ሔዋኔ
ክፍል 3
ሀይ ዮኒ ብላ መለሰቸልኝ በጣም ይቅርታ ካርድ ዘገቶብኝ ነው ነው ሞልቼ ነበር እኮ የት እንደሄደ እንጃ እንዳልበደር መከረኛ ኔትዎርክ አስቸገረኝ በዛ ላይ ብዬ የቆት የባጡን መቀባጠር ጀመርኩ ኧረ ችግር የለውም ዮኒ ደግሞ አለችኝ ምን እንደማውራት ግራ ሲግባኝ አማርኛ ፊልም ላይ እንደማየው እራት በላሽ ብዬ ጠየኳት እራት ባልበላው አንጀቴ አወንታዊ መልሷ ከብዙ ሴቶች ይለያል ‘’አዎ በላው እቤት እንደገባዉ ለራሴ የሚበቃ ፍርፍር ነገር በዳቦ እና የቅመም ሻይ አለችና አንተስ ብላ ጥያቄውን ወደራሴ አመጣች። የእራት ዝርዝሯ ምራቄን አስዋጠው ይባሱኑ እራበኝ መልስ ሳልመልሰላት ሮጬ ኩሽና ገባው እቃ ተልኬ የማላገኘው ልጅ ወጥ ለመፈለግ ግን ያልገባሁበት የለም ከዛ ግን ሳስበው ፍሪጅ ውስጥ ይሆናል በማለት ሄጄ አየው እውነትም አለ ወጡን የያዘውን እቃ ይዤ ወደ ኩሽና ሄድኩ ወጡን እያሞኩ እያለ በመሃል መብራት ድርግም አለ ከመጥፋቱ እንኳን ደቂቃ ሳይቆይ እንደ አክቲቪስት ሃገሬን መርገም ጀምርኩ። አይ አንቺ ሃገር ቆይ ምን አደረኩሽ ለዓባይ አዋጥቻለው መኪናዬ ላይ አባይ የኔ ነው የሚል ስቲከር ለጥፊያለው እሺ ከዚ በላይ ምን ላደርግ ብሶት አይሉት ትችት ለፈለፍኩባት ጦቢያዬ አትችልም እንጂ ብትችል በጥፊ ብትለኝ ደስታዋ ነው ነገር ግን አስዘንኳት መሰለኝ መብራቱ መጣ። ወጡ ሞቀ እራት በላሁ ጨራረስኩና ወደ አልጋዬ ሄድኩ ሆኖም ግን ሄዋኔ አልነበረችም የት ሄደህ ነው ቆየህ እኮ ብቃ ደና እደር የሚል መልዕክት አስቀምጣ ተኛች መቆየቴ አናደደኝ የተጣላን መሰልኝ እኔም ብዙም ሳልቆይ ተኛው ከረጅም ጊዜ በኋላ ገና ዛሬ ከእንቅልፌ እንደተነሳው የሄዋኔን ቴክስት ለማየት ቴሌግራም ገባው የሄዋኔን ቴክስት ሳይ ከእንቅልፌ በደንብ ነቃው። የላከችልኝ ቴክስት ይህን ይመስላል ‘’ ዮኒ ቆየህብኝ እኮ ካሁን ካሁን ትገባለህ እያልኩ ስጠብቅ የለህም እንቅልፌን መቆጣጠር ሲያቀተኝ ተኛው በል ደና እደር ’’ ለሄዋኔ መልስ ምት ከሰጠው በኋላ ከአልጋ ተንሳውና ሻውር ገባው ቁርስ በላውና የበርንዳ ወንበር ላይ ሆኜ በዓይኔ መጽሃፍ እያነበብኩ በልቤ ደግሞ የሄዋኔን ቴክስት መጠበቅ ጀምርኩ ግን የሚገርመው ሄዋኔ ቴክስቱን ሳትመልስ የልብወልዱ ፀሃፊ ማመስገን ሚፈልጋቸዉን አካላት መዘርዘር ጀመረ። ድንገት ሳይታሰብ ሰዓቱ ሄደ ለሄዋኔ ደውዬ ለምን ምሳ አልጋብዝሽም ማለት ፈልኩ ግን እንዴት ፈሪ አንደበቴ ጠፍንጎ ያዘኝ ያም ሆኖ ግን ከመገኘት አልቀረንም ግብዣዬን ተቀብላ ቀጠሮ ያዝን ከቀጠሯችን ሰአት ቀድሞ ለመገኘት መዘጋጀት ጀመርኩ ብዙ ጊዜ ለቀጠሮ ቀለል ያለ ልብስ አዘወትራለው እንዳልኩትም ቀለል ያለ ልብስ አድርጌ በጊዜ ከቤት ወጣው። ቆይ ግን ልክ ቀጠሮ ሲኖረኝ ለምንድነው ታክሲ የማይኖረው የሁልጊዜ ጥያቄዬ ነው ምን ማድረግ ይቻላል ደግሞ ለሄዋኔ አልኩና ላዳ ታክሲ ይዤ ወደ ቀጠሯችን ቦታ ሄድኩኝ እንደፈራሁት አይደለም በአካባቢው አልነበረችም ቀድሚያት ነው የድረስኩት። ሳንባ እንደምትጠብቅ ድመት አይኔን እያንከራረተትኩ ሄዋኔን መጠበቅ ጀምርኩ የሆነ ሰአት መቀመጡ ቢሰለችኝ መጸዳጃ ቤት ሄድኩኝ ስመለስ ሄዋኔ ተቀምጣ አየኋት በውሃ የረጠበው አጄ ይብሱን እረጠበ በግንባሬ ላቦች ችፍ አሉ በቃ ተደናበርኩ አጠገቧ ስደርስ አቅፋ ሰላም አልችኝ አሷን ካስቀምጥኩ በኋላ ተቀምጬ እንዴት እንዳማረባት እንግራት ጀመር እየሰማችኝ ታፍራለች ብዙም ላሳቀቃት ስላልፈልኩ ውበቷን በአንድ ቃል አጠቃለልኩትና ‘’ሔዋኔ’’ አልኳት። ምሳ በላን ብዙ ነገር ተጨዋወትን ከዛ ትኩስ ነገር ከተጠቀምን በኋላ ጸሃይዋ ስለጠለቀች walk ማደረግ ጀምርን በመንገዳችን መሀል ኪሩቤል ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የሚል ፖስተር ላይ እጁን ወደ ምስራቅ የዘረጋ ሰውዬ አየን ሳቄ አመለጠኝና ሳኩ ምነው ብላ ፈገግ አለች አይ ገርሞኝ ብዬ ደግሜ ሳኩኝ በፊት ጓደኛዬ ያለኝ ነገር ትዝ እያለኝ ‘’ 12+ እያለን አንዱ ጓደኛዬ ዉጤት ከመውጣቱ በፊት ያለው ጊዜ ላይ ሆነን ምንም እንኳ ዉጤት እንደጠበቅነው ባይሆንልን ችርች እንከፍታለን አለኝ ’’ አሁን ላይ የብዙ ሰው ራእይ ይሄ አየሆነ መቷል ቤተክርስቲያን አባል ሳይሆን አገልጋይ ነው የምትፈልገው አንደዚ ሲሆን ዉጤትማ አንሆናለን ይህ ካልሆነ ግን አሜን ብቻ የሚል በድን ሰው አቅፎ እንደመኖር ነው ብዬ ነገርኳት በኛ ቤትክርሲቲያን ሳትቀና የቀረች አይመስለኝም ደስ አላት በጣም። ሰአቱ እየሄደ አየሩም እየጨለመ መጣ ሴት ናት ያውም ሄዋኔ ለዚህ እሷን ለመሸኘት ወደ ቤቷ መሄድ ጀምርን ለካ የምር ነው ፊልም ላይ ብቻ ይመስለኝ ነበር የሆነ ሰአት ላይ በጣም ሀይለኛ ብርድ መጣና ጃኬቴን አወልቄ አለበስኳት ደስ አላት እኔ ግን ጭራሽ ነው ያልበረደኝ እሷ ሰላለች ነው እንጂ እቤት ሆኜ እራሱ ጋቢ ደርቤ ያንቀጠቅጠኛል። ወደ ቤቷ እየተቃረብን ስንመጣ ሻይ ጠጥተህ ትመለሳለህ የሚል ትእዛዝም ዛቻም የሚመስል ንግግር ሰነዘረችብኝ እንደመግደርደር አምቢ እንደማለት አረገኝ ጭራሽ አይሆንም ብላ ደረቀች እሺ ብዬ ገባው እቤቷ ታምራለች(ማሳሰቢያ ታምራለች የሚለው ቃል የቤቱን ማነስ ለመግለጽ ሳይሆን የቤቱን ዉበት ለማድነቅ እንደሆነ ይታወቅልኝ) ዉስጧ የተስተካከለ ነው ሁሉንም ወድጄዋለው ነገር ግን በግራ በኩል ግድግዳ ላይ ያለው የወንድ ፎቶ ረበሸኝ የቲቪዉን ሪሞት ሰጠችኝና ልብሷን ለመቀየር ወደ ዉስጥ ገባች። ትንሽ ቆይቶ በሩ በሀይለኛ ተንኳኳ. . . ክፍል 4 ይቀጥላል
@yonitomtom

❤6👍2
"መቼም አይሁድ ታምራዊ ምልክትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ መሰናክል፣ ለአሕዛብ ደግሞ ሞኝነት ነው። እግዚአብሔር ለጠራቸው ግን፣ አይሁድም ሆኑ ግሪኮች፣ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል፣ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው።
@yonitomtom
@yonitomtom
#happyeaster
@yonitomtom
@yonitomtom
#happyeaster
👍3
🎤🎼አንድ ስሙን የማልነግራችሁ የ tv ሾዉ ላይ አንዱ ዘፋኝ ሲናገር ዘፈኑን በጣም ነዉ የወደድኩት እያለ በግነት ዘይቤ ሳይቀር ያስረዳል ድንገት የሆነ ሰዓት እንደዉም መዝሙር በለዉ ሲል ካለሁበት ቦታ በማላቀዉ መንገድ እራሴን ሪሞት ይዤ ሶፋ ላይ አገኘሁት ራሴን ጆሮዬን ለማመን ከበደኝ ተሳስቶ መሆን አለበት ብዬ በርጋታ ማዳመጥ ጀመረኩ ደግሞ መዝሙር በለዉ አለ እንዴ ኧረ እባክህ እፈር አንድን ፍጡር ወይም ሀገር ማወደስ አልያም መተቸት እንዴት ነዉ መዝሙር የሚሆነዉ ተዉ እንጂ ተዉ መረዳት ያልቻልነውን ነገር ለማስረዳት አንሞክር አቻ የሌለውን አምላካችንን ስለኛ በደል በመስቀል ሞት እራሱን አሳልፎ የሰጠ ከሞትም ለተነሳው ለናዝሬቱ እየሱስ ማዜም መቀኘት ይሄ ነዉ መዝሙር ማለት።
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
👍5❤4
ሔዋኔ
ክፍል4
ድንግጥ አልኩና ሄጄ ስከፍተው አንድ ህጻን ልጅ በተብታባ አንደበት ህሊና የለችም ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ ሮጦ ሄደ ሄዋኔ(ህሊና) ከውስጥ ሆና ማነው ዮኒ ብላ ጮህች የሆነ ህጻን ልጅ ህሊና የለችም ብሎ እየሮጠ ሄደ ብዬ መለስኩላት ብዙም ሳትቆይ ሻይ ጥዳ በለሊት ልብሷ መጣችና ሻዩ እየፈላ ነው ሱቅ ደርሼ መጣው ተጫወት እሺ ብላኝ ሄድች የቅድሙ ህጻን የሄዋኔ አከራይ ልጅ እንደሆነ ያወኩት እሷ እንደወጣች ተመልሶ መጣና ለህሊና እማማ የቤት ኪራዩን ብር በብርሃን ሳይሆን በአዋሽ አስገቢለኝ ብለውሻል በላት ብሎ ነግሮኝ እንደለመደው ሮጦ ሄደ። ሄዋኔ ከሱቅ መጣች ሻይ እየጠጣን በዛዉም ስለ ቤተሰብ እያወራን የሆነ ሰአት ላይ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች አጠገቧ ሆኜ አጽናናሗት አባቷን ካጣች ቆየች እናቷ እህት ወንድሞቿ በጌታ በመኋኗ ምክኒያት ተጣልተዋታል ጊቢ ክላስ የጨረሰችው በራሷ ወጪ ነው ለ7 አመት የምታፈቅረው እጮኛዋ በማታዉቀው ምክኒያት ተጣላት በዚ ሁሉ ዉስጥ ሆና ግን በ እግዚያብሄር ተስፋ አትቆርጥም አሁንም እግዚያብሄር አለ ትላለች እኔን በሷ ዉስጥ ሆኜ ለማሰብ ሞከርኩ ጭራሽ ከባድ ነው ያዉም በዚ ተስፋ አስቆራጭ ዘመን ግን በዚህ ነገር ዉስጥ ሆነን የሚያስችለን የእግዚያብሄር ጸጋ ብቻ ነው ባሁኑ ጊዜ አሁን ባለንበት ዘመን የእግዚያብሄር መኖር ከአይናችን ሊያፈዙብን ሚሰሩ ብዙ ናቸው ብዙዎቻችን በትናንሽ ችግሮች ነገርን ሁሉ ከእግዚያብሄር ጋር እናገናኛለን ግን የእግዚያብሄር ዝምታው እራሱ መልስ ነው። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው በዛ ላይ ለሁሉም ጊዜ አለው ደግሞ እግዚያብሄር ሉአላዊ አምላክ ነው። ድንገት ሳናስበው ሰአቱ ሄደ በቃ ልሂድ በማለት አቅፌ ተሰናበትኳትና ከቤቷ ወጣው ታክሲ አየጠበኩ መንገድ ላይ የማላየው ጉድ የለም አንዳንዱ ዉስጡን ሳይሆን ላዩን ለመሞቅ በእንጨት እሳት ይጭራል አንዳንዱ ከመጠጣት አልፎ መሬቱን እያጠጣ ይሄዳል አንዳንዱ ሄዋኑን ፍለጋ ይባዝናል አንዳንዱ ቀን በእንቅልፍ ዉሎ ማታ ይነጋለታል ሌላው ደግሞ በሰከረ አንደበት መርጦ የሰቀለውን መንገስት ይዉረድ ይዉረድ እያለ ይፎክራል ጦቢያዬ ከቀን ይልቅ ማታማታ እውነተኛ ገጿ ይታያል ቀንቀን እኛን የሚመዝን የሚዛን ሰራተኛ ማታ ጨንቀላቱን በሚዛኑ ደግፎ ራሱን እየመዘነ ያድራል ደግሞ ሌላዉ ቀንቀን በታሪፍ መሰረት ይሰሩ የነበሩ ታክሲዎች ማታ ላይ ገና ሊጨልም ሲመስላቸው የታሪፉን 2 እና 3 እጥፍ ማስከፈል ይጀምራሉ አሁን ያልኩትን አይነት ታክሲ ከስንት አሰልቺ ጥበቃ በኋላ አገኘው ታክሲዉ ሞልቷል በታክሲዉ ራዲዮ ሆና የምታወራው ሴትዮ ከራዲዮኑ ሳይሆን እዛው ታክሲ ዉስጥ ሆና የምታወራ ነዉ ምትመስለው ስለ ሰላም መረበሽ ጸጥታ እያወራች ሰላም ነሳቸኝ ረበሸችኝ በዚህ ብስጭት ዉስጥ ሆኜ አንድ ግዙፍ ሰውዬ አጠገቤ ተቀመጠ እንዳቀማመጡ ግን መቀመጥ የሚለው ቃል ሳይሆን ማረፍ የሚለው ቃል ድርጊቱን ይበልጥ ስለሚገልጥልኝ አረፈ ብል ይቀለኛል እንደዛ ተጣበን እራሱ ረዳቱ አሁንም ሌላ ተሳፋሪ ይጠራል ነገሩ ቢጨንቀን ልንወርድ ነው እያለን እናስፈራራው ጀመር ከብዙ የአሮጊቶችና የሽማገሌዎች ጭቅጨቃ በ30 ሰዉ ብቻ ታክሲዉን ጉዞዉን ጀመረ። ብዙ ጊዜ ስልኬ ባትሪ ካላለቀው በቀር ሙዚቃና መዝሙር እየሰማው መሄድ አዘወትራለው ዛሬ ግን እንደወትሮዉ ማድረግ አልቻልኩም ለምን ብትሉ አጠገቤ ተቀምጧል ማነዉ እሱ አርፏል ያልኳቹ ሰዉዬ በየ 5 ደቂቃዉ ትከሻዬን እየጎሰመ ወሬዉን ያወራል ሰውዬዉ ቢሰለችኝ ወደ መስኮት ዞሬ በሬዲዮኑ ራሷን ስላጠፋችዉ ሴት ዜና ማዳመጥ ጀመርኩ ዜናዉ ይህን ይመስላል “ በእገሌ ክ\ከተማ በተለምዶ ቦሌ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ትኖር የነበረች አንዲት ወጣት ሴት ራሷን ከፎቅ ላይ ከስክሳ አረፈች ለዜናው ጥንቅር በአካባቢው የነበሩትን የአይን እማኞች አነጋግረን ነበር እናም በሰጡን መረጃ መሰረት ልጅቷ ከመሞቷ በፊት ደጋግማ ታፕ ታፕ እንደምትል መብራት ሲጠፋ ደግሞ እንደሚጨንቃት ሌላው ደግሞ ዋናው ነገር ራሷን ያጠፋችበት ምክኒያት ነው የቲክቶክ ተከታዮቼ ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ ነው እራሷን ከፎቅ ላይ ወረዉራ ያረፈችው ለቤተሰቦቿ እንዲሁም ለተከታዮቿ ሁሉ ጣቢያችን መጽናናትን ይመኛል የዜናዉን ማለቅ ሳይጠብቁ ከኋላዬ የነበሩት አሮጊቶች አይ ዘመን አዬ ጊዜ እያሉ ምሬታቸዉን ያሰማሉ እንደተለመደው እኔና ህሊናዬ ዉዝግብ ጀመርን ቆይ ግን አንተ ብትሆን ምን ታደረግ ነበር አለችኝ ደንግጬ እንዴ አረ በስማም መቼም አልኩና ደሞ ማሰብ ጀመርኩ የእግዚያብሄር ፍጡር ሆነን በምድር ላይ ልክ እንደ እየሱስ ልንኖር የተጠራን ሰዎች የእግዚያብሄርን እቅድ በህይወታችን ልንገልጥ የሚገባን እኛ ይህን ሁሉ እረስተን በነገሮች መሆን እና አለመሆን እራሳችንን እናጠፋለን። መንገድ ክፍት ስለነበር በጊዜ ገባው ገና እንደገባው የታየኝ አልጋዬ ነው እሰራለው ያልኩትን ሁሉ ለመስራት ከበደኝ የለሊት ልብሴን ቀይሬ ከመጽሃፎች ሁሉ ቅዱስ የሆነዉን የህይወት መጽሃፍ (መጽሃፍ ቅዱስ) አነበብኩና ከጌታዬ ጋር መነጋገር ጀመርኩ በመሃል በተደጋጋሚ ስልክ እየጠራ ይረብሸኝ ጀመር ስልኬን ላመጣ ስሄድ… ክፍል 5 ይቀጥላል

❤3👍1
yoni tom_tom pinned «ሔዋኔ ክፍል4 ድንግጥ አልኩና ሄጄ ስከፍተው አንድ ህጻን ልጅ በተብታባ አንደበት ህሊና የለችም ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ ሮጦ ሄደ ሄዋኔ(ህሊና) ከውስጥ ሆና ማነው ዮኒ ብላ ጮህች የሆነ ህጻን ልጅ ህሊና የለችም ብሎ እየሮጠ ሄደ ብዬ መለስኩላት ብዙም ሳትቆይ ሻይ ጥዳ በለሊት ልብሷ መጣችና ሻዩ እየፈላ ነው ሱቅ ደርሼ መጣው ተጫወት እሺ ብላኝ ሄድች የቅድሙ ህጻን የሄዋኔ…»
ሔዋኔ
ክፍል 5
ሄዋኔ የሚለዉን ስም ከሩቅ አየሁ መደወሏ ግራ አጋባኝ ወደ ሰልኩ ስደርስ ተዘጋ ለመደወል ፈራው ምክኒያቱም ሰአቱ ሄዷል ስልኬን ሳይለንት አድርጌ ወደ ጸሎቴ ተመለስኩ ስጨርስም በጣም ደክሞኝ ስለነበር ጥቅልል ብዬ ተኛው። ጠዋት እንደተንሳው በሶኬት በኩል ያለችዉን ጸሃይ መሞቅ ጀመርኩ የወፎች ጫጫታ አይ አይ ጫጫታ ሳይሆን የወፎች ዜማ ብል ይሻለኛል የሰማዩን ብርሃን የወፎቹ ዜማ ሌላ ደስታ ይፈጥራል መሽቶ መንጋቱ የተፈጥሮ ስራዎች የኛ መውጣት መግባት እጅግ ሚደንቅ ነዉ የጠዋት ልምዴን ላካፍላቹ ጠዋት እንደተነሳው ካልሁበት ሳልነሳ ወይም ደግሞ ተንስቼም ቢሆን ለተወሰነ ደቂቃ አሰላሰላለዉ(meditate) ማታ እንደ ሞተ ሰዉ ተኝቼ ጠዋት ግን ተነሳዉ መቼም ጤነኛ ስለሆንኩ አይደለም እራት በልቼ ስለተኛውም አይደል በቃ በኔ ሳይሆን በርሱ ቸርነትና በማያልቀው ምህረት እንሳለዉ ታዲያ ዛሬም በዚሁ ልምዴ እያለዉ። ስልኬን አዉጥቼ የሄዋኔን ሚስድ ኮል(missed call) መመለስ ፈለኩ ነገር ግን ስእቱን ሳየዉ ፈራዉ ደሞ በዚ ጠዋት ምን አስበህ ነዉ ብትለኝስ መደውሉን ትቼ ስልኬን አስቀምጬ ሻወር ገባው በመሃል የስልኬን ጥሪ ሰማዉ ማመን ስላለችልኩ የከፈኩትን ባንቧ ዘጋዉ አሁንም ደግሞ ተደወለ በቃ ሄዋኔ ናት አልኩና ከነሳሙናዬ በፎጣ ከሻወር ቤት ወጣዉ እንደምንም እጄን አድርቄ ስልኩን አነሳዉ ማታ ደውላ ሳላነሳ ጠዋት ደግሞ እደውላለዉ ብዬ ሳልደዉል ቀድማ መደውሏ አሳፈረኝ አንዲህ በሃሳብ ተውጬ ከራሴ ጋር ሳወራ ሄዋኔ በስልክ ሄሎ አረ ዮኒ ትላለች ዉይ በስማም አልኩና
እኔ- ህሊና እንዴት ነሽ እንዴት አመሸሽ
… አልኳት እየተንተባተብኩ
ሄዋኔ- እንዴ ምን ሆነሃል ዛሬ የምን ማምሸት ነው አሁን እኮ ጠዋት ነው
እኔ- አይ የኔ ነገር አይሽ እራሴን አሞኛል እና አልተሻለኝም ማለት ነው
ሄዋኔ- ውይ እኔን አይዞህ እኔ እኮ ደግሞ ማታም ስደዉል አታነሳም ብጠብቅ ብጠብቅ አትደዉልም አስጨንከኝ እኮ
ከስንት አመት በኋላ እንደዚ ምትለኝ እንስት አገኘው በሳሙና አረፋ የተሞላዉ ገላዬ ሲደርቅ ተሰማኝ ደስታው ነው መሰለኝ በረጅሙ ተነፈስኩና
እኔ- አረ ደና ነኝ አትጨነቂ
ሄዋኔ- ምን ደና ነህ ይህዉ አሞህ የለ አይ በቃ እሺ በኋላ ከስራ ስወጣ እደውልልሃለው ቻው ብላኝ መልሴን ሳትሰማ ዘጋችዉ ስልኩ እንደተዘጋ በደስታ ፈነጠዝኩ። ሻውር ወስጄ ጨረስኩ ቁርሴን በላዉና የአለምን ህዝብ በግልጥ ወደ ማገኝበት የማህበራዊ ጉድ ገጽ ገባው 16 ያልታዩ መልእክቶች አሉኝ ፣ 8 የጓደኛ እንሁን ጥሪ እንዲሁም ደግሞ 4 የጽሁፍ መልእክት። ከጓደኛ እንሁን ጥሪ ገባው ሁሉንም እሺ ብዬ ተቀብዬ የአንዲትን ሴት ልጅ ጥሪ ግን ሳልቀበላት ተውኩት ነገሩ እንዲህ ነዉ ክልጀቷ ጋር 3ኛ ክፍል ላይ አንድ ላይ ስለተማርን ተዉዉቅ አለን ለ1 አመት ያህል ያህል በጓደኝነት ዘለቅን ደሞ እጮኝንት ሳይሆን ጓደኛ ነዉ ያልኩት አናም የሆነ ጊዜ ላይ በጣም የሚያምረውን የሷን እራሳስ ወስድኩባት እናም በአመቱ ክላስ ስንገባ ልጅቷ ት/ቤት እንደቀየረች ሰማው ታዲያ አሁን ደሞ እዚ ፌስቡክ ላይ አምጣ እያለች ብትጨቀጭቀኝስ አይ አይ ይቅርብኝ ወደ ጽሁፍ መልእክቱ ገባው ያው የተለመደ ነው ምፈልገውን መልሼ ሌላውን ተውኩት ዋናው ገጽ ላይ ሄጄ አዳዲስ ልጥፎችን ማየት ጀመርኩ አንዱ ልጥፍ ደሞ ግጥም፡
“እኔ እሮጣለው አንቺ እንዳትመጪ ደሞ ይመጣል ብለሽ ቆመሽ እንዳትቀሪ”
ደጋግሜ አንበብኩት ምንም ምንም ሊገባኝ አልቻለም የሰውን አስተያየት ገብቼ ማንበብ ጀምርኩ አረ ሰው ግን ለአማርኛ ፈተና የሚጠፋበት ቅኔ እዚህ ያውም ለስድብ ሲሆን ይመጣለታል አይ የኛ ነገር የማያቸው ልጥፎች ህመሜን ስለባሱበኝ ትቼ ወጣው ሳላስበው ሰአቱ በጣም ሄደ የጀመርኩት ኦንላይን ክላስ ስለነበር ወደ ክፍሌ ገብቼ ኮርሱን ወስድኩ እንደጨረስኩ በዛውም ፊልም አየሁና ሶፋ ላይ ሄጄ ጋደም አልኩ። የጎረቤት ዉሻ በጠበጠኝና ከእንቅልፌ ባነንኩ ስልኬን ሳየው 12;15 ሰአቱ ደግሞ አበዛው በቃ ዝም ብሎ ነዉ እንዴ የሚሮጠው በዛ ላይ የሄዋኔ 5 missed call አለ ምን እንደማደርግ አላውቅም ለሷም ቢሆን አወቄ ነው ሚመስላት ደጋግሜ ብደውል አታነሳም ይባስ አስደነገጠቸኝ ወዲያዉኑ ደበረኝ ከቤት ወጣውና በረንዳ ላይ ተቀመጥኩ ትንሽ ቆይቶ በሩ በሃይለኛ ተንኳኳ ዝም አልኩ ደግሞ ተንኳኳ ማነው ብል መልስ የለም አሁንም ከቅድምሙ በባሰ ጩህት ተንኳኳ ማነው አቦ መጣው ብዬ በብስጭት በሩን ከፍትኩት… ክፍል 6 ይቀጥላል

❤4👍2
yoni tom_tom via @vote
ከላይ ባለው ፅሁፍ ላይ በሩን ያንኳኳው ሰው ማን ነው?
public poll
ሔዋኔ🙍♀️ – 7
👍👍👍👍👍👍👍 50%
@Dani_Tad, @aklogbrhanu, @Jveroxa, @terryGodsgirl, @Dagmawi111, Barkot, miri
ጏደኛዬ🙎♂️ – 4
👍👍👍👍 29%
@SORETII7, @sami11w, @Lyd_ia, @Temshka
ወንድ ተከራይ🙎🏻♂️ – 2
👍👍 14%
@brshye_enate, @hanii
ሴት ተከራይ🙎🏻♀️ – 1
👍 7%
@WithChrist
👥 14 people voted so far.

ሄዋኔ
ክፍል 6
ሄዋኔን አየኋት ማመን አቃተኝ ከፍቶት የነበረው ፊቴ ፈገግ ለማለት ሲሞከር ታወቀኝ እ… እንዴት ነሽ ሰላም ነዉ አልኳት እየተደናበርኩ ደና ነኝ ብላ አቀፈችኝ በዚህ መሃል አንዷ ተከራይ ዮኒዬ እንዴት ዋልክ ብላኝ አለፈች ወዲያው ሄዋኔም እጇን ከወገቤ ላይ አንስታ እንግባ አለችኝ እኔም እጇ ላይ የነበረውን ፌስታል ተቀብዬ እጇን ይዤ እቤት አስገባኋት እኔም እሷን አስቀምጬ ቤቱን ማጽዳት ጀመርኩ። እያጸዳው በመሃል እራት እንደሌለ ትዝ አለኝ እየሮጥኩ ኩሽና ገባው ምንም ነገር የለም ከውጪ takeaway ለማምጣት ለሄዋኔ ሳልነግራት ወጣው የጠፋው ልጁ እንደተገኘለት አባት በደስታ መዝለል ጀመርኩ የማውቀው ሁሉ ቤት ሄጄ ለሄዋኔ ሚሆን ምግብ አጣው ነገር ግን atm card ይዤ ስለነበር ለእራት ሚሆነን ብር አወጣውና እቤት ተመለስኩ ። እቤት ስገባ ሄዋኔ ቤቱን አጽድታ ስልኳን እየነካካች አገኘኋት የት ሄደህ ነው አለችኝ አይን አይኔን እያየች አይ እዚ ጎረቤት አልኩና መጣው ቆይ ጠብቂኝ ልብሴን ልቀይር መጣው አልኩና ወደ መኝታ ክፍል ገባው ለሄዋኔ የሚሆን ደስ የሚላት አይነት አይነት ልብስ እየፈልኩ በመሃል የሄዋኔን ድምጽ ሰማው…እኔም እኮ ናፍቀሀኛል ግን ታውቅ የለ ስራው ተደራርቦብኛል ለምን አትረዳኝም አንተ እንዴ እያለች ትጮሃለች በለኝ ማለት ጀመርኩ ለባብሼ ጨረስኩና ወደ ሄዋኔ ሄድኩኝ። ገና እንዳየችኝ ቆይ ግን የት ልትሄድ ነው እንዲ ጽንጥ ያልከው አለችኝ አረ አብረን ነው የምንሄደው ብዬ እጇን ይዤ ከተቀመጠችበት አነሳዋት ልክ የጊቢ በር ላይ ስንደርስ ዮኒ እቃ እረስቻለው ብላ ቆመች መጣው እኔ አመጣልሻለው ብዬ ቦርሳዋን ይዤ መጣው ከዛም አሪፍ የሆነ ምግብ ወደምናገኝበት ምርጥ ቤት ይዣት ሄድኩኝ ቤቱን በጣም ወደደችው መሰለኝ ገና ከመቀመጣችን አይገርምም እስከዛሬ መጥቼ አላውቅም ወይኔ በናትህ አለች የረጅም ጊዜ የቤቱ ደንበኛ እመስል እ…አይደል አሪፍ ቤት ነው አልኳት እንድናወራ እንኳን እድል ሳይሰጠን ምን ልታዘዝ ብሎ አጠገባችን ስግጥ አለ ምን እንብላ ምረጪ ብዬ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄድኩኝ። ከሄዋኔ ጋር መገናኘት ከጀመርን ቆየን ነገር ግን እስከዛሬ የረባ ነገር አውርቻት አላውቅም አሁን ግን ማውራት አለብኝ ብዬ እራሴን እያነቃቃው ወደሷ ሄድኩኝ ከመቀመጤ ምንው እስካሁን አልተሻለህም እንዴ አዎ በናትሽ አሁን ላይ ምንም አልልም እንዴ እኔ እኮ ጠዋት አመመኝ ስላልከኝ ሳላየው አላድርም ብዬ ነው ደሞ አይዞህ እሺ ይሻልሃል እኔን አለችኝ ንግግሯ ልቤን ነካው የልብ የልብ ተሰማኝ እውነተኛ ሄዋኔን ያገኘው መሰለኝ ከሁሉም ሰው የተሻለ ሰው እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አረገችኝ አመሰግናለው ብዬ ፈገግ አልኩ አረ አዳም ግን እንዴት እድለኛ ሰው ነው አጠገቡ ቁጭ አለች ወሰዳት አይ መከራችን በአዳም እድለኝነት እየተገረምኩ የታዘዘው እራት መጣ በልተን ጨረስንና የሆድሆዳችንን ማውራት ጀመረን በመሃል ስለ ስራ ተነሳና አንድ የስራ ዶክመነት እኔ እቤት እንደረሳች አስታወሰች ችግር የለውም እናመጣዋለን ሰአቱን ሳየው ሳየው ሄዷል ለ5 ሩብ ጉዳይ ይላል በቃ እንሂድ ብዬ አስተናጋጁን የሂሳብ ቢሉን እንዲያመጣ ስነግረው እኔ ነኝ ምከፍለው እኔ ነኝ እየተባባልን ጭቅጭቅ ጀመርን ቢጨንቀኝ ብሩን አስቀምጬ መልስ ሳልጠብቅ ተነሳው ደሞ እኮ ደና መልስ እራሱ አልነበረም እየተነጫነጨች ወጣች። ምቼም በዚ ሰአት ታክሲ አይታሰብም እያልኩ እየነገርኳት ትንሽ እንደሄደን ራይድ አገኘን እና ወደ ቤት መሄድ ጀመርን ሄዋኔ በጣም ደክሞት ስለነበር ትከሻዬ ላይ ጋደም እንዳለች ቤት ደረስን አቅፌ ቤት አስገባኋት ደሞ ተሸከምኳት አላልኩም አድራ እቤት እንደገባን ዉሃ ጠጥታ ከነቃች በኋላ ዶክመንቱን ከጠረቤዛ ላይ አንስታ በቃ ወደ ቤት ልሂድ ብላ ቆመች አረ እንዴ ምን ሆነሻል ሰአቱ እኮ በጣም መሽቷል በፍጹም አትሄጂም እዚው እደሪና ነገ እሸኝሻለው ብይ የሳሎኑን በር ቆለፍኩት ከዛም ወደ መኝታ ክፍል ሄድኩኝና ለሄዋኔ ፒጃማ ሚሆን ቁምጣና ሰፊ ቲሸርት ይዤላት መጣው እኔ መኝታ ክፍል መቀየር ትችያለሽ ብዬ ሰጠኋት ፒጃማ ቀይራ ተጣጥባ መጣች ቁምጣዬን እሷ እግር ላዬ ሳየው ሳቄ መጣ ምነው እብድ መሰልኳ ብላ በራሷ ሳቀች አረ እንደውም አንቺ ላይ ያምራል እና የት ትተኛለሽ ወይም እኔ ሳሎን ፍራሽ አንጥፌ እተኛለው አንቺ እኔ ጋር ተኚ አልኳት አይ እኔ ፍራሽ ላይ እትኛለው እንደውም ከአልጋው ፍራሹ ይሻለኛል አለች እንግዲ ምን ይደረጋል እንደተመቸሽ ብዬ ፍራሽና 1 አንሶላ comfort ብርድልብስ አምጥቼላት መልካም አዳር ተመኝቼ ወደ መኝታ ክፍል ገባው የለሊት ልብስ አድርጌ የዘውትር ልምዴን አከናውኜ ጋደም ብዬ ስለ ዉሎዬ ማሰብ ጀመርኩ ከደቂቃዎች በኋላ በሩ ተንኳኳ ዮኒ ዮኒ ብላ ተጣራች ምነው በዚ ሰአት ብዬ ከአልጋዬ ተነስቼ…ክፍል 7 ይቀጥላል

የልጅነት
የልጅነቴ ፀሎት ናፈቀኝ ተንበርክኬ ምህረትን ምልምንበትን "ሳላውቅ በስህተት አውቄ በድፍረት የምሰራውን ሀጢያት ይቅር በለኝ" የሚለው ቆይ ግን ለምንድነው በጉብዝናዬ ወራት ፈጣሪን ማሰብ ባለብኝ ጊዜያት ትልቁ እና ትንሹ ሀጢያት የሚለውን መፅሀፍ ገዝቼ ማንበብ የጀመርኩት ወይ ጉድ ያሰኛል እንጃ ብቻ ጌታ ወደ ልጅነታችን ፀሎት ይመልሰን አሁን አሁንማ እኮ ጭራሽ ብሶብናል ጌታችን በቃሉ ላይ ያስተማረንን ፀሎት እራሱ ማሳጠር ጀምረናል ↘️
"አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር
ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ
እንቅልፌ መጣ"
ብለን ሀሳባችንን በእግዜር ሳይሆን በነገ ተስፋችን ላይ በራሳችን ጉብዝና ብለን በምንጠራው ላይ አድርገን እንተኛለን ታዲያ ጌታ መቼ ይጨክናል ምህረት አያልቅበት አሁንም መልሶ ይምረናል ጌታችን ሆይ ወደ ልጅነታችን ፀሎት መልሰን ሳናውቅ በስህተት አውቀን በድፍረት ስለበደልንህ ይቅር በለን🙏🙌 አሜን‼️‼️

❤4
🤩አንዳንዴ ይሄ የቴሌ ቴክስት ደስ ይለኛል ብድርዎ በሙሉ ተከፍሏል... አስቡት እዳን እንደመክፈል ሚያስደስት ነገር የለም የህይወት ሀጥያት እዳችንንስ?? እሱን ደሞ እየሱስ ከፍሎታል ያዉም በነፃ እንዲሁ በፀጋ የቴሌውን ብድር ግን እራሳችን አልያም ሌላ ስው ነው ሊከፍለው ሚችልው ከዛ ነው ብድርዎ በሙሉ ተክፍሏል የምንባለው የህይወት እዳችንን ግን እየሱስ በመስቀሉ ስራ ከፍሎልናል🤩🙌🏾 ዛሬ ይሄን እያሰባቹ ዋሉ መልካም ቀን ጌታችን ሆይ እናመሰግንሀለን🙏🏾🙌🏾
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
❤2
ይቅርታ አድርጉልኝና እንደ አማኝ ስርአት የራቀዉ የአምልኮ ዝግጅት የለም አሁን ባለንበት ጊዜ መቼም ይህን ያላስተዋለ የለም አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ካልሆነ በቀር አዎ ሁላችንም የዳነዉ በጸጋ ነው ግን ደግሞ በጸጋ መዳናንችን ስርዓት ካለመያዝ ጋር አይገናኝም መቼም formal ስለመሆን እያወራሁ እንዳልሆነ ግልጽ ነው ወትሮም እግዚአብሔር ለፍቃዱ የሰጠዉ ሰዉ አካሄዱ ከባድ ነዉ። ልጅ እያለሁ ወጣቶች ሚከራከሩበትን ሀሳብ ልብ ሰጥቼ አዳምጥ ነበር የሚከራከሩት ተንበርክኮ እና ሳይንበረከክ ስለመጸለይ ነበር ያነሱ የነበሩት ሀሳብ ዉሀ እንኳን አያነሳም ብቻ ሳነሳዉ ከነበረው ሀሳብ ጋር አዛምዳችሁ አሰላስሉት አንተስ ካላችሁ እኔ በስርዓት ማምለክ ነዉ ምፈልገው። በእዉነት ከልቤ ልመርቃችሁ እግዚአብሔር ለገዛ ፍቃዳችሁ አሳልፎ አይስጣቹ🙏
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
@yonitomtom
❤5👍1🥰1😍1
ፍ❤ር
አምላክ ለኛ ያለዉን ፍቅር መዉደድ ይበልጥ የምንረዳዉ ከሱ የተካፈልነዉን ፍቅር ልክ በምግብ ቋንቋ ስንቀምሰዉ ነዉ ቆይ ላብራራዉና ላስረዳቹ እሺ ካላቹ ልቀጥል አምላክ እኛን ሲወደን ያለ ምክንያት ነዉ ከዚም ብሶ ሚወደድ ነገር ሳይኖረን። የኢየሱስ ፍቅር የሚጠሉትን እና የሚሰድቡትን መዉደዱ ነዉ የእኛን የሰዉ ልጆች ደግሞ ሚወደንን መዉደድ ነዉ እሱም ሚከብደን ጊዜ አለ ለምሳሌ ብዙዎቻችን እስከዛሬ እንዲህ ብለናል የሆነን ስወደዉ አይወደኝም እሱ ሲወደኝ ደግሞ እኔ አልወደዉም ይሄ ሌላ ግኝት አይደለም ሰዉ መሆናችንን ማሳያ ነዉ ስለኔ ግል ህይወት ሳወራ ሰሞኑን ከ 4 ዓመት (ወጋሁት ጊዜዉን😂🙌) በኋላ ጭልጥ ያለ ፍቅር ያዘኝ ከበድ ያለ ይሄ ምፅፍላቹ ታሪክ ሀሳብ የመጣልኝ በዚሁ ሰሞን ነዉ ሰዉ እኛን ሳይወደን መዉደድ ከባድ ነዉ እግዚአብሔር እኔንም እንዲረዳኝ ፀልዩልኝ🙌 ወደ መጀመሪያው ሀሳብ ስመለስ እኔን በያዘኝ ፍቅር የተረዳሁት እና ይበልጥ የገረመኝ ፍቅር የኢየሱስ ፍቅር ነዉ ለኛ ያለዉ መዉደድ ያስገርመኛል በዚሁ አጋጣሚ ስለትዳር እና ስለ እጮኛ ማትፀልዩ ሰዎች ወዪዉላችሁ ፀልዩ እግዚአብሔር ያሰበዉ ይሻላችኋል በዚህ ዙሪያ ያለኝን ታሪክ ሌላ ጊዜ አጫዉታችኋለዉ ወዳችኋለዉ❤🙌

🔥2👍1
ቸርች የተሰበክነውና ባሰብኩት ቁጥር ምፅናናበት ስብከት😊!
የእግዚአብሔር ተስፋ ከሞተ ነገራችን ጋር አብሮ አይሞትም።
(ሙሴ ሲሞት የእስራኤል ተስፋ አልሞተም ነበር)
እግዚአብሔር አንዱ መንገድ ባይሳካ ሌላ መንገድ አለው።
በእግዚአብሔር ተስፋ መቁረጥ እግዚአብሔርን ማሳነስ ነው።
እግዚአብሔር ለሰጠው ተስፋ ታማኝ ነው።
ኢያሱ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
² ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።
…
⁵ በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም።

👍1🔥1