Ethio Standard
5.56K subscribers
5.67K photos
31 videos
6.05K links
Ethio Standard
Download Telegram
አክቲቪስት እና የሕ/ተ/ም/ቤት አባል መሐመድ አልሩሲ እንቅፋት እንደበዛበት ይናገራል!!
***

አገራችንን ለመገንባት እየጣርን ባለንበት ግዜ ለሀገራችን እና ለሕዝባችን እየሰራን ያለነው ተጠቅመው አብሮ ከመገንባት ይልቅ የምንገነባውን ለማፍረስ የሚጥሩ አካላት መኖራቸው በጣም ያሳዝናል።

በትሑት አቅማችን ለህዝባችንንና ለአገራችንን እየመከትን እና እየታገልን ባለንበት ጊዜ በምላሹ ትግላቸውንና ጥረታቸውን ለሀገራችን እና ለህዝባችን ለመከላከል ከማዋል ይልቅ እኛን ለመጣል የሚታገሉንና የሚጥሩ አካላት መኖራቸው በጣም ያሳዝናል…!

ሀገራችን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለህጋዊ መብታቸው ለክብራቸው ለስማቸው ጠንክረው በብርቱ የመታገል መብት እንዳላቸው እና የሀገራችን ህዝቦች በቋንቋዎች እና ቀለሞች ቢለያዩም ሀገራችን አንድ እንደምታደርገን ድሮም አሁንም ትልቅ እምነት አለኝ።ያም በአንድ ሀገር ህዝቦች መካከል ትንሽ ልዩነት ቢፈጠርም የሀገር ጥንካሬ እንጂ በምንም መልኩ ለችግር እና ያለመግባባት ምንጭ ይሆናል ብየ በጭራሽ አስቤ አላውቅም።

እናም በአላህ ቸርነት ከዚያም በኢትዮጵያውያን አበራታችነት እና በረከት በልቤ ውስጥ በወርቅ ቃላት የተቀረፀ የምኮራበት ታሪክ መሥራት ችያለሁ።

በእውነት ላይ የታነፁት መርሆቻችን በአላህ ፈቃድ አይለወጡም...!

ማንንም ጠልተን አናውቅም፣ አላጭበርበርንም፣ አልሰረቅንም፣ አልዋሸንም፣ ማንንም ለራሳችን ብለን አልተበቀልንም..!

ይልቁንም በክፉ የጀመረንን ሰው በበጎነት እና በቸርነት እናስተናግደዋለን። በጠብና በጥላቻ ወደ እኛ የመጣን ሰው በፍቅር እና በደስታ ፊት እንገናኘዋለን...!

መልስ መስጠት አቅቶን ሳይሆን አንድነትን የሀገርንና የህዝብን ብልፅግናን የማጠናከር አላማ ስላለን ነው።

ንግግር አበዛን መሰል እና የዝምታ ጊዜ ያስፈልጋ
BREAKING: Supreme Court unanimously upholds election of President-elect William Ruto in last month’s presidential poll

“We declare the election of the 1st Respondent as president-elect to be valid under Article 143 of the constitution”
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሕክምናቸውን አጠናቀው ነገ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ አዲስአበባ እንደሚደርሱ ተጠቆመ።
ቅዱስነታቸው ሕክምናቸውን አጠናቀው በነገው ዕለት ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ሲመለሱ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸውም ታውቋል።
ስድስት አትሌቶች በልምምድ ላይ እንዳሉ የትራፊክ አደጋ ደረሰባቸው

እሁድ እለት በልምምድ ላይ የነበሩ ስድስት ስማቸው ያልተጠቀሰ አትሌቶች ደርቦ በመሄድ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ተገጭተው ከባድ እንዲሁም ቀላል የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው በኦሮሚያ ልዩ ዞን አዲስ አበባ ዙሪያ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ የሆኑት ረዳት ኢኒስፔክተር ድሪባ ኩማ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ላይ ስልጠና ላይ በነበሩ ስድስት አትሌቶች ላይ ሲሆን ኮድ 3 55562 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ከሰንዳፋ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ላይ በነበረበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡አደጋው ልዩ ቦታው ገብርኤል መሳለሚያ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ላይ ሲሮጡ በነበሩ ስድስት አትሌቶች ላይ አደጋ ማድረሱ ተነግሯል፡፡

አያይዘውም እንደገለጹት አደጋው ከደረሰ በኃላ አትሌቶቹ ወደ አዲስ አበባ ምኒሊክ ሆስፒታል መወሰደቸውን እና በቀጣይ ልምምድ በሚያደርጉበት ጊዜ መኪና መንገድ ወጣ ያለ አካባቢ እንዲሆን እንዲሁም በእንቅስቃሴያቸው በሙሉ ጥንቃቄም እንዳይጎድላቸው ረዳት ኢኒስፔክተር ድሪባ ኩማ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
“የሰላም ጥሪ” ለማቅረብ የተሰባሰቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ተከለከሉ
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ “አስቸኳይ የሰላም ጥሪ” ሊያቀርቡ የነበሩ የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች፤ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ተከለከሉ። ድርጅቶቹ ዛሬ ማክሰኞ ጷጉሜ 1፤ 2014 ጋዜጣዊ መግለጫውን ሊሰጡ የነበረው በአዲስ አበባው ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ነበር።
ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ የነበሩት ድርጅቶች የተሰባሰቡት፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ስላሳሰባቸው መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን አስቀድመው በላኩት ደብዳቤ ገልጸው ነበር። ጋዜጣዊ መግለጫው ሊሰጥ በታቀደበት ሆቴል የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ እና ሲቪል የለበሱ የጸጥታ አካላት ነበሩ።
ሲቪል ከለበሱ የጸጥታ አካላት መካከል “ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ነው የመጣሁት” ያለ አንድ ግለሰብ፤ መግለጫውን ለመዘገብ በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞችን ለማናገር ሙከራ ሲያደርግ ተስተውሏል። ይኸው ግለሰብ ጋዜጠኞችን ለምን በሆቴሉ እንደተገኙ እና ከየትኛው መገናኛ ብዙሃን እንደመጡ ሲጠይቅ ነበር።
ግለሰቡ ጋዜጠኞችን ካነጋገራቸው በኋላ የሆቴሉ ሰራተኞች “የአሁኑ ስብሰባ አይኖርም” በማለት ለጋዜጠኞቹ አስታውቀዋል። መግለጫውን ሊሰጡ የነበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮች በተመሳሳይ ጋዜጣዊ መግለጫውን እንዳያደርጉ መከልከላቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ሆኖም ጋዜጣዊ መግለጫውን “ማን እንደከለከለው ሊነግሩን አልፈለጉም” ሲሉ የክልከላውን ውሳኔ ያስተላለፈው አካል ማን እንደሆነ አለማወቃቸውን አስረድተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
በአሁኑ ጦርነት ግንባር ላይ ባለመሆኔ አዝኛለሁ’ አምባሳደር ባጫ ደበሌ
በሰሜን ኢትዮጵያ ከተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ስማቸው ሲነሳ ከነበሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል ጄኔራል ባጫ ደበሌ አንዱ ናቸው።

ከወራት በፊት ከጦር ሠራዊት አመራርነታቸው ወጥተው በአምባሳደርነት የተሾሙት ጄኔራል ባጫ፣ ከሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ ጎረቤት እና የምሥራቅ አፍሪካ ኃያል አገር በሆነችው ኬንያ አምባሳደር ሆነው በቅርቡ ሥራቸውን ጀምረዋል።

ከወታደራዊው ኃላፊነት ወጥተው በዲፕሎማሲው ዘርፍ ከተሰማሩ በኋላ አምባሳደር ባጫ ደበሌ የመጀመሪያውን ቃለ ምልልሳቸውን ከቢቢሲ ጋር አድርገዋል።



ቢቢሲ፡ ህወሓት በቅርቡ ለተለያዩ አካላት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከመንግሥት ተወካዮች ጋር በምስጢር ተወያይቻለሁ ብሎ ነበር። ይህ እውነት ነው? ከሆነ ውይይቱ የት ተደረገ? እነማን ተገናኙ?

አምባሳደር ባጫ፡ ይህ በምስጢር ተገናኙ የሚባለውን ነገር አላውቅም። ህወሓት የሚናገው ነገር በሂሳብ ነው። አንድ እና አንድ ሁለት ነው ይላል። ከፈለገም አንድ ሺህ ነው ይላል። ስለዚህ ህወሓት ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲል የፈለገውን ነገር ይላል። በምስጢር የተገናኙበትን ሁኔታም አላውቅም፤ ሁለተኛ ደግሞ ቦታውንም አላውቅም።

በምስጢር የሚገናኙበት ምንም ምክንያትም የለም። ምክንያቱም በግልጽ ድርድር ያስፈልጋል ተብሎ ኮሚቴ ተዋቅሮ እያለ፣ በድብቅ የሚኬድበት ምንም ምክንያት ያለ አይመስለኝም።

ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የአሁኑን ጦርነት የትግራይ ኃይሎች ጀመሩ ሲል ይከስሳል። ምን ማስረጃ አለው?

አምባሳደር ባጫ፡ ህወሓት ቆቦን ይዤያለሁ ብሎ ሲያወጅ የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነቱን አለመጀመሩ ለማወቅ ይቻላል። ጦርነት ተቀሰቀሰብኝ የሚል ኃይል በምን ቅጽበት ነው የኢትዮጵያን ሠራዊት፣ ዋጃን ፊት ለፊቱ አድርጎ መከላከል የያዘን የኢትዮጵያ ሠራዊት፣ በቆቦ በስተቀኝ ደግሞ የዞብል አምባን መሠረት አድርጎ መከላከል የያዘን የኢትዮጵያን ሠራዊት፣ በአንድ ጊዜ ንዶ ቆቦን የሚይዝበት ተዓምራዊ ኃይል የሚኖረው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ማጥቃቱን ቢጀምር ኖሮ ህወሓት ቆቦን ሊይዝ አይችልም። ምክንያቱም አንድ ሰው፣ ሁለት ሰው ሦስት ሰው አይደለም የምትልከው። በውጊያ ሕግ አንድን ጠላት ስታጠቃ የኃይል የበላይነት ሊኖርህ ይገባል። እኛ ልናጠቃ ብንፈልግ ኖሮ እኮ በዚያ አካባቢ የኃይል የበላይነት ፈጥረን ነው የምነገባው።

ስለዚህ ህወሓት በዚያ አካባቢ ያሰለፈው አዲስ ያመጣው ኃይል ስድስት አርሚ ነው። አንዱ አርሚ ሦስት ክፍለ ጦሮች አሉት። ወደ 18 ክፍለ ጦር ነው እዚያ ያሰለፈው ማለት ነው። ስለዚህም የኃይል የበላይነት አለው ማለት ነው። ከእኛ የኃይል የበላይነት ነበረው።

ቢቢሲ፡ በቆቦ ግንባር ብቻ ማለት ነው ይኼ?

አምባሳደር ባጫ፡ በቆቦ ግንባር አዲስ ያሰለፈው ማለት ነው። አንድን ማጥቃት ስታደርግ ደግሞ የኃይል የበላይነት ከሌለህ አጥቅተህ የምትፈልገውን ግብ መያዝ አትችልም። ስለዚህ እኛ የምናጠቃ ቢሆን ኖሮ፣ የኃይል የበላይነት እንፈጥራለን፣ ወያኔ መልሶ በማያጠቃበት ሁኔታ ነው የምናጠቃው እና ቆቦን መልሶ የሚይዝበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ምናልባትም በተገላቢጦሽ መኾኒን እና የመሳሰሉትን ከተሞች መቆጣጠር እንችል ነበር።

ለማጥቃት ለማጥቃቱ እኛ እኮ ከደብረ ሲና ስናስወጣቸው የኃይል የበላይነት ፈጥረን የውጊያ ቀጣይነትን ጠብቀን፣ ብረት በግለቱ ነው የሚቀጠቀጠው እና መቀለ ማድረስ ይቻል ነበር።

ግን ደግሞ ያንን ትተን ለሰላም ሲባል፣ ሕዝብ እንዳያልቅ፣ ሕጻናት እንዳያልቁ ሲባል አላማጣ ነው ጦርነቱ የቆመውና የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ያወጀው። ስለዚህ እኛ አላጠቃንም። እኛ ብናጠቃ ልክ ከደብረሲና እንዳስወጣናቸው እዚህም እንደሱ ነበር የምናደርገው። ስለዚህ ወያኔ ራሱ አጠቃ፣ ራሱ ተጠቃሁ አለ።

ቢቢሲ፡ በዚህ ጦርነት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ዘልቆ የመግባት እቅድ አለው? መከላከያ መቀለ ቢገባ የመጨረሻው ግቡ የሚሆነው ምንድን ነው?

አምባሳደር ባጫ፡ አሁን የኢትዮጵያ መንግሥት መቀለን ነው የምቆጣጠረው፣ የሆነ ቦታን ነው የምቆጣጠረው ብሎ አቅዶ የተነሳው ጦርነት የለውም። ምክንያቱም ወያኔ የፈጠረውን በፀረ ማጥቃት የመጣውን ኃይል ማጥፋት ነው። በግልጽ የምነግርህ ወያኔ ከበረታ የኢትዮጵያን ሠራዊት ደምስሶ ኢትዮጵያን ያፈርሳል። እኛ ደግሞ ከበረታን ወያኔን አጥፍተን እፎይታ እናመጣለን። ጦርነት ነው። ይህንን ነው የምትጠብቀው። አንዱ ያሸንፋል። እኛ ጦርነቱን የመቀስቀስ ግብ አልነበረንም፤ ቢሆን ኖሮ በደንብ ተዘጋጅተን፣ የት መድረስ አለብን፣ ምን ማድረግ አለብን የሚል ነገር ትወስናለህ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ቢያጠቃ ለምንድን ነው በቆቦ በኩል የምናጠቃው? የአላማጣን እና የግራ ካሱን ተራራ ልንገፋ? ለምንድን ነው በዚያ በኩል የምናጠቃው? [መልክዓ ምድሩ] በዚያ እንድታጠቃ አይጋብዝም።

ምክንያቱም ከፍተኛ የሆኑ መሬቶች ከፊት ለፊት ነው ያሉት። እና ደግሞ ይኼ በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ የሚፈጥረው ጉዳት ከፍተኛ ስለሚሆን እንደ ማጥቂያ አቅጣጫ አንመርጠውም። የሚመረጡ ሌሎች ቦታዎች ስላሉ ማለት ነው። ስለዚህ አሁን የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔው ህወሓት ጠመንጃ እስካላስቀመጠ ድረስ ሁሉንም ዓይነት ርምጃ ይወስዳል።

ቢቢሲ፡ መቀለ መቆጠጠርም ቢሆን?

አምባሳደር ባጫ፡ ማንኛውንም ዓይነት፣ መቀለ ምንም አይደለም። መቀለ ከተንቤን ከአክሱም ከሽረ የተለየ ነገር የለውም።

ቢቢሲ: መቀለን መቆጣጠር ስል የህወሓትን ከሥልጣን አውርዶ አዲስ አስተዳዳሪ መሾም ማለቴ ነው።

አምባሳደር ባጫ፡ መንግሥት እርሱ ዕቅድ የለውም። አካባቢው ጦርነት ቀጠና ስለሆነ ህወሓትን የያዘው ሥልጣን ስለሌለ፣ የሚወርድበት ሥልጣን የለውም። ዋናው ነገር የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት የተከፈተበትን ጥቃት ደምስሶ፣ ህወሓትን አስገድዶ ወደ ውይይቱ ማምጣት ነው። አለበለዚያ ግን ጨርሶ ማጥፋት ነው የሚሆነው።

ቢቢሲ፡ ባለፈው ሳምንት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከኤርትራው አምባሳደር ጋር ውይይት ማድረጎትን ተመልክተናል። ባለፉት ቀናት ደግሞ የትግራይ ኃይሎች፤ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሠራዊት ጥቃት ከፈቱብን ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ኤርትራን ያሳተፈ ጥቃት ከፍቷል?

አምባሳደር ባጫ፡ እኔ ኤርትራን ያሳተፈ ጥቃት አላውቅም። ...የኤርትራ ሕዝብ ራሱን የመከላከል መብት አለው። የኤርትራ መንግሥት ራሱን የመከላከል መብት አለው።... አሁን መንግሥት ከኤርትራ መንግሥት ጋር አደረገ ስለሚባለው ትብብር ለማሳየት አይደለም እኔ ከአምባሳደሩ ጋር የተገናኘሁት።

የኤርትራው አምባሳደር በየነ ርዕሶም፣ እዚህ አገር ረዥም ጊዜ ቆይተዋል። የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን ናቸው። ስለዚህ እርሳቸው የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን ከሆኑ ደግሞ የመጀመሪያው ‘ከርተሲ ኮል’ [ትውውቅ] የሚደረገው ከእርሳቸው ጋር ነው። ከእርሳቸው ጋር መጀመሪያ ከተገናኘሁ በኋላ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ጋር እገናኛለሁ።

ስለዚህ ከእርሳቸው ጋር መገናኘቴ ህወሓት በጀመረው ጦርነት ላይ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትሰለፍ ጥሪ ለማቅረብ አይደለም። ጥሪ ለማድረግ ከሆነ እኔ ቅርብ አይደለም ያለሁት። ወይንም ደግሞ ክቡር አምባሳደር በየነ ርዕሶም ቅርብ አይደሉም። እርሳቸውም አይጠየቁም። የኤርትራ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርብ ስለሆነ መንግሥታት ይነጋገራሉ። ስለዚህ ይህ የአጋጣሚ በመሆኑ ወደዚያ ባይተረጎም።



ቢቢሲ፡ የሰላም ጥረቶች የከሸፉት የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረታዊ
ጋሎቶችን ባለማስጀመሩ እና ከበባው ባለመነሳቱ ነው ሲሉ የትግራይ ኃይሎች ይከስሳሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የአገልግሎቶቹን አለማስጀመር እንደ መደራደሪያ አድርጎታል?

አምባሳደር ባጫ ደበሌ፡ ...ለትግራይ ውሃ፣ ኤሌትሪክ እና ሁሉን ነገር የማስገባት ጉዳይ የመንግሥት ግዴታ ነው። እነሱ ስለጠየቁ የሚሆን ስላልጠየቁ የማይሆን ነገር ስለጠየቁ የሚሆን ስላልጠየቁ የማይሆን ነገር አይደለም። እነሱ ትግራይን በጠበመንጃ አጥረው፣ የጦርነት ቀጠና አድርገው፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት የፈጠረ የማያዳግም እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አውጀዋል።

እንዲህ ጦርነት አውጀህ የትኛውን የባንክ አገልግሎት ነው የምትከፍተው? የቴሌኮም ሠራተኞችን ነው ወደ እዚያ የምትልከው? የመብራት ኃይል ሠራተኛ የውሃ ሠራተኛ ልትልክ ነው?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በነበረበት ወቅት እንደዚህ ዓይነት ሥራዎችን ሊያስቀጥሉ የሄዱትን ሠራተኞች እኮ ገድለዋል። አንድ ሁለት ሦስት አይደለም። ሁሉም ቦታ የተሰማሩትን አጥፍተዋቸዋል። መድኃኒት ሲላክ ለራሳቸው ተጠቅመዋል...ስለዚህ እንዴት አድርጎ ነው አንድ ጦርነት ባለበት ቀጠና፣ ይህንን ሲጠይቁት የነበረውን ነገር የምትሟላው? . . .

ቢቢሲ፡ ለድርድሩ መክሸፍ እና ለጦርነቱ ድጋሚ መጀመር ገፊ ምክንያቶች ታድያ ምንድን ናቸው?

አምባሳደር ባጫ ደበሌ፡ ወያኔ። ወያኔ ያለ ጦርነት አይኖርም። ወያኔ ሁለት ትልልቅ ነገሮች አሉት። እያቀያየረ የሚጠቀምባቸው ሁለት ካርዶች አሉት። አንዱ ካርድ ቅጥፈት፣ ውሸት ነው። አንድን ውሸት በሌላ ማለት ነው። እርሱም አሁን ባለንበት ሁኔታ ጦርቱን ሲጀምሩ ዋሹ። ሁለተኛም ደብረ ሲና ያደረሳቸውንም ጦርነት ሲጀምሩ መንግሥት አጠቃኝ ብለው ጀመሩ። ደብረ ሲና ደረሱ።

ሦስተኛው ደግሞ አሁን እኛ ስለእነርሱ ማጥቃት ምንም እሳቤ ሳይኖረን 18 ክፍለ ጦር አሰማርተው፣ 18 ለስድስት ማለት ነው። ምናልባት ስድስት ክፍለ ጦር ነው ቆቦ አካባቢ ሊኖር የሚችለው ብዬ ነው የማስበው። ከዚያ ያነሰም ሊሆን ይችላል። ይህንን ሁሉ ክፍለ ጦር ቆቦ አስቀምጠው ከዓለም ምግብ ድርጅት ነዳጅ ሰርቀው፣ ምግብ ሰርቀው፣ ሕጻናትን አሰልፈው ወደ ጦርነት ገቡ።

ስለዚህ ውሸትና ጠመንጃ ይዞ ነው ያለው። ሁለቱ ናቸው መጫወቻ ካርዶቹ። ጠመንጃውን በውሸት ይደግፋል። ውሸቱንም በጠብመንጃ ይደግፋል።. . .በተጨማሪም ሁልጊዜ ወደ ድርድር ሲገባ አደናቃፊ ቅድመ ሁኔታዎችን ያመጣል። ምክንያቱም ወደ ድርድር ከገባ ጠመንጃ ሊያስቀምጥ ነው። ህወሓት ደግሞ ጠመንጃ አስቀምጦ እንቅልፍ አይወስደውም። ስለዚህ ዋናው የዚህ ችግር ባለቤት ህወሓት ነው። ህወሓት ደግሞ የኢትዮጵያ ችግር ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ችግርም ነው።

ቢቢሲ፡ ጦርነቱ መልሶ ከተጀመረ በኋላ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች ጦርቱን ለማስቆም ሙከራዎችን እያደረጉ ነው?

አምባሳደር ባጫ፡ በግልጽ የምናውቀው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሁሉም ኃይሎች ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር መግባት አለባቸው ማለቱን ነው። ነገር ግን የሚጠበቀውን ያህል ውግዘት የለም።

...ተጠቅቻለሁ ብለህ ዘለህ አማራ ክልል መግባት የመጠቃት ምልክት አይደለም፤ የማጥቃት አንጂ። ይኼ እየታየ ለሕዝብ የተላከ እህል እየዘረፈ፣ ነዳጅ እየዘረፈ፣ ይኼ ለጦርነት እና ለከፍተኛ ማጥቃት ዝግጅት መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን ማውገዝና ጠመንጃውን አስቀምጦ ወደ ድርድር እንዲገባ ተጽዕኖ መፍጠር ተገቢ ሆኖ እያለ፣ እኔ ከዓለም ማኅበረሰብ ‘እንደው ሁሉም ወገኖች’ የሚል ካልሆነ ሌላ አላየሁም። ሁሉም ዝምታን ነው የመረጠው።

. . . የዓለም ማኅበረሰብ የአፍሪካ ቀንድን ሰላም፣ ወይንም ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ ሰላም የሚፈልግ ከሆነ፣ ጠመንጃውን እንዲያስቀምጥ መደረግ አለበት። ስስለዚህ የዓለም ማኅበረሰብ ይህንን ተጽዕኖ ማድረግ አለበት። ነገር ግን ለጊዜው እኔ በግልጽ ያየሁት ነገር የለም።

ቢቢሲ፡ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሲጀመር እርሶ ጄኔራል ነበሩ። በጦርነቱ ላይ የኢትዮጵያን ሠራዊት በመምራት ተሳትፈዋል። አሁን ደግሞ ዳግም ጦርነቱ ሲያገረሽ ዲፕሎማት ሆነው ኬንያ መጥተዋል። ይህ እርሶ ላይ የሚፈጥረው ስሜት ምንድን ነው?

አምባሳደር ባጫ ደበሌ፡ እኔ የሚፈጥርብኝ ስሜት፣ በአሁኑ ጦርነት እዚያ አለመሆኔ በጣም አሳዝኖኛል። ግን ደግሞ ይህም ትልቅ ተልዕኮ ስለሆነ ይህንኑ ተልዕኮዬን እቀጥልበታለሁ።

መጀመሪያ ጥሪ ተደርጎ ከመከላከያ ከወጣን በኋላ ነው ከጓደኛዬ ጋር የተመለስነው። ስመለስ እኔ በደስታ እግዚአብሔር ልዩ ነገር እንደፈጠረልኝ በግልጽ ተናግሬያለሁ። ያኔ ስሜቴ እርሱ ነው። ኢትዮጵያን መከላከል ስለሆነ ማለት ነው።

ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች ጋር እኔ ረዥም ዓመት ኖርያለሁ
ስለዚህ የሚሰሩትን ነገር በደንብ አድርጌ አውቃለሁ። በዚያ ላይ አገርን ለመበተን ሲሮጡ፣ እነሱ ጠመንጃ ሲመዙ፣ ቢያንስ ይህንን ለመከላከል መሰለፌ በጣም ደስታን ሰጥቶኛል፤ ግዳጄን ተወጥቻለሁ ብዬ ነው የማስበው በዚያ ሰዓት።

ቢቢሲ፡ የአምባሳደርነት ሹመትዎ እንደተሰማ፣ ይህ ለእርሳቸው ሹመት አይደለም ዲሞሽን [ዝቅ መደረግ] ነው ያሉ ነበሩ። እርስዎ እንደዚያ ተሰምትዎታል?

አምባሳደር ባጫ ደበሌ፡ ኢትዮጵያን ለማገልገል ዲሞሽን አይደለም። ወደ ኋላ ልውሰድህና ያልኩትን ላስታውስህ። ልክ ለውጡ እንደመጣ በሰጠሁት ቃለ ምልልስ ላይ ‘ተመለስና አገርህን አገልግል ብትባል ምን ሃሳብ አለህ?’ ተብዬ ተጠይቄ ነበር። መልሴም ‘እኔ ባለሁበት ፖዚሽን ሳይሆን፣ እንደ አንድ ተራ ወታደር ኢትዮጵያን አገለግላለሁ’ ነበር ያልኩት።

አሁንም ኢትዮጵያ ጭንቅ ላይ ነው ያለችው። እኛ የምንሰራበትን፣ የእኛን ምቾት ፈልገን፣ እዚህ መስራት አለብን፣ እዚያ መስራት አለብን፣ ብለን የምንመርጥበት ጊዜ አይደለም። አሁንም እዚህ ቦታ ላይ ገብተህ አገልግል ከተባልኩ፣ አይደለም አምባሳደር፣ ተራ ጥበቃ ሆኜ ኢትዮጵያን አገለግላለሁ።

. . . እኔ እያለሁ ወጣቶች ናቸው እያለቁ ያሉት። ስለዚህ አገራችን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እያለች፣ እዚህማ አልሰራም ከእኔ ብቃት በታች ነው። እኔ እነደዚህ ዓይነት ሰው ነኝ እና እዚህ አልሰራም የሚባልበት ወቅት አይደለም አሁን። ያንን ለልጆቻችን እንተውላቸው።

ልጆቻችን ቦታ እየመረጡ ካልፈለጉ የሚተዉበትን ሁኔታ እንፍጠርላቸው። ያንን የምንፈጥረው እኛ ደግሞ፣ ወደላይም፣ ወደ ታችም፣ ወደጎንም እየሄድን ሁሉም ቀዳዳ መሸፈን ትችላለህ በሚባልበት ቦታ ሁሉ ገብተን በመሸፈን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ነው።

ስለዚህ እኔ በተመደብኩበት ቦታ በጣም ደስተኛ ነኝ። በጣም በሚገርም ሁኔታ እዚህ አገር ትልቅ ሥራ ነው ያለው። አሁን ለእናንተ ይኼ ይኼ ነው ብዬ አልነግራችሁም። ነገር ግን እኔ እዚያ ከተሰለፈው ሠራዊት ባልተናነሰ የምትሰራበት ከፍተኛው ግንባር ነው ይኼ። ስለዚህ በደስታ እሰራለሁ አገሬን አገለግላለሁ።
ይድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤
ይድረስ ለአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፤
*****
አብን እሁድ ነሐሴ 29/2014 ዓ/ም የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ምልዓተ ጉባዔው ባለመሟላቱ ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል። እውነታው ይኼ ሆኖ እያለ ባልተካሄደ ስብሰባ፣ ውይይት ባልተደረገበት አጀንዳና ተገቢ ፖለቲካዊ ምክክር ተደርጎ ባልተላለፈ ውሳኔ፤ ስብሰባ እንደተጠራ፣ አጀንዳ ተዘርግቶ ውይይት እንደተካሄደና ውሳኔዎች እንደተላለፉ ተደርጎ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ የስነስርዓት ጥያቄዎች የሚቀርቡበበት፣ ድርጅታዊ አሰራርንና መርኅን የጣሰ እንዲሁም ከዴሞክራሲ ልምምድ ያፈነገጠ የነውር ሥራ ነው። የስንስርዓታዊ ጉዳዮች መሟላት ስብሰባው ከመካሄዱና በስብሰባው ከሚወሰነው ውሳኔ እኩል ወይንም የበለጠ አስፈላጊ በመሆኑ ባልተሟላ ምልዓተ ጉባዔ ስብሰባዎች አይካሄዱም።

ለውጥ ፈር በሆኑ ጥቂት የአብን ከፍተኛ አመራሮች እየተደረገ ያለው ሁኔታ ግን ለንቅናቄው አባላትና አመራሮች ብቻ ሳይሆንም ለስርዓት ግንባታም ደንታ የሌላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሰኞ ነሐሴ 30/2014 የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርገን ውሳኔዎችን አሳልፈናል ይበሉ እንጂ የሰኞ ስብሰባ ስለመኖሩ የትኛው የድርጅቱ አካል፣ መቼና በምን መንገድ ጥሪ አስተላለፈ? ጥሪውስ ለሁሉም የማዕከላዊ አባላት እኩል ተላልፎላቸው ነበር ወይ? የድጋሚ ስብሰባ ቀኑ ሲወሰን ከስብሰባ ቦታው ርቀው የሚገኙ አባላትን የመጓጓዣ ቀናት ታሳቢ ያደረገ ነበረ ወይ? ወዘተረፈ ቀላል ግን መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል ተጨባጭ ነገር ማቅረብ አይቻላቸውም።

ባለፈው እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ማኅተም ስለያዙ ብቻ የንቅናቄው የሥራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ ያልመከረባቸውንና ያላፀደቃቸውን የኦዲት ሪፖርት እና የሪፎርም ጉባዔ (የደንብ ማሻሻያና የአመራር አመላለመል እንዲሁም አወቃቀርን ጨምሮ) ውይይት ተካሂዶባቸው የጸደቁ በማስመሰል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የደብዳቤ ልውውጦች ማድረጋቸውን ስለታዘብን፤ጉዳዩ የወንጀል ተጠያቂነትን ጭምር የሚያስከትል ጉዳይ ያለው ስለሆነ ይህንንም የሚመለከታቸው ተቋማት በተለይም የንቅናቄው በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች፣ አመራሮችና አባላት በልዩ ልዩ አማራጮች አሳውቀናል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔው የተወሰነበት ቃለጉባዔ ይምጣልኝ የሚል ደብዳቤ ስለፃፈ፤ የቦርዱን ጥያቄ አሰነባብቶና ቀባብቶ ምላሽ ለመስጠት በሚል ከስነስርዓት ውጭ ስብሰባ ተደርጎ፥ ውሳኔ እንደተላለፈ መግለጫ ማውጣት፤ በተደጋጋሚ ጊዜ የተፈፀመ ነውር እና የምርጫ ቦርድን በተሳሳተ ደብዳቤ የተሳሳተ ውሳኔና ግንዛቤ ላይ እንዲደርስ የሚደረግ የወንጀል ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር ነው። መሰል ስህተቶችን ነቅሰን ጉዳዩ ለሚመለከተው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገብተናል። ቦርዱ ተገቢውን ማጣራትና ምርመራ አድርጎ ተገቢ ውሳኔ ላይ እንደሚደርስም እምነት አለን። በተለይ ከኦዲት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ከንቅናቄው አመራሮች ጭምር ይመርመርልን ጥያቄ የቀረበበት በመሆኑ እና የምርጫ ቦርድም መሰል ጥርጣሬዎችና ጥያቄዎች ሲቀርቡለት የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን ልዩ ኦዲት እንዲሰራለት የመጠየቅ መብት ስላለው፤ ይኽንኑ እንዲያደርግ ደግመን ማስታወስ እንፈልጋለን።

መላው የአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ንቅናቄያችን የሚያደርገው የለውጥ እንቅስቃሴ ለግላዊ ጥቅማቸው ሲሉ ከገዥው ፓርቲ ጋር በተጣበቁ ጥቂት ግለሰቦች መታገቱን በውል በመረዳት፤ ፓርቲው የተሟላ ሪፎርም አድርጎ መላው ሕዝባችን የሰጠውን አደራ እንዱወጣ በተገቢው ሁኔታ ብርቱ ትግል ታደርጉ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ
ፌስ ቡክ መቼም ፌዘኞች በነጻነት የሚቧልቱበት፣ ሀሜተኞች ስማቸውን ደብቀው ወሬ የሚሰለቅጡበት፣ ዋልጌዎች ደግሞ ነጋ ብለው በማለዳ ለስድብ አሹለው የሚቀመጡበት፣ ከሰብእናችን የሚያወርዱን ብዙ አስጸያፊ ነገሮችን የምናይበት መድረክ ቢሆንም ቅሉ፤ በአንጻሩ ደግሞ በየትም በኩል አግኝተን ልንተዋወቅቸው፣ ልናዋራቸውና ሀሳብ ልንለዋወጥ የሚከብዱን እድሜያቸውን ለታላላቅ ቁም ነገር ያዋሉ፣ የማይደገም ተግባራትን ፈጽመው መቼም ከልባችን የማይጠፉ፣ እንቁ እንቁ ሰዎችን አስተዋውቆናል፣ አቀራርቦ ጓደኛ ወዳጅ አድርጎናል፡፡ ~~~~ ከእነዚህም መካከል አንዷና ዋነኛዋ ጋዜጠኛና ደራሲ ገነት አየለ ነች፡፡

ገነት አየለ ከአንድ ወገን ብቻ በሚፈስ መረጃ፣ በሚነገር ዜና፣ በሚጠረቅ ታሪክ ትውልድ ሁሉ “አሜን” ብሎ ተቀብሎ እየተጓዘ በነበረበት በዚያ የጭለማ ዘመን በድንገት ተከስታ የሌላውንም ጎን ታሪክ እንድንሰማ፣ እውነት እንድናውቅ፣ ሚዛን እንዳንስት ያደረገችን እንቁ ነች፡፡

ገነት ያውም “የህወሀት መንግስት ወደ ሀራሬ ዝምቧቤ፣ ኮለኔል መንግስቱን ለማስገደል ካልቻለ አንጠልጥሎ ሊያመጣው ነው” እየተባለ የእንጉዳይ ጀግንነት በየቀኑ እያፈራ ፍርሀት በነገሰበት ወቅት ማዕበሉን ተሻግራ የኮለኔሉን በር አንኳክታ የሚሊየኖችን ጥያቄ እያዥጎደጎደች “መስል ይጡበት” ብላ መልሶቹን በብዕሯ እየከተበች አሰባስባ በመጽሀፍ ደጉሳ ያቀረበችልን(እንደ ሀገራችን ልማድ ንግግር) የሴት ወንድ ጀግና ነች፡፡

ይህ ብቻም አይደለም! ያ ውለታው ተዘንግቶ፣ ተገፍቶ፣ ተረስቶ፣ ያለስሙ ስም እየተሰጠው ለአመታት አንገቱን በሀሰት ትርክት እንዲደፋ የተደረገው የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና አባላቱ (በተለይም ከለውጡ በኋላ) እንዲታወሱ፣ እንዲሰባሰቡ፣ ታሪካቸው እንዲነገር፣ ብዙ ብዙ ጥረት ስታደርግ አይተናል፡፡

አሁን ደግሞ የትግራይ ወራሪ ሀይል የሰሜን ሀይላችን ላይ ጥቃት አድርሶ አጎራባች ክልልን መውረርና ማሸበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ግንባር ድረስ ወርዳ መረጃ ስታካፍለን የቆየች፣ ከእኛም አልፎ አለም የኛን ሀቅ ቀረብ ብሎ በገዛ አይኑ እንዲያይና በራሱ ቋንቋም እንዲዘግብ የውጭ ጋዜጠኞችን እየመራች ይዛ በመጓዝ በርካታ አኩሪ ጀብድ የፈጸመች እህታችን ናት፡፡

ዘመን አልፎ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ በቅርብ ተቀይሮ፣ ያሰብነው ሰላምና እድገት እውን ሆኖ፣ ኢትዮጵያ የታለመላት የመፍረስ አደጋ ተገፎ በነጻነቷዋ ጉዞዋን ስትቀጥል ድርሻ ያበረከቱ፣ ያቅማቸውን ያቀበሉ ሁሉ በእውነትና በእኩልነት መድረክ ሲታሰቡና ሲሸለሙ፤ ገነት አየለ አክሊል ከሚደፉት መካከል እንደምትሆን ፈጽሞ አልተራጠርም፡፡

ረዥም እድሜ ከጤና ጋር እመኝልሻለሁ
የዛምቢያው ፓስተር ጀምስ ሳካራ ከቀናት በፊት ልክ እንደ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን መቃብር ፈንቅዬ እነሳለሁና ከነህይወቴ ቅበሩኝ በማለት በቸርቹ የነበሩትን አማኞች ጠየቀ፡፡ ተከታዮቹም በጠየቀው መሰረት ጉድጓድ ቆፍረው ከነነፍሱ ቀበሩት፡፡ ይሁንና ፓስተራቸው ባለው ቀን ህይወት ዘርቶ መቃብሩን ፈንቅሎ ሊመጣ አልቻለም፡፡ የዛምቢያ ፖሊስም ይህን ድርጊት የፈጸሙትን ማምሻውን ሰብስቦ ዘብጥያ ማውረዱን አፍሪካን አርካይቭስ የተሰኘ ድረ ገጽ ከጥቂት ሰአታት በፊት ዘግቧል፡፡
በመሐሉ ምን ተፈጥሮ ይሆን? What Happened in Between?

ጌታቸው ረዳ ከ20 ቀናት በፊት በ"African Report" መፅሔት ላይ የአፍሪካ ሕብረትን የማሸማገል ጥረትን በዜሮ አባዝቶ መፃፉ ይታወሳል። በዚሁ ፅሁፉ ጌቾ የአፍሪካ ሕብረትን የማሸመገል ሚናን እስከ ወዲያኛው አብጠልጥሎታል፤ የትግራይ "ጄኖሳይድ" ተባባሪ የ"ጨካኙ"(Brutual) የአቢይ አገዛዝ ጠበቃ ወዘተ እያለም አውግዟል። እስቲ የተወሰኑትን እንመልከት፦

1. የጌቾ ፅሁፍ ርዕስ፦ "The African Union can not Deliver Peace to Tigray! በቃ በአጭሩ...የአፍሪካ ሕብረት ለትግራይ ሰላምን ማምጣት አይችልም... ነበር ያለን! CANNOT!

2. ንዑስ ርዕስ ፦ "Abiy hides behind AU"
አቢይ የአፍሪካ ሕብረትን እንደመሸሸጊያ ተጠቅሞታል እያለ ነው። ይህም ጌቾ በአፍሪካ ሕብረት ላይ የሰነዘረው ሌላው ውግዘት ነው!

3. ጌታቸው ረዳ "Pan-African’ subterfuge" ከሚለው ንዑስ ርዕሥ ሥር በሁለተኛው አንቀፅ ላይ ይህን አስፍሯል፦

"However, the AU, under the leadership of Moussa Faki Mahamat, has become an apologist for a brutal regime seeking to starve and bomb its own people into submission."

ጌቾ...በሙሳ ፋቂ መሃመት የሚመራው የአፍሪካ ሕብረት የአቢይ መንግስት ጠበቃ ሆኗል... እያለን ነው።

4. ሌላም አለ፦ ጌቾ "Isiais as spoiler" በሚለው ርዕስ ሥር በአምስተኛው አንቀፅ ላይ የአፍሪካን ሕብረት "Champion of the Oppressor" በማለት ከመወንጀሉም ባለፈ የ"ጄኖሳይድ" ጦርነቱም ተባባሪ ነው እስከማለትም ዘልቋል።

""The AU Commission’s conduct under the current leadership has done considerable damage to the institution, turning it into a champion of the oppressor at the expense of the victim. Having failed to play a constructive role in preventing the outbreak of the war on Tigray, the AU Commission would also go on to bless the genocidal war once underway, turning a blind eye to the unimaginable atrocities committed, and being committed, against the people of Tigray."

5. በመጨረሻም ጌቾ "An ineffective African Union" በማለት የወረፈውን የአፍሪካ ሕብረትን አንድ ነገር ተማፅኗል ...ሕብረቱ ከሰላም ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ራሱን እንዲያገል...complete exclusion from the peace process."

"Despite our well-justified concerns about the AU’s impartiality, we have too much respect for the AU as an institution to insist on its complete exclusion from the peace process."

ተቃርኖ

በትናንትናው ዕለት ጌቾ ከ20 ቀናት በፊት ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ቀናት በፊትም "ምዕራባዊያን ያደራድሩን" ከሚለው አቋሙ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚላተም ሌላ መግለጫ አውጥቷል። በዚሁ መግለጫው ጌቾ ቀደም ሲል በአፍሪካ ሕብረትና በወቅቱ መሪ በሙሳ ፋቂ መሃመት ላይ ለዘረገፈው የጄኖሳይድ ተባባሪነት ውርጅብኝ ይቅርታ እንኳን ሳይጠይቅ "የአፍሪካ ሕብረት ያደራድረን" ሲል ተማፅዕኖውን አቅርቧል፦.

"To that end , the Government of Tigray is prepared to participate in a robust peace process under the auspices of the African Union...We expect a credible AU-Led peace" በማለት አቋሙን ቀይሯል።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩልም ይሁን በአፍሪካ ሕብረት በኩል ይህን የነጌቾን የአቋም ለውጥን መቀበል አለመቀበል አንድ ነገር ሆኖ ከሁሉም አስቀድሞ ሁለት እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ባይ ነኝ።

1. የኢትዮጵያ መንግሥት የትናንትናው መግለጫ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚቃወም በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረግ አለበት። በመግለጫው በጣም ግልፅ በሆነ መልኩ "The Government of Tigray" እየተባለ ነው "address" የተደረገው። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ደግሞ " The Government of Tigray" የሚባል ነገር የለም። ያለው "The Regional Government of Tigray"...የትግራይ ክልላዊ መንግሥት...ነው። ስለዚህም መግለጫው የሕወሓት የወደፊት ምኞቷና ሕልሟ ምን እንደሆነ ይፋ ያደረገ ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት በእነ ጌቾ የድረሱልኝ ዓይነት መግለጫ ላይ ምንም ዓይነት ምላሽ ከመስጠቱ በፊት መግለጫውን ውድቅ ማድረግ አለበት፤ አሊያም "የትግራይ መንግሥት" የሚለውን "የትግራይ ክልላዊ መንግሥት" በሚለው ኢዲት አድርገው እንደገና ፅፈው ማመልከቻቸውን ያስገቡ። ጥያቄው ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው።

2. የአፍሪካ ሕብረትም ቢሆን ጌቾ ቀደም ሲል በ"African Report" ላይ ሕብረቱን "የጄኖሳይድ ተባባሪ" እያለ ለወነጀለው ይቅርታ እንዲጠይቅ ለትህነግ ደብዳቤ መላክ ይጠበቅበታል። ይህ የመርህ ጉዳይ ነው፤ ሲያሻቸው የጄኖሳይድ ተባባሪ ሲያሻቸው ደግሞ ያንኑ በጄኖሳይድ ተባባሪነት የፈረጁትን ተቋም ይቅርታ ሳይጠይቁ "ቶሎ አደራድረን" ብሎ መማፀን ከመርህ ያፈነገጠ አካሄድ ነው። ጌታቸው ረዳ እዚያው "Africa Report" ላይ "Ethiopia: The African Union can deliver peace to Tigray" በሚል ርዕስ ሌላ ፅሁፍ አቅርቦ ሕብረቱን "አፉ በለኝ" ማለት ይጠበቅበታል።

ዋናው ጥያቄ ግን እንደዚህ የትህነግ አቋም በብርሃን ፍጥነት እንዲቀያየር ምክንያት የሆነ በ20 ቀናት መካከል የተፈጠረ ምን አዲስ ነገር አለ? ማለትም "What Happened in Between?"
ኢትዮጵያን እያደር አስቂኝ እያደረጉ ከመጡ በርካታ ነገሮች መካከል የመኪናናየሪልስቴት ንግድ ተብዬዎች ይጠቀሳሉ፡፡ የመኪና ንግድ ከፍተኛ ወረት ባላቸው ኩባንያዎች መካሔድ ሲገባው ጭራሽወደ ኮረሪማና ጥቁርአዝሙድ ችርቻሮ ደረጃ ወርዶ "ሱቅ በደረቴ " ሆኗል፡፡ ከእንቅልፋቸው በባነኑ ቁጥር ቅዠታዊ የሀብት ምኞታቸውን ለማርካት ደስያላቸውን ረብጣ በመጨመር ብሩን--እፉዬ ገላ ያደረጉ ነጋዴዎች ማንኛዋንም 50 ካሪ ሜትር ግቢ ቀለም እያስቀቡ እንደ አሸን መፍላታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባጃጅን ጨምሮ ማንኛዋም ብጥሌ-ተሽከርካሪ በማርቸዲስ ደረጃ የምትሸጥበትና ሀገሪቱ እንደመርካቶ የአይጥ መርዝ ማስታወቂያ "እዛው በላች፤እዛው ሞተች!" ዐይነት የንጥቂያ ንግድውስጥ እስካንገትዋ ተነክራለች፡፡ ትልልቅ ኩባንያ ከፈትን ብለው መገናኛ ብዙሀንን ያጥለቀለቁ መኪና መገጣጠሚያ ተብዬዎችም ዋንኛ መለያቸው ወረፋ ነው--የዓመታት፡፡ እንደ ሞኤንኮ ያሉ "ትልቅ"ኩባንያዎች ዋንኛ መታወቂያቸው ብዙ አምጥተው ከብዛት በማትረፍና ቢያንሥ የ3 ወር የክሬዲት አገልግሎት ማስተዋወቅ ሳይሆን ዋጋ መቆለልና የማይቀመስ መሆን ነው፡፡አሁን በኢትዮጵያ ብር የተረፈው ሀብታም ሁሉደርግ ያጠፋውን "መደብ" ለመፍጠር የሚያደርገው ቀሊል ጥረት ያስቀኛል!ባጣናበነጣ ህዝብ መሀልሁሉንም ነገር በተጠየቀው ዋጋ መግዛትና ያንኑ ያህል"ቲፕ" መሥጠት፡፡እንደው ሳስበው ለእነዚህ በየጎሬው ለፈሉ የመኪና ሱቅ በደረቴዎችም በአንበሳ ዋጋ ለሚሸጡ ቅራቅንቦዋቻቸው የኛዎቹ ባለሀብት ገዢዎች "ቲፕ"ሊጨምሩላቸው እንደሚችሉ፡አስባለሁ::
ሌሎቹ ደግሞ ሪልስቴት ገንቢ ተብዬዎችናቸው፡፡አሁን አሁንማ አየር ላይ የተንጠለጠለ የውሻ ቤት100 ሚሊዮን ሊሸጡልን ነው፡፡የዚህ የመጀመሪያ ተጠያቂ መንግስት በእጁ ያለውን መሬት በአግባቡአስልትቶና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትአልሞ ስር ያለውዕድገት ከማስቻል ይልቅ "አዲስ አበባ በመሬት ውድነት ቶኪዮን በለጠች" መባሉን እንደ ዕድገት ያየው ይመስላል፡፡ኢኮኖሚስት ባልሆንም ኋላ የኑሮ ውድነትን የሚያባባብስና ምግባር፣ሰላምና ስክነት የሚያሳጣ የገንዘብ መዐት ካዝና ቢያጨናንቅ ፋይዳ የለውም፡፡መደበኛው ማህበረሰብ ከምህዋር እየወጣ ነው፡፡ ዲያስፖራ ከሚባል በእጁ ያለውን ሁሉ አገኘው ቦታ ዘርግፎ በመሄድ ከማህበረሰቡ የኢኮኖሚ ዕውነታጋርምንም ግንኙነት የሌለው ስልተ-ምርት አራብቶ የሚሄድ ማህበረሰብ ራሱንም ሀገሪቱን በዘላቂነት እየጎዳ ነው፡፡
ይቺ አገር ፖለቲካዊ ስር ነቀል እርምጃዎቿ ለዜጋው ፋይዳ ያለው ኢኮኖሚያዊ መሠረት በሚጥል ኢኮኖሚያው ለውጥ መደገፍ አለበት፡፡"የውሻ ቤት በሰማይ" በብዙ ሚሊየኖች የሚቸበችቡና ሱቅ በደረቴ የመኪና ነጋዴዎች የዚህ አገር የንግድ ነቀርሳመገለጫዎች ናቸው፡፡እንደባንኩ ሁሉ የውጭ ሪልስቴትናየመኪና መሸጫ ኩባንያውች ይግቡልን፡፡ዕውቀትም ፈሪሀ እግዚአብሄርም ሆነ ምግባርና ለአሥርተ ፡ዓመታት የመኖር ህልም በሌለው የሀበሻ እዛው በላች እዛው ሞተችወረት አልባ ንግድ እንደ ሙቀጫ መወቀር ሰልችቶናል፡፡በአዲስ ዓመት አዳዲስ መፍትሔዎች እናስብ፡፡
በነገራችን ላይ የዘንድሮው ባለ10ሚሊዮንየእንቁጣጣሽ ሎተሪ አሸናፊ ከየትኛውም ሪልስቴት ግንባታ ባለአንድ መኝታ አፓርትመንት መግዛትአያስችለውም፡፡ኮሚኒስቱነትኑም ሆነ ካፒታሊስቱነቱን አልቻልንበትም፡፡ሁሉም በጎ ነገር እኛ ጋ ሲደርስ ይበላሻል፡፡
ለግል መገልገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው የሚገቡ ዕቃዎች የትኞቹ ናቸው ?
- ሲጋራ | መለኪያ ➤ ግራም | የሚፈቀደው መጠን ➤ 200
- ሲጋር | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 20
- ብትን ትንባሆ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 250
- የአልኮል መጠጥ | መለኪያ ➤ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 2
- ለስላሳ ሽቶ | መለኪያ ➤ ሚሊ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 500
- ሽቶ | መለኪያ ➤ ሚሊ ሊትር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 500
- #ሞባይል | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 2 (#ሁለት)
- #ላፕቶፕ | መለኪያ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን 1 (#አንድ)
- #የፎቶግራፍ_ካሜራ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1
- #ዊልቸር | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1
- #የእጅ_ሰዓት | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1
- የፂም ወይም የፀጉር መላጫ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1
- የፀጉር ማድረቂያ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1
- የፀጉር መተኮሻ | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ 1
- መንገደኛው የሚጠቀምባቸው መድሃኒቶች እና የህክምና በቁጥር መገልገያዎች | መለኪያ ➤በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ ለአንድ ሰው በሚያስፈልግ መመጠን
- በጉዞ ወቅት ጥቅም ላይ የሚውሉ እና ለቤተሰብ የሚያገለግሉ ፣ ልብሦች፣ ጫማዎች፣ እና የፅዳት እቃዎች | መለኪያ ➤ በቁጥር | የሚፈቀደው መጠን ➤ ለአንድ ቤተሰብ ከሚያስፈልገው ያልበለጠ
የተሻሻለው የግል መገልገያ እቃዎች - የጉምሩክ መመሪያ 👇
Channel name was changed to «Ethio Standard»