውሃ
ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስትን አያይምምምምም

ስለዚህ አሁን ኦርቶዶክሶች ስንጠመቅ በፊት አዳም
ከተወለደበት ውሃ ተወልደናልና የእግዚአብሔርን የልጅነት
ፀጋ ተቀብለን ወደ መንግስተ ሰማያት እንገባለንንንንንንን።
የተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግስት ይወርሳል
ያልተጠመቀ ደግሞ አይወርስም ይህንንንም ጌታ ነው ያለው እኛ
የተዋህዶ ልጆች የተጠመቅን ነን መንግስቱ የኛ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም የተጠመቅን ብቻ ነው አርባ አራት ነጥብ።
የተጠመቁ ብቻቻቻቻቻቻ።።።።። ክብር ለእግዚአብሔር ከእናቱ
ከድንግል ማርያምና ከፃድቃን ከሰማእታት ከቅዱሳን መላእክት ጋር
ይሁንልን አሜን፫
# ኦርቶዶክስ_ሃይማኖት_ለዘለአለም!!!

@timhirte_tewahido

ለተዋህዶ ልጆች ሸር ያድርጉ
ግእዝ ቋንቋ በእፀ ሳቤቅ ቲዩብ።።ተከታታይነት ያለው በአጭር ጊዜ ግእዝ መናገር በሚያስችል መልኩ የቀረበ! ።።ክፍል...
https://youtube.com/watch?v=b4KsqEZ8RiM&feature=share
Hey, I have been using a site and earned $66 today! You get paid for testing apps, voicing opinion and posting on social media. Its just that easy. Sign up with my link for a $50 bonus instantly! https://socialrebel.co-ga4.xyz/ref/BFmhb3Pd