..
እንወያይበት ኣንድ ግዜ
ይለቀን እንደሆን የያዘን ኣባዜ
እንምከር እኛው ለኛ
ኣያስፈልገንም መሃል ገቢ ዳኛ
ያልተባባልነውን
በሰው በኩል ሠምተን
ከምንቀር ስተን..
ዋጥ እናርገውና ክብር ይሉት ብሂል
ዝቅ ብለን ኣንዴ ኣንዳችን ላንዳችን
እንምከር ሃቅ ሃቁን
ባንመለስ እንኳ ወደነበርንበት
ባንመልሰው እንኳ ያንን ወዳጅነት
ተነጋግሮ ተሰማምቶ መሰናበት
ኣልሆን ካለን በሰላሙ መለያየት
እስኪ እኛ እንወቅበት፥
...meron.
እንወያይበት ኣንድ ግዜ
ይለቀን እንደሆን የያዘን ኣባዜ
እንምከር እኛው ለኛ
ኣያስፈልገንም መሃል ገቢ ዳኛ
ያልተባባልነውን
በሰው በኩል ሠምተን
ከምንቀር ስተን..
ዋጥ እናርገውና ክብር ይሉት ብሂል
ዝቅ ብለን ኣንዴ ኣንዳችን ላንዳችን
እንምከር ሃቅ ሃቁን
ባንመለስ እንኳ ወደነበርንበት
ባንመልሰው እንኳ ያንን ወዳጅነት
ተነጋግሮ ተሰማምቶ መሰናበት
ኣልሆን ካለን በሰላሙ መለያየት
እስኪ እኛ እንወቅበት፥
...meron.
❤8🥰2
በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚሰማኝ ስሜት ነው ,,, መፅሐፍቶችን አነባለሁ ግን ያነበብኩትን አላስታውስም ። መፅሐፍት እያነበብኩ ቁርሴን ዘልየ አውቃለሁ የመፅሐፍ ሽታ እየማግኩ ፣ ገፆችን ስገለብጥ የሚሰማኝ ድምፅ ከምንም ይለይብኛል ።
እኛ ቤት ቤተሰቦቼ ቡና እየጠጡ በወሬ ጩሀት ቤቱን ያደምቁታል ፤ እኔ ግን አንድ ነገር ላይ ትኩረት ሰጥቸ እፈዛለሁ ፣ ትክዝ እላለሁ ግን ስሜቱ ደስ ይለኛል ። ቤተሰቦቼ ስለ ፖለቲካ ይተነትናሉ ፣ እኔ ግን ወደ ውስጤ እሰጥማለሁ ፣ የቤተሰቦቼ ወሬ የቅቤ ገበያ ላይ እንዳሉ አሮጊቶች ይሆንብኛል ። ብቻዬን መሆን መገለል ሳይሆን ነፃነት ነው ለኔ። . በሰው መኃል ተከቦ የሰውን ወሬ ሳይሰሙ ለብቻ መሆን እንደሚቻል ተገነዘብኩ ።
" ዛሬ ይሄን ልጅ ምን ነክቶታል ? አሞት ይሆን ?" ትላለች እናቴ በፊት የወሬ አማካይም አጥቂም ተከላካይም ነበርኩ ፤ አሁን ግን ታዛቢ ሁኛለሁ ። እንደ ሃበሻ ተረት < በለፈለፉ በአፍ ይጥፉ > የሚለውን መፈክር ይዤ አይደለም ዝምታን የመረጥኩት እራሱ መፅሐፍ ነው አድቦልቡሎ የሰራኝ ። እኔማ እንደ Major course ያነበብኩት እንዳይረሳኝ እጋጋጥ ነበረ ግና ብረሳውም የዚህን ዓለም ከንቱነት ፣ ሚጠቅመኝንና ማይጠቅመኝን ፣ ለስኬቴ የሚያስፈልገኝን ስንቅ ፣ የማሰብን ችሎታ ፣ የሕይወትን መልካም ገፅን ብቻ ሳይሆን መጥፎ ገፅንም እንድመለከት ፣ ከናርስሲስትና ከቶክሲክ ሰዎች እራሴን ጠብቄና private boundary አስጠብቄ እንድኖር አስተምሮኛል ።
✍ Henok🔥9👏4
ዕድሜየ የደስታ(ግልብነት) እንጂ ጥልቅ ማንነትን የማይመረምር ሳለ ስነ ጽሑፍ ጻፍ ብትሉኝ ስለፍቅር፣ አሊያም ስለ አዝናኝ ነገሮች እፅፍላችሁ ነበር። እናንተም በማነብላችሁ ቅጽበት ደስታ ይሰማቹህ ይሆናል።
አሁን ግን "ነፍስ ማወቅ" የሚባለው ደረጃ ልደርስ ነው መሰል ደስተኝነት እንዴት እንደሚመጣ አላውቅም እና ፅሁፎቼን ደስታ ማሳዘል አልችልም። ታዲያ ይች የአምስት ስድስት ዓመት ልዩነት ነች።
ያኔ ሀገር ሁሉ ሰላም ነበር ፣ ሌሊት ወጥተን ምሽት እንገባ ነበር። እና ስለሰላም ያኔ ብዙ አናውቅም ነበር አብሮን ስላለ።
ለካስ የራቀ ሰው ፣ ያልተተኛ እንቅልፍ፣ ያልሄዱበት ሀገር ፣ ያልጎበኙት ዘመድ ፣ ያልተሳቀ ደስታ ፣ መኖር ሲቻል ያልተኖረ ህይወት ነው ስላልኖረ የሚናፈቅ።
ዘረዘርኩት እንጂ ሁሉም ሰላም ካለ የሚገኝ ነው።
ማርያምን ሰላም ናፈቀኝ😢❤5😢2
የካሳንቺስ ምሽት ቅዝቃዜ አጥንት ይሰብራል። የመንገዱ ደብዛዛ ብርሃን በዝናብ አውራ ጎዳናው ላይ ሲንጸባረቅ ይታያል። ብሩክ በዝናብ የራሰውን ኮቱን ሰብሰብ አድርጎ በእጁ የያዘውን ትልቅ ፖስታ አቅፎ በእግሩ ይጓዛል። በፖስታው ውስጥ ያለው ለሁለት ዓመታት ያህል ደሙንና ላቡን አፍስሶ የጻፈው ልቦለድ መጽሐፍ ነበር። ዛሬ ግን ለአምስተኛ ጊዜ ከአሳታሚዎች በር "አይሸጥም" ተብሎ ውድቅ ተደርጎበታል።
ልቡ ተሰብሯል። "እኔ ለማን እረባለሁ? መጻፍስ ለምን አስፈለገኝ?" የሚለው የውስጥ ጥያቄ እንደ እሾህ ይወጋዋል። እግሮቹ ወዴት እንደሚወስዱት ሳያውቅ ሲጓዝ፣ በመንገዱ ዳር ካለች አሮጌ የሸራ ሱቅ ውስጥ ደብዛዛ ብርሃንና የታወቀ ድምጽ ሰማ።
"ክላክ... ክላክ... ክላክ..." የሸማ መወርወሪያ ድምጽ ነበር።
ብሩክ ቆም አለ። ወደ ሱቁ ሲመለከት ጋሼ አበራ የተባሉ ዕድሜ የጠገቡ ሸማኔ፣ በደብዛዛዋ አምፑል ስር ሆነው ሸማቸውን ይሸምናሉ። ብርዱን ለመቋቋም ሻይ እየጠጡ ፣ በረጅሙ ክር ላይ በፍቅር ያተኩራሉ። ብሩክ ከቅዝቃዜው ለመጠለልም ጭምር ፈቀቅ ብሎ ወደ ሱቁ ገባ።
"እንኳን ደህና መጣህ ልጄ፣ በጣም በርዶሃል እኮ?" አሉት ጋሼ አበራ፣ መወርወሪያቸውን ለጥቂት ሰከንድ አቁመው።
"አዎ ጋሼ... በጣም። እስካሁን አልገቡም እንዴ?" አለ ብሩክ ፣ ድምፁ እየተንቀጠቀጠ።
"ይህቺን ቀሚስ ሳልጨርሳት አልተኛም፤ ነገ ለአንዲት ሙሽራ መድረስ አለባት" አሉት። ብሩክ ወደ ሸማው ጠጋ አለ። ወደ ራሱ እያየ ያለው የሸማውን የኋላ ክፍል ነበር። በአይኑ ሲመለከተው ክሮቹ በሙሉ የተዘበራረቁ፣ አንዱ ክር ከሌላው ጋር የተያያዘ፣ እዚህም እዚያም የተቋጠሩና የተንዘረፈፉ ምስቅልቅል ነገሮች ብቻ ነበሩ። ምንም ውበት የለውም።
ብሩክ በረጅሙ ተነፈሰና፦ "ጋሼ አበራ... ግን ህይወት በጣም አልሰለቸዎትም? ሁልጊዜ ይህን የተዘበራረቀ እና የተቋጠረ ክር ደጋግሞ መሳብ? እኔ እኮ ህይወቴ ልክ እንደዚህ ሸማ ጀርባ የተቋጠረችና የተበላሸች ትመስለኛለች። የትም የማልደርስ፣ የተሳካልኝ ነገር የሌለኝ ከንቱ ሰው ነኝ" አላቸው። የልቡን ህመም መቋቋም አቅቶት አይኖቹ በእንባ ተሞሉ።
ጋሼ አበራ መወርወሪያቸውን አስቀመጡ። ብሩክን በጥሞና ካዩት በኋላ ፈገግ አሉ። ከዚያም ከመቀመጫቸው ተነስተው ሸማውን ወደ ሌላኛው አቅጣጫ ገለበጡት።
"ልጄ ብሩክ... እስኪ አሁን ተመልከት" አሉት።
ብሩክ አይኑን ማመን አቃተው። በሌላኛው በኩል የነበረው ሸማ እጅግ አስደናቂ፣ ባለብዙ ቀለም፣ በጥበብ የተሞላና አይን የሚማርክ የሀበሻ ቀሚስ መጋረጃ (ጥበብ) ነበር። ቅድም የታዩት የተቋጠሩትና የተበላሹት ክሮች በሙሉ አሁን ተሰባስበው ያንን ውብ ስዕል ፈጥረውታል።
ጋሼ አበራ በትከሻው ላይ እጃቸውን ጭነው እንዲህ አሉት፡-
"ልጄ... ህይወት ልክ እንደዚህ ሸማ ናት። እኛ ሁልጊዜ የምናየው የራሳችንን ህይወት ጀርባ ነው። ጀርባው ላይ ስንመለከት የሚታየን የተበላሸ ክር፣ መከራ፣ ውድቅ መሆን፣ ህመም እና እንባ ብቻ ነው። 'ሁሉም ነገር ተበላሽቷል' ብለን እናስባለን። ነገር ግን ፈጣሪ ከፊቱ እያደረገ የሚሸምነው፣ እኛ የማናየው ውብ የሆነ የህይወታችን ምስል አለ። ያ አሁን የምታየው ምስቅልቅልና የተቋጠረ ክር ከሌለ፣ የፊተኛው ውብ ስዕል ሊወጣ አይችልም። መከራህ ለስኬትህ ግብዓት ነው።"
ብሩክ የተናገሩትን ነገር በጥልቀት አሰላሰለ። በእጁ የያዘውን ፖስታ አጥብቆ አቀፈው። ዛሬ ውድቅ የተደረገው ጽሑፍ፣ ነገ ለሚመጣው ትልቅ ስኬት አንዱ 'የተቋጠረ ክር' መሆኑን ተረዳ።
"አመሰግናለሁ ጋሼ..." አለ።
ከሱቁ ሲወጣ የካሳንቺስ ቅዝቃዜ ጠፍቶ፣ በልቡ ውስጥ አዲስ የሚነድ የተስፋ እሳት ተሰማው።
✍ Henok❤14
፡
ጠላኸኝ ፡ ጠላሁህ
ብላ ተራገመች፡
ዝምታዬ ቢነግስ፣
መንገዱን ላነጸ፡
ትርጉሙ ሽኝት ነው፡
የጥያቄ ሁሉ መልስ።
አይመልስሽ🙌!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
ጠላኸኝ ፡ ጠላሁህ
ብላ ተራገመች፡
ዝምታዬ ቢነግስ፣
መንገዱን ላነጸ፡
ትርጉሙ ሽኝት ነው፡
የጥያቄ ሁሉ መልስ።
አይመልስሽ🙌!
አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
❤4👍2🔥1
በአንድ ገጠር ውስጥ የሚኖሩት መርጌታ ገብረማርያም እጅግ የተከበሩ፣ ግርማ ሞገስ ያላቸውና ፊታቸው የማይፈታ ጥብቅ ሰው ነበሩ። በሳቸው ግቢ ውስጥ የሚማሩት የቆሎ ተማሪዎች እሳቸውን ከማክበራቸው የተነሳ ቀና ብለው ለማየት እንኳ ይፈሩ ነበር።
አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ፣ ተማሪዎቹ በሙሉ በዝምታ ተቀምጠው የዳዊት ዜማ እያጠኑ ነው። ክፍሉ ውስጥ ከመስከኑ የተነሳ የዝንብ ክንፍ ቢንቀሳቀስ ይሰማል። መርጌታም መሃል ላይ ተቀምጠው በመጽሐፋቸው ላይ አቀርቅረዋል።
በድንገት ግን... ማንም ያልጠበቀው፣ እንደ መብረቅ የሚያስገመግም «ጡርርርርርርር!» የሚል ኃይለኛ ድምፅ ከመቶ አለቃው (ከመርጌታ) በኩል ተሰማ!
ክፍሉ ውስጥ ያለው ተማሪ በሙሉ ደነገጠ። ሁሉም ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ እርስ በእርስ መተያየት ጀመረ። መርጌታ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ፊታቸውን ኮስተር አድርገው መጽሐፋቸውን ማንበባቸውን ቀጠሉ።
ነገር ግን ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ፣ ክፍሉ ውስጥ በአይን የማይታይ ግን አፍንጫን የሚሰነጥቅ ከባድ «ጋዝ» ተበተነ። ሽታው በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ የክፍሉ ግድግዳ ራሱ የሚላጥ ይመስል ነበር።
ተማሪዎቹ ሳቃቸውን ለመቆጣጠር ከንፈራቸውን ይነክሳሉ፣ ሆዳቸው ይንቀጠቀጣል፣ አይኖቻቸው በእንባ ይሞላሉ። ነገር ግን መርጌታን ከመፍራታቸው የተነሳ ማንም ለመተንፈስም ሆነ ለመሳቅ አልደፈረም።
መርጌታ ነገሩን ለማስተባበልና ክብራቸውን ለማዳን ወዲያውኑ ቀና አሉና በጥልቅ እና በተቆጣ ድምፅ እንዲህ አሉ፦
«ይህ አሁን የሰማችሁት ድምፅ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?»
ተማሪዎቹ በጭንቅላታቸው «አናውቅም» በሚል ምልክት አነቃነቁ።
መርጌታም ቀጠሉ፦ «ይህ... በክፍሉ ውስጥ በስውር ሲያንዣብብ የነበረው ሰይጣን ሲባረርና ሲበተን የወጣው የድል ድምፅ ነው! ሰይጣን ሲወጣ ደግሞ ሁልጊዜም እንዲህ መጥፎ ሽታ ይተዋል! ስለዚህ ሁላችሁም አፍንጫችሁን ይዛችሁ ፀልዩ!»
በዚህ መሃል አንድ ከበስተጀርባ የተቀመጠ ተማሪ ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ድምፅ አውጥቶ «ክክክክክ!» ብሎ ሳቀ።
መርጌታም ወዲያውኑ በዱላ እያመለከቱት በቁጣ ጮኹ፦
«አያችሁት አይደል? በውስጡ ያለው ሰይጣን ሲጋለጥ ነው የሚስቀው! አንተ ሰይጣን... ውጣ ከእሱ ላይ!»
ተማሪውም እየተንፈራገጠ፦ «መርጌታ... ሰይጣኑማ ቀድሞ በድምፅ ወጥቷል፤ እኔን እየገደለኝ ያለው ግን <<ጡርርርር>> ያለው ጪስ ነው!» ብሎ በሩን ከፍቶ ሮጦ አመለጠ።
ከዚያ ቀን ጀምሮ መርጌታ ክፍሉ ውስጥ ሳል እንኳ ሲያስነጥሳቸው፣ ተማሪዎቹ «ዛሬስ የትኛው ሰይጣን ሊወጣ ይሆን?» እያሉ በሹክሹክታ ይቀልዱ ነበር።
✍ Henok😁5❤3
እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ህመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።
ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።
ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።
ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....
እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...
ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!
<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።
ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ ።
ጠላኋቸው !!
አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።
<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...
እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...
በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!
የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....
አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...
እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...
የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>
© Adhanom Mitiku
ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።
ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።
ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....
እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...
ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!
<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።
ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ ።
ጠላኋቸው !!
አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።
<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...
እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...
በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!
የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....
አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...
እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...
የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>
© Adhanom Mitiku
1❤10🥰3
ብዙ ጊዜ የመኖር ቀመር ከእውነታ ትርቃለች!
በዋሸኸው መጠን ተቀባይነት የማግኘት እድልህ የሰፋ ነው።
በዋሸኸው መጠን ተቀባይነት የማግኘት እድልህ የሰፋ ነው።
❤5👍1
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
