ሕይወት ስለሚሰጠው /ስለ ሆነውም/ ስል የክርስቶስ ሥጋና ደም ሳይሆን ለሥጋችን ስለሚታረደው የእንስሳት ሥጋና ለልማዳችን ስለሚፈሰው ደም ለጉዳያቸው ብለው ጉዳያችን ከሚያደርጉብን 'መምህራን' እንጠበቅ።
የራበንን የክርስቶስ ሥጋና ደም ትተው በሰለቻቸው የእንስሳት ሥጋና ደም "ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማያውቅ (ሰንበት ብለው 'ሰበር ትንታኔ' ማለታቸው አይቀርም) እያሉ business ይሠሩብናል!

#አነቃቂዎች_የማይደፍሩት_ተስፋ
የይዞታ ካርታን'ኳ የሌለውን፣ ከተመሠረተ ከእኔ ዕድሜ በብዙ የሚያንሰውን ቤተ ክርስቲያን እያስተዳደሩ፤ የአጥቢያው ገሚሱ ምእመን በሌላ ቤተ እምነት ተወስዶ ገሚሱ ደግሞ በጎሳና በፖለቲካ መንጋነት ተጠምዶ በተገኘው መድረክ ሁሉ "የታላቁ፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል አስተዳዳሪና የመንጋው ሁሉ ጠባቂ" የሚሉ ደጅ ጠኝዎችና ደጅ አጥኚዎች ተይዞ ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ ለማሻገር ማሰብ አነቃቂዎች ሳይቀር የማይደፍሩት ተስፋ ይመስለኛል።

ስሕተት ስሕተት እንዳይባል "አትፍረድ" እያላችሁ በማሸማቀቅ ስሕተት እንዲጎመራ የምታደርጉ በአትፍረድ ስም የምትፈርዱ ትሑታን ፈራጆችች ሆይ "ፈራጅ ነህ/ሽ" እያላችሁ አትፍረዱ!!!
◈በሰፈር የሚያስብ ኦርቶዶክስ ጸረ ኦርቶዶክስ ነው።
◍የኦርቶዶክሳውያን የማሰቢያ ምንጫችን፦ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን የተገለጠው አስተሳስብ ነው።
◈ኦርቶዶክሳዊነት፦በሃይማኖት፣በጥምቀት፣በማኅተመ ሜሮን፣በቅዱስ ቁርባን፣በኅብረተ ቤተ ክርስቲያን፣በሐዋርያዊነት፣በቅዱስ ምግባር የተመሠረተ ቅዱስ ሕይወት ነው።
◈በዚህ ቅዱስ ሕይወት የወይን ግንዱ ክርስቶስ ሲሆን ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን የወይኑ ግንዱ ቅርንጫፎች ነን።
የኅብረቱ ራስ ክርስቶስ ሲሆን ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስ ኅዋሶች ነን።
◈ከዚህ ርቱዕ አስተሳስብ ውጪ ወጥቶ፦በሰፈር፣በቋንቋ፣በቡድን፣በወንዝ፣በሥሁት ርዕዮተ ዓለም..የሚያስብ ሰው ጸረ ኦርቶዶክስ ነው።
◈ኦርቶዶክሳውያንን በሰፈር የሚከፋፍሉ ሁሉ ኦርቶዶክሶች አይደሉም ጸረ ኦርቶዶክሶች ናቸው።
◈ያንድ ክርስቲያን ደስታው ደስታችን ነው ኀዘኑም ኀዘናችን ነው።አባታችን ቅዱስ ጳውሎስ"ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ ከሚያለቅሱም ጋራ አልቅሱ።"ሮሜ.፲፪፥፲፭ብሎ እንዳስተማረን።
◈"እንደ አንድ ልብ ተናጋሪ እንደ አንድ ቃል መካሪ"ሁነን እንድንኖር ወደ ወንጌል ተጠርተናል።፩.ቆሮ.፩፥፲
◈በተለይም በዚህ የመከራ ወቅት በኦርቶዶክሳውያን ላይ ልዩነትን የሚሰብክ፣በሰፈር የሚያስብ ሰው ለኦርቶዶክሳውያን ጥፋት ተባባሪ አካል ነው።
◈ኅብረታችንን ረስተን ሳናውቀው ጸረ ኦርቶዶክስ እንዳንሆን እንጠንቀቅ።
የኔታ ገብረ መድኅን እንየው

👏2
#የመርከባችሁ_ጭነት_አቅልሉ
አስፈላጊ ሲሆን እግዚአብሔር የማያስፈልጉ ቁሳዊና ምድራዊ ኮተቶች እንድታስወግድ በ ”የሕይወት መርከብህ” ላይ ከፍተኛ ዓውሎ ነፋስ ወይም ማዕበል ሊያስነሳ ይችላል። የሕይወትህ መርከብ ምናልባትም ራስን የማጽደቅ መንፈስ ተጭኗት ይሆናል፤ ወይም ከፍተኛ ትዕቢት፣ አልያም ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ዓለምን መውደድ ተጭኗት ሊሆን ስለምችል ማዕበሉ ሲመታት ትነዋወጻለች።
ወንድሞቼ የመርከባችሁ ጭነት አቅልሉ። ምናልባትም እግዚአብሔር መርከባችን እንድትናጥ የሚያደርገው ራሳችን እንደ ፍጹም ጻዲቅ የመቁጠር፣ የትዕቢት፣ የልበ ደንዳናነት፣ የከንቱነት ሻንጣችን አውጥተን እንዲንወረውር ፈልጎ ይሆናል። የሚያሰናክሏችሁ ሁሉ አውጥታችሁ ጣሉ። በልቡናችሁ ከእግዚአብሔር ፍቅር ውጭ ምንም አታስቀሩ።
በእናንተ ላይ ይህ መንገድ ካልሠራ እግዚአብሔር እንዲውጣችሁ ዓሣ አንበሪን ይልከዋል። እናንተም "እግዚአብሔርም ሆይ ዓሣ አንበሪውንም ሆነ ዓውሎ ነፋሱ መሸከም የሚችል አቅም የለኝም። ትንሽ ቅጣት ወደ አንተ ይመራኛል። እጆችህ በእኔ ላይ ይሁኑ፣ የምሕረት እጆችህ እንጂ በትርህስ በእኔ ላይ አይሁን" እያላችሁ ወደ እግዚአብሔር ታለቅሳላችሁ።
👉 አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ መጽሐፈ ዮናስ ካብራሩበት የተወሰደ

ኦርቶዶክስንና ኦርቶዶክሳዊያንን የማጥቅያ ሌላኛው ክንፍ!
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለማጥቃት በርካታ ጦሮች ተወርውረዋል። የተወረወሩትም ጦሮች የተለያዩ አካላቶቿ ክፉኛ አቁስለዋታል፤ እያቆሰሏትም ነው። ልጆቿ በተከፋፈልን ልክ እነርሱ ጦራቸውን እያበዙ ሄደዋል።
ባለፉት 50 ዓመታት ሀገራችን በመምራት ያሉ አካላት በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ከአድኃሪ ጋር የመደቡና ለብልጽግና አትሆንም ባሉ በሌላ በኩል ደግሞ ጥንካሬዋና የጥንካሬ ምንጭነቷ የጣልያን ያክል ስለ ሚፈሯት "Demoblizing orthodoxy" የፖለቲካ መርሐቸው ባደረጉ አካላት ነው። ለዚህም በቤተ ክርስቲያኗ ሐሰተኛ ትርክቶች በመፈብረክ ከየትኛውም ሀገራዊ ጸጋዎች ባይተዋር እንድትሆን ጥረት ተደርጓል።
በመሆኑም በማሕበራዊ ዘርፍ የባህል አፋኝና የአንድ ቋንቋ ሰባኪ፣ በኢኮኖሚው ተስፋፊና አስገባሪ፣ በፖለቲካው ከነገሥታት ጋር ተጠግታ የጨቆነች ወይም ጨቋኝ ነገሥታትን የደገፈች፣ በሃይማኖት ሌሎች ሃይማኖቶች እንዲኖሩ የማትፈልግ ወዘተ ተደርጋ እንዲትሳል ብዙ ተሰርቶባታል።
ለዚህም በፖለቲካ የሚዘወረው የአካዳሚክ ዘርፉ ሳይቀር በተለጣፊ ምሁራን በጥናታዊ ጽሑፍ ስም አስቻይነቱ አሳይቷል።
ሁኔታው የፈቀደላቸው ሃይማኖት ሳይሆን በሃይማኖት ስም የሚገኘው ጥቅም የሚገዳቸው አንዳንድ ጠብደል ባለ የግል ቸርቾች ፖለቲካው የጀርባ አጥንት ሆኖላቸው ያለ ስሟ ስም ከመስጠት፤ የማታስተምረውን እንደ ምታስተምር፣ የምታስተምረውን እንደ ማታስተምር አድርገው በሐስት ከመክሰስ አልፈው በአደባባይ ሲዘልፏት፣ የእሷ የሆኑትን "ሲወርሱ"፣ ቅርሶቿን ሲዘርፉ ኖረዋል።
የሰሞኑ የአሕመዲን ጀበልና የመሰሎቹ መንገድም ቤተ ክርስቲያንን የማጥቅያ የተለመደ ሌላኛው ክንፍ እንጂ አዲስ ነገር አይደለም። እንጂማ "Demoblizing orthodoxy Mobilizing/Restoring/ Islam" መርሑ ባደረገ፣ በዚህም ቤተ ክርስቲያን በታጠቁ ካድሬዎች እንድትመራ አድርጎ መንበረ ሰላማን አምጦ በወለደ፣ የክልሉ ወጣቶች የስልጣን መገበርያው ያደረገ፣ ለበርካታ ባዕድ ልማዶች የዳረገና ለሃይማኖት አልባነት አሳልፎ በሚሰጥ ፓርቲ በምትመራ ክልል ላይ "ክርስቲያናው አፓርታይድ" ይኖራል ብለው ስለ ሚያምኑ አይደለም።
የከፋው ደግሞ ለዚህ የበቃነው የቤተ ክርስቲያ መዋቅር ከሃይማኖት ይልቅ በስልጣንና ገንዘብ ፍትወት ሰክረው ለገዳዮች አስቻይ ሁኔታ በሚፈጥሩ የውስጥ አርበኞች መዘወሩ ነው።

የጸለይነውን ሁሉ አለ መስማቱ የእግዚአብሔር መሐሪነቱ!
እግዚአብሔር ያዘጋጀው ሁሉ ያለ ጥርጥር ለመልካም ነው። ዮናስን የከለለው ጥላው መልካም እንደሆነ ሁሉ ፀሐይ ዮናስን መምታቷም እንዲሁ ለመልካም ነው። ሥጋ ሊዝል ቢችልም መንፈስን ያነቃቃልና ለመልካም ነው። ምንም እንኳ ዮናስ ክፉኛ ቢጨነቅም፣ ነብሱ ተረብሻ ሞት እስከ መመኘት ቢደርስም ይህ ሁሉ ጭንቀትና መረበሽ መንፈሱን ለመፈወስና ልቡናው ለማንጻት የእግዚአብሔር ዓላማ በመሆኑ ለመልካም ነው።
እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ለነፍሳችንም ለሥጋችንም በጊዜአዊነት የሚረብሸን ነገርም ቢሆን ለድኅነታችን የትኛውም መንገድ ይጠቀማል። በዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ዓላማ ዮናስ በራሱ ቁሳዊ ፍላጎት ውስጥ ዋኘ። ስለ ራሱ ድኅነትና ከእዚአብሔር ጋር ስለ መታረቅ ለአፍታ እንኳ ሳያስብ በዛፏ ደስ እንደተሰኘው ሁሉ በመጥፋቷ ተቆጣ።
ዮናስ እስኪዝል ድረስ ፀሐይዋ ክፉኛ ስትመታው ሞትን ተመኘና " ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ።” (ዮናስ 4፥8)። ለሁለተኛ ጊዜ በራሱ ሞትን ተመኘ።
የመጀመርያው በተናገረው ቃል አለመፈጸም ለክብሩ ተጨንቆ በንዴት የተናገርው ነው። ሁለተኛው ደግሞ በዛፏ መድረቅ ምክንያት ፀሐይ በመታችው ጊዜ ተቆጥቶ ነው። የመጀመርያው የክብር ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው አካላዊ ጉዳት ስለደረሰባት ነው። በእነዚህ ምክንያቶች ሁሉ አንድም መንፈሳዊ ይዘት ያለው የለም።
ብዙ ሰዎች ለተቀደሰ ዓላማ ሞትን ይመኛሉ። የዮናስ ሞትን መመኘት ግን ለዓለማዊ ጉዳይ ከማጉረምረምና ከትዕግስት ማጣት የሚመነጭ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤” (ፊል 1፥23) በማለቱ አልተሳሳተም። አረጋዊ ስምዖንም “ጌታ ሆይ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤” (ሉቃስ 2፥29-30) ቢል በፍጹም አልተሳሳተም።
ዮናስ ግን ከማጉረምረምና ለሞትም ዝግጁ ሳይሆን “አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ” (ዮናስ 4፥3) በማለቱ አጥፍቷል። እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ጸሎቱን ቢሰማና ዮናስ ቢሞት ኖሮ ለዮናስ ጉዳት በሆነ ነበር። #አንዳንድ ጊዜ በግድየለሽነት ለሚንጎዳበት ጉዳይ ስንጸልይ #እግዚአብሔር_ጸሎታችን_አለመስማቱ_የእግዚአብሔር_መሓሪነት_አታዩበትም? ሐዋርያው "ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።” (ያዕ 4፥3) በማለት በትክክል ገልፆታል። ዮናስ ሞትን ተመኝቶ ለመሞት እስከመጸለይ ሲደርስ እግዚአብሔር ስለ "በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን?” (ዮናስ 4፥4) በማለት ከዮናስ ጋር መነጋገር ጀመረ።
👉 አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ መጽሐፈ ዮናስን ካብራሩበት የተወሰደ

❤1
አስደንጋጩ ጥናት! ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ይልቅ ነገ እንዲያስፈራን የሚያደርግ መረጃ ወጥቷል። ከዲ/ን ኃ/ገብርኤል ጋር የተደረገ ቆይታ #ethiopia #youth
http://sharevideo1.com/v/YzdrNEdBR2p1QVU=?t=ytb&f=sy
🔥Trending video shared via VidMate🔥
🎉Best downloader for video and image on YouTube, WhatsApp status, Facebook, Instagram...
🎉Platform for FREE latest movies🎥🎥
👇Download VidMate Now!👇
https://www.vidmateapp.com/?subpub=sharing

Vidssave
VidMate — Easy & Powerful Website Video Downloader
Discover VidMate, the leading online video downloader for quick and easy saving from YouTube, TikTok, Instagram, Facebook, and more — no installation needed, allowing you to Download Video from link anytime on any device.
ዶክተር አለማዮህ ዋሴን እናድመጠው - በተቻለን መጠንና ባለን እውቀት እናውጋበት።
ዓለማየሁ ዋሴ (ዶ/ር) ፡ እንደገና መማር አለብን | Alemayehu Wassie
https://youtube.com/watch?v=qF4S1IKoq4I&si=l8_R2krrohp9rUt_

YouTube

Alemayehu Wassie (PhD) is here on Dejaf once again. This time he discusses about his latest novel titled "Fekare" with dawit. He also reflects on his social media writings.
#dejaf #podcast #alemayehuwassie #dawittesfaye #interview #ቁጥር፵፯ #ethiopia #habesha…

ልበ፦ 8 ማለት ግን 8 ብቻ ማለት አይደለም!
8 Reasons to Convert to Oriental Orthodoxy | A Beginner’s Guide to the A...
https://youtube.com/watch?v=dRDPaQbgMF8&si=O0wKvhCnWxSGzgGF

8 Reasons to Convert to Oriental Orthodoxy | A Beginner’s Guide to the Ancient Church
In this video, I explain 8 reasons to consider the Oriental Orthodox Church—an ancient Christian tradition rooted in the apostles, the Church Fathers, and a living, sacramental faith. If you’ve ever felt that something is missing in modern Christianity, this…
#እመርጣለሁ!
#ምርጫ በእኛ ሀገር ከፖለቲካም ከፍ ብሎ (ወይም በብዙ አንሶ) ፉከራም፣ ሽለላም፣ ፖለቲካም የሆነ ዘውግ አለው። ከምንም በላይ ጎልቶ የሚታየው "ማንም አያስቆመኝም" የሚል እንትን ነው።
በተለይ 2012 ዓ. ም ጀምሮ (በተለይ ነው ያልኩት) በትግራይ ፖለቲካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክፉኛ ትመታ ነበር። አንዱ መምቻዋ ማኅበረ ቅዱሳን በትግራይ ምርጫ እንዲካሄድ አይፈልግም የሚል የሐሰት ፍረጃ ነው። (ለዚህም በአለቃ ፀጋይ በርሄ ከሚመራ ልዑክ ጋር እስከ መወያየት አድርሶናል - ከፌስቡክ ሠራዊቶቻቸው የሰበሰቡትን እንደ ማስረጃ በድንፋታ ሲናገሩ ሽክክ አይላቸውም። መልእክቱም ባጭሩ "እኔን (ህወሓትን) ምሰሉ" ነው ) እኔም ፖለቲካ የሠራሁ መስሎኝ "ኣነ ክመርፅ እየ" ብየ የምርጫ ካርዴን በፌስ ቡክ ገፄ ላይ አጋራሁ። ብዙዎች የስድብ በየዓይነት አቀረቡልኝ። እኔም ጉዳት የሌላቸውን (ለሰውነቴ አለርጂክ የማይፈጥሩትን፣ ጨጓራ የማይነኩትን፣ ደም ግፊት የማይጨምሩትን) ትንሽ ትንሽ አንስቼ ሌሎችን ባላየ አለፍኩ። የስድቦቹ መነሻነት የነበረው ሙቀት (የመንጋነት ከፍታ) የወለዳቸው መሆናቸው ይታወቃል። እኔም በሰበቡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊያሳድሩት ካሰቡት አንጻር ልክ ነበርኩ። የእውነትን አንጻራዊነት አየህ!
ያቺ ካርድ ('ኣነ ክመርጽ እየ' የምትለዋ) በዘመኔ ለምርጫ ካወጣኋቸው ካርዶች ሁለተኛ ሆና ትመዘገብልኝ ነበር። ምን ያደርጋል በፕሪቶርያ ስምምነት መሠረት እንቆልልጭ ተብያለሁ። የመጀመርያዋ የ 97 መሆኗ ነው። በዕድሜዬ ማውጣት ከነበረብኝ ካርድ 1 ብቻ ማለት ነው ሕጋዊ ሆኖ የተመዘገበልኝ። ይህ ማለት የሀገራችን ምርጫ ትርጉም ከማይሰጣቸው ሰዎች ውስጥ የሚዶለኝ ይመስለኛል። ዲምክራስያዊ ምርጫ ትርጉም የማይሰጠኝ ሆኘ ግን አይደለም "ቅድመ ውሳኔ" ዶግማው ያደረገ ምርጫ እንጂ።
የሀገር ብሔራዊ አንድነት የሚገደው፣ ዜጎችን በዜግነታቸው እኩልነት እንዲሰማቸው የሚሠራ፣ በጎሳ ያልተደበቀ፣ ሐሰተኛ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ትርክቶች ያልተጫኑት፣ በሥልጣን ጥመኝነት ያልሰከረ፣ ለሌሎች ምቹ መደላድል የሚፈጥር ተመራጭ ፓርቲም ሆነ ግለ ሰብ አላገኘሁም ነበርና ከአንድ ጊዜ በላይ አልመረጥኩም። የ 97 ሰባቱም ቢሆን በተለያየ መንገድ ፈፅሞ ባልጠበቅኩት ሁኔታ ዱላ ሲበዛብኝ የተበቀልኩ መስሎኝ እንጂ የመረጥኩት ፓርቲ ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ ልመርጠው አይደለም "ያጥፋህ" የምለው ነው። በዚህም እንደ ህዝቤ የጭቃ ጅራፋቸው ባይቀርልኝም "ባልመረጥኩ" ከሚል ጸጸት ተጠብቄ ኖሬያለሁ።
ዘንድሮስ! ዘንድሮም እመርጣለሁ። ምርጫየም ማናቸውንም አለመምረጥ ሆኗል።

የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሦስተኛ በደርግ ልኡካን ላይ (ደርግ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን በግፍ አስሮ በብፁዕ አቡነ ተ/ሃይማኖት በዓለ ስሜት እንዲገኙ ለመጋበዝ የተላኩ ልኡካን) ያነሷቸው ጥያቄዎች ፦
(1) ከሥልጣን የወረዱት ፓትርያርክ ሁኔታ እንዴት ነው?
(2) ከሥልጣን ያወረዷቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው ወይስ መንግሥት?
(3) የቀድሞው ፓትርያርክ በሕይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ መሾም የቤተ ክርስቲያን ሕግና ትውፊት ነውን?
(4) ቅዱስ ፓትርያርክ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት የቀረበባቸው ክስ (ወንጀል) ለማስተባበል መብት ተሰጥቷቸው ዕድሉን አግኝተው ነበርን?
(5) ስለ መውረዳቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ብሎ ለምን ኦፊሻል ደብዳቤ አልጻፈልንም?
(6) መንግሥት ወንጀለኛን ያስራል እንጂ ሥልጣን ክህነትን መግፈፍ አይችልም። ስለዚህ የቀድሞ ፓትርያርክ ሥልጣን አሁን ምንድን ነው? ሊቀ ጳጳስ ናቸው? ጳጳስ ናቸው? ተራ መነኩሴ ናቸው? ወይስ ምዕመን ናቸው?

ከምትነጋገሩበት 'አጀንዳ' ይልቅ #መነጋገርያ_ሆናችኋል!
እንዴት? አላችሁኝ።
👉 እንደ ቤተ ክርስቲያን
💔 ምእመኖቿ በጅምላ ተገድለው በጅምላ የሚቀበሩባት፣
💔 አገልጋዮቿ በቤተ መቅደስ የሚታረዱባት፣
💔 ምእመኖቿ ድኅነት የሚያገኙበት ምሥጢራት የሚትፈጽምባቸው አብያተ ክርስቲያኖቿ የሚቃጠሉባት፣
💔 አስተዳዳሪዎች ከሰው ይልቅ ገንዘብ የሚያስቀድሙባት። በገጠር ተዋፍ ጠፍቶ በከተማ አዲስ ሞዴል መኪና የሚሸላለሙባት፣
💔 ምእመኑ በቅጡ የሚያስተምረው አጥቶ ብዙ ሐሰተኞች ተከትሎ የሄደባት፣
💔 በሐሰተኛ ትርክት በብዙ የምትከሰስ፣ ከየትኛውም የሀገር ጉዳይ የተገለለች፣
💔 በአጭር ዓመታት 20 ሚልዮን የሚሆን ምእመኗ ያጣች፣
የዚህች ቤተ ክርስቲያን በክህነቱም በአስተዳደሩም ከፍተኛ ቦታ ያላችሁኮ አትመስሉም።
👉 ደግሞ እንደ ሀገርም
💔 ብዙ ዜጎቿ በረኃብ በሚሰቃዩበት፣
💔 ብዙ ዜጎቿ ሃብት ንብረታቸው በቅጽበት እያጡ ተመጽዋች የሚሆኑባት፣
💔 በሀገር ውስጥ ብዙ ዜጎቿ በስደት አሳራቸውን በሚያዩባት፣
💔 ከሀገር ውጭ የሚሰደዱ ዜጎቿ በየዕለቱ በመቶዎች በበረሃ የሚቀሩባት፣ የዓሳ ቀለብ የሚሆኑባት፣ በጅምላ ሊሰቀሉ የተፈረደባቸው ዜጎች ያሏት፣
💔 ብዙ ዜጎች በሰው ሠራሽ ምክንያት እርስ በርስ በሚጠፋፉባት (ምክንያቱ ምንም ይሁን ሞትን የማስቆም እንጂ መገዳደልን ፍትሐዊ ማድረግ ከእናንተ አንጠብቅማ)፣
💔 ረሃቡ፣ ስደቱና ሞቱ ከትናንት ይልቅ ዛሬ የባሰባት፣ ከዛሬ ይልቅ ነገ በሚያሰጋት
ሀገር የምትኖሩ አልመስል እያላችሁን "#በየት_ነው_የሚኖሩት?" ብለን #እንነጋገርባችኋለን።

❤4
በዚህ ትችት የተተቸ ሰው እጅ ነስቶ የሚያመሰግን መስሎኝ ነበርክ እናንተው😆
#የለመለመ_የወይራ_ቅጠል_ይዛ_ነበር
🌿 🌿 🌿
በኖኅ ዘመን ዓለም እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠሩ የሚያጸጽት ክፋት ፈጸመ። የሰው ልጅ የልብ ሐሳቡም ምኞቱም ፈጽሞ የጥፋት ሆነ፥ በግፍም ተሞላች፡፡ ዘፍ 6፡ 5-11
ምንም እንኳ "ሥጋ የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበር" ዘፍ 6፡12 ብሎ የሰዎችን የክፋት ጥግ ቢነግረንም ኖኅ ግን በፊቱ ሞገስን አገኛ - እርሱ #የጽድቅ_ሰባኪ_ነበረና፡፡ 2ኛ ጴጥ 2፡5
እግዚአብሔርም ይህን የጽድቅ ሰባኪ ከሚመጣው ጥፋት የሚድነብትን መንገድ ነገረው። ኖህም እንዲሁ አደረገ … እንደተነገረው።
ነገር ግን 150 ቀናት በመርከብ ሆኖ በሚያስጨንቅ ማዕበል ውስጥ ነው። የጥፋት ውኃውን መጉድል በጉጉት መጠበቁ አልቀረም። እናም መልእክተኞችን ላከ … መድረቁን ያዩ ዘንድ። ወድያና ወድህ እየበረረ የቀረውን ቁራን ትተን ስለ እርግብ ግን መጽሐፍ እንዲህ ይላል "#ርግብም_በማታ_ጊዜ_ወደ_እርሱ ተመለሰች፥ #በአፏም_እነሆ_የለመለመ_የወይራ_ቅጠል ይዛ ነበር፥ ኖኅም ከምድር ላይ ውኅ እንደቀለለ አወቀ" ዘፍ 8፡ 11
ርግብ ፍጥረታቱን ሁሉ የጎዳው ይህ አስፈሪ የጥፋት ውኅ መድረቁን (ማለፉን) የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዛ በመምጣት አበሰረች።
❤ ❤ ❤ ❤
ዓለም ግን ሌላ የምስራች ያስፈልገው ነበር። በኃጢአቱ (የእግዚአብሔር ትእዛዝ በመጣሱ) ምክንያት ከፈጣሪው ርቆ፥ ከጸጋ ሁሉ ተራቁቶ፥ ለሞት ተገዝቶ ነብርና የመከራው ዘመን አልፏል የሚል አብሳሪ ያሻዋል። እናም የ5500 የፍዳ ዘመን ሊጎድል (ልያልፍ) 15 ዓመት ሲቀረው (በዓመተ ምሕረት ዋዜማ) ሰላምን ልታበስር ርግብ (ማርያም) ከ/በ ሊባኖስ መጣች (ተወለደች)።
ይህ ብቻ ግን አይደለም መካኖች የነበሩት የሥጋ ወላጆቿ (እናትና አባቷ ሐናና እያቄም) በመካንነታቸው ምክንያት ሲደርስባቸው የነበር መገለልን አስወገደች እንጂ፡፡ ከዝህ የሚልቀው ግን በኃጢአት ምክንያት ከመንፈሳዊ እድገት (ጸጋ) መክነው የነበሩት እናቷ ሔዋን አባቷ አዳም ወደ ክብራቸው ይመልሱ ዘንድ የእርሷ መወለድ አስፈለገ።
አሁንም ድንግል ሆይ፡-
✍ሥጋ ለበስ ሁሉ ከመልካም ግብር መክነን ከእግዚአብሔር በመራቃችን እግዚአብሔር ያዘነብን የጥፋትም ደዌ የመጣብን ነንናን ፈጥኖ ማለፍን አብስሪን።
✍የልባችን ሐሳብ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አልሆን ብሎ፣ ምኞታችንም የአመጻና የጥፋት ሆኖብናልና የቀናውን እንመለከት፥ እንሻም ዘንድ እግዚአብሔርም ገጸ ምሕረቱ ይመልስልን ዘንድ የለመለመ የወይራ ቅጠል ይዘሽ ከሊባኖስ ወደ እኛ ነይ፡፡
የእመቤታችን ልደት የሁላችንም ልደት ነውና እንኳንም አደረሰን፡፡

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ናብ መን ከም እንጥምት #ተደናጊሩና_ኣይፈልጥን!